ማኅበረ ቅዱሳን በወልዲያ ከተማ ለሚገኙ ተፈናቃዮች የምግብ ግብዓቶች ድጋፍ አደረገ፡፡የማኅበረ ቅዱሳን ሙያ፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎት በሀገራችን እያጋጠሙ ያሉ ሰፊ ማኅበራዊ ቀውሶች በማኅበረሰብ ክፍሎች፣ በገዳማትና አብነት ት/ቤቶች ላይ እያስከተሉት ያለውን ችግር ለማቅለል ሁለገብ ማኅበራዊ ድጋፍ እያደረገ ይገኛል።
በዚህ መሠረት ከተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው ላለፉት ዓመታት በሰሜን ወሎ ዞን ወልዲያ ከተማና ዙሪያው በሚገኙ ተፈናቃይ ጣቢያዎች በሺዎች የሚቆጠሩ ወገኖች በከፋ ችግር ውስጥ ይገኛሉ።
ማኅበረ ቅዱሳንም ይህን ማኅበራዊ ቀውስ ለማቃለል ባለፉት ሳምንታት በወልዲያ ከተማ በሚገኙ ጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያዎች በመገኘት ከ614,000 (ከስድስት መቶ አሥራ አራት) ሺህ ብር በላይ ወጭ የሆነበት የምግብ ግብዓቶች ድጋፍ ያደረገ ሲሆን በዚህ የድጋፍ ርክክብ ወቅትም የማኅበረ ቅዱሳን ወልዲያ ማእከል ልዑካን እና የተፈናቃይ አስተባባሪዎች ተወካዮች በመገኘት ድጋፉን ለተጎጅዎች አስረክበዋል።
የማኅበረ ቅዱሳን መሰል የነፍስ አድን ድጋፎችን ለማድረስ በሚደረገው የሰብአዊነት ሥራ ምእመናን የተለመደ ድጋፍ እንድታደርጉልን ሲል ማኅበሩ ጥሪውን ያቀርባል።
ድጋፍ ለማድረግ፡-
#በማኅበረ ቅዱሳን የማኅበራዊ ድጋፍና መልሶ ማቋቋም ሒሳብ ቁጥሮች፡-
1. በአሐዱ ባንክ - 0025393810901
2. በአቢሲንያ ባንክ - 37235458
3. በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ - 1000309803648
4. በወጋገን ባንክ - 0837331610101
5. በአዋሽ ባንክ 01329817420400
6. በወገን ፈንድ ፡-
https://Www.wegenfund.com/mknu መጠቀም የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
የማኅበረ ቅዱሳን ሙያ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎት