ክለባችን የተሻሻለ የዝውውር ጥያቄን ለማቅረም በስራ ላይ ነው !!
በክለባችን አይን ከገባ የሰነበተው ፓትሪክ ዶርጉ የዝውውር ሂሳቡ አልቀመስ ብሏል። በዚህም ክለባችን ሁለት ጊዜ ጥያቄ ቢያቀርብም ሁለቱም ውድቅ ሁኖበታል።
እንዲሁም አሁን እየወጡ ባሉት መረጃዎች ክለባችን ለሊቼ የተሻሻለ የዝውውር ሂሳብ ሊያቀርብ እንደሆነ ተሰምቷል።
አዲሱ የክለባችን የዝውውር ጥያቄም ጉርሻን በማካተት 40 ሚልየን ዩሮ ይደርሳል ተብሏል። ይህም የተጨዋቹን ክለብ ያስማማል ተብሎ ይጠበቃል።
ክለባችን ከተጨዋቹ ጋር በግል ስምምነት ላይ የደረሰ ሲሆን። እንዲሁም ሌላው ተጫዋቹን ፈላጊ ሁኖ የቀረበው ክለብ ናፖሊ ነው።
ሆኖም ግን የኔፕልሱ ክለብ ተጨዋቹን በክረምት ነው ማዘዋወር የሚፈልጉት።
ዘገባውን ከፋብሪዝዮ ሮማኖ አጠናቀርን።
@man_united332@man_united332