🔖የረመዷን መልዕክት ከዛዱል መዓድ
👇 ፆምን አያፈርስም (ለፆመኛም ይቻላል)1/ በየትኛውም የቀኑ ክፍለ-ጊዜ ውስጥ መፋቂያ ካስፈለገም የጥርስ ቡሩሽ መጠቀም (የጥርስ ቡሩሽ ሳሙናው ወደ ውስጥ እንዳይገባ ከመጠንቀቅ ጋር)፣
2/ በውዱእ ጊዜም ይሁን በየመሃሉ አፍ ደርቆ ሲያስቸገር በውኃ መግሞጥመጥና መልሶ መትፋት (ውኃውን አንዴ ከተፉት በቂ ነው! አፍ እስኪደርቅ ድረስ ደጋግሞ መትፋት አያስፈልግም። ማጥበቅ/ተሸّዱድ ነው ተብሏል!)
3/ ሙቀት ከበዛና ድካም ከተሰማ ቤትኛውም ሰዓት ገላን በመታጠብ፣ በፎጣ ቀዝቃዛ ውኃ አድርጎ ልብ ወይም አናት ላይ ማድረግ ወዘተ አቅም የሚሰጡ ነገሮችን መጠቀም (ይቻላል።)
4/ አስፈላጊ ወይም የግድ ከሆነ ብቻ ምግብ ቀምሶ መትፋት፣
5/ ለምርመራ ደም መስጠትና ምግብነት የሌለውን መርፌ መወጋት፣
6/ ከአክታ ውጭ ያለን ምራቅ መዋጥ ፆምን አያፈርስም። ሆን ብሎ ምራቅን እየሰበሰቡ መዋጥ ግን ይጠላል። የከንፈርን የውጨኛ አካል ከነካ በኋላ መልሶ መዋጥ ግን ፆምን ያፈርሳል።
▪️አክታ ቆሻሻና ጎጂ ስለሆነ ምንግዜም መዋጡ ክልክል ነው። በፆም የተዋጠ እንደሆነ ፆም ያፈርሳል አያፈርስም ኺላፍ ያለበት ጉዳይ ሲሆን እያወቁ ይህን ከማድረግ መታቀቡ በላጭና ተመራጭ ነው፣
7/ የአይንና የጆሮ ጠብታ አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ መጠቀ ይቻላል ። (ሁለቱንም ወደ ማታ ማዘግየቱ ከተቻለ ተመራጭ ነው። በተለይ የአይኑ ከወሰዱት በኋላ ጉሮሮ ላይ የመድሃኒቱ ጣዕም ከተሰማ ፆም ይፈርሳል ያሉ የፊቅህ ሊቃውንት ስላሉ ቀን ላይ መጠንቀቁ በላጭ ነው)፣
8/በተኙበት ሳያውቁ የዘር-ፈሳሽ መውጣት እና፣
9/ ሳያስቡት አቧራና መስል ነገሮች በአፍ ወይም በአፍንጫ ወደ ሆድ መድረስ ፆምን አያፈርስም።
10/ ኩልና የከንፈር ማለስለሻ መጠቀም
በአፍ በኩል ወደ ሆድ እስካልዘለቀ ደረስ፣
11/ፀጉርንም ይሁን ሌላ ሰውነትን ቅቤና ቅባት መቀባት፣
12/ ቀጥታ ሳይታጠኑት (ሳይስቡት) የእጣን፣ቡኹርና ቀበርቾ፣ወዘተ ጭስ ማሽተት ፆምን አያፈርስም።
ሆን ብሎ ግን ጭሱን መታጠን (ወደ ውስጥ መሳብ) ፆምን ያፈርሳል።
✍🏻 ኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም
(حفظه الله) ረመዷን 4/1441@ዛዱል መዕድ
🔸🔹🔸🔹🔸🔹
🌐
https://t.me/hidaya_multi~~~~