ማኅበረ መድኀኔዓለም መዝሙር ጥናት


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: Din


✝️ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮን ስርዓትን የጠበቁ መዝሙሮች እና ግጥሞችን ከነዜማቸው እንለቃለን ✝️
🙏🙏🙏 (መዝሙር ጥናት) 🙏🙏🙏

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
Din
Statistika
Postlar filtri


የግንቦት ወር የንግስ በዓል

ሐሙስ ግንቦት 1 - ቅድስት ልደታ - የተወለደችበት

ቅዳሜ ግንቦት 3 - ቅዱስ ፋኑኤል - በመሪ እና በዓለም ባንክ

ረቡዕ ግንቦት 7 - ጠሮ ሥላሴ - ቅዳሴ ቤቱ

እሁድ ግንቦት 11 - ቅዱስ ያሬድ -  የተሰወረበት ጎተራ አጎና

ሰኞ ግንቦት 12 - አቡነ ተክለሃይማኖት - ፍልሰተ አፅማቸው
                      - ቅድስት ክርስቶስ ሰምራ - በአማላጅነቷ እልፍ ነፍሳት ከሲዖል ያወጣችበት መታሰቢያ እለት

ማክሰኞ ግንቦት 13 - ቅዱስ እግዚአብሔር አብ - ቅዳሴ ቤቱ በአዲሱ ገበያ እና በኮዬ ፈጪ እግዚአብሔር አብ(ጎጆ አርሴማ)

ረቡዕ ግንቦት 14 - አቡነ አረጋዊ ወገብረ ክርስቶስ - ገብረክርስቶስ ከጫጉላ ቤት ወጥቶ የመነነበት መታሰቢያ እለት

አርብ ግንቦት 16 - ቅድስት ኪዳነምህረት - ፈረንሳይ ጉራራ - ቅዳሴ ቤቷ

ሰኞ ግንቦት 19 - ቅዱስ ገብርኤል - አየርጤና ደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል ቤ/ክ ቅዳሴ ቤቱ

- ጎሮ - ቅዳሴ ቤቱ
 _ አያት ጣፎ ቅዱስ ገብርኤል ቅዳሴ ቤቱ
                     - አቡነ ዓብየ እዝጊ - በብስራተ ገብርኤል - በዓለ እረፍታቸው

ረቡዕ ግንቦት 21 - እመቤታችን - በደብረ ምጥማቅ ለአህዛብ ሳይቀር የተገለጠችበት መታሰቢያ በዓል

ቅዳሜ ግንቦት 24 - ቁስቋም ማርያም - እንጦጦ
                         - ቅዱስ ዮሴፍ - ንፋስ ስልክ
                          ስደት የጀመሩበት መታሰቢያ እለት


ሰኞ ግንቦት 26 - አቡነ ሃብተማርያም - በዓለ ልደታቸው

ማክሰኞ ግንቦት 27 - የመድኃኔዓለም በዓል ጎተራ አጎና በሚገኘው በቅዱስ ያሬድ ቤተክርስቲያን  እና ለገሀር በሚገኘው ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን ይከበራል(በዓሉም ኢህአዴግ 1983 በገባ ሰዓት ጎተራ አካባቢ በነበረ ከፍተኛ ፍንዳታ የአካባቢው ምዕመን እና የሌላ እምነት ተከታይ ሳይቀር በቅዱስ ያሬድ ቤተክርስቲያን  ተሰባስቦ በመድኃኔዓለም ታምር በቅዱስ ያሬድ ምልጃ የዳነበትን መከራውን ያለፈበትን እለት መታሰቢያ በማረግ ሁሌም በያመቱ ግንቦት 27 ታቦተ ዕጉ ወጥቶ በደመቀ ሁኔታ ይከበራል ቅዱስ ቂርቆስ የሚወጣበትም ምክንያት ተመሳሳይ ነው።

ረቡዕ ግንቦት 28 - ቅዱስ አማኑኤል - ቅዳሴ ቤቱ

@mahberemedhaniyalem
@mahberemedhaniyalem
@mahberemedhaniyalem

UPDATED


" በፍልሰቴ ቀን አባቴ አባቴ የሚለኝ ሁሉ ይምጣ ያኔ እኔ ወዳጄ ሚካኤል እና ልጄ ፊሊጶስ አብረን መጥተን እንባርካለን "   

#ደብረሊባኖስ_አብነ_ተክለ_ሃይማኖት

መንፈሳዊ የንግስ ጉዞ ወደ ደብረሊባኖስ ገዳም

መነሻ ቀን እሁድ ግንቦት 11
መመለሻ ቀን በ 12 ከንግስ በኃላ


❗️ውስን ቦታ ስላለን ቀድመው ቦታ ያሲዙ


❗️ክርስቲያናዊ አለባበስ እንዳይለዮት

☎️
0966037164
0963004353


🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
        
#ተወልዳለችና
==========
ተወልዳለችና የጌታ እናት የእኛ መድኃኒት
እናመስግናት እናወድሳት እንውደዳት/2/
የአዳምን ሕይወት

አ.ዝ----------------------//

አዳም ሲሰደድ ከጥንት እርስቱ
ፊቱን ሸፈነው ጭንቀት ፍርሃቱ
እያለቀሰ ገነትን ሲያጣ
ተስፋ አንቺ ሆንሽው የመዳኑ ዕጣ

አ.ዝ-----------------------//

ሊባኖስ ተራራ ተሰማ ዜና
ምሥራቅ ወለዱ እያቄም ወሐና   
ዳግማዊት ሄዋን ምክንያተ ድህነት
ልደቷን ሰማን በቅድስት እለት

አ.ዝ------------------//

የልደትሽ ቀን ልደታችን ነው
በአንቺ ነውና ልጅ የተባልነው
ፋራን የተባልሽ ቅድስት ተራራ
በአንቺ መወለድ ዓለሙ በራ

  🌹  በማህበረ ቅዱሳን 🌹
        በህብረት_እናመስግን

@mahberemedhaniyalem
@mahberemedhaniyalem
@mahberemedhaniyalem


🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
        
#ምሥራቀ_ምሥራቃት

ምሥራቀ ምሥራቃት ሙፃአ ፀሐይ እግዝእትነ ዘመና ሙዳይ
ዘመና ሙዳይ ማርያም ዘመና ሙዳይ /2/

#ትርጉም ፡ምስራቀ ምስራቃት የፀሐይ መውጫ እግዝእትነ ማርያም ሆይ መና ያለብሽ ሙዳይ ነሽ ፡፡

       


🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
        
#አማን በአማን

አማን በአማን/፪/ተወልደት
ተወልደት/፪/እመብርሀን

        በህብረት_እናመስግን


🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
       
#ኢያቄም_ወለዳ
     

ኢያቄም ወለዳ ኢያቄም/2/
ዳዊት ዘመዳ ኢያቄም ወለዳ/4/
  ትርጉም:- የኢያቄም ልጅ የዳዊት ዘመድ ናት


  🌹በማህበረ ቅዱሳን🌹
        በህብረት_እናመስግን


🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
        
#አዕይንታ_ዘርግብ


አዕይንታ ዘርግብ(፪) ኢያቄም ወለዳ (፪)
ኢያቄም ወለዳ (፭) ዘርግብ ኢያቄም ወለዳ (፪) እኸ (፫)

  ትርጉም:-አይኖቿ የርግብ የመሰሉ/የሆኑ/ልጅን ኢያቄም ወለደ::



  🌹በማህበረ ቅዱሳን🌹
        በህብረት_እናመስግን


📍 የግንቦት ልደታ መዝሙሮች


✝️እሰይ ተነሳ✝️

እሰይ ተነሰ እሰይ እሰይ ተነሳ/2/
ተደመሰሰ በአምላክ የዓለም አበሳ
አዝ-----
ክብርና ምስጋና እሰይ እሰይ ተነሳ
ይግባው ፈጣሪያችን ″
ሞትን ድል አድርጎ ″
አርዓያ ለሆነን ″
አዝ-----
በከርሰ መቃብር እሰይ እሰይ ተነሳ
ሦስት ቀን ሦስት ሌሊት ″
ተቀብሮ አልቀረም ″
ተነስቷል በሰንበት ″
አዝ-----
ለሐዋርያቱ እሰይ እሰይ ተነሳ
የምስራች ያለች ″
ማርያም መግደላዊት ″
ምንኛ ታደለች ″
አዝ-----
ዘበኞች ቢያቆሙ እሰይ እሰይ ተነሳ
አይሁድ ተሞኝተው ″
አልቻሉም ሊያስቀሩት ″
ሞትን ድል አደረገው ″
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

@mahberemedhaniyalem
@mahberemedhaniyalem
@mahberemedhaniyalem


#ሁሉን_የያዘውን_ያዙት
#ሁሉን_የሚገዛውን_ገዙት
#የህያው_የአምላክን_ልጅ_አሰሩት
#በሐይል_ገፉት_በቁጣም_ጎተቱት
#እርሱ_ግን_በፍቅር_ተከተላቸው።

"የምስመው እርሱ ነው ያዙት ተጠንቅቃችሁ ውሰዱት" ብሏቸው ነበርና ወደ ጌታ ቀርቦ ሳመው "መምህር ቸር ውለሃል?" ብሎ አቀፈው ይህች ምሽት የመከራው ጅማሬ ሆነች።

#እምበለደዌ_ወሕማም፤ ✞✞✞
#እምበለ_ጻማ_ወድካም ✞✞✞
#አመ_ከመ_ዮመ_ያብጸሐነ፤ ✞✞✞
#ያብጸሐክሙ_እግዚአብሔር_በፍሥሓ_ወበሰላም። ✞✞✞

🙏🏼🙏🏼🙏🏼


አማኑኤል አምላክ

አማኑኤል አምላክ ምስጋና ይገባሀል
ለአዳም ልጆች ሁሉ ህይወትን ሰጥተሀል
እልልታ ይገባል ለታላቁ ጌታ
ምሕረትን ለሰጠን በሐጢአታችን ፋንታ
አዝ..........
እንደምስኪን ደሃ አንገቱን ቀልሶ እሰይ የምስራች
ምህረት ላረገልን እምባችን አብሶ እሰይ የምስራች
ከባርነት ቀምበር ፍፁም ነፃ ወጣ እሰይ የምስራች
ደስይለናል ባንተ በትንሳኤው ብርሀን እሰይ የምስራች
አዝ.......
ከለሜዳ ለብሶ እርቃኑን የቆመው እሰይ የምስራች
የኛ መድኃኒዓለም ሞትን ድልአረገው እሰይ የምስራች
ጨረቃና ከዋክብት ደም ለአለቀሱለት እሰይ የምስራች
ሞትን ድልለነሳው እናመስግን በእውነት እሰይ የምስራች
አዝ........
መቅደላዊት ማርያም በጣም ደስይበልሽ እሰይየምስራች
አምላክሽ ተነስቷል ከሐጢአት ያነፃሽ እሰይ የምስራች
እናንተ ሐዋርያት በእምነት የፀናችሁ እሰይ የምስራች
ፍራቻው ይወገድ ተነስቷል ጌታችሁ እሰይ የምስራች
አዝ........
ንገሩ ለዓለም ያረገላችሁን እሰይ የምስራች
ከሲኦል እስራት ያላቀቃችሁን እሰይ የምስራች
እሰይ የምስራች ሰይጣን ድል ተመታ እሰይ የምስራች
ዝማሬን እናቅርብ ሁላችን በእልልታ እሰይ የምስራች

@mahberemedhaniyalem
@mahberemedhaniyalem
@mahberemedhaniyalem


#ነበርኩ_መች_ያድናል

ሀጢያትን ስትሰራ አምላክን እረስተህ
ቅዱሱን ሰውነት በሀጢያት አርክሰህ
ትእዛዝን ሳትፈጽም መልካምን ሳትሰራ
ዘይት ሳታዘጋጅ መብራትህ ሳይበራ
በተጠራህ ጊዜ መልዐከ ሞት ሲመጣ
ለማያልፈው አለም ሲወጣልህ እጣ
ለሚዛን ስትቀርብ አገልጋይ ነበርኩኝ እያልክ መናገሩ
መዝሙር ዘምሬያለው ሄጃለው ከበሩ
ብሎ መከራከር ያኔ መች ይጠቅማል
ይዞ መገኘት ነው ነበርኩ መች ያድናል !!!

🙏🏼


✞ #የሚያዚያ_ወር_የንግስ_በዓላት ✞

ሰኞ ሚያዝያ 7 - ቅዱስ እያቄም - እረፍቱ - በኮተቤ ሐና ማርያም ቤተክርስቲያን

ረቡዕ ሚያዚያ 9 - አቡነ እስትንፋስ ክርስቶስ  እረፍታቸው - በቤተል ሚካኤል ቤተክርስቲያን በቀበና መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን - በወይራ ሰፈር ቅድስት አርሴማ ወአቡነ እጨጌ ዮሐንስ ቤተክርስቲያን

ማክሰኞ ሚያዝያ 15 - መጥምቁ ዮሐንስ - አንገቱ ለ15 ዓመት ያስተማረችበት መታሰቢያ በዓል - በቤላ ዮሐንስ ቤተክርስቲያን

እሁድ ሚያዝያ 20 - በለቡ ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን

ማክሰኞ ሚያዝያ 22 - ቅዱስ ዑራኤል - ቅዳሴ ቤት ጎፋ መብራት ሀይል

ረቡዕ ሚያዝያ 23 - ቅዱስ ጊዮርጊስ በዓለ እረፍቱ

እሁድ ሚያዝያ 27 - ቸሩ መድኃኔዓለም በ 6 ኪሎ ምስካየ ኃዙናን መድኃኔዓለም ገዳም ብቻ

ረቡዕ ሚያዝያ 30 - ቅዱስ ማርቆስ - በዓለ እረፍቱ -በ6 ኪሎ ቅዱስ ማርቆስ

🚨!!! ማሳሰቢያ !!!🚨

ሚያዝያ 22 እና ሚያዝያ 23 ሕማማት
ላይ ስለዋለ ለሌላ ጊዜ ተላለፏል።
ሚያዝያ 27 ደግሞ ትንሣኤ ስለሆነ
በጌታ በዓል ላይ ሌላ በዓል አይከበርም
እና እሱም ለሌላ ጊዜ ተላለፏል።

@mahberemedhaniyalem
@mahberemedhaniyalem
@mahberemedhaniyalem
         ።።።🙏🙏🙏።።


ድንቅ አድርጎልኛል

ድንቅ አድርጎልኛል የሠራዊት ጌታ (2)
አልረሳኝም አምላክ አነሳኝ ከትቢያ (2)

ድንቅ አድርጎልኛል በደሌን ሳይቆጥር
ድንቅ አድርጎልኛል ወደቤቱ ጠራኝ
ድንቅ አድርጎልኛል ረክሼ ሳለሁ
ድንቅ አድርጎልኛል ልጄ ሆይ ና አለኝ
ድንቅ አድርጎልኛል በዳግም ምፅዓቱ
ድንቅ አድርጎልኛል መንግስቱን ሊያወርሰኝ

ድንቅ አድርጎልኛል ከአንበሳ መንጋጋ
ድንቅ አድርጎልኛል ከጉድጓድ አወጣኝ
ድንቅ አድርጎልኛል በጠላቶቼ ፊት
ድንቅ አድርጎልኛል ግርማ ሞገስ ሰጠኝ
ድንቅ አድርጎልኛል ምን እመልሳለሁ
ድንቅ አድርጎልኛል እንዲ ለወደደኝ

ድንቅ አድርጎልኛል ጠላቶቼ ሁሉ
ድንቅ አድርጎልኛል ሲጓደዱብኝ
ድንቅ አድርጎልኛል ማን ይደርስለታል
ድንቅ አድርጎልኛል እያሉ ሲሉኝ
ድንቅ አድርጎልኛል ፈጥነህ ደረስክልኝ
ድንቅ አድርጎልኛል ከሞት አዳንከኝ


@mahberemedhaniyalem
@mahberemedhaniyalem
@mahberemedhaniyalem
።።።🙏🙏🙏።።


እንኳን ደስ አለን ደስ አላችሁ
ወንጌላዊው ፍቁረ እግዚእ ወልደ ነጎድጓድ ቅዱስ ዮሐንስ እና ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሩፋኤል በደብራችን በደብረ መድኀኒት መድኀኔዓለም ቤ/ክ ፅላታቸው ገብቷል እንኳን ደስ አላችሁ 🙏🏼🙏🏼🙏🏼🙏🏼

ዘወትር በ 4 ቅዱስ ዮሐንስ
ዘወትር በ 13 ቅዱስ ሩፋኤል ይታሰባሉ


አልተወኝም ጌታ ለካስ ይወደኛል /2/
ዛሬም ስበድለዉ ልጄ ነህ ይለኛል
ዛሬም ስበድለዉ ልጄ ነሽ ይለኛል

አዝ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥

በበደል ጉራንጉር በኃጢአት ጫካ
ብጠፋበት እንኳን አልተወኝም ለካ
/ ዛሬም ልጄ ብሎ ዳግም ይጠራኛል
ለካስ አልጠላኝም ጌታ ይወደኛል / 2

አዝ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥

ለሥልጣን ለክብር ብዬ ስክደዉ
ለገንዘብ አድልቼ እኔ ስረሳዉ
ለእኔ ያለዉ ፍቅር አልቀነሰብኝም
ዛሬም ይወደኛል ጌታ አልጠላኝም
ለእኔ ያለዉ ፍቅር አልቀነሰብኝም
ዛሬም ይወደኛል ጌታ አልተወኝም

አዝ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥

ታዲያ ለዚህ ፍቅሩ ለሌለዉ ወሰን
ከጭንጫ መቃብር ላወጣኝ እኔን
/ በሕይወቴ ሁሉ ፍጹም ለመራኝ
ክብርና ምስጋና አቀርባለሁኝ / 2

@mahberemedhaniyalem
@mahberemedhaniyalem
@mahberemedhaniyalem
         ።።።🙏🙏🙏።።


#ሰው_ለሰው

ሰው ለሰው/2/ ቢፋቀር ምነው /2/

ለሰው ይመስለዋል ብዙ የሚቆይ
ግን በድንገት ያልፋል ሁሉንም/2/ ሳያይ
ሀብትን ያከማቻል ቀኑን ሳያውቀው
በድንገት ሲጠራ/2/ ላይከተለው

#አዝ

የሰው ልጅ በተራው መጠራቱ ላይቀር
ምነው አንዱ ለአንዱ መቃብር/2/ ባይቆፍር
አይጠቅምም መጨነቅ እንዲያው ለውበት
ይረግፋል ይጠፋል ሁሉም/2/ ከመሬት

#አዝ

ዋ! ቁንጅና ከንቱ ማማርም ብላሽ
አፈር ትቢያ ሲሆን ሲጨለም/2/ ሲመሽ
ደሀ ባለጸጋ አንድ ነው መንገዱ
በጨርቅ ተገንዞ በሳጥን/2/ መሄዱ

#አዝ

ሰው ዙሪያውን ቢያጥር መዝጊውን ቢሠራ
በሕንፃ ላይ ሕንፃ ቢያስመስል ተራራ
አይቀርም መሄዱ ሁሉም/2/ በየተራ

ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ

@mahberemedhaniyalem
@mahberemedhaniyalem
@mahberemedhaniyalem
         ።።።🙏🙏🙏።።


#ዛሬስ_ተይዣለሁ

ዛሬስ ተይዣለሁ በፍቅርህ ስጦታ
ውለታህ ማርኮኛል የሠራዊት ጌታ
ከአመድ ያነሳኸኝ በትቢያ ተጥዬ
ውለታህ ከበደኝ ማረከኝ ጌታዬ
ማረከኝ ጌታዬ


ያልሰጠኸኝ ነገር በዚህ ምድር የለም
ፍቅርህ ወሰን የለው ድንቅ ነው ዘላለም
እኔነቴን ሳስብ ምንድን ነኝ እላለሁ
ፍቅርህን ሳስተውል ሁልጊዜ አለቅሳለሁ
ሁልጊዜ አለቅሳለሁ

አዝ

ለብቻዬ ሆኜ አምላኬን ሳስበው
ከሕሊና በላይ ውለታህ ብዙ ነው
የተጣለውን ሰው ማንሳት ያውቅበታል
ምስኪንን ሲያጽናና ከሁሉም ይበልጣል
ከሁሉም ይበልጣል

አዝ

ሰው ነህ ተብያለሁ አንተ ሰው ስላልከኝ
ማን ያስታውሰኛል አንተ ባታከብረኝ
አትጣለኝ አንተ ሁሉም ያከብረኛል
ሐጢአቴን ባትቆጥር ለእኔ ይበቃኛል
ለእኔ ይበቃኛል


🌺ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ🌺


@mahberemedhaniyalem
@mahberemedhaniyalem
@mahberemedhaniyalem
         ።።።🙏🙏🙏።።


 ወንበዴ ነበርኩኝ



ወንበዴ ነበርኩኝ ሀገር ያስለቸው 
በመስቀል ላይ ሆኖ ታሪኬን ለወጠው 
አስበኝ ስላልኩት በኋላ ስትመጣ 
ገነትን ለማየት የመጀመሪያው ሰው ሆነኩኝ ባለእጣ
 
አቤት ፍቅሩ የእግዚእሔር/2/ 

       ግሩም ፍቅሩ ›› ›› 
        ኃያል ፍቅሩ ›› ›› 
        ግሩም ፍቅሩ ›› ›› 
አስበኝ ስላልኩት አሰበኝ ጌታዬ 
ወንበዴ ነበርኩኝ ስርቆት ነው ሙያዬ 
በመስቀል ላይ ሆኖ ሕዝቡን ያስብ ነበር 
እኔስ አላየሁም /2/ እንዲህ ያለ ፍቅር 

አልታይም ብዬ ኃጢአትን ስሠራ 
ተመለስ ይለኛል ስሜን እየጠራ 
እንዳልሞትበት ነው በኃጢአት ታስሬ 
ፍቀሩን አልዘልቀውም/2/ እንደዚህ ዘርዝሬ 

መከራ ሲከበኝ መጥቶ ያጽናናኛል 
በሐዘኔ ጊዜ እግዚአብሔርም ያዝናል 
ዓይኑ ከእኔ አይርቅም ጥበቃው አይጠፋም 
ስሙን እጠራለሁ/2/ በጌታዬ አላፍርም 

@mahberemedhaniyalem
@mahberemedhaniyale
m
@mahberemedhaniyalem
         ።።።🙏🙏🙏


✞ #የመጋቢት_ወር_የንግስ_በዓላት ✞

እሁድ መጋቢት 1 - ቤተል ማርያም - ህንፃ ቤተክርስቲያን ምርቃት

አድራሻ ቤተል አደባባይ ወረድ ብሎ በግ ተራው አካባቢ

ሐሙስ መጋቢት 5 አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ - ዕረፍታቸው

ቅዳሜ  7 ቅድስት ሥላሴ  - ቤተክርስቲያኑ የተመሰረተበት(ጠሮ ሥላሴ)

ማክሰኞ 10 መስቀለ ኢየሱስ - በቀጨኔ መድኃኔዓለም በዕንቁ ልደታ በዘነበ ወርቅ አቡነ አረጋዊ በማንጎ ገብርኤል

አርብ 27 ቸሩ መድኃኔዓለም - ጥንተ ስቅለት

እሁድ  29 የኢየሱስ ክርስቶስ ፅንሰት -በ4 ኪሎ በዓለ ወልድ ቤተክርስቲያን እና እኩለ ፆም ደብረዘይት በገነተ ፅጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ በመካኒሳ አቦ በቃሉ አቡነ ሀብተማርያም

@mahberemedhaniyalem
@mahberemedhaniyalem
@mahberemedhaniyalem
         ።።።🙏🙏🙏።።

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.