👂 #ምን_ተሰማ⁉️ 👂
🏃♂ በሸበጥ ማራቶን ያሸነፈው አትሌት 🏃♂
ከቀናት በፊት በታይላንድ በተከናወነ የማራቶን ውድድር አሸናፊ የሆነው ኬኒያዊው አትሌት በርናባስ ኪፕሊሞ ውድድሩን ለመከወን የተጫማው ጫማ አነጋጋሪ ሆኗል።
የ28 ዓመቱ አትሌት ከታይላንድ የሩጫ ጫማ ብራንድ ጋር በመሆን "የዓለም የመጀመሪያው ድንቅ ሸበጥ" የሚል ስያሜ የተሰጠውን ጫማ አጥልቆ ማራቶኑን የከወነ ሲሆን ውድድሩን አሸናፊ የሆነበት ሸበጥም ቀላል ክብደት ካላቸው ካርቦኖች እንደተሰራ ተብራርቷል።
ጥቂት ቁጥር ያላቸው ሸበጦች ከማራቶኑ በኋላ ለገበያ የበቁ ሲሆን በምርቱ ላይ ግን አሁንም ጥናቶች እና ምርምሮች እየተከናወኑ እንደሚገኝ ተጠቁሟል። በቀጣዩ የፈረንጆች ወር የተሻሻለው የመሮጫ ሸበጥ ይፋ እንደሚሆን የገለፀው የጫማው አምራች ተቋም በመጋቢት ወር ላይ በሚደረገው የሎስ አንጀለስ ማራቶን ምርቱን ለማሳየት መታቀዱን ጨምሮ አስታውቋል።
ውድድሩን ያሸነፈው አትሌት ዓምና በናይሮቢ በተከናወነው የማራቶን ውድድር 43ኛ መውጣቱ የማይዘነጋ ሲሆን ዘንድሮ እጅግ መሻሻል ባሳየበት ማራቶን በልዩ የሸበጥ ጫማው 2:18.55 በመሮጥ የወርቅ ተሸላሚ ሆኗል።
@goferesportswear