ፍቅር እና ጥበብ✍️✍️ ያኖስ(уαиσѕ)


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: Kitoblar


አዲሱ እና የመጨረሻው ንጉስ

Связанные каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Statistika
Postlar filtri


ምንማኔሽን አይተው ለመኑሽ አደል ጅማት
በውሃሽ አሾፉ አደል ተጎናፅፈሽ ጥማት
ምን አፍ አለኝና እኔስ ሸንጎ ልቁም
ስንፍናዬን እንኳን ሸምጋዮቼ
መላህቅት አይደብቁም
ሞልፋጣ ነኝ እቴት እሪላ ቅራቅንቦ
ሀቂቃዬን ያሟጠጡኝ
ነጫጭ እርኩሳናት በደቦ
ዛሬ ግን ነሸጠኝ ምኞት ተቆራኘው
የአርናሽ አርነት ብሆነው ተመኘው
እቴትዋ ላክንፍሽ እራፊሽን አስጥዬ
ዳግም ላልመለስ ደጀሰላም ምዬ
ምን ተንገብር ንገሪኝ አልዝልም
ለዛሬ ብርቱ ነኝ ድሮ አላክልም

✍አቤል(ያኖስ)




መልካም የገና በአል


አፈቀረኝ/2/,ከሰማይ እስከ በረት
ግርማውን እስከማደንገዝ ያለቅንጣት ወረት
ከትዕቢቴ በላይ ከክህደቴ ልቆ
ከብቶች ስር ተገኘ ሞገሱን ደብቆ

ምን ?ትዝታ ከአዳም ምን ናፍቆት ቢኖርበት
እረኛ ስር አደረ....... ንቆ ንጉስነት
አፈቀረኝ ሳላፈቅረው
ቤቱ አስጠጋኝ ሳላስጠጋው

አፈቀረኝ
✍️አቤል(ያኖስ)
እንኳን ለጌታችን ለመድሀኒታችን ለእየሱስ ክርስቶስ የልደት በአል በሰላም አደረሳቹ.።


ሲሳቅልሽ ሲሳቅብሽ....
✍️አቤል(ያኖስ)
https://t.me/legtm_tm
https://t.me/legtm_tm
https://t.me/legtm_tm


ሲያምሽ ያመኛል
✍አቤል(ያኖስ)
https://t.me/legtm_tm
https://t.me/legtm_tm
https://t.me/legtm_tm


ቃል አይገልፅሽም
.
.
.
.
አቤል(ያኖስ)
https://t.me/legtm_tm
https://t.me/legtm_tm
እረዥሙ ግጥሜ ቃል ለማትገልፅሽ


ወዶ ገዳይ
እሷ ትሞት ብዬ ብዬ የምምለው
በትደፋ መሀላ እሷን የምገለው
እውነቴን በጉያዬ አጥብቄ ይዤ ነው
ደሞም ስለምወዳት ደሞ ስለማፈቅራት
ዘወትር ሳይታክተኝ ለዛ ነው ምገላት
ግና ምን ያደርጋል ላይኖረኝ ገለታ
በሀቄ እምዳላቆየውት የልቧን ትርታ
በሌላ ሰው ማለች እኔን መግደል ትታ
✍️✍️✍️ገጣሚ አቤል (ያኖስ)  ✍️✍️✍️
https://t.me/legtm_tm
https://t.me/legtm_tm
https://t.me/legtm_tm
https://t.me/legtm_tm


ልክ እንደ ጴጥሮስ
ባላስጮህም ዶሮ ትንቢት ባይኖረኝም
ሰርክ እክዳለው እምነት አይገደኝም
ልክ እንደ ፔጥሮስ ክጄ ባደባባይ
በእልፍኜ እገኛለው እራሴን ሳሰቃይ
ዋይ ዋይ ዋይ ማንባት በናፍቆት
ልቤ ተበገረ ትዝታ ማርኮት
ልክ እንደ ጴጥሮስ ፍቅሬን ሸፋፍኜ
ብቻዬን ኖራለው ህዝብ መሀል ሆኜ።
✍️✍️አቤል(ያኖስ)
https://t.me/legtm_tm
https://t.me/legtm_tm
https://t.me/legtm_tm


ከቅርጫው ጮሌዎች

ዘንቢሌን አስጠጋው መደቤን ላፋፍሰው
በሀሳቤ ስጎመዥ ስቆርጥ ስቀምሰው
ቀይና ጮማውን ጨምሬ ጨጓራ
እያፈስኩ ሳለ ሁሉን በየተራ
ከቅርጫውጩሌዎች ይመስል ለቅምሻ
ልቤን መነተፈችኝ የተዋበች ውሻ ።

✍️ገጣሚ አቤል (ያኖስ)

https://t.me/legtm_tm
https://t.me/legtm_tm


አቤል(ያኖስ)


አንቺ ካለሽበት
አንቺ ካለሽበት ቢሆን ምንም ቦታ
ፂሆን ይሆናል የፍቅር ገለታ
አንቺ ካለሽበት ሲኦልም ይደላል
እድልም ይቀናል በርባኖስ ይበራል
ምንም ቢያስፈራ የትኛውም ስፍራ
አንቺ ካለሽበት  ነው እንደተራ
ሊማሊሞን ቢወጡ ወደታች ቢወርዱ
ሰማዩ ባይጠራ በጉም ቢጋረዱ
አንቺ ካለሽበትበውሃ እንደመፍሰስ
ገደላ ገደሉም ያሰኛል የደስ ደስ
አንቺ ካለሽበት መቃብር ይሞቃል
ሞትም ይቀልና ሞቶ ይሳቀቃል
አንቺ ካለሽበት ምድርም ራማ ናት
ወይም ሬማ አልያም ፀባኦት
አንቺ ካለሽበት የበረዶ ግግር
ለመላፋት ቢሆን ይመቻል ለፍቅር
አንቺ ካለሽበት ኤርታሌን ቢዋኙት
ይልቁን ይበርዳል ፍቅርን ቢቀኙት
አንቺ ካለሽበት ልቤም ይጠብሻል
ለቤም እንዲሰፋ ልብ ይገዛልሻል
✍️✍️✍️✍️✍️ገጣሚ አቤል(ያኖስ)
https://t.me/legtm_tm


እንዳንቺ
ልክ እንደጨረቃ ታምሪያለሽ አልልም
ምሳሌ ሰጥቼሽ አንቺን አላቀልም
ምሳሌ ነሽና የቁንጅና ቡርቃ
ባንቺ ስውነት ላይ ውበት ስላበቃ
ልክ እንዳንቺ ታምራለች ጨረቃ።
✍️✍️✍️✍️ገጣሚ አቤል ታዬ✍️✍️✍️
አንቺ ጨረቃን አትመስይም ጨረቃ ግን አንቺን ትመስላለች።ጨረቃ ቆንጆ ነች!!!!!
https://t.me/legtm_tm
https://t.me/legtm_tm
https://t.me/legtm_tm
ያኖስ


ወዶ ገዳይ
እሷ ትሞት ብዬ ብዬ የምምለው
በትደፋ መሀላ እሷን የምገለው
እውነቴን በጉያዬ አጥብቄ ይዤ ነው
ደሞም ስለምወዳት ደሞ ስለማፈቅራት
ዘወትር ሳይታክተኝ ለዛ ነው ምገላት
ግና ምን ያደርጋል ላይኖረኝ ገለታ
በሀቄ እምዳላቆየውት የልቧን ትርታ
በሌላ ሰው ማለች እኔን መግደል ትታ

✍️✍️✍️ያኖስ(አቤል)
https://t.me/legtm_tm


አቤል (ያኖስ)😭😭😭😭


አቤል (ያኖስ)


ከእራስጌ👱👱
እኔማ ለቀረበሽ ሁሉ እራቋት እላለው
አንቺን አሳንሼ አንቺን አክላለው
ስድ ነች ብላቸው ቅናት መሰላቸው
ምስክሬ አንቺ ነሽ እስኪ ንገሪያቸው
ስድ ነኝ ባለጌ ስድ ነኝ ዋልጌ
በያቸው ውዴ ይጣሉሽ ከእግርጌ🦵🦵🦵
እኔ መሬት ልሁን እንድትሆኝ ከእራጌ

ያኖስ


Yanos


አቤል(ያኖስ)


ቀምሼ........ ልኮላተፍ

በምን ቃል ልግባባት በየትኛው ቋንቋ
እንኳን ንግግሯ ኮልታፋ ነው ሳቋ

ማር ልሼ አለችኝ የሆንኩት ኮልታፋ
ፊደል የማበላሽ የቋንቋ ቆላፋ

ላያስችል አይሰጥም ይላል የሀገሬ ሰው
ከጣፋጭ ከንፈሯ ማር ነው የሚፈሰው
እግባባት ነበረ ቅንጣቱን ብቀምሰው😁😁😁

#join_and_share
አቤል#ያኖስ

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.