Postlar filtri


የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ስፖርት ፌስቲቫል በታላቅ ድምቀት ተጠናቀቀ።

ጥር 27/2017 ዓ፣ም፤አዲስ አበባ

"ስፖርት ለአንድነት እና ለጋራ ዕድገት"በሚል መሪ ቃል አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ከጥር 17-27 /2017 ዓ፣ም ሲካሄድ የቆየው የኢትዮጵያ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የስፖርት ፌስቲቫል ዛሬ ሲጠናቀቅ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ  በአጠቃላይ ውጤት 9ኛ ሆኖ አጠናቋል።

እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ በዚህ ፌስቲቫል በ4 የስፖርት አይነቶች ማለትም በእግር ኳስ፣በአትሌቲክስ፣በወርልድ ቴኳንዶ እና በባህላዊ ስፖርት ተሳትፎ በባህላዊ ስፖርት ቡብ ጨዋታ ዋንጫ እና ማዳሊያ በማግኘት አንጋፋ እና ነባር ዩኒቨርሲዎችን በመፎካካር በውድድሩ  ከ49 የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች 9ኛ ሆኖ በማጠናቀቅ ስኬታማ ውድድር አሳልፏል።
ይህ ውጤት ከ4ኛ ትውልድ ዩኒቨርሲቲዎች ቀዳሚ ሲያደርገው በአማራ ክልል ከሚገኙ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ከወልዲያ እና ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲዎች በቁጥር 3ተኛ ደረጃ ላይ ሆኖ አጠናቋል  ።
የዚህ ስፖርት ፌስቲቫል አጠቃላይ አሸናፊ እና የዋንጫ ተሸላሚ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሲሆን የፀባይ ዋንጫ አዲግራት ዩንቨርሲቲ ወስዷል ።
በፌስቲቫሉ በባህላዊ ስፖርት ቡብ ጨዋታ ሴት እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ፣በቡብ ወንድ ደብረ ብርሀን ዩኒቨርሲቲ፣በገበጣ ሴት ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፣በገበጣ ወንድ ወልዲያ ዩንቨርሲቲ ፣ ፣በወርልድ ቴኳንዶ  ደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ፣በእግር ኳስ ወሎ ዩንቨርሲቲ፣በቼዝ ሴት አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ፣በቼዝ ወንድ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣አትሌቲክስ ወንድ ሀረሚያ ዩኒቨርሲቲ እና አትሌቲክስ ሴት የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ  የዋንጫ አሸናፊ ሆነዋል።


ያለህን ዕምቅ አቅም ለይተህ ተጠቀም!


“የኢትዮጵያ ህብረብሔራዊ አንድነት ግንባታ ተሞክሮና ተግዳሮት” በሚል ርዕስ ሴሚናር ተካሄደ፡፡

ጥር 27/2017 ዓ.ም፤ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ

በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ በታሪክና ቅርስ አስተዳደር ትምህርት ክፍል “የኢትዮጵያ ህብረብሔራዊ አንድነት ግንባታ ተሞክሮና ተግዳሮት” በሚል ርዕስ በተዘጋጀ ሴሚናር ውይይት ተካሄዷል፡፡

የውይይት መነሻ ጽሑፉን ያቀረቡት የወሎ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ መምህርና ተመራማሪ አለማየሁ እርቅይሁን (ዶ/ር) ሲሆኑ ኢትዮጵያ በመንግስት መዋቅር ስትመራ ቀደምት ሀገር መሆኗን ጠቅሰው ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ብሔርን ያማከለ መንግስት ለመገንባት በሚደረገው ሂደት የሚስተዋሉ ክፍተቶችን በመጠቀም የአንዳንዶችን መብት የሚጥስ ድርጊት ይፈጸማል ብለዋል፡፡ ሀገራችን ኢትዮጵያም ብዝሀነትን የምታስተናግድበት መንገድ ላይ የሚስተዋሉ ክፍተቶችን አንስተው በህብረ ብሄራዊ አንድነት እና ግንባታ ሂደት መፍትሄ ያሏቸውን ሃሳቦችንም ጠቁመዋል፡፡

በሴሚናሩ የተገኙት የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዝደንት ክንዴ ብርሃን (ዶ/ር) የኢትዮጵያን ህረብሔራዊ አንድነት ግንባታ በአተገባበር ላይ የምሁራን ድርሻ በእንዲህ አይነት ትምህርታዊ ጉባኤዎች የኢትዮጵያዊያን አንድነትን የሚያጠነክሩ ጉዳዮችን ማምጣት ይጠበቃል ብለዋል፡፡ እንዲህ ዓይነት ውይይትና ምሁራዊ እይታን ወደ መድረክ ማምጣት ችግሮችን ለመፍታት ወሳኝ ነውም ብለዋል፡፡

በሴሚናሩ መምህራን እና ተመራማሪዎች የተሳተፉ ሲሆን በቀረበው መነሻ ጽሑፍ ላይ አስተያየት እና ጥያቄ ተነስተው ማብራሪያ እና ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል፡፡


እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የዋንጫ አሸናፊ ሆነ ።

በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ከጥር 17-27 /2017 ዓ፣ም ሲካሄድ በቆየው የኢትዮጵያ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች አመታዊ የስፖርት ፌስቲቫል ዛሬ ሲጠናቀቅ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ በባህላዊ ስፖርት በሴቶች የቡብ ፍፃሜ ጨዋታ አሸናፊ በመሆኑ ዩኒቨርሲቲው በመጀመሪያ ተሳትፎው የዋንጫ ተሸላሚ ሆኗል፡፡

ጥር 27/2017ዓ፣ም፤አዲስ አበባ
ያለህን ዕምቅ አቅም ለይተህ ተጠቀም!!


በተማሪ ወላጅ ትስስር ለተማሪ ግዛቸው ተሻለ የላፕቶፕ ኮምፒውተር እና የአልባሳት ድጋፍ ተደረገለት፡፡

በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ አካቶ ትግበራ ሥራ አስፈጻሚ ከሚከናወኑ ተግባራት አንዱ በሆነው በተማሪ ወላጅ ትስስር የህክምና ሳይንስ ተማሪ ግዛቸው ተሻለ ከአቶ መኩሪያ ጎሼ የላፕቶፕ እና አልባሳት ድጋፍ ተደርጎለታል፡፡

የዩኒቨርሲቲው የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ አካቶ ትግበራ ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ባንቻለም ካሴ ክፍሉ ከሚሰራቸው ተግባራት መካከል ኢኮኖሚያዊ ችግር ያለባቸውን ተማሪዎች ለይቶ አስፈላጊውን ድጋፍ እና ክትትል ማድረግ መሆኑን ጠቅሰው ሥራው የሚከናወነውም በጎ ፈቃደኛ የሆኑ አካላትን ጋር ትስስር በመፍጠር ለተማሪዎች አስፈላጊ የሆኑ ቁሳቁሶችን በማሟላት ትምህርታቸውን በአግባቡ እንዲማሩ ማድረግ ነው ብላዋል፡፡
ቀደም ሲል በዚህ ሂደት የተለዩትን ተማሪዎች ከበጎ ፈቃደኛ ወላጆች ጋር የተማሪ ወላጅ ትስስር በመፍጠር ኢኮኖሚያዊ ችግር ያለባቸው ተማሪዎች በተደረገላቸው ድጋፍ መመረቃቸውን ተናግረዋል፡፡ አያይዘውም አሁንም ቢሆን ከ400 በላይ ድጋፍን የሚፈልጉ ተማሪዎች ያሉ በመሆናቸው በዚህ በጎ ተግባር ሁሉም ሰው እንዲሳተፍ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡
ድጋፉን ያደረጉት አቶ መኩሪያው ዛሬ ካደረጉት ድጋፍ በተጨማሪ ተማሪ ግዛቸው ትምህርቱን አስከሚያጠናቅቅ ድረስ በየወሩ 500 ብር እና በአስፈላጊ ነገሮች ሁሉ አግዘው እንደሚያስመርቁት ቃል ገብተዋል፡፡ ድጋፉን የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝደንት አእምሮ ታደሰ (ዶ/ር) በተገኙበት አስረክበዋል፡፡

ጥር 26/2017 ዓ.ም፤ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ



5 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.