[ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa]


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: ko‘rsatilmagan


እራስህን ሁል ጊዜ ለቁርኣንና ለሀዲስ ተጎታች አድርግ!
በአንድ ነገር ላይ ከቁርኣንና ከሀዲስ ማስረጃ ሳታገኝ አቋም አትያዝ!
ሁሌም ለሰዎች መልካምን ተመኝ!
ለሀቅ እንጂ ለሰዎች ወጋኝ አትሁን

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri


[ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa] dan repost
የእለተ ጁምዓ ሱንናዎችና ስርኣቶች
—————
መታጠብና መቀባባት
ከሰልማነል ፋሪሲይ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል አለ:- “አንድ ሰው በእለተ ጁምዓ ታጥቦ፣ ከመፀዳዳትም የቻለውንም ተፀዳድቶ፣ ከሚቀባባ ነገርም ተቀባብቶ፣ ቤቱ ውስጥ ከሚገኝ ሽቶ ተቀብቶ፣ ከዚያም ከቤቱ ወጥቶ በሁለት ሰዎች መካከል ካልለያየ፣ ከዚያም የተፃፈለትን ከሰገደ፣ ከዚያም ኢማሙ በተናገረ ጊዜ ዝም ካለ፣ በዚያች ጁምዓ እና በቀጣዩዋ ጁምዓ መካከል ያለውን ወንጀል ይቅር ይባላል።” [ቡኻሪ 883 ላይ ዘግበውታል]

ከሌላ ጊዜ የተሻለ ቆንጆ የሆነውን ልብስ መልበስ
ከሙሀመድ ኢብን የህያ ኢብን ሂባን (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል:- “አንዳችሁ ለእለተ ጁምዓ ከሌላ ጊዜ የተሻሉ ሁለት ልብሶችን ብይዝ የተሻለ ነው” [አቡዳውድ 1078 ላይ የተዘገበ ሲሆን አልባኒ ሶሂህ ብለውታል]

በጊዜ ወደ መስጂድ መግባት
ከአቢሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል:- “በእለተ ጁምዓ ለጀናባ የሚታጠብ አይነትን ትጥበት የታጠበ፣ ከዚያም (ወደ መስጂድ) የተጓዘ ሰው ልክ ግመል ለሶደቃ እንዳቀረበ ነው፣ በሁለተኛው ጊዜ ወደ መስጂድ የተጓዘ ሰው ልክ ለሶደቃ ከብት (ላም) እንዳቀረበ ነው፣ በሶስተኛው ጊዜ የተጓዘ ሰው ልክ ቀንዳማ የሆነ ሙክት እንዳቀረበ ነው፣ በአራተኛው ጊዜ ወደ መስጂድ የተጓዘ ሰው ለሶደቃ ዶሮ እንዳቀረበ ነው፣ በአምስተኛው ጊዜ ወደ መስጂድ የተጓዘ ሰው ለሶደቃ እንቁላል እንዳቀረበ ነው፣ ኢማሙ ሚንበር ላይ ከወጣ መላኢካዎች ኹጥባውን ለማዳመጥ ይሳተፋሉ።” [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል]

መስጂድ ከገቡ በኋላ በሁለት ሰዎች መካከል አለመለያየት (በሁለት ሰዎች ትከሻ ላይ አለመረማመድ)
ጃቢር ኢብን ዐብደላህ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዲህ አለ:- የአላህ መልእክተኛ ﷺ እየኾጠቡ እያለ አንድ ሰው ገባ፣ ሰዎች ላይ እየተረማመደ ነበርና የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ አሉት:- “ቁጭ በል! በእርግጥም አስቸግረሃል አርፍደሃልም።” [ኢብን ማጀህ 923 ላይ የዘገቡት ሲሆን አልባኒ ሀሰን ብለውታል]

ሱረቱል ከህፍን መቅራት (ማንበብ)
ከአቢ ሰዒድ አል-ኹድሪይ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል:- “በእለተ ጁምዓ ሱረቱል ከህፍን ያነበበ ሰው በእርሱና በበይተል ዐቲቅ መካከል ብርሃን ይበራለታል።” [አልባኒ በሶሂሁል ጃሚዕ 6471 ላይ ሶሂህ ነው ብለውታል።]

ዱዓ ማብዛትና በእለተ ጁምዓ ዱዓ ተቀባይ የሚሆንባትን ሰኣት መጠባበቅ
ዐብደላህ ኢብኑ መስዑድ (ረዲየላሁ ዐንሁ) የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል አለ:- “የጁምዓ ቀን አስራ ሁለት ሰኣት ነው፣ ከእርሷ ውስጥ አንዲት ሰኣት አለች ሙስሊም የሆነ ባሪያ በዚያች ሰኣት አላህን ከጠየቀ አላህ የጠየቀውን ይሰጠዋል፣ (ያቺን ሰኣት) በመጨረሻ ሰኣት ከአስር በኋላ አካባቢ ፈልጓት።” [ሶሂሁል ጃሚዕ 8190 ላይ አልባኒ ሶሂህ ነው ብለውታል።]

ከአነስ ኢብን ማሊክ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል:- “የዱዓ ተቀባይነት የሚከጀልባትን ሰኣት ከአስር በኋላ ፀሀይ ወደ መግቢያዋ እስከምትቃረብ ድረስ ባለው ጊዜ ፈልጓት።” [ትርሚዚይ 1237 ላይ የዘገቡት ሲሆን አልባኒ ሀሰን ብለውታል።]

በነቢዩ ﷺ ላይ ሶለዋት ማብዛት
ከሶፍዋን ኢብን ሱለይም (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል:- “የጁምዓ ቀን እና የጁምዓ ሌሊት ከሆነ (ከገባ) በኔ ላይ ሶለዋት አብዙ።” [በሶሂሁል ጃሚዕ 776 ላይ አልባኒ ሶሂህ ብለውታል።]

ማሳሰቢያ:- ይህ ተግባር የሚመለከተው ወንዶችን ነው። በተለይ ሽቶ ተቀብቶ መውጣት ለሴት ልጅ ሙሉ በሙሉ ሀራም ነው። ሴቶች ምንም አይነት ጌጣጌጥ ያለውን እና ወንዶችን ሊፈትን የሚችል ልብስም ሆነ ሽታ ያለው ቅባትና ሽቶ ሳይጠቀሙ ሙሉ በሙሉ የሴቶችን ሸሪዓዊ ስርኣት ያሟላ አለባበስ ለብሰው በአደብ ወደ መስጂድ መሄዱ አይከለከሉም።
✍🏻ኢብን ሽፋ (t.me/ibnshifa)
የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa


ለወራቤ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች 🎤 ማይክራፎን ለመግዛት የተቋቋመ ጊዜያዊ ግሩፕ dan repost
ለየት ያለ ደማቅ ፕሮግራም
➩➪➩➪➩➪➩

አሰላሙአለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱህ

✍🏻 የተከበራችሁ የሱና ቤተሰቦች ሆይ በአላህ ፍቃድ በመጪው ጁምዓ ምሽት ለየት ያለ ፕሮግራም አዘጋጅተናል።

ፕሮግራሙ ቃለ-መጠየቅ ሲሆን
🔎 ርዕሱ ፦ ስለ ሸይኽ አቡ ዘር ኪታብ ሲሆን
ጠያቂዎች ወንድማችን አቡ ዘከሪያ እና አቡ ዒምራን ሲሆኑ
🪑 ማብራሪያ የሚሰጡት ደግሞ የተከበሩ ሸይኻችን ሸይኽ አቡ ዘር ሀሰን አቡ ጦልሃ ይሆናሉ።

የውይይቱ መድረክ

➴➘➴➘➴➘
https://t.me/WRU_Selefy_Students

🗓 በቀጣይ ዕለተ-ጁምዓ 3:00 አካባቢ ቆይታችሁን ከኛ አድርጉ!

የወራቤ ዩኒቨርስቲ አል-አቅሷ ጀመዓህ

🏝 𝙖𝙙𝙙 👉 𝙟𝙤𝙞𝙣 👉 𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚
t.me/WRU_Selefy_Students
t.me/WRU_Selefy_Students
t.me/WRU_Selefy_Students


Bahiru Teka dan repost
👉 ልዩ ፕሮግራም

የፊታችን ማክሰኞ የካቲት 4/2017 በእነሞር ወረዳ አጋታ ቀበሌ ጃቢር መስጂድ ተማሪዮችን ታሳቢ ያደረገ የዳዕዋ ፕሮግራም ተዘጋጅቷል።

በዚህ ፕሮግራም ላይ ውዱ ሸይኻችን ሸይኽ ዐ/ሐሚድ ይገኛሉ። በተጨማሪም ወንድማችሁ ባሕሩ ተካና ዐ/ሰመድ በድሩ ይገኛሉ።

https://t.me/bahruteka




🚨 ታላቅ እና አስደሳች የምስራች!

እነሆ የፊታችን ጁሙዓ ሻዕባ 08 ጥር 30 2017 E.C ጀምሮ እስከ እሁድ ሻዕባን 10 የካቲት 02 ድረስ የሚቀጥል በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ አማካኝነት የተሰናዳ የ wellcom (የእንኳን ደህና መጡ) የኮርስ እና የዳዕዋ ፕሮግራም ተሰናድቶ ይጠብቃቹሀል። በዚህ ፕሮግራም ላይ በርካታ ምክሮች እና እውቀቶች እንደምታገኙ ተስፋ እናደርጋለን።

⌚️ የፕሮግራሙ ዝርዝር ሰአታት እንደሚከተለው ይሆናል

1, ጁሙዓ ከመግሪብ እስከ ዒሻእ ኮርስ
2, ቅዳሜ ከፈጅር ቡሀላ እስከ 02:00 ኮርስ
3, ቅዳሜ ከ 03:00 ጀምሮ እስከ ዝሁር ወይም 07:00 ድረስ የዳዕዋ ፕሮግራም
4, ቅዳሜ ከ ዐሱር ሶላት ቡሀላ ኮርስ
5, እሁድ ከጠዋቱ 03:00 ጀምሮ እስከ ዝሁር ድረስ ኮርስ ይኖረናል!

🎤 በቅዳሜው የዳዕዋ ፕሮግራም የሚሰየሙ ተጋባዥ እንግዶች

1, ኡስታዝ አብራር አወል (አቡ ዑበይዳህ) ሀፊዘሁላህ ከአዲስ አበባ
2, ኡስታዝ ኑራዲስ (አቡል በያን) ሀፊዘሁላህ ከቡታጅራ
3, ወንድም ሙሀመድ (አቡ ዘከሪያ) አል-ወልቂጢይ ሀፊዘሁላህ ከሌራ

📙 የኮርሱ ኪታብ አና አስተማሪ

* የኪታቡ ስም፦ "ከይፈ ነስተቅቢሉ ሸህረ ረመዳን"

* አዘጋጅ፦ ዶክተር ሸይኽ አቡ ሙሀመድ ሁሰይን ቢን ሙሀመድ አስ’ሲልጢይ ሀፊዘሁላህ

* አስተማሪ፦ ወንድም አቡ ዘከሪያ ሙሀመድ ዐብዲላህ አል-ወልቂጢይ ሀፊዘሁላህ

🕌 ቦታ ወይም አድራሻ

ጉብርየ ክፍለ ከተማ በኤዋን ቀበሌ ከኤዋን ህንፃ በግራ በኩል ገባ ብሎ በሸሄ መንደር ሰዕድ መስጂድ

አስተውሉ፦ ለወንዶችም ለሴቶችም በቂ ቦታ ስላለ እንዳይጨነቁ። የኮርሱ ኪታብ እዛው ይከፋፈላል 15 ብር ብቻ አዘጋጅታችሁ ኑ!

http://t.me/Deawaaselefiyah
http://t.me/Deawaaselefiyah


الرد على يحيى الحجوري.pdf
782.9Kb
👉 አዲስ pdf   

عنوان:- الرد على يحيى الحجوري

للشيخ الفاضل الدكتور حسين بن محمد بن عبد الله الإتيوبي السلطي حفظه الله

✍🏻አዘጋጅ:- ሸይኽ ዶ/ር ሑሰይን ኢብኑ ሙሀመድ ኢብኑ ዐብደላህ አስ-ስልጢ (ሀፊዘሁላህ)

Pdf ን ለማግኘት👇👇
https://t.me/IbnShifa/4730

(ዐረቢኛ የምትችሉ pdf ን አውርዳችሁ አንብቡት፣ የምታቀሩም አቅሩት)

#join ⤵️ ቴሌግራም ቻናል
https://t.me/HussinAssilty
https://t.me/HussinAssilty


هذا الرد قبل أربع سنوات تقريبا وكان محمد حسن مامي يتألم من رد السلفيين على الإخوان المسلمين(وكل إناء بما فيه ينضح) فاليوم أعلن انضمامه إليهم. وفي هذا البحث ذكر ابن منور وسادات قبل أن ينحرفا فاليوم ابن منور كهف التمييع وحاطب ليل في نشر شبهات أهل التمييع والتجميع كما بينا مرارا وهو أخس من إلياس ومحمد حسن مامي . اللهم ثبتنا على المنهج السلفي حتى نلقاك

🔸ይህ ምላሽ ተፅፎ ከተለቀቀ ወደ አራት አመት አካባቢ ይጠጋል፣ ሙሀመድ ሀሰን ማሜ ሠለፊዮች በኢኽዋኑል ሙስሊሚን ላይ ምላሽ ሲሰጡ ይታመም ነበር፣ "ሁሉም እቃ በውስጡ ያለውን ነው የሚረጨው" እንደሚባለው ዛሬ ላይ ወደ አል ኢኽዋኑል ሙስሊሚን መካተቱን (አንድ ላይ መሆኑን) ግልፅ አድርጓል።

በዚህ ጥናታዊ ፅሁፍ (ምላሽ) ላይ የኢብኑ ሙነወርና የሳዳት መጠቀስ በወቅቱ ጠንካራ አቋም ላይ እያሉና ወደ ቢድዐህ ከመዘንበላቸው በፊት ነው፣ ዛሬማ የሙነወር ልጅ የተምይዕ ዋሻ ነው፣ የመሰብሰብና የተምይዕ ባለቤቶችን ብዥታ በመበተን ረገድ ወደር የሌለው የሌሊት እንጨት ሰብሳቢ ነው። (በሌሊት በጭለማ ለማገዶ እንጨት የሚሰበስብ ምኑንም ከምኑም ሳይለይ ትላትል እባብም ሊሰበስብ ይችላል ማለት ነው)
በተደጋጋሚ እንዳብራራነው ከኢልያስ አህመድና ከሙሀመድ ሀሰን ማሜ የከፋ ሆኗል።

አላህ ሆይ! በመንሀጀ'ሰለፍ ላይ አንተን እስክንገናኝ ድረስ አፅናን!!

ሸይኽ ዶ/ር ሑሰይን አስ-ሲልጢ (ሀፊዘሁላህ)

#Join ⤵️ ቴሌግራም ቻናል
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa


[ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa] dan repost
الرَّدُ_الحَسَنُ_عَلَى_ابْنِ_مامِي_مُحَمَّدِ_بْنِ_حَسَنِ_.pdf
364.4Kb
الرَّدُ الحَسَنُ عَلَى ابْنِ مامِي مُحَمَّدِ بْنِ حَسَنِ

الشيخ حسين بن محمد السلطي

ለ ሙሀመድ ሀሰን ማሜ የተሳሳተ አመለካከት የተሰጠ መልስ

የታላቁ ዓሊም ሸይኽ ረቢዕ እና በቅርብ ወደ አኼራ የሄዱት የታላቁ ዓሊም ሸይኽ ሙሀመድ ዐሊ አደም ተማሪ በሆነው በሸይኽ ሑሰይን ኢብኑ ሙሀመድ ኢብኑ ዐብደላህ አስ-ስልጢ

(ዐረቢኛ የምትችሉ pdf ን አውርዳችሁ አንብቡት)
https://telegram.me/IbnShifa


ስንት አለ…?!
አጋር የሚፈልግ ሚረዳው ከፊቱ
አብሽር ባይ የሚመኝ ተቀምጦ ከቤቱ
ካጠገቡ ሚሆን ሚጋራው ጭንቀቱን
መናገሩን ፈርቶ ሚሰማውን ስሜቱን
መውጣት እና መውረድ ቁልቁለት ዳገቱን
ፈርቶ ዝም ያለ ሰው አቀርቅሮ አንገቱን
አለሁ አብሽር ሚለው ከልብ ካንደበቱ
ሚከጅል ብዙ ነው ከወንድም ከሴቱ

ከገንዘብም በላይ ከጥቅምም በላይ
ችግር የሰፋበት ከሁሉም በላይ
ከሁሉ አብልጦ የሚሻ አይዞህ ባይ
ስንት አለ ከቤቱ የሚጠብቅ አባባይ

ችግሮችህ ቢገዝፉ አክለው ተራራ
ኢንሻ አላህ ያልፋሉ ሁሉም በየተራ
ታገስ አንተ ብቻ በአላህ አታጋራ
ማያልፍ አይምሰልህ ዘንቦ ማያባራ

አንተ ብቻ ሁን የተውሒድ አርበኛ
ሱናን አጥብቀህ ያዝ የዲኑ ዘበኛ

አላህ ሁን ካላለው ሊጠቅም        ካላከው
ማንም ሰው አይጠቅምም ፍቃዱን ካልሰጠው

ችግሩ ቢያይል ከእይታችን       አልፎ
በቅርብ እናያለን አንድ በአንድ ተቀርፎ

ኢንሻ አላሁ ታዓላ...............
                                 ኮፒ
#Join ⤵️ ቴሌግራም ቻናል
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa


አዲስ ሙሃደራ

🎤 ኡስታዝ በህሩ ተካ

🗓   ጥር25/05/2017

    👉 በቀቤና ልዩ ወረዳ

  🕌  ቃጥባሬ አሊፍ መስጅድ
        የተዳሠሡ ነጥቦች

✅ ለተውሂድ የተከፈለ ዋጋ

✅ የሁዘይፋ ሀዲስ የተብራራበት

✅የሙስአብ ኢብኑ ኡመይር ታሪክ

✅ለዲኑ ሲል ከሀብት ማማ
ወደ ድህነት ወለል መውረድ

✅ እንዲሁም ከሞተ በኋላ ከፈን
እስማጣት ደረሠ

✅ እኛ ያለንበትን ጭልጥ ያለ
እንቅልፍ መሆናችንን ፍንትው
አድርጎ ያሳየ ሙሃደራ ነው

👉 እናም ሁላችንም በትኩረት
አዳምጠን እራሣችንን
እንመርምርበት



   

https://t.me/DarAnnedwa


Bahiru Teka dan repost
👉   በቀብር ላይ ጠዋፍ

   ጠዋፍ ማለት መዞር ማለት ሲሆን በተለያየ መልኩ ሊከሰት ይችላል ። በአንድ ነገር ዙሪያ መሄድ ጠዋፍ ይባላል ። ሀገር ለሀገርም መሄድ ጠዋፍ ይባላል ይህ ቋንቋዊ ትርጓሜው ሲሆን በሸሪዓ የሚፈለግበት ካዕባን በመዞር አላህን መገዛትን ነው ። አላህ ይህን አስመልክቶ ባሮቹን ዚያዝ እንዲህ ይላል : –

"  وَلْيَطَّوَّفُوا بِالْبَيْتِ الْعَتِيقِ "
                     الحج  ( 29 )

{  በጥንታዊውም ቤት ይዙሩ } ፡፡ 

    ጠዋፍ እንደየአድራጊው ንያ ብይኑ ይለያያል ። – አላህን የሚገዙበት ዒባዳ ይሆናል ።
– ከእስልምና የሚያወጣ ሽርክ ሊሆን ይችልል ።
– ከባድ ወንጀል ሆኖ ከሽርክ በታች ሊሆንም ይችላል ።

↪️  አላህን የሚገዙበት ዒባዳ የሚሆነው በካዕባ ዙሪያ በዒባዳ ንያ ሲደረግ ብቻ ነው ። ከካዕባ ውጪ በዒባዳ ንያ ጠዋፍ ማድረግ አይፈቀድም ።
↪️  ከእስልምና የሚያወጣ ሽርክ የሚሆነው በቀብር ላይ ወደተቀበረው አካል ለመቃረብ ተብሎ ሲደረግ ነው ። በቀብር ላይ ጠዋፍ ማድረግ በጣም አሳዛኝና አስከፊ ተግባር ከመሆኑም በላይ ጠዋፍ አድራጊው ከብዙ የአላህ ፀጋዎች የራቀ በተቃራኒው ወደ አላህ ቁጣ የቀረበ ነው ።
   አላህ ለባሮቹ ከሰጠው ፀጋ ዋነኛው በካዕባ ዙሪያ ለአላህ ራሱን አስገዝቶ ወደ ጌታው በሁለመና ቀርቦ ከዐለም ከሚመጡ ወንድሞቹ ጋር ልቡ በፍሳሃ መልቶ ዒባዳ ማድረጉ ነው ። ይህን ፀጋ የሚያውቀው እዛ ቦታ ላይ ለመቆም ከጌታው የተመረጠ ሰው ነው ። ቀብር ላይ ጠዋፍ የሚያደርግ ሰው የዚህ አይነቱ ፀጋ በራሱ ላይ እርም ያደርጋል ። ልቡ በኢማን ከሞሞላት ይልቅ በሽርክና ኩፍር ጨለማ ይሞላል ። 
    በጣም የሚያሳዝነው አላህ የኢስላምን ፀጋ ካሳወቀው በኋላ ወደ ቀብር አምልኮ ገብቶ ፈጣሪን ከማምለክ ፍጡርን ወደ ማምለክ መሸጋገሩ ነው !!!!!! ።
    ሰው አላህ ለቅናቻ ልቡ ከፍቶለት ላ ኢላሀ ኢልለላህ ካለ በኋላ መልሶ ወደ ኩፍር ጨለማ መሄዱ ምን እንደሚባል ግራ ይገባል ።
     ይበልጥ የሚገርመው ይህን ተግባር ኢስላም ነው ብለው ተውሒድን ኩፍር ማለታቸው ነው ። የተውሒድ ተጣሪዎችን የነብዩን ዲን የሚያጠፉ እያሉ ስም ማጥፋታቸው ደግሞ ገርሞ የሚገርም ነው ።
↪️  ከሽርክ በታች ያለ ወንጀል የሚሆነው ደግሞ አንድ ሰው ከቀብር አምላኪዎች ጋር በጭንቅንቁ ውስጥ ኪስ ገብቶ ለማውጣት ( ለመስረቅ ብሎ) ጠዋፍ ሲያደርግ ነው ።
   የሚገርመው ካዕባ ላይም ለዚህ አላማ ብሎ ጠዋፍ የሚያደርግ መኖሩ ነው ። ይህ ሰው በሁለቱም ቦታዎች ንያው ሌብነት በመሆኑ ከባድ ወንጀል ውስጥ ይገባል ።
    በቀብር ላይ የሚደረግ ጠዋፍ ፍጡርን ከማምለክ በተጨማሪ የሁለት ሀገር ኪሳራ የሚያስከትል ለውድቀት ሰበብ የሚሆን ተግባር ነው ።
   የኢስላም ጠላቶች ሙስሊሞችን ለማሸነፍ የነደፏቸው ስልቶች ሁሉ በእነዚያ ብርቅዬ ትውልዶች ሶሓቦች ፊት መና ሆኖ ሲቀር ። ሚስጥሩን ለማወቅ ብዙ ጊዜ ቢፈጅባቸውም መጨረሻ ላይ የእነዚያ የኢስላም የበኩር ልጆች የማሸነፍ ሚስጥር በውስጣቸው ያለው የተውሒድና የኢማን ሀይል መሆኑን ስለደረሱበት    የመጨረሻውና ውጤታማ የሆኑበት እስትራቴጂ ለሙስሊሞች የቀብር አምልኮን ደጋግ የአላህ ባሮችን መውደድ በሚል አላህን ከማምለክ ሙታንን ወደ ማምለክ በማሸጋገር የቀብር አምላኪዎች ማድረግ ነበር ።
   ይህ ተግባር ከአይሁዳዊው ዐብዱላህ ኢብኑ ሰበእ የሺዓዎች መስራች የጀመረ ሲሆን እስካሁንም የኢስላሙን ዐለም አጥለቅልቆ ይገኛል ።
    ዐብዱላህ ኢብኑ ሰበእ የነብዩን ቤተሰቦች እንወዳለን በሚል ወደ ቀብር አምልኮ ሙስሊሞችን በማዞር የተዋጣለት ስራ ሰርቶ ለሚቀጥለው ትውልድ ሽርክን እንደ ቅርስ አበርክቶ ነው የሄደው ።
   ከዛ በኋላ ሱፍዮች ይህን ቅርስ አንስተው የቁርኣንና ሐዲስን ቅርስነት ጥለው የቀብር አምላኪዎች ሆኑ ። ሙስሊሙንም ወደ አላህ አምልኮ ከመጣራት ይልቅ ወደ ወልይ የሚሏቸው የሸይጣን ወዳጆች አምልኮ ተጣሩ ። በዚህም ሙስሊሞች ከልባቸው የአላህ ፍርሃትና የኢማን ሀይል ወጥቶ ተራ የሚንቀሳቀስ አካል ሆኑ ።
    በዚህም የኢስላም ጠላቶች ህልማቸው እውን ሆነ በስፋት ኢንቨስት ማድረግም ጀመሩ ። ብዙ የሽርክ ፋብሪካዎችን ከፈቱ ከኢስላም ልጆችም የሚፈልጉትን መጠን ለፋብሪካቸው ቀጠሩ ።
    ቀብር አምልኮትም በሚገርም ሁኔታ የተውሒድን ቦታ አስለቅቆ ባላባት በመሆን ተውሒድ ጭሰኛ እንዲሆን አደረገው ።
     አሁንም ይህ እውነታ የሙስሊሙን ዐለም አጥለቅልቆት ይገኛል ። የተውሒድ ሰራዊቶች ዋጋ ከፍለው ተውሒድን ወደ ቦታው መመለስ ይኖርባቸዋል ። ይህ ሲሆን የኢስላም ጠላቶች ይከስራሉ ሙስሊሞች የበላይ ይሆናሉ ።
    አላህ በተውሒድ የበላይ የምንሆን ያድርገን ።

https://t.me/bahruteka


↪️ ታላቅ የምስራች

እነሆ የፊታችን ቅዳሜ ሻዕባን 09 ወይም የካቲት 01 2017 E.C በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ አማካኝነት የተሰናዳ የ wellcom (የእንኳን ደህና መጡ) ፕሮግራም ተደግሶ ይጠብቃቹሀል።

🎤 በእለቱ የሚሰየሙ ተጋባዥ እንግዶች

1, ኡስታዝ አብራር አወል (አቡ ዑበይዳህ) ከአዲስ አበባ
2, ኡስታዝ ኑራዲስ (አቡል በያን) ከቡታጅራ
3, ወንድም ሙሀመድ (አቡ ዘከሪያ) አል-ወልቂጢይ ከሌራ

⌚️ ቀን እና ሰአት

ቅዳሜ ከ 02:30 ጀምሮ እስከ ዝሁር ሶላት ወይም 07:00 ድረስ ነው በግዜ ለመገኘት ሞክሩ!

🕌 ቦታ ወይም አድራሻ

ጉብሬ ክፍላ ከተማ በኤዋን ቀበሌ ከኤዋን እንፃ በግራ በኩል ገባ ብሎ በሸህ መንደር ሰዓድ መስጂድ

አስተውሉ፦ ለወንዶችም ለሴቶችም በቂ ቦታ ስላለ እንዳይጨነቁ።

t.me/Deawaaselefiyah
t.me/Deawaaselefiyah


Abu abdurahman dan repost
ታላቅ የምስራች በአይነቱ ልዩ እና አጓጊ ታላቅ የሙሓደራ ድግስ በአዳማ ከተማ



    እነሆ የፊታችን እሁድ የካቲት 2/2017 በአዳማ ከተማ 03 ቀበሌ በመደረሰቱል ፈትህ ወነስር ልዩ የሙሐደራ እና ደማቅ የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ተዘጋጅቶ ይጠብቃችኋል ።

     የእለቱ ተጋባዥ እንግዶች : –

①ታላቁ እና ተወዳጁ ዶ/ር ሸይኽ ሑሰይን ብን ሙሐመድ አስልጢይ (ሀፊዘሁሏህ)

②ተወዳጁ ዳዒ ኡስታዝ ሻኪር ሱልጣን (ሀፊዘሁሏህ)
  
በአሏህ ፍቃድ ሌሎችም ይኖራሉ

     ፕሮግራሙ በአላህ ፈቃድ ከጠዋቱ 2 : 30 የጀመራል ። 

https://t.me/adama_ahlusuna_weljemea


ከዚክር ትሩፋቶች
———
ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያ (ረሂመሁላህ) እንዲህ አሉ:-

በእርግጠኛነትና በእውነተኛነት ላ! ኢላሀ ኢለላህ ብሎ ምስክርነት መስጠት፣ ሺርክን ትልቁንም ትንሹንም፣ሆን ተብሎ የተፈፀመውንም በስህተት የተፈፀመውንም፣ የመጀመሪያውንም የመጨረሻውንም፣ ድብቁንም ግልፁንም፣ ከሁሉም (መጥፎ) ባህሪ ቀለል ያለውንም ደቃቁንም ታስወግዳለች።

ኢስቲግፋር ከሺርክ የቀሩ እንጥብጣቤዎችን እና ከሺርክ ቅርንጫፍ የሆኑ ወንጀሎችን ያብሳል፣ ወንጀል ሁሉ ከሺርክ ቅርንጫፍ ነው።
ተውሒድ የሺርክን መሰረት ያስወግዳል። ኢስቲግፋር ደግሞ ቅርንጫፉን ያስወግዳል።
የውዳሴ ጥጉ ላ! ኢላሀ ኢለላህ ማለት ሲሆን የዱዓ ጥጉ ደግሞ አስተግፉሩላህ ማለት ነው።
” [መጅሙዕ አልፈታዋ 11/697]
✍ ኢብን ሽፋ (t.me/ibnshifa)
#Join ⤵️ ቴሌግራም
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa


የሴት ልጅ መስተካከልና መበላሸት በባሏ ላይ ከባድ ተፅእኖ ያሳድራሉ!!
—————

➡️ ሀሰኑል በስሪይ (አላህ ይዘንላቸውና) እንዲህ ይላሉ:-

መካ ውስጥ ልብስ ሻጭ የሆነ አንድ ሰው ዘንድ ልብስ ለመግዛት ቆምኩኝ፣ እየማለ ልብሱን ማወደስ ጀመረ፣ ይህን ጊዜ ከሱ መግዛቱን ተውኩት። ከእንደዚህ አይነት ሰው መግዛቱም ተገቢ አይደለም አልኩና ከሌላ ሰው ገዛሁኝ። ከዚያም  ከሁለት አመት በኋላ (ወደዚያው) ጉብኝት  አደረግኩ፣ እርሱ ዘንደም ቆምኩኝ፣ እየማለም እያወደሰም ሆኖ አላገኘሁትም፣ ለርሱም እንዲህ አልኩት:- ያ  ከአመታት በፊት ያገኘውህ ሰው አይደለህምን? አዎ ነኝ አለ፣ ከዚህ በፊት ከነበርክበት ሁኔታ አሁን ወደ ምመለከትህ ሁኔታ ምን አወጣህ? እየማልከና እያወደሰክም ሆነህ አላይህም፣ አልኩት።

እንዲህ በማለት መለሰ:-
1⃣ ለኔ አንዲት ሚስት ነበረችኝ፣ ትንሽ ነገር ይዤ ስገባ የምታመናጭቅና አሳንሳ የምትመለከት፣ ብዙም ይዤ ስገባ አሳንሳ ተየዋለች፣ ከጊዜ በኋላ ሞተች።

2⃣ ከሷ በኋላ ሌላ ሴት አገባሁ፣ ወደ ሱቅ መውጣት ስፈልግ ልብሴን ይዛ "እገሌ ሆይ! አላህን ፍራ ጥሩ ነገር እንጂ አትመግበን፣ ትንሽ ብታመጣልን ብዙ አድርገን እንቆጥረዋለን/እናብዛዘዋለን፣ ምንም ይዘህ ባትመጣ እንኳን እናግዝሃለን።" ትለኛለች።
[ምንጭ:- አል ሙጃለሰቱ ወጀዋሂር አል-ዒልም 5/251]

↪️ ጥያቄ ለእህቶቼ፣ ለመሆኑ እናንተ ከየትኛዋ ሴት ናችሁ ከመጀመሪያዋ ወይስ ከሁለተኛዋ???
መልሱን… ለአላህ ብላችሁ ከልባችሁ ቆም ብላችሁ በማሰብ ለራሳችሁ መልሱት!።

ከመጀመሪያዋ የሆናችሁ አላህን (ተባረከወተዓላ) ፈርታችሁ ተፀፅታችሁ ወደ ሁለተኛዋ ተመለሱ!!

ከሁለተኛዋ የሆናችሁ ሸይጧን ድንበር እንዳያሳልፋችሁ ነፍሳችሁን ዝቅ እንድትልና ከጌታዋ ከጃይ እንድትሆን አድርጓት!። አላህ ፅናት እንዲሰጣችሁም የዘውትር ዱዓችሁ ይሁን!! ምክንያቱም ይህ እጅግ በጣም ከባድ ነገር ነውና‼

ባል ሆይ! ለቤተሰብህ ሀራም አታብላ!! የሚስትህንና ልጆችህን ሰውነተ በሀራም አትገንባ!!
የትውልዱ መበላሸት አንዱ ምክንያት ሰውነት በሀራም መገንባቱ ነው!!

ሚስት ሆይ! ባልሽ ከነ ልጆችሽ ሀራም እንዳያበላሽ አደራ በይው!! በሀላሉ አምጣ እንጂ ትንሹም ይበቃል ብለሽ በትንሹም ተብቃቂ!!

ተቅዋ (አላህን መፍራት) ማለት በትንሹ መብቃቃትና ለቀጣዩ አለም መዘጋጀት ማለት ነውና!! አንገብግበሽ አንቺንም ልጆችሽንም ሀራም እንዲያበላችሁ አታድርጊው!!
✍ኢብን ሽፋ: (t.me/ibnshifa)

የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa




የቢድዐህ ባለ ቤቶችን መለያየት አይክበዳችሁ!!
———
ታላቁ የኢስላም ሊቅ ኢብኑ'ል ቀይም (ረሂመሁላህ) የሚከተለውን የቁርኣን አንቀፅ አውስተው እንዲህ አሉ:-
{احْشُرُوا الَّذِينَ ظَلَمُوا وَأَزْوَاجَهُمْ} الصافات ٢٢
«እነዚያን ነፍሶቻቸውን የበደሉትን ሰዎች ጓደኞቻቸውንም ሰብስቡ፡፡” በተባለ ቀን ጓደኛ ከመሆን በአላህ ይሁንብኝ በዚህ ሀገር የቢድዐህ እና የስሜት ባለ ቤቶችን መለያየት ቀላል ነው።» [አል-ካፊየቱ ሻፊያ…]

ኢማሙ'ል አል-ባኒይ (ረሂመሁላህ) እንዲህ አሉ:-
በብቸኝነት ምንም አይነት ግኑኙነትና የሚያሰባስብ ነገር የሌለን ሆነን መሞት ለኛ የተሻለ ነው በአንዲት ነጥብ አላህንና መልክተኛውን ከምናምፅ። ለእኛ በጥመት ከመሰባሰብ ቁርኣንና ሀዲስን በመፃረር ላይ በሚያዘጋጁት መንገድ፣ ሸሪዓውን የሚፃረር መሆኑን እያወቁ ከትእዛዙ ብዙውን እያመፁ ከእነሱ ጋር ከመሰባሰብ ብቸኝነት በላጭ ነው።” [ሲል ሲለቱል ሁዳ ወንኑር]

የየመኑ ሙሀዲስ በመባል የሚታወቁት ሸይኽ ሙቅቢል ቢን ሓዲ'ል ዋዲዒይ (ረሂመሁላህ) እንዲህ አሉ:-
ሠለፊይ የሆነ ሰው: የተሰጠውንም ያህል (ጥቅምና ገንዘብ) ቢሰጠው ሱናን፣ ደዕዋን አይሸጥም! እሷ ከገንዘብም ከዝምድናም ከሁሉም ነገር በላጭ ናት!!።” [አል ኢማም አል'መዒይ 253]

ስንቱ ነው "አገሌኮ የረጅም ጊዜ ጓደኛዬ ነው፣ አገሌማ ቤተሰብ ስለሆነ ነው፣ አገሌማ ወደ ሱንና ለመምጣት ሰበብ ሆኖኛል…" እያለ በጭፍን ወደ ቢድዐህ እና ጥመት የሰመጠው?! ወደ ሱንና እንድትመጣ ሰበብ ቢሆንህም ሱንናን ከተወ እሱን ትተህ ሱናን አጥብቀህ መያዝ ነው!፣ ይህ ጓደኝነትና ቤተሰባዊነትም ከሐቅ ከተቀደመ ነገ አላህ ፊት ያዋርዳል!! ሐቅ ከሁሉም በፊት ቀዳሚ ነው!! ፈፅሞ ከሐቅ ጋር የሚወዳደር ነገር የለም!!

በዚህ ወቅት ስንቱ ነው ሱናን ለገንዘብ፣ለክብርና ለዱኒያ ጥቅማጥቅም ሽጦ ትላንት ያውቀው የነበረውን ሐቅ መልሶ ሲተች፣ ትላንት ያወግዘው የነበረውን ባጢል መልሶ ሲያደንቅና እውቅና ሲሰጠው የሚስተዋለው!! ትክክለኛ ጥመት ማለት ይህ ነው!!
አላህ በሐቅ ላይ ፀንተው ከሚገናኙት ባሪያዎቹ ያድርገን!!
✍🏻ኢብን ሽፋ (t.me/ibnshifa)
#join ⤵️ ቴሌግራም ቻናል
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa




የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ dan repost
የሰይጣን ድንፋታ
 
ባየህ ጊዜ፡-
      የኔዎቹን ክንብንቤ
      የኔዎቹን ሽፍንፍኔ
ባየህ ጊዜ፡-
     የኔዎቹን ጅቡንቡኔ
     የኔዎቹን ዝይንይኔ፤
ለምን ይሆን- አራስ ነብር እንዳየ - አይንህ የሚፈጥ?
ለምን ይሆን - እንጥልህ እስኪወርድ - የም'ደነግጥ?
ለምን ይሆን - በቁጭትህ ማእበል - የምትናወጥ?

እንስቶችህ ሆነው - ለእርቃን ሩብ ጉዳይ
ውብ ገላቸው ሆኖ - የጎዳና ሲሳይ፤
    ሆና እያለች ሚስትህ - በግድ የለበሰች
    ሆና እያለች እህትህ - ለብሳ ያልለበሰች  
    ሆና እያለ አማትህ - ለብሳ እንዳለበሰች
   ሆና እያለች ልጅህ - ለብሳ እንዳወለቀች፤
አክስት፣ እናቶቼ - ስለተከናነቡ
ሚስት፣ እህቶቼ - ስለተሸፋፈኑ
እንስት፣ ልጆቼ - ስለተጀቧቦኑ
በኒቃብ ተውበው - ስለተዘየኑ፤
      ለምን ይሆን የምትለኝ፡-
          "ባህላችን - በዶዘር ፈንጅ ተናደ
          "እሴታችን - በ'ቶን እሳት ነደደ
          "ትውፊታችን - አገር ጥሎ ተሰደደ"?
ከዚህ ወዲያ ምን አለ?
የጋኔን ሹክሹክታ
የሰይጣን ድንፋታ፡፡

ካይን፣ ከከንፈር ላይ - የሚሰነቀሩ
ከፊት፣ ከጡት ላይ - የሚቸነከሩ
ከፀጉር፣ ዳሌ ላይ - የሚተከሉ
ከባት፣ ተረከዝ ላይ - የሚቸከሉ
       የዝሙት ቀስቶች
       ያመንዘራ ጦሮች
       የሰይጣን አረሮች
መክነው ውለው - መክነው ስላደሩ
ከስረው ሰንብተው - ከሽፈው ስለቀሩ?
      እንዴት ትለኛለህ፡-
         "ባህላችን - በዶዘር ፈንጅ ተናደ
         "እሴታችን - በ'ቶን እሳት ነደደ
        "ትውፊታችን - አገር ጥሎ ተሰደደ"?
ከዚህ ወዲያ ምን አለ?
የጋኔን ሹክሹክታ
የሰይጣን ድንፋታ፡፡

እንስቶችህ  ሆነው - እትዬ እርቃን ቀረሽ
                         -  ያልለበሰች ለባሽ
ውብ ገላቸው
  - እንደ ሳልባጅ ጨርቅ - ክፉኛ ተረካክሶ
  - እንደ መኸር ገለባ - በየቦታው ተልከስክሶ
ውብ ገላቸው - ሜዳው አንሶት
          - አደባባይ ጠቦት
         -  ጎዳናው ተፍቶት
በየቀዬ - በየስርጣስርጡ ሲመናሽ
በየጢሻ - በየጉራንጉሩ ሲፍነሸነሽ፤
 
ለምን ትለኛለህ፡-
"ባህላችን - በዶዘር ፈንጅ ተናደ
"እሴታችን - በ'ቶን እሳት ነደደ
"ትውፊታችን - አገር ጥሎ ተሰደደ"?

ከዚህ ወዲያ ምን አለ?
የጋኔን ሹክሹክታ
የሰይጣን ድንፋታ::

በዶክተር ጀማል ሙሃመድ

የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ

https://t.me/alateriqilhaq

كن على بصيرة


[ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa] dan repost
የእለተ ጁምዓ ሱንናዎችና ስርኣቶች
—————
መታጠብና መቀባባት
ከሰልማነል ፋሪሲይ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል አለ:- “አንድ ሰው በእለተ ጁምዓ ታጥቦ፣ ከመፀዳዳትም የቻለውንም ተፀዳድቶ፣ ከሚቀባባ ነገርም ተቀባብቶ፣ ቤቱ ውስጥ ከሚገኝ ሽቶ ተቀብቶ፣ ከዚያም ከቤቱ ወጥቶ በሁለት ሰዎች መካከል ካልለያየ፣ ከዚያም የተፃፈለትን ከሰገደ፣ ከዚያም ኢማሙ በተናገረ ጊዜ ዝም ካለ፣ በዚያች ጁምዓ እና በቀጣዩዋ ጁምዓ መካከል ያለውን ወንጀል ይቅር ይባላል።” [ቡኻሪ 883 ላይ ዘግበውታል]

ከሌላ ጊዜ የተሻለ ቆንጆ የሆነውን ልብስ መልበስ
ከሙሀመድ ኢብን የህያ ኢብን ሂባን (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል:- “አንዳችሁ ለእለተ ጁምዓ ከሌላ ጊዜ የተሻሉ ሁለት ልብሶችን ብይዝ የተሻለ ነው” [አቡዳውድ 1078 ላይ የተዘገበ ሲሆን አልባኒ ሶሂህ ብለውታል]

በጊዜ ወደ መስጂድ መግባት
ከአቢሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል:- “በእለተ ጁምዓ ለጀናባ የሚታጠብ አይነትን ትጥበት የታጠበ፣ ከዚያም (ወደ መስጂድ) የተጓዘ ሰው ልክ ግመል ለሶደቃ እንዳቀረበ ነው፣ በሁለተኛው ጊዜ ወደ መስጂድ የተጓዘ ሰው ልክ ለሶደቃ ከብት (ላም) እንዳቀረበ ነው፣ በሶስተኛው ጊዜ የተጓዘ ሰው ልክ ቀንዳማ የሆነ ሙክት እንዳቀረበ ነው፣ በአራተኛው ጊዜ ወደ መስጂድ የተጓዘ ሰው ለሶደቃ ዶሮ እንዳቀረበ ነው፣ በአምስተኛው ጊዜ ወደ መስጂድ የተጓዘ ሰው ለሶደቃ እንቁላል እንዳቀረበ ነው፣ ኢማሙ ሚንበር ላይ ከወጣ መላኢካዎች ኹጥባውን ለማዳመጥ ይሳተፋሉ።” [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል]

መስጂድ ከገቡ በኋላ በሁለት ሰዎች መካከል አለመለያየት (በሁለት ሰዎች ትከሻ ላይ አለመረማመድ)
ጃቢር ኢብን ዐብደላህ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዲህ አለ:- የአላህ መልእክተኛ ﷺ እየኾጠቡ እያለ አንድ ሰው ገባ፣ ሰዎች ላይ እየተረማመደ ነበርና የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ አሉት:- “ቁጭ በል! በእርግጥም አስቸግረሃል አርፍደሃልም።” [ኢብን ማጀህ 923 ላይ የዘገቡት ሲሆን አልባኒ ሀሰን ብለውታል]

ሱረቱል ከህፍን መቅራት (ማንበብ)
ከአቢ ሰዒድ አል-ኹድሪይ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል:- “በእለተ ጁምዓ ሱረቱል ከህፍን ያነበበ ሰው በእርሱና በበይተል ዐቲቅ መካከል ብርሃን ይበራለታል።” [አልባኒ በሶሂሁል ጃሚዕ 6471 ላይ ሶሂህ ነው ብለውታል።]

ዱዓ ማብዛትና በእለተ ጁምዓ ዱዓ ተቀባይ የሚሆንባትን ሰኣት መጠባበቅ
ዐብደላህ ኢብኑ መስዑድ (ረዲየላሁ ዐንሁ) የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል አለ:- “የጁምዓ ቀን አስራ ሁለት ሰኣት ነው፣ ከእርሷ ውስጥ አንዲት ሰኣት አለች ሙስሊም የሆነ ባሪያ በዚያች ሰኣት አላህን ከጠየቀ አላህ የጠየቀውን ይሰጠዋል፣ (ያቺን ሰኣት) በመጨረሻ ሰኣት ከአስር በኋላ አካባቢ ፈልጓት።” [ሶሂሁል ጃሚዕ 8190 ላይ አልባኒ ሶሂህ ነው ብለውታል።]

ከአነስ ኢብን ማሊክ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል:- “የዱዓ ተቀባይነት የሚከጀልባትን ሰኣት ከአስር በኋላ ፀሀይ ወደ መግቢያዋ እስከምትቃረብ ድረስ ባለው ጊዜ ፈልጓት።” [ትርሚዚይ 1237 ላይ የዘገቡት ሲሆን አልባኒ ሀሰን ብለውታል።]

በነቢዩ ﷺ ላይ ሶለዋት ማብዛት
ከሶፍዋን ኢብን ሱለይም (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል:- “የጁምዓ ቀን እና የጁምዓ ሌሊት ከሆነ (ከገባ) በኔ ላይ ሶለዋት አብዙ።” [በሶሂሁል ጃሚዕ 776 ላይ አልባኒ ሶሂህ ብለውታል።]

ማሳሰቢያ:- ይህ ተግባር የሚመለከተው ወንዶችን ነው። በተለይ ሽቶ ተቀብቶ መውጣት ለሴት ልጅ ሙሉ በሙሉ ሀራም ነው። ሴቶች ምንም አይነት ጌጣጌጥ ያለውን እና ወንዶችን ሊፈትን የሚችል ልብስም ሆነ ሽታ ያለው ቅባትና ሽቶ ሳይጠቀሙ ሙሉ በሙሉ የሴቶችን ሸሪዓዊ ስርኣት ያሟላ አለባበስ ለብሰው በአደብ ወደ መስጂድ መሄዱ አይከለከሉም።
✍🏻ኢብን ሽፋ (t.me/ibnshifa)
የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.