⚖Ethiopian law by Daniel Fikadu Law office⚖


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Inglizcha
Toifa: Huquq


ዳንኤል ፍቃዱ ተስፋዬ በሁሉም የፌደራል ፍርድ ቤቶች ጠበቃና የህግ አማካሪ
ስልክ - 0913158507 ወይም 0978554559
Daniel Fikadu Tesfaye Certified Attorney of law at all Federal Courts of Ethiopia.
Email- nurotekore@gmail. Com
⚖️⚖️Ethiopian Law by Daniel Fikadu channel ⚖️⚖️⚖️

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Inglizcha
Toifa
Huquq
Statistika
Postlar filtri


ኢሰመጉ'ን ጨምሮ በሰብዓዊ መብቶች ላይ የሚሠሩ 4 የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ላይ የተጣለው እገዳ ተነሳ
***
በሰብዓዊ መብቶች ላይ የሚሠሩ አራት የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ላይ ተጥሎ የነበረው እገዳ ከዛሬ የካቲት 24 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ በማስጠንቀቂያ ማንሳቱን የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን አስታዉቋል ።

ባለስልጣኑ በኅዳር ወር 2017 ዓ.ም. የመብቶች እና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል፣ የሕግ ባለሙያዎች ለሰብአዊ መብቶች እና ስብስብ ለሰብአዊ መብቶች በኢትዮጵያ የተባሉ 3 በሰብአዊ መብቶች ዙሪያ የሚሠሩ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ላይ ጥሎት የነበረውን እገዳ ማንሳቱ ይታወቃል ።

ይሁን እንጂ ባለስልጣኑ እግዱን ካነሳ በኃላ በታህሳስ 2017 ዓ.ም. የመብቶች እና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል እና የሕግ ባለሙያዎች ለሰብአዊ መብቶችን በድጋሚ እንዲሁም የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ ( ኢሰመጉ) እና የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከልን አግዶ ላለፉት 4 ወራት ቆይቷል።

ይህን ተከትሎ ባለስልጣኑ በ4ቱም የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ላይ ጥሎት የነበረዉን እገዳ ማንሳቱን ካፒታል ከተቋሙ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።#Capital


የቴምብር ቀረጥን በተመለከተ ፓርላማው ያወጣው ህግ በህግ አስፈጻሚው ህግ-በመተርጎም ሰበብ እንዲቀየር ሆኗል፡፡ግልጽ ህግ ግን ለትርጉም አይቀርብም!!

#Birhanu Beyene

- ከህግ አተረጓጎም መርኾች አንዱ "ህግ ግልጽ ከሆነ  አይተረጎምም" የሚል ነው፡፡ በተንቀሳቃሽ ንብረት ላይ የሚመሰረት የዋስትና መበት አዋጅ ቁ. 1147/2011 አንቀጽ 89 እንዲህ ይነበባል፡- "በዚህ አዋጅ መሰረት የዋስትና መብትን ለመመስረት የሚደረግ ስምምነት ወይም ግብይት ከቴምብር ቀረጥ ነጻ ነው፡፡"

- ይህ ድንጋጌ ግልጽ ስለሆነ ሊተረጎም አይገባም ፡፡ ይሁንእንጂ፣ ገንዘብ ሚኒስቴር በቀን 16/8/2015 በተጻፈ ሰርኮላር ከኢንቨስተርሮች ፣ ኤክስፖርተሮች እና ምናልባትም ነጋዴዎች በቀር  ሌሎች ሰዎች  በአዋጁ መሰረት የመያዣ ውል ቢገቡም የቴምብር ቀረጥ መክፈል አለባቸው ብሏል፡፡ ይህ ግልጽ ህግ መተርጎም ግን አዲስ ህግ እንደማውጣት ነው( ህግ የማውጣት ስልጣን ደግሞ የፓርላማው ነው፣የገንዘብ ሚኒስቴርን አይደለም፡፡)

- በመሆኑም አንድ ነጋዴም፣ ኢንቨስተርም ፣ ኤክስፖርተረም ያልሆነ ተጠቃሚ(consumer) ወይም በግብርና የሚተዳደር ግለሰብ(የሚያበድረው ካገኘ 😁 )  መኪና በብድር ቢገዛ እና አበዳሪው መኪናዋን በመያዣ ቢይዝ የቴምበር ቀረጥ የመኪናውን ዋጋ 1% እንዲከፍል እየተደረገ ነው፡፡  በተንቀሳቃሽ ንብረት ላይ የሚመሰረት  የዋስትና መበት አዋጅ ቁ. 1147/2011 አንቀጽ 89 ግን በግልጽ ቋንቋ "በዚህ አዋጅ መሰረት የዋስትና መብትን ለመመስረት የሚደረግ ስምምነት ወይም ግብይት ከቴምብር ቀረጥ ነጻ ነው፡፡"  ሲል ያስቀምጣል፡፡  ህጉ የዚህ ድንጋጌ ተፈጻሚነት ለነጋዴ፣ ኢንቨስተር እና  ኤክስፖርተር ብቻ ነው የሚል ገደብ የለውም።










ችሎት መድፈር(Contempt of court )

ችሎት የፍትህ አደባባይ እንደመሆኑ ሊከበር የሚገባው ነው፡፡ ሆኖም በተለመደው የህብረተሰብ አኗኗር ዘይቤ ስለችሎት ሲነሳ ችሎት እና የችሎት ዳኛን ከማክበር ባለፈ ፍርድ ቤት ገብተው እስኪወጡ ድረስ እታሰር ይሆን ብለው በፍርሀት የሚዋጡ ሰዎች ቁጥር ቀላል አይደለም፡፡ በአንፃሩ በእውቀት ማነስና ሌሎች ምክንያቶች የችሎትን ክብር የማያከብሩ በዛው ልክ ይኖራሉ፡፡ በዚህ አጭር ፅሑፍ የችሎት መድፈርን ምንነትና የሚያስከትለውን ተጠያቂነት እንመለከታለን፡፡

#የችሎት መድፈር ምንነት

ጠቅለል ባለ መልኩ ችሎት መድፈር ማለት ለሕግ ወይም ለፍርድ ቤት አለመታዘዝ፣ ለችሎት ክብር መንፈግ ወይም የፍርድ ቤትን ሥራ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ለማወክ መሞከር አልያም ደግሞ በዳኝነት ሥራው ጣልቃ መግባት እና መሰናክል መፍጠር ነው፡፡ ለፍርድ ቤት አለመታዘዝ የምንለው በችሎት ሂደት ውስጥ በዳኛው የሚተላለፉ ትዕዛዞችን አለማክበር ወይም መተላለፍ ነው፡፡ ለችሎት ክብር መንፈግ ደግሞ ፍርድ ቤት ማህበረሰቡ ፍትሕ የሚያገኝበት ስፍራ በመሆኑ ሊሰጠው የሚገባውን አክብሮት ለተቋሙና ለዳኛው አለመስጠት ነው። በሌላ በኩል ፍርድ ቤትን ማወክ፣ ፍርድ ቤት ስራውን እንዳያከናውን መሰናክል መሆን፣ የዳኝነት ሂደቱ ሊካሄድ በማይችልበት ሁኔታ እንዲቋረጥ ማድረግ ወይም ለማቋረጥ መሞከር አልያም ደግሞ ዳኛው በነፃነት ተግባሩን እንዳያከናውን መሰናክል መፍጠርን የችሎት መድፈር ልንለው እንችላለን።

በኢትዮጵያ የሕግ ማዕቀፍ ችሎት መድፈር ቀጥተኛ ትርጓሜ ተሰጥቶት ባናገኘውም ከአጠቃላይ ስለችሎት መድፈር የሚያነሱት የፍትሐብሔር ሥነ ሥርአት ህግ ቁጥር 480፣ 481 እና የወንጀል ህግ ቁጥር 449 መንፈስ ሲተነተን ፍርድ ቤቶች በዕለት ተዕለት ተግባራቸው በፍርድ ቤት ውስጥ እና ከፍርድ ቤት ውጪ ሊፈጠሩ የሚችሉ ከችሎት ሂደቱ ጋር ቀጥታ ግንኙነት ያላቸው ማንኛውንም የፍትሐብሔርም ሆነ የወንጀል ጉዳይ የዳኝነት ሥራዎችን የሚያውኩ ወይም የሚያደናቅፉ ተግባራትን የሚያካትት ነው፡፡ ይህም በችሎት ውስጥ በተገኘ በማንኛውም ግለሰብ፣ ችሎቱ ከተሰየመበት ጉዳዩ ጋር ግንኙነት ባለው ባለ ጉዳይ፣ ችሎት በመከታተል ላይ ባለ ወይም ሌላ ከችሎቱ ውጭ በሆነ ግለሰብ ቢፈፀም ተጠያቂነት የሚያስከትል ነው። በመርህ ደረጃ በወንጀል የተጠረጠረ ሰው ለጥፋት በሕግ የተቀመጠውን የሕግ ሥርዓት ተክትሎ ማስረጃ በማጣራት በዐቃቤ ሕግ ክስ ተመስርቶና ማስረጃ አቅርቦ ቅጣት የሚወሰን ሲሆን በችሎት መድፈር ሁኔታ ግን ጉዳዩ የሚፈጠረው ችሎት ውስጥ በመሆኑ ፍርድ ቤቱ ጥፋተኛውን ወዲያው አስቀርቦ ሊቀጣ ይችላል፡፡

#ችሎት መድፈር የሚያስከትለው ተጠያቂነት

በኢ.ፌ.ድ.ሪ የወንጀል ህግ በአንቀፅ 449 መሰረት ማንም ሰው በፍርድ ቤት ምርመራ በሚደረግበት ወይም የፍርድ ሥራ በሚከናወንበት ጊዜ
 ፍርድ ቤቱን ወይም የዳኝነት ሥራ በማከናወን ላይ ያለውን ዳኛ በማናቸውም መንገድ፣ የሰደበ፣ ያወከ፣ በችሎቱ ላይ ያፌዘ፣ የዛተ እንደሆነ ወይም
 የፍርድ ቤቱን ሥራ በማናቸውም ሌላ መንገድ ያወከ እንደሆነ የችሎት መድፈር ወንጀል ይፈፅማል።
ይህ ወንጀል ተፈፅሞ ሲገኝ ፍርድ ቤቱ ቀጠሮ ሳያደርግ ወዲያውኑ በጥፋተኛው ላይ ቅጣት ሊወስን የሚችል ሲሆን ቅጣቱም ከአንድ አመት የማይበልጥ ቀላል እሰራት ወይም ከሶስት ሺ ብር የማይበልጥ መቀጮ ይሆናል፡፡
 ወንጀሉ የተፈፀመው ከችሎት ውጭ ሆኖ ዳኛው ሥራውን እያከናወነ ባለበት ጊዜ ከሆነ ቅጣቱ ከስድስት ወር የማይበልጥ ቀላል አስራት ወይም ከአንድ ሺ ብር የማይበልጥ መቀጮ ይሆናል፡፡ ከችሎት ውጭ ስንል መደበኛ ችሎት ውጪ በዳኞች ፅህፈት ቤቶች ላይ የሚሰሩ የዳኝነት ወይም የምርመራ ስራን ሊያካትት ይችላል፡፡
 ወንጀሉ የተፈፀመው በችሎት ወይም በማናቸውም ቦታ የዳኝነት ሥርአት በሚካሄድበት ጊዜ ሆኖ በሀይል ወይም በማስገደድ እንደሆነ አግባብ ያለው የወንጀል ህግ አንቀፅ 441 በተደራቢነት ይፈፀማል፡፡ ይህም በዛቻ፣ በማስገደድ ወይም በሀይል ድርጊት የፍርድ ቤቱ ባለሞያዎች ሥራቸውን እንዳያከናውን ወይም ማድረግ የሌለባቸውን እንዲያደርጉ ማስገደድን ወይም ሰራተኛውን መደብደብ የሚያካትት ሲሆን እንደ ጥፋቱ ክብደት፣ እንደተበዳዩ የሥራ ደረጃ እና ወንጀለኛው ወንጀሉን ለመፈፀም እንደተጠቀመው መሳሪያ ሁኔታ ቅጣቱ ከ5 አመት የማይበልት ፅኑ እስራት ይሆናል፡፡

በሌላ በኩል የፍትሐብሔር ሥነ ሥርአት ህግ ቁጥር 480 የችሎት ሥነ ሥርአትን ለማስከበር ስለሚወሰዱ እርምጃዎች የደነገገ ሲሆን በዚህም መሰረት የማንኛውም ችሎት ሰብሳቢ ዳኛ የዳኝነት ሥራ አካሄድ ሥነ ሥርአት ለማስከበር ማንኛውንም አስፈላጊ መስሎ የታየውን እርምጃ ሊወስድ እንደሚችል አመልክቷል፡፡ ስለሆነም ፍርድ ቤቱ ለችሎቱ ክብር ወይም ለዳኝነት ሥነ ሥርአት መልካም አመራር ተቃራኒ የሆነ ጠባይ በሚያሳይ ማንኛውም ተከራካሪ፣ ጠበቃ፣ ወይም በችሎቱ ውስጥ የሚገኘውን ማንኛውንም ሰው ተቃራኒ ተግባሩን በሰራበት ጊዜ በያዘው መዝገብ ላይ መቀጮ ሊወስን ይችላል፡፡ አስፈላጊ የሆነው ማናቸውም እርምጃ ሲባል አጥፊውን መገሰፅ፣ ማረም፣ መምከር፣ ማስጠንቀቅ ወይም ከችሎት እንዲወጣ ማዘዝ ሊያጠቃልል ይችላል፡፡ በተጨማሪም በወንጀል ህጉ የተመለከተውን ድንጋጌ በመተላለፍ የወንጀል ተግባር በተፈፀመ ጊዜ ጥፋቱ በተደረገበት ጊዜ በያዘው ፍትሐብሔር መዝገብ ላይ ወዲያውኑ የእስራት ቅጣት ሊወስን ይችላል፡፡

በአጠቃላይ ችሎት መድፈር በህጉ የሚታይበት ሁኔታ ከላይ የተመለከተው ሲሆን ማህበረሰቡም የችሎት መድፈርን ምንነት በአግባቡ ተረድቶ ሊያስቀጡ ከሚችሉ አላስፈላጊ ተግባራት እስከታቀበ ድረስ የለምንም ፍርሀት ችሎት መታደም የሚችል መሆኑን ሊያውቅ ይገባል፡፡

በንቃተ ህግ ትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ


file number 24 2482.09 Diriba Gela.pdf
3.3Mb
ለህዝብ ጥቅም በሚል ለእምነት ተቋም የግለሰብ መሬት መሰጠት የሌለበት ስለመሆኑ፤ የሚሰጥ ከሆነም ተገቢው ካሳ መከፈል ያለበት ስለመሆኑ፡፡
በፌዴራልም ሆነ በኦሮሚያ ክልል የገጠር መሬት አዋጅ መሰረት የአንድን አርሶ አደር የእርሻ መሬት ለህዝብ ጥቅም በሚል ሰበብ መሬቱን በሙሉ ወስዶ ለእምነት ተቋም አንዲሰጥ የሚፈቅድ የህግ ድንጋጌ የለም፡፡ የገጠር መሬትን ከግለሰብ አርሶ አደር ወስዶ ለእምነት ተቋም መስጠት ለህዝብ ጥቅም አንደተሰጠ መሬት አይቆጠርም፡፡ መሬቱ ለህዝብ ጥቅም የተወሰደ ነው የሚባል ከሆነም በሕጉ አግባብ ተተኪ መሬት እና ካሳ ሊከፈል ይገባል በማለት የፌዴሬሽን ምክር ቤት በመዝገብ ቁጥር 98/13 ላይ የሕገ መንግስት ትርጉም ውሳኔ ሰጥቷል፡፡


ደንብ_ቁጥር_178_2016_በሆቴልና_መሰል_አገልግሎት_ሰጪ_ተቋማት_ባለሙያዎች_የደንብ_ልብስ_አለባበስ.pdf
1.0Mb
ደንብ ቁጥር 178/2016 በሆቴልና መሰል አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ባለሙያዎች የደንብ ልብስ አለባበስ


1692016-2025-01-09-677f7f9bbe375.pdf
1.5Mb
ደንብ ቁጥር 169/2016 የመሥሪያ ቦታ ልማትና አስተዳደር የአሰራር ደንብ
ደንብ ቁጥር፻፷፱/፪፻፲፮ የመሥሪያ ቦታ ልማትና አስተዳደር የአሰራር ደንብ መሰረተ-ልማት የተሟላላቸው፣ ምቹና ደረጃቸውን የጠበቁ መሥሪያ ቦታዎች እና የለሙ የኢንዱስትሪ ፓርኮችን ለኢንተርፕራይዝና ለአምራች ኢንዱስትሪዎች የመሥሪያ ቦታ በፍትሃዊነት በማቅረብ ድጋፍ መስጠት የሚያስችል አሰራር መዘርጋት በማስፈለጉ፤ የነባር ወይም አዳዲስ ግንባታዎች የተጠናከረ የመረጃ ሥርዓት በመዘርጋት ከብክነትና ከህገ-ወጥነት በፀዳ መልኩ የመሥሪያ ቦታዎችን ማልማት፣ ማስተላለፍ እና ማስተዳደር አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤ የመሥሪያ ቦታዎች ለታለመላቸው ዓላማ ለማዋል ባለድርሻ አካላት ንቁ ተሳትፎ እንዲኖራቸው በማድረግ አገልግሎት አሰጣጡ ግልጽ፣ ፈጣን፣ ቀልጣፋና ከሌብነትና ብልሹ አሰራር የፀዳ እንዲሆን ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤የአዲስ አበባ ከተማ ካቢኔ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስፈጻሚ አካላት አስፈጻሚ አካላት ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር ፹፬/፪ሺ፲፮ አንቀጽ ፺፬ መሠረት ይህንን ደንብ አውጥቷል፡፡




ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ደህንነት ጋር ተያይዞ በወንጀል የተከሰሱት እነ ዮሃንስ ዳንኤል እንዲከላከሉ ብይን ተሰጠ
***
የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 1ኛ ልዩ ልዩ ከባድ ወንጀል ችሎት ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ደህንነት ጋር ተያይዞ በወንጀል የተከሰሱት እነ ዮሃንስ ዳንኤል እንዲከላከሉ ብይን ሰጠ።

የፍትህ ሚኒስቴር የተደራጁና ድንበር ተሻጋሪ ጉዳዮች ዐቃቤ ሕግ በዮሃንስ ዳንኤል (ጆን ዳንኤል)፣ አማኑኤል መውጫ፣ ናትናኤል ወንድወሰን፣ ኤልያስ ድሪባ፣ ይዲድያ ነጻነት እና እሌኒ ክንፈ ላይ በነሐሴ 16 ቀኔ 2016 ዓ.ም ከምሽቱ በግምት 3፡30 ሰዓት ላይ ከአበባ ከተማ ወደ መቐለ ከተማ ለመጓዝ አውሮፕላኑ ለበረራ ዝግጁ ቢሆንም የአየር ሁኔታ ለበረራ አዳጋች በመሆኑ በረራው ቢደረግ በሰው ህይወት እና በንብረት ላይ የሚያደርሰውን ከባድ አደጋ ለመከላከል ጉዞው ተሰርዞ መንገደኞች ከአውሮፕላኑ እንዲወርዱ ሲነገራቸው በረራው በግድ መደረግ አለበት፤ አውሮፕላኑ ይከስከስ፤ አንወርድም በማለት ቀሪ ተሳፋሪዎችም እንዳይወርዱ በመክልከል አሳድመዋል በሚል በዝርዝር ጠቅሶ ክስ አቅርቦባቸው ነበር።

በተጨማሪም ዐቃቤ ሕግ 1ኛ ተከሳሽን ጆን ዳንኤል በተባለ ተከሳሽ ላይ በ3ኛ ክስ የኮምፒዩተር ወንጀል ለመቆጣጠር የወጣውን አዋጅ ቁጥር 958/2008 አንቀጽ 13 ንዑስ ቁጥር 3 ሥር የተመለከተውን ድንጋጌ መተላለፍ ቲክቶክ በተባለ ማሀበራዊ ሚዲያ በተንቀሳቃሽ ምስል ቀርጾ በቀጥታ ስርጭት ማስተላለፍ የሚል ክስ አቅርቦበት ነበር።

በዚህ መልኩ ተከሳሾቹ የክስ ዝርዝሩ ከደረሳቸው በኋላ ያቀረቡትን የዋስትና ጥያቄ ውድቅ ተደርጎ በማረሚያ ቤት ሆነው ጉዳያቸውን እንዲከታተሉ በተሰጠ ትዕዛዝ መሰረት ከማረሚያ ቤት ቀርበው ጉዳያቸውን ተከታትለዋል።

ተከሳሾቹ "የወንጀል ድርጊቱን አልፈጸምንም" በማለት የዕምነት ክህደት ቃላቸውን በመስጠታቸው ዐቃቤ ሕግ ለወንጀሉ መፈጸም ያስረዱልኛል ያላቸውን ምስክሮች ቃል አሰምቷል።

ፍርድ ቤቱ የዐቃቤ ሕግ ማስረጃን መርምሮ ዛሬ በዋለው የችሎት ቀጠሮ ሁሉም ተከሳሾች በ1ኛ ክስ ማለትም በወንጀል ህግ አንቀጽ 504 መሰረት እንዲከላከሉ ብይን ሰጥቷል።

ሁለተኛውን ክስ በሚመለከት ፍሬ ነገሩ በአንደኛ ክስ ተጠቃሎ የተገለጸ በመሆኑ ተከሳሾቹን በሁለተኛ ክስ ነጻ በማለት በአንደኛው ክስ ብቻ እንዲከላከሉ ፍርድ ቤቱ ብይን ሰጥቷል።

በተጨማሪም ፍርድ ቤቱ ጆን ዳንኤል የተባለው 1ኛ ተከሳሽን በተደራቢነት በቀረበበት በ3ኛ ክስ የኮምፒዩተር ወንጀል ለመቆጣጠር የወጣው አዋጅ ቁጥር 958/2008 አንቀጽ 13 ንዑስ ቁጥር 3 ሥር የተመለከተውን ድንጋጌ መተላለፍ በሚለው ክስ እንዲከላከል ብይን ሰጥቷል።

ፍርድ ቤቱ የተከሳሾቹን የመከላከያ ማስረጃ ለመጠባበቅ ለመጋቢት 16 ቀን 2017 ዓ.ም ቀጥሯል።

በታሪክ አዱኛ


180017-2025-02-03-67a10ad7ae7f6.pdf
992.3Kb
180/017 የወንዞች ዳርቻ ልማት እና ብክለት መከላከል ደንብ


Federal Negarit Gazeta Regulation No. 565.2025.pdf
4.4Mb
በኢትዮጵያ ሂሳብ አያያዝ እና ኦዲት ቦርድ የሚሰጡ አገልግሎቶች የሚከፈል የአገልግሎት ክፍያን በተመለከተ የወጣ ደንብ ቁ.565/2017


File number 2861 Wendimu Telila.pdf
4.0Mb
የፌዴሬሽን ምክር ቤት በ2017 ዓ.ም ከወሰናቸው ውሳኔዎች ውስጥ አንዱ ከጥብቅና አገልግሎት ክፍያ ጋር በተያያዘ በፍርድ ቤቶች የተፈፀመ የፍርድ አፃፃፍ ግድፈት የጠበቃውን ሕገ መንግስታዊ ፍትህ የማግኘት መብት የሚጥስ ስለመሆኑ የተወሰነው ነው፡፡ በመፅሃፌ ገፅ 64 ላይ ይገኛል፡፡
የፌ/ም/ቤት መዝገብ ቁጥር 120/16 (እነ አቶ ወንድሙ ተሊላ)
የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት አመልካቾች ለሰጡት የጥብቅና አገልግሎት በውላቸው መሰረት ክፍያ የሚገባቸው ስለመሆኑ በፍርዱ ክፍል ተንትነዋል፡፡ ለአመልካቾች ሊከፈል የሚገባው የገንዘብ መጠንም ሊስተካከል የሚገባው ስለመሆኑም በዋና የፍርድ ክፍል ውስጥ ተገልፃል፡፡ ነገር ግን በምን አግባብ እና በየትኛው ፍርድ ቤት መጠኑ ተጣርቶና ተስተካክሎ መወሰን አንዳለበት በችሎቱ የተሰጠ ግልፅ ትእዛዝ የለም፡፡ ይህም ፍርድ ቤቶች ለቀረበላቸው ጉዳይ በበቂ ምክንያት የተደገፈና ሊፈፀም የሚችል ፍርድ የመስጠት ሃላፊነታቸውን ሳይወጡ የሚሰጡት ውሳኔ የአመልካቾችን ፍትህ የማግኘት ሕገ መንግስታዊ መብት የሚጥስ ነው፡፡




በፍ/ቤት ክስ የመሰረተ (ያቀረበ) ወገን የክስ መሰማቱ ሂደት ከመጀመሩ በፊት ክሱን በማንሳት መዝገቡ እንዲዘጋ ያደረገ ከሆነ ለዳኝነት ከከፈለው ገንዘብ ለፍ/ቤቱ በኪሣራ ስም የሚቀነሰው ተቀንሶ ቀሪው ገንዘብ ሊመለስለት ይገባል።

ይህን አስመልክቶ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕጉ በግልፅ የሚለው ነገር ባይኖርም፣ የዚሁ ሕግ አንቀፅ 3 የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕጉ በግልፅ ያልሸፈናቸውና ለፍ/ቤት የቀረቡ ጉዳዮችን አካሄድ (አሰራር) በተመለከተ ሕጉ ከመውጣቱ በፊት ተጽፈው በሥራ ላይ የነበሩ አግባብነት ያላቸው ሕጎች እንደ አግባብነቱ ሥራ ላይ ሊውሉ የሚችሉ ስለመሆኑ ያመለክታል።

በ1945 ዓ.ም በወጣው የሕግ ክፍል ማስታወቂያ ቁጥር 177 አንቀፅ 11 ላይ ከሳሽ ክሱን ካቀረበ በኃላ በራሱ ተነሳሽነት ክሱን ከተወው አስቀድሞ ከከፈለው የዳኝነት ገንዘብ በዚሁ ሕግ በተመላከተው ዝርዝር አሰራር (ስሌት) መሰረት የደንቡ ተቀንሶ ሊመለስለት እንደሚገባ ተደንግጎ ይገኛል።

ስለሆነም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 3 እና በሕግ ክፍል ማስታወቂያ 177/74 አንቀጽ 11 መሰረት በፍ/ቤት ክስ የመሰረተ ወገን የክስ መሰማቱ ሂደት ከመጀመሩ በፊት ክሱን በማንሳት መዝገቡ እንዲዘጋ ያደረገ ከሆነ ለዳኝነት ከከፈለው ገንዘብ ላይ የደንቡ ተቀናሽ ተደርጎ ቀሪው ገንዘብ ሊመለስለት ይገባል።

(የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ቅፅ 13፣ ሰ/መ/ቁ. 76786)




NBE-Draft Directive- Reserve Requirement.pdf
149.2Kb
LICENSING AND SUPERVISION OF BANKING BUSINESS
RESERVE REQUIREMENTS (9TH-REPLACEMENT)
DIRECTIVE NO.SBB/…/2025 (DRAFT)


NBE- (Draft) Insurance Corporate Governance Directive.pdf
412.2Kb
LICENSING AND SUPERVISION OF INSURANCE BUSINESS
INSURANCE CORPORATE GOVERNANCE DIRECTIVE NO. SIB/ /2025

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.