❗ጥር 11 በዓለ ኤዺፋንያ | በዓለ ጥምቀት❗
🔷👉 ጌታችን ለምን ተጠመቀ ?
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
🔵👉 ጥር አስራ አንድ በዚች ቀን የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከአጥማቂው ዮሀንስ ዘንድ በዮርዳኖስ ወንዝ ውኃ ተጠመቀ። ይችም እለት በዮናኒ ቋንቋ ኤጲፋንያ ትባላለች ትርጓሜውም "መለኮት የተገለጠበት ማለት ነው።
🔴👉 ' ኤዺፋንያ' የሚለው ቃል ከግሪክ (ጽርዕ) ልሳን
የተወሰደ ሲሆን በቁሙ 'አስተርእዮ: መገለጥ' ተብሎ
ይተረጐማል:: በነገረ ድኅነት ምሥጢር ግን ኤዺፋንያ ማለት 'የማይታይ መለኮት የታየበት: እሳተ መለኮት በተዋሐደው ሥጋ የተገለጠበት' እንደ ማለት ነው::
🔷👉 አንድም: ምሥጢር ሆኖ የቆየ አንድነቱ: ሦስትነቱ
የተገለጠበት ቀን ነውና ዕለተ ጥምቀቱ 441ኤዺፋንያ
ይሰኛል:: መድኃኒታችን ክርስቶስ አዳምንና ልጆቹን ያድን ዘንድ ከሰማያት ዙፋኑ ወርዶ: እንደ ሰውነቱ በሥጋ ማርያም ለ33 ዓመታት ተመላልሷል::
🔴👉 ጊዜው ሲደርስም በፈለገ ዮርዳኖስ: ከዮሐንስ ዘንድ ሊጠመቅ ሔደ:: መድኃኒታችን ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ የወረደው ጥር 10 ቀን አመሻሽ ላይ ሲሆን በፍጹም ትሕትና ተራ ሲጠብቅ አድሮ ሌሊት 10 ሰዓት ላይ ደረሰውና ሊጠመቅ ቀረበ::
🔷👉 10 ሰዓት መሆኑም ርግብ (መንፈስ ቅዱስ) ሲወርድ ሰዎች ሥጋዊት ርግብ ናት ብለው እንዳይጠራጠሩ ነው:: ርግብ በሌሊት መንቀሳቀስ አትችልምና::
🔵👉 መድኃኒታችን ወደ ቅዱስ ዮሐንስ ሲጠጋ አምላክነቱን ተረድቶ "እንዴት ፈጣሪየ ወደ እኔ ትመጣለህ? እንዴትስ በእኔ እጅ ትጠመቃለህ?" አለው:: ትህትና ለእናትና ልጅ ልማዳቸው ነውና:: (ሉቃ. ማቴ. ) ጌታ ግን "ጽድቅን ሁሉ ልንፈጽም ይገባል" ሲል እንዲያጠምቀው ፈቀደለት::
🔴👉 ቅዱስ ዮሐንስም "ስመ አብ በአንተ ሕልው ነው:: ስመ ወልድ ያንተ ነው:: ስመ መንፈስ ቅዱስም በአንተ ዘንድ ሕልው ነው:: በማን ስም አጠምቅሃለሁ?" ሲል ጠየቀው:: ጌታ "ወልዱ ለቡሩክ ከሣቴ ብርሃን ተሣሐለነ :: አንተ ካህኑ ለዓለም በከመ ሲመቱ ለመልከ ጼዴቅ እያልክ አጥምቀኝ" አለው:: ትርጉሙም "የቡሩክ አብ የባሕርይ ልጁ ብርሃንን የምትገልጥ ሆይ ይቅር በለን! አንተ እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመት የዓለም ካህኑ ነህና" እንደ ማለት ነው::
🔷👉 ከዚያም ጌታ ወደ ዮርዳኖስ ሲገባ ባሕር አይታ
ደነገጠች: ሸሸችም:: (መዝ) ዮርዳኖስ ጨንቆት ግራ ቀኝ
ተመላለሰ:: እሳተ መለኮት ቆሞበታልና ውሃው ፈላ:: በጌታ ትዕዛዝ ግን ጸና:: ጌታ ተጠምቆ: ሥርዓተ ጥምቀትን ሠርቶ: ዮርዳኖስን ብርህት ማሕጸን አድርጐ: የእዳ ደብዳቤአችንም ቀዶ ከወጣ በኋላ ሰማያት ተከፈቱ:: ማለትም አዲስ ምሥጢር ተገለጠ::
🔴👉 አብ በደመና ሆኖ "የምወደው: የምወልደው: ሕልው ሆኜ ልመለክበት የመረጥኩት የባሕርይ ልጄ ይህ ነው!" ሲል በአካላዊ ቃሉ ፍጹም ተዋሕዶን መሰከረ:: መንፈስ ቅዱስም በአምሳለ ርግብ ወርዶ በራሱ ላይ ተቀመጠ:: ራሱንም ቆንጠጥ አድርጐ ያዘው:: በዚህም የሥላሴ አንድነቱ: ሦስትነቱ ታወቀ: ተገለጠ::
🔷👉 ቅዱስ ዮሐንስ "መጥምቀ መለኮት" የሚባልበትን ታላቁን ክብር ሲያገኝ ዮርዳኖስ የልጅነት መገኛ ቅዱስ ባሕር ሆነ::
❗ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለምን ተጠመቀ?❗
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
🔴👉 ጌታችን እርሱ ባወቀ ለብዙ ምክንያቶች ተጠመቀ ጥቂቶቹን እንይ
❗👉 ትህትናን ሊያስተምረን -
🔵👉 ጌታችን በደቀመዝሙሩ በፍጡሩ በዮሐንስ እጅ ባህረ ዮርዳኖስ በሰላሳ ዘመኑ ተጠምቋል፡፡ ይህን ምስጢር የፈጸመው በደቀ መዘመሩ እጅ ለመጠመቅ ወደ ነበረበት ስፍራ በመሄድ ነውና መምህረ ትህትና ያሰኘዋል፡፡
❗👉 ሥርአትን ሊመሰርትልን-
🔵👉 ጌታችን ጥምቀት የማያስፈልገው ሲሆን፤ አድርጎ አድርጉ እንደሚል ደገኛ መምህር ተጠምቆ ተጠመቁ አለን፡፡
❗👉 ምስጢር ሊገልጥልን-
🔴👉 በጌታችን ጥምቀት ሰማያት ተከፍተዋል ፤የአብ ምስክርነት መንፈስቅዱስ ስምረት በርግብ አምሳል ተገልጧል፡፡ ለዚህም የሥላሴ የአካል፣ የስም የግብር ሦስትነት ተገልጧል፡፡
❗👉 የእዳ ደብዳቤያችንን ለመደምሰስ-
🔴👉 በዲያብሎስ ሥራ ተሸሽጎ የኖረውን የዕዳ ደብዳቤ እንደ ሰውነቱ ረግጦ እንደ አምላክነቱ አቅልጦ ሊደመስስልን ጌታ ተጠመቀ፡፡
🔵👉 በመሆኑም በልደቱ ያገኘነውን ጸጋ በጥምቀት ልጅነት አጽንተን በመጠበቅ የመንግስቱ ወራሽ የክቡር ስሙ ቀዳሽ እንሆን ዘንድ የጌታችን ቸርነት የእመቤታችን አማላጅነት አይለየን፡፡አሜን
❗እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሠላም አደረሳችሁ❗
🔷👉 መልካም በዓል
#ፎሎው_ማድረግ_እንዳይረሳ
፨፨፨ #ወስብሐት_ለእግዚአብሔር ፨፨፨
።።።።። #ወለወላዲቱ_ድንግል ።።።።።
።።።።። #ወለመስቀሉ_ክቡር ።።።።።
ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም
ጥር 11 /2017 ዓ.ም
ሆለታ
ፔጁን #Like_Follow_Share በማድረግ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንዲሁም መረጃ ያግኙ
🔴👉 በቴሌግራም | Telegram
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat_yonas_holet_debreedom🔴👉 በዋትስአፕ | whatsapp
👇👇👇👇👇
https://whatsapp.com/channel/0029Va4Ter67T8bV5NlRGJ2w🔴👉 1ኛ ዩትዩብ | 1st YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/@yonastube🔴👉 2ኛ ዩትዩብ | 2nd YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://youtube.com/@yonasmedia16