✨✨ወርቃማው የሰሀቦች ታሪክ✨✨
✨✨የመጨረሻው ክፍል✨✨
.
.
ቢላል ከነቢዩ ሙሐመድ (ﷺ) ጎን ሳይነጠል ኑሮውን መግፋት ቀጠለ። እርሳቸው በተገኙበት ዘመቻ ሁሉ ተሰልፏል። ለሶላት "አዛን" ያደርጋል። ከጨለማ ወደ ብርሀን ፥ ከባርነት ወደ ነፃነት ያወጣውን ታላቅ ዲን አርማ ያስተጋባል። ቢላል ከነቢዩ ሙሐመድ (ﷺ) ጋር ያለው ቀረቤታ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ በመምጣቱ መልዕክተኛው( ﷺ ) "የጀነት ሰው" እያሉ ያሞካሹት ነበር። እርሱ ግን ትናንት ባሪያ የነበረ ሀበሻ መሆኑን ብቻ ነበር የሚያወሳው።
ከዕለታት አንድ ቀን ለራሱና ለወንድሙ ሚስት ለማጨት ወደ አባቶቻቸው ሄደ። እንዲህም አላቸው። "እኔ ቢላል እባላለሁ ይህ ደግሞ ወንድሜ ነው። ሀበሻዊ ባሪያዎች ነን ...በተሳሳተ እምነትም ላይ ነበርን ፥አላህ መራን...ባሪያዎች ነበርን ነፃ አወጣን። ልጆቻችሁን ከዳራችሁልን አልሀምዱሊላህ እንላለን፤ ከከለከላችሁን ደግሞ፦ "አሏሁ አክበር " እንላለን (የአላህን ታላቅነት እንድታውቁ እናሳስባለን )!"
ነቢዩ ሙሐመድ (ﷺ) ወደ ተከታዩ ዓለም ከተሻገሩ በኋላ የሙስሊሞች የበላይ ሞግዚት ሆነው የተሾሙት አቡበክር ሲዲቅ رضي الله عنه ነበሩ።
ቢላል ወደ መልዕክተኛው (ﷺ) ኸሊፋ (አስተዳደራዊ ምትክ) በመሄድ እንዲህ አላቸው፦ "አንተ የአላህ መልዕክተኛ ምትክ (ኸሊፋ) ሆይ! እኔ የአላህ መልዕክተኛ (ﷺ) ለአንድ አማኝ ብልጫ ያለው ሥራ በአላህ መንገድ "ጂሃድ" ማድረግ ነው፥ ሲሉ ሰምቻለው።"
አቡበክርም (رضي الله عنه) ፦ "ቢላል ለመሆኑ የፈለግከው ነገር ምንድነው ?" አሉት።
ቢላልም፦ "እስክሞት ድረስ በ'ፊ ሰቢሊላህ' ላይ ለመሳተፍ እሻለሁ" አለ።
አቡበክርም (رضي الله عنه) "ማን አዛን ያደርግልናል?" አሉ። ቢላልም ፦"እኔ ከአላህ መልዕክተኛ (ﷺ) በኋላ ለማንም ቢሆን 'አዛን' አላደርግም " አለ ዓይኖቹ እያነቡ። አቡበክርም (رضي الله عنه) ፦ "ቢላል ሆይ! እባክህ ከኛ ጋር ቀርተህ 'አዛን' አድራጊያችን ሁን አሉት። ቢላል ግን ቁርጥ አቋሙን አሳወቀ፦ "ከባርነት ነፃ ያወጣኸኝ ለአንተ አገልጋይ እንድሆን ከሆነ ያሻህን መፈፀም ትችላለህ። ነፃ ያወጣኸኝ ለአላህ ከሆነ ለርሱ ተወኝ።" አቡበክርም (رضي الله عنه)፦ "ቢላል ሆይ! እኔ ነፃ ያወጣሁህ ለአላህ ስል ነው" አሉ።
ከዚህ በኋላ ስላለው የቢላል የሕይወት ታሪክ መፅሐፍት የተለያየ አቋም ይዘዋል። ከፊሎቹ የአቡበክርን (رضي الله عنه) ተማፅኖ በመቀበል እሳቸው እስካሉ ድረስ በመዲና ቆይቷል፤ ከዚያም በዑመር (رضي الله عنه) ጊዜ ወደ ሻም ይዛወር ዘንድ ፈቃድ ጠይቆ በሻም መኖር ጀምሯል ሲሉ፥ ሌሎች ደግሞ ከመጀመሪያው ወደ ሻም በመሄድ ባሰበው መስክ በየጊዜው በ"ፊ ሰቢሊላህ" በመገኘት ሕይወቱን አሳልፏል ይላሉ።
ያም ሆነ ይህ ግን ቢላል የመጨረሻ ሕይወቱን እንደ ጅማሪው ሁሉ በ"ጂሃድ" ለማሳለፍ ችሏል። 'አዛን' ዳግም ለማድረግ ግን አቅም አልነበረውም። "አሽሃዱ አንነ ሙሐመደን ረሱሉሏህ" የሚለውን ሐረግ ጮኾ ለማሰማት ሳግ ይይዘዋል-ዕንባ ያሸንፈዋል።
የነቢዩ ሙሐመድ( ﷺ )ትዝታ በአዕምሮው ይቀረፃል-ትንፋሽ ያጥረዋል። የመጨረሻ 'አዛን' ያደረገው ዑመር ኢብኑል ኸጧብ (ﷺ) ለጉብኝት ሻም በገቡበት ወቅት ነበር። የሻም ሰዎች ቢላል አንድ ወቅት ሶላት እንኳ "አዛን" ያሰማቸው ዘንድ ዑመር(رضي الله عنه) ግፊት እንዲያደርጉ ጠየቁ። ቢላል ተስማማ፥ "አዛን" አሰማ። እርሱና በነቢዩ (ﷺ) ዘመን የነበሩ ሶሐባዎች በዕንባ ተራጩ። በተለይ ዑመር (رضي الله عنه ) እንባቸውን ለረጅም ጊዜ መግታት አልቻሉም።
🌺🌺
✨✨ቢላል በ"ፊ ሰቢሊላህ" ላይ እያለ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ -በሻም።✨✨🌺🌺
ተ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
ፈ✨✨✨✨✨✨✨✨✨
ፀ ✨✨✨✨✨✨✨
መ✨✨✨✨✨✨
እንዴት ነበር❓👇👇
t.me/HANIF_TUBE01 t.me/HANIF_TUBE02