ለሴት አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች የህይወት ክህሎት እና የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ተሰጠ፡፡
------
ስልጠናው ሴት አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች በትምህርታቸው እና በህይወታቸው ስኬታማ እንዲሆኑ የሚያግዝ መሆኑ ተገልጿል።
የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ትምህርት እና ስነ-ባህሪይ ኮሌጅ ዲን ገበያው ተሻገር(ዶ/ር) ኮሌጁ በትምህርት ዙሪያ የተለያዩ የአቅም ማጎልበቻ እና የህይህወት ክህሎት ስልጠናዎችን እየሰጠ እንደሚገኝ ጠቅሰው የዚህ ስልጠና ዓላማ ሴት አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች የህይወት ክህሎታቸውን ለማሳደግ እና አቅማቸውን በመገንባት አካል ጉዳተኝነታቸው ሳይበግራቸው በትምህርታቸው እና በህይወታቸው ስታኬታማ እንዲሆኑ የሚያግዝ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በስልጠናው ራስን የመምራ ክህሎት፣ ለራስ የሚሠጥ ግምትን ማሳደግ፣ የችግር አፈታት እና ውሳኔ አሰጣጥ ክህሎት፣ ጭንቀትን እና ንዴትን የመቆጣጠር ክህሎቶች ተዳሰውበታል፡፡
ከስልጠናው በተጨማሪም የእንጀባራ ዩኒቨርሲቲ የልዩ ፍላጎትና አካቶ ትምህርት መ/ር ሀብታሙ አላምነህ
እና የታሪክ እና ቅርስ አስታዳደር መ/ር ብርሃኑ ጉዳይነህ የትምህርት እና ህይወት ተሞክሮአቸውን ለተማሪዎች አካፍለዋል።
ለአምስት ቀናት የተሰጠውን ስልጠና በዩኒቨርሲቲው ትምህርት እና ስነ-ባህሪይ ኮሌጅ የትምህርት ዕቅድና ስራ አመራር መ/ር ሀብታም ገኔ፣ የልዩ ፍላጎትና አካቶ ትምህርት መ/ር ሀብታሙ አላምነህ እና የታሪክ እና ቅርስ አስታዳደር መ/ር ብርሃኑ ጉዳይነህ አማካኝነት
የተሰጠ ሲሆን 30 የሚደርሱ ሰልጣኖች ተሳትፈውበት ዛሬ ተጠናቋል፡፡
https://www.facebook.com/100069178971700/posts/pfbid0GrKbauTBgkiHpxLdam4kDUNxbV367caR5WjNvEKt1MGoKFB9f96e95ztzkswrv6sl/?app=fbl