“ለ50 ሚሊዮን ብሩ እመጣለሁ” ይህን ያለን የልዩ ዕድል ሎተሪ የ5 ሚሊዮን ብር ዕድለኛው ገነቱ ታምራት ነው፡፡
በህይወቱ ብዙ ውጣውረዶችን ላለፈው፤ ፈተናዎቹን ደግሞ በአሸናፊነት ለተወጣው፣ጓደኞቹ ተው የሎተሪ ፍቅርህን ቀንስ ሲሉት እኔ ብቻ ሳይሆን እናንተም ይደርሳችኋል ለሚለው ገነቱ በሚሊየን ሎተሪ የ50 ሚሊዮን ብር ዕድለኛ እሆናለሁ ማለቱ እውነት አለው፡፡
ገነቱ ታምራት የተወለደው በከምባታ ዱራሜ ከተማ ነው፡፡ በትምህርቱ በችግር ምክንያት ከስምንተኛ ክፍል ማለፍ አልቻለም፡፡ ትምህርቱን አቋርጦ ሊስትሮ ሆነ፤ ከዚያም እዚያው ዱራሜ ከተማ የጎሚስታ ስራ ጀመረ፡፡ ዱራሜ አልሆንልህ ሲለው ሀዋሳ ገብቶ ጎሚስታ ስራውን ቀጠለ፡፡ ጎሚስታ ስራውን ትቶ ደግሞ የሲኖትራክ ተሽከርካሪ ረዳት ሆነ፡፡ሚስትም አገባ፡፡ ብዙም ሳይቆይ መንጃ ፈቃድ አውጥቶ የሲኖትራክ ሹፌር ሆነ፡፡ አሁን የአንድ ልጅ አባት ነው፡፡
ከሊስትሮ ስራው ጀምሮ ሎተሪ ያለማቋረጥ የሚቆርጠው ገነቱ በሀዋሳ ከተማ ከስራው አረፍ ብሎ ቡና እየጠጣ የቆረጣት የልዮ ዕድል ሎተሪ የ2ኛ ዕጣ የ5 ሚሊዮን ብር አሸናፊ አድርጋዋለች፡፡
በደረሰው ገንዘብ ምን ለመስራት እንዳቀደ በቃለ መጠይቃችን ጊዜ ስንጠይቀው ቤተሰብ መርዳትና ያቋረጥኩትን ትምህርት መቀጠል አንዱ ትልቁ እቅዴ ነው፡፡ የሲኖትራክ ተሽከርካሪ ገዝቼ በራሴ መኪና መስራት ሌላው ትልቁ እቅዴ ነው ብሏል፡፡
ለተጨማሪ መረጃ ይህን ሊንክ ይጫኑ፡
https://linktr.ee/etiopianlotteryservice