መሪጌታ አምደብርሃን የባህል ህክምና መስጫ ማዕከል 🌿🌿🌿


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha


☑ ከጥንት አባቶቻች በተቸረን ሰሎሞናዊ ጥበብ ተፈጥሮ ያበቃላቸው የእፅዋት መድሀኒቶችን በመጠቀም ክፉ ዓይነ ጥላ ፣ በቤተሰብ ወይም በዘር የሚተላለፉ መናፍስት መፍትሔዎቻቸው ይተነተናሉ።
☑ አድራሻ ቁጥር 1 ምዕራብ ጎጃም ቡሬ ቁጥር 2 አ/አ እንዲሁም በተለያዩ የክልል ከተሞች እንልካለን
📞#0918487073
📞#0920253444
መልዕክት ካለዎት @mergetaam

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Statistika
Postlar filtri


የፊንጢጣ ኪንታሮት መንስኤ እና መፍትሔ

የኪንታሮት ህመም ምልክቶች እንደኪንታሮቱ ቦታ የሚወሰን ሲሆን የዉስጠኛዉ የኪንታሮት አይነት ብዙዉን ጊዜ በአይን የማይታይ ቢሆንም በሚፀዳዱበት ወቅት ማማጥ ካለዎ የደም ስሮቹ ሊቆጡና በቀላለ ሊደሙ ይችላሉ፡፡
አንዳንዴ በሚያምጡበት ወቅት የዉስጠኛዉ ኪንታሮት አይነት ወደታች በመምጣትና በፊንጢጣ ዉስጥ በማለፍ ህመምና የመቆጥቆጥ ስሜት ሊኖረዉ ይችላል፡፡

የዉጪኛዉ የኪንታሮት አይነት በፊንጥጣ ዙሪያ ባለዉ ቆዳ ስር የሚገኝ ሲሆን የደም ስሮቹ በሚቆጡበት ወቅት ሊያሳክኩ ወይም
ሊደሙ ይችላሉ፡፡ አንዳንዴ ደም በዉጭኛዉ ኪንታሮት ዉስጥ በመጠራቀምና በመርጋት ከፍተኛ ህመም፣ እብጠትንና መቆጣትን/ መለብለብን ሊያመጣ ይችላል፡፡

በሚፀዳዱበት ወቅት/ሰገራ በሚወጡበት ወቅት ከፊንጢጣ የሚወጣ ህመም የሌለዉ ደም/መድማት፡- ይህን ክስተት በመፀደጃ ሳህን ላይ ወይም በሶፍት ላይ ሊያዩ ይችላሉ፡፡
በፊንጥጣ አካባቢ የማሳከክ ወይም የማቃጠል ስሜት ካለዎ!
በፊንጥጣ አካባቢ ህመም ወይም ምቾተ ያለመሰማት ካለዎ!
በፊንጥጣ ዙሪያ እብጠት ካለዎ!
የሰገራ ማምለጥ ካለዎ!
ወደ ህክምና ባለሙያ በመሔድ መፍትሔ ይውሰዱበት
ምንም እንኳ ለኪንታሮት ዋነኛ ምልክቱ በሚፀዳዱበት ወቅት የደም መፍሰስ ቢሆንም በፊንጢጣ ደም መምጣት ሁሌ ከኪንታሮት ጋር ብቻ የተያዘ ሳይሆን እንደ የትልቁ አንጀት ካንሰር ወይም የፊንጥጣ ካንሰር
ምልክትም ሊሆን ስለሚችል የህክምና ባለሙያዎን
ማማከር ያስፈልጋል፡፡

ኪንታሮት ህመም ካለዉ፣ በተደጋጋሚ ወይም በጣም የሚደማ ከሆነ፣ወይም በኪንታሮት ማስታገሻ ህመሙ የማይሻሻል ከሆነ! ከኪንታሮት የህመም ምልክቶች ጋር አስፋልት/ሬንጅ የመሰለ ሰገራ ካለዎ፣የረጋ ደም ካለዎ ፣ከሰገራዎ ጋር ደም ካዩ!

በጣም ከፍ ያለ የደም መፍሰስ ካለዎ፣ የመደበር ወይም የማዞር ስሜት ካለዎ!

የኪንታሮት በሽታ መንስኤዎች በጥቂቱ።
ኪንታሮት በፊንጥጣ ዙሪያ ባሉ የደም መልስ ላይ ጫና በሚበዛበት ወይም በሚፈጠርበት ወቅት የደም ስሮቹ ስለሚያብጡና ስለሚወጠሩ የህመሙ ምልክቶች ይታያሉ፡፡ በደም ስሮቹ ላይ ጫና እንዲጨምር
ከሚያደርጉ ነገሮች ዉስጥ የሚከተሉት ይጠቀሳሉ።
በሚፀዳዱበት ወቅት ማማጥ ካለ!
መፀዳጃ ላይ ለረጅም ጊዜ መቀመጥ ተቅማጥ ወይም የሆድ ድርቀት ረዘም ላለ ጊዜ ከነበረዎ ውፍረት መኖር
እርግዝና የፋይበር መጠናቸዉ አነስተኛ ወይም ፋይበር የሌላለቸዉን ምግቦች ማዘዉተር ናቸዉ፡፡

የኪንታሮት ህመም ጉዳቶች
• የደም ማነስ እንዲከሰት ያደርጋል።
• የኪንታሮት መታነቅ/ Strangulated hemorrhoid

የሊቃውንቶች የዕጽዋት መፍትሔ
- የዕሬት ፍሬ እና የክንፉ ግንድ
- የምድር እንቧይ ፍሬ
እነዚህን ዕጽዋት ፍሬያቸውን አድርቆ በብረት ምጣድ በጣም ሳያሳርሩ ቆልተው በደንብ አድርጎ ሰልቆ በርከት አድርጎ በማዘጋጀት!
ግማሽ የሻይ ማንኪያ የተቆላ ግማሽ የሻይ ማንኪያ ያልተቆላው ዕጽዋቱ በመለካት በንፁህ ቅቤ አልያም በንፁህ ማር በመለወስ ማታ ማታ ኪንታሮቱ ያለበት ቦታ ቀብተው መተኛት ጧት ሲነሱ ትንሽ ውኃ ለብ አድርገው ይታጠቡት።
ይህ ድርጊት ከ ሁለት ሳምንት እስከ አንድ ወር ድረስ መጠቀም ይኖርቦታል።ሳያቆስል በሽታውን የሚያመክን ፍቱን መፍትሔ ነውና በአግባቡ ይጠቀሙ።

አምደብርሃን ይትባረክ
✅ቴሌግራም መልክት @mergetaam




#የሚጥል በሽታ (ኢፕሊፕሲ) መፍትሔ ከነዕፀዋት አዘገጃጀቱ

በበርካታ ሚሊየኖች የሚገመቱ ሰዎችን የሚያስቸግር የማይጋባ ህመም መሆኑን የህክምና ባለሙያዎች ይናገራሉ፤ ኢፕሊፕሲ ወይም በዘልማድ የሚጥል በሽታ በሚል የሚታወቀውን የጤና እክል ነው።

የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) በሁሉም የዕድሜ ክልል የሚገኙ ሰዎችን ሊጎዳ እንደሚችል የገለፀው ይህ የጤና ችግር በመላው ዓለም 50 ሚሊየን የሚሆኑ ሰዎችን እንደሚያሰቃይም ጠቅሷል።

#ይህ በሽታ በድንገት ሳይታሰብ እንደአጋጣሚ ብዙ ሰው በተሰበሰበበት ሥፍራ በገበያ፣ በሠርግ ፣በልቅሶ እንዲሁም ሕዝቡ በርከት ብሎ በሚገኝበት ሥፍራና እና በሚመላለስበት ቦታ ላይ ሁሉ የሚጥል የሚያሳቅቅ እና የሚዘገንን አስነዋሪ ይሉኝታ ቢስ በሽታ ነው።

#የሚጥል በሽታ በፍርሐት እና በድንጋጤም የሚከሰት በሽታ ነው።
ይህ ሕመም ጠቅላላ የሠራ አካላቱን ሁሉ እያንዘፈዘፈ የሚገዝፍና የሚያንቀጠቀጥ አስቸጋሪ በሽታ ይሁን እንጂ ከጣለ በኃላ ከሩብ ሰዓት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ሊለቅ ይችላል።

#የሚጥል በሽታ ሰው በታመመ ጊዜ ሰውየው ታሞ ከወደቀበት ሲነሳ ያየው ሰው እንኳን ቢነግረው ሕመምተኛው ሁኔታውን ያስተባብላል እንጂ ምን እንደደረሰበት የማያውቅ እና የማይገነዘበው ሰው አለ።
ሕመምተኛው ሰውነቱ ሲቆስል ልብሱም በቆሻሻ ሲበከል በዚህ ዓይነት ምን ደርሶበት እንደነበረ ሊረዳው ይችል ይሆናል ::
አንድ አንዱ በሽታ ደግሞ ዓይን የሚያስፈጥጥ እና ከማንም ሰው ጋራ የሚያጣላ እና የሚያጋጭ ልዩ ዓይነት በሽታም አለ።

#የሚጥል በሽታ በትክክል በምን እንደሚከሰት ባይታወቅም ቅሉ!

#አንደኛው አንጎላችን ክፍል ላይ በተለይ ደግሞ ኮርቴክስ( cortex) የሚሉት ቦታ ላይ ችግር ከተነሳ፤ ለምሳሌ የደም መዘዋወር እዚያ ላይ ከቆመ፣ ወይም ደግሞ ባልታወቀ ምክንያት ተጎድቶ ጠባሳ ካለበት፣ ወይም ደግሞ በኢንፌክሽን የተጎዳ ከሆነ፣ ወይም እዚያው አንጎል ውስጥ የሚፈጠሩ እጢዎች ወይም ደግሞ ከሌላ የሰውነት ክፍላችን ወደዚያ ተዘዋውረው እዚያ ሊበቅሉ የሚችሉ እጢዎች የሚጥል በሽታ ሊያስነሱ ይችላሉ።

#የሚጥል በሽታ በነርቭ መታወክ የተነሳ ተደጋጋሚ የሆነ በሰዉነት ላይ ማንቀጥቀጥን፣ የጡንቻ መገታተርን እና ማርገፍገፍን የሚያስከትል በሽታ ነዉ። የነርቭ መታወክ ሲጀምር የስሜት ህዋሳት ላይ ለዉጥ ይከሰታል፣ የህሊና መሳት ወይም የባህሪ ለውጥ ይስተዋላል። ይህም የሚሆነው በአንጎላችን ዉስጥ የሚገኘዉ የኤሌክትሪክ ስርጭት ለአጭር ጊዜ ስለሚታወክ ነዉ። አንድ ሰዉ የሚጥል በሽታ አለዉ ተብሎ የሚወሰነዉ የነርቭ መታወክ ቢያንስ ከሁለት እና ከዝያ በላይ ተደጋግሞ ሲከሰት ነዉ።

# እንዲሁም በርኩሳን መናፍስት በአየር አጋንንትም የሚከሰት ህመም እንደሆነም ሊቃውንት ይዘግባሉ።
ዘመናዊ ህክምና ባያምንበትም ቅሉ!
#በዘር እንደሚተላለፍም ብዙ ምሁራን በመዛግብታቸው ይዘግባሉ።

#እኔ ግን እላለሁ የሚጥል በሽታ አልያም epilepsy እየተባለው የሚጠራው እጅግ መጥፎ እና አስቸጋሪ በሽታ ከክፉ መናፍስት ዘንዳ የሚመጣ ክፉ በሽታ ነው እላለሁ።

ለዛውም በአየር አጋንንቶች ፣በዛር መናፍስቶች ለምሳሌ ያክል ሌጌዎን፣ጠቋር፣አዳልሞቴ፣ሰይፉጨንገር ...ወዘተ እየተባሉ በሚጠሩ መናፍስት እንዲሁም ከቤተሰብ ሲወርድ ሲዋረድ በመጣ ከባድ የባዕድ አምልኮ ወይም የዛር አምልኮ አማካኝነትም ይከሰታል ብየ የማምን ሰው ነኝ።
እነዚህ ክፉ መናፍስቶች ለመበቀል ሲፈልጉ ከቤተሰብ ወደ ልጅ በመውረድ ይህን ክፉ በሽታ የሚጥል በሽታ ሁነው ይቆራኛሉ።

#የሚጥል በሽታ መፍትሔ

#በቅድሚያ ይህንን ትልቅ በሽታ ለማስወገድ ወደ ፈጣሪያችን ቀና ብለን በየ እምነታችን በጸበልም ፣በቁርባንም፣በጾም ፣በጸሎት፣ በስግደትም፣በጥበብ አባቶችም ዘንዳ መፍትሔውን መሻት ትልቁ ተግባር ነው።

እንዲሁም እዚህ ከስር የምለጥፍላችሁ ከዕፀዋት የሚቀመሙ የእግዚአብሔር ኃይልን የተላበሱ ችግርን ለመቅረፍ በተሰጣቸው ተፈጥሮአዊ ፀጋ በ ፈጣሪ እርዳታ ችግራችንን ይቀርፉልን ዘንድ በጥንቃቄ እንጠቀም።

#የሚጥል በሽታ መፍትሔ

#የወርቅ በሜዳ ሥር
አንደኛው የሚያስነጥሰው የድንቹ ምስል ከስር ለጥፌላችኋለሁ።

#ወርቅ በሜዳ ከሰኔ ጀምሮ እስከ ጥቅምት መጨረሻ አከባቢ ብቻ በቅሎ የሚቆይ ዕፅ ነው።

ይህ ዕፀዋት ዘርፈ ብዙ ጥቅም ያለው መልካም ዕፀዋት ነው።ወርቅ በሜዳ በቆላማ አከባቢ የሚገኝ ሥሩ ወደ ድንች የሚያደላ ቅጠለደካማ ዕፅ ነው።

#ወርቅ በሜዳ ጥንቃቄ የሚሻ ዕፅ ነው በተለይ በእርጥቡ ሰውነትን ቢያስነኩት የማሳከክ ስሜት የሚፈጥር ቢያሸቱት የማስነጠስ ኃይል ያለው ዕፅ ነው።
ዓይን ቢያስነኩት ይበጃል።

#ወርቅ በሜዳ ለለምጽ፣ ለሥራይ፣ለስጋ ደዌ፣ለችፌ፣ለነቀርሳ፣ለዛር መንፈስ እና ለቡዳ መንፈስ ማስለቀቂያ የሚሆን ታላቅ እንደ ስሙ ወርቅ የሆነ ዕፅ ነው።

#አጠቃቀም
፦የወርቅ በሜዳ ሥር አምጥተው አድርቀው በደንብ ላም አድርገው በመደቆስ ነፍተው ሲያበቁ!

#የሚጥል በሽታ የታመመው ሰው በሽታው በሚጥለው ሰዓት የተዘጋጀውን መድኃኒት በንጹህ ሻሽ በመቋጠር ውኃ ነከር አድርገው በግራ እና በቀኝ አፍንጫው ሶስት ሶስት ጠብታ በአጠቃላይ ስድስት ጠብታ መክተት ነው።
በሚጥለው ሰዓት ሁሌም ሳያቋርጡ
ሳይጥለውም አንድ ቀን እየዘለሉ በደረቁ ያሽትቱት!

#በአዘቦት ቀን አልያም የዘመናዊ መድኃኒት ለሚጠቀሙት ደግሞ ጧት እና ማታ መድኃኒቱን በንፁህ ሻሽ በመቋጠር በአፍንጫው ለ 30 ደቂቃ ያክል ያሽትቱት

#ይህን ድርጊት አንድ ቀን እየዘለሉ ለአንድ ወር አከባቢ ይጠቀሙ።ይድናል
ለህጻንም መጠኑን በመቀነስ ይሆናል።

#እንዲሁም ከተዘጋጀው መድኃኒት በትንሿ ማንኪያ አንድ በመለካት በግማሽ ሊትር ወተት በማፍላት ጧት በባዶ ሆድ ይውሰዱ።
ምግብ ሳይበሉ ለ 4 ሰዓታት ያክል ቆይተው ትኩስ ነገር ቀምሰው ምግብ ይውሰዱ።
ይህ ለአዋቂ ሰው ብቻ ነው።

ታድያ ትዕግስት የሚፈልግ መፍትሔ ነው!!!

♦️ ኋላቀር የሆነ አስተሳሰባችን ትተን መርምረን እንጠቀምበት።

አምደብርሃን ይትባረክ
✅ቴሌግራም መልክት @mergetaam




⏩የሽንት ቱቦ ኢንፌክሽን የሽንት ቱቦ ኢንፌክሽን ማለት ሽንትን ከሰውነት ለማስወገድ የሚጠቅሙ የአካል ክፍሎች ማለትም፤ ኩላሊት፣ የሽንት ፊኛ እና የሽንት ቱቦዎች በባክቴሪያ አማካኝነት ሲጠቁ የሚፈጠር ኢንፌክሽን ነው።

⏩የሽንት ቱቦ ኢንፌክሽን ምልክቶቹ
💛ሽንት ሲሸኑ ማቃጠል
💛ከእንብርት በታች ህመም
💛የጎን ህመም
💛የሽንት ቀለም መቀየር
💛መጥፎ ጠረን ያለው ሽንት
💛የሽንት ቶሎ ቶሎ መምጣት (ሽንት ቤት ቶሎ ቶሎ መመላለስ)
💛የሽንት መጠን መቀነስ እና ከሸኑ በኋላ ያለመጨረስ ስሜት ወይም መንጠባጠብ
💛ትኩሳት
💛ማቅለሽለሽ እና ማስመለስ ናቸው።

⏩ለሽንት ቱቦ ኢንፌክሽን አጋላጭ ሁኔታዎች
የኩላሊት ጠጠር በሽታን የመከላከል አቅምን የሚቀንሱ በሽታዎች እንደ
👉የስኳር በሽታ
👉ኤች.አይ.ቪ
👉የሚጥል በሽታ
👉እርግዝና
👉በሰው ሰራሽ የሽንት ቱቦ መጠቀም
👉በማህፀን የሚቀበር የወሊድ መከላከያ
👉ያልተገረዘ ወንድ
??የፕሮስቴት እጢ ማደግ

⏩#የሽንት ቱቦ ኢንፌክሽን መከላከል ዘዴዎች
➥ሽንት በሚሸናበት ወቅት ሙሉ በሙሉ ወጥቶ እስኪያልቅ መጠበቅ
➥ከግብረ ስጋ ግንኙነት በኋላ ቶሎ መታጠብ
➥በምንጸዳዳበት ወቅት ከፊት ወደ ኋላ መታጠብ
➥በቀን ውስጥ ከ ሁለት ሊትር በላይ ውሃ መጠጣት
➥አትክልትና ፍራፍሬ በደንብ መመገብ
➥በቀን ዉስጥ በጣም በተደጋጋሚ አለመታጠብ
➥ሽንት ሲመጣ ይዞ አለመቆየት ወይም አለመቋጠር ናቸው።

⏩#ለሽንት_ቱቦ_ኢንፌክሽን_መፍትሔ
✅ውሃ በደንብ መጠጣት ቢያንስ በቀን ከሁለት ሊትር በላይ
✅በቂ እረፍት ማድረግ
✅ሽንት ሲመጣ ወዲያዉኑ መሽናት
✅የሽንት ቱቦ መቆጣትን የሚያባብሱ ነገሮችን እንደ አልኮል እና ቡና መቀነስ በምትኩ የእንጆሪ እና አናናስ ጭማቂ መውሰድ።

ጥበብን መረዳት ዘመናዊነት እንደሆነ ሁሉ።
በጭፍን መነዳትም የዘመኑ ሰለባ መሆን ነው።

አምደብርሃን ይትባረክ
✅ቴሌግራም መልክት @mergetaam




✔የመዝሙረ ዳዊት ገቢር
1. መዝሙር 2- ለጠላት በብር ቀለበት 7ጊዜ ደግመህ ያዝ
2. መዝሙር 3- የጸሎት- በጫት ልምጭ 7 ጊዜ ደግመህ ምታ እቃ ለመሸጥ
3. መዝሙር 5 - ለአቤቱታ ስትሄድ ጧት 7 ጊዜ ድገም
4. መዝሙር 7- የጠላት መከላከያ የሚደገም
5. መዝሙር 18- ጌታህ በተቆጣ ጊዜ 7 ጊዜ ድገምና ተቀባ
6. መዝሙር 19 - መዳመጫ ላይ ሆነህ 49 ጊዜ ድገም እግዚአብሔር ያሰብከውን ሁሉ ይፈጽምልሃል
7. መዝሙር 20 ለበረከት በውሃ ድገምና ቤቱን እርጨው 49ጊዜ ነው የሚደገመው

8. መዝሙር 22 በታሰርክ ጊዜ በዉሃ 7 ጊዜ ድገምና እግርና እጅህን ታጠበው
9. መዝሙር 29- ህልም ለማየት 7 ጊዜ ደግመህ ተኛ
10. መዝሙር 31 -ለምትሰራው ሁሉ በወይን 7 ጊዜ ደግመህ ጠጣ

11. መዝሙር 32 መኪና ላይ በተቀመጥክ ጊዜ በከርቤ 7 ጊዜ ደግመህ ተቀመጥ
12. መዝሙር 33- ሲሳይና ረድኤት ስታጣ ፀሐይ ሳይወጣ 7 ጊዜ ድገም
13. መዝሙር 36- በገንዘብህ በቀኑብህ ጊዜ ብቻህን ሆነህ በቀስታ 7 ጊዘዜ ድገም
14. መዝሙር37- በአደባባይ በቀስታ ድገም ንግግር ያቆማል በአደባባዩው
15. መዝሙር41- ሴት ስትጠላህ 7 ጊዜ ደግመህ ቀባት መመለሻው መዝሙር 42 ነው
16. መዝሙር 46 ሰው አልታዘዝም ባለህ ጊዜ በሸክላ ላይ ቆመህ 7 ጊዜ ድገም
17. መዝሙር 49- ሰው በከንቱ በተነሳብህ ጊዜ 7 ጊዜ ጠዋ ቆመህ ድገም።
18. መዝሙር 51 - ሰው ከሳት( ጠላት) ሲነሳብህ ከ 7 ቀለማት ፅፈህ ከደጅ ቅበር።
19. መዝሙር 61- ጠላት በተነሳብህ ጊዜ የቀብር አፈር 16 ጊዜ ደግመህ ከባህር ጣል፡፡

20. መዝሙር 69- ሰው እንዳይመታህ ጧት ጧት 7 ጊዜ ድገም
21. መዝሙር 72- ለፍቅር በቅባ ቅዱስ 4/9 ጊዜ ደግመህ ገፅህን ተቀባ
22. መዝሙር 73- ለብር በተነሳብህ በፍየለፈጅ ተቀጽላ ደግመህ በክንድህ ያዝ
23. መዝሙር 74 -ጠላት ከተነሳብህ በሎሚ 7 ጊዜ ደግመህ ፊትህን ተባበስ (ተቀባ)
24. መዝሙር 75- ሰው በሐብት ነገር በተነሳብህ ጊዜ ከበቀል ድንጋይ ቆመህ 7ጊዜ ድገም
25. መዝሙር 79- ገንዘብክን በወሰዱብክ ጊዜ ሲነጋ 14 ጊዜ ድገም ይመለስልሃል
26. መዝሙር 80 ወደ አረመኔ ሀገር ስትሄድ 7 ጊዜ ደግመህ ሂድ
27. መዝሙር 81- ጋኔን የያዘው ሰው በውሃ 7 ጊዜ ደግመህ አጥምቅ
28. መዝሙር 82 - በታሰርክ ጊዜ 7 ጊዜ ድገም
29. መዝሙር 83- ለሥራይ በአቱችና በፍየል ቅቤ ደግመህ ጠጣ

30. መዝሙር 57- ከብት እንዳይበላ ለጅብ መከላከያ ቦኑ አጋፍሬ ለፃድቃን አለው ድረስ 7 ጊዜ ድገም
31. መዝሙር 84- ማደርያ ስታጣ ከታቦት ፊት ቆመህ 7 ጊዜ ድገም
32. መዝሙር 85- ንጉሥ በተቆጣህ ጊዜ እህል ሳትቀምስ 7 ጊዜ ድገም
33. መዝሙር 87- ወደምስራ በሚፈስ ዉሃ 7 ጊዜ ደግመህ ታጠብ ከመኪና አደጋ ትድናለህ
34. መዝሙር 88- ልጅህና አሽከርክን በካዱህ ጊዜ ሌት ብቻህን ክህልህን ይዘህ ድገም
35. መዝሙር 90 ማታ 3 ጊዜ ጧት 3 ጊዜ ድገም ከመኪና አደጋ ትድናለህ
36. መዝሙር 92- ፍቅር ስታጣ በውሃ 30 ጊዜ ተባበሰው ጠጣ ደግመህ በምራቅህ ተቀባ
37. መዝሙር 94- የቤት ሰው አላፈቅር ሲልህ በርግብ ደም 32 ጊዜ ደግመህ ቤቱን እርጭ
38. መዝሙር 97 -ስደትና መኪና ባገኘህ ጊዜ በበግ ደም 3 ጊዜ ደግመህ ቤቱን እርጭ
39. መዝሙር 100- ባልንጀራህ እንዳይከዳህ ከከከርቤ 9 ጊዜ ደግመህ ተቀባ

40.መዝሙር በክፉ ወር- በዘበ 4.4.ጊ
41. መዝሙር 101- ሀብትህን በወሰዱብህ ጊዜ 7 ጊዜ ድገም
42. መዝሙር 111-ንብረትህን ለማብዛት በዶቅማ ተቀጽላ 7 ጊዜ ደግመህ ከቤት አስቀምጥ
43. መዝሙር 112- ሰው በናቀህ ጊዜ ዕለት ዕለት 7 7 7 ጊዜ ድገም
44.መዝሙር 115- ሲይዙህና ስትታሰር በውሃ ደግመህ ጠጣ
45. መዝሙር 117- ለሥራይና ጥላ ወጊ 47 ጊዜ ደግመህ ጠጣ
46.መዝሙር 118-መንገድ ስትሄድ ደግመህ ሂድ ጥሩ ነው
47. መዝሙር 119-- ክፉ ነገር ሲነሳብህ ድንጋይ ተሸክመህ 3 ጊዜ ደግመህ ጠጣ
48.መዝሙር 125- ለምትሰራው ስራ ሁሉ እንዲቀናህ 7 ጊዜ ድገም
49.መዝሙር 133- ከመኝታህ ተነስተህ 3 ጊዜ ድገም
50. መዝሙር 14 - ለመንገድ 7 ጊዜ ድገም
51. መዝሙር 49 ለምጥ 7 ጊዜ ደግመህ በብርሌ(በጠርሙስ) አጠጣ

ጥበብ ትበልጽግ
አምደብርሃን ይትባረክ
✅ቴሌግራም መልክት @mergetaam




Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish




🔀#ዛሬ በደም በውርስ ስለሚወርደው የዛር መንፈስና ዓይነ ጥላ የቤት ተያዥ ከዓያት ከቅማት የሚመጡ የቤተሰብ ዛር ዓይነጥላ በተለያዬ መልኩ እንደሚተላለፉ በዚህ መልኩ እናያለን።
ከአንዱ ወደአንዱ እንዴት እንደሚተላለፍ ጭምር መገንዘብም አለብን።

👉የዛር መናፍስቶች እንደየ አካባቢው ቋንቋና ባሕል የተለያየ ነገድና ስያሜ የተሰጣቸው  ሲሆኑ
#የቤት_አምላክ
#የቤት_ውቃቤ
#ጌታየ
#ክራማ
#እቴቴ
#ጨሌ
#አውሊያ ወዘተ በመባል ይመለካሉ።

⏩#ወደዝርዝሩ ከመግባቴ በፊት በሰው ልጆች ላይ የሚያደርሰውን የዛር መናፍስት የሚፈጥሩት ችግሮች፦
💠ጤና ማሳጣት
💠በረከት ማጣት
💠መጨናነቅ
💠ሀብት ማሳጣት
💠ከቤት ያለምንም ነገር ተቀምጠን እንድንውል
💠ዓላማ የለሽ ማድረግ
💠ተስፋ ማስቆረጥ
💠የበታችነት ስሜት ማምጣት
💠ቁም ነገር መገርገር
💠ትዳር እንዳይዙ ትልቅ እንቅፋት ይፈጥራሉ
💠በሰዎች ዘንድ እንድንጠላ
💠የሰውነት ጠረን
💠የአፍ ጠረን
💠ሆድ ውስጥ መንፋት የመንቀሳቀስ
💠ጨጓራን በመመሰል ትልቅ ሁከት ይፈጥራሉ።
💠ፅንስን ማስወረድ
💠የወገብ ህመም
💠ህልመ ሌሊት
💠ፍራቻን በመጫር የህይወት ስጋት ይሆናሉ

⏩#የቤተሰብ ዛር
ከቤተሰብ ወርዶ ለልጅ ልጅ የሚተርፍ የባዕድ አምልኮ የዛር መንፈስ የቤት አምላክ፦
👉የዛር መንፈስ ማለት በአብዛኛው ጊዜ ፈቅደንና ወደን ከፈጠረን አምላካችን ይልቅ ክፉ የዛር መንፈስ ያዘዝከኝን አደርግልሃለሁ ያዘዝኩህን አድርግልኝ ብለን ቃል በመግባት ከራሳችን ጋር እንደ አምላክ አምነን የምንዋረሰው ክፉ የውርስ መንፈስ ነው

👉የዛር መናፍስት ከሰው ልጅ ማህበራዊ ኑሮ በመቆራኘት የሰው ልጅ ስጋውን ለብሰው ከደሙ ጋር ተዋህደው ህይወታቸውን የሚመሩ ረቂቃን መናፍስት ናቸው።

👉የዛር መናፍስት ከአያት ከአባት እናቶቻችን ዘንድ  በደም ሐረጋችን በመውረድ ልጅን እንዲሁም የልጅ ልጅን ትልቅ ፈተና ውስጥ የሚጥሉ የከፉ መናፍስት ናቸው።

👉የዛር መናፍስት ከሰው ልጅ ጋር ከመላመዳቸው የተነሳ የሰውን ልጅ የእለት ተእለት እንቅስቃሴ በመቆጣጠር ህይወቱን በሙሉ ምስቅልቅል ሲያደርጉት ይኖራሉ።

👉የዛር መናፍስቶች ዓይነጥላ ገርጋሪና የሕይወት መሰናክል በመሆን በመልካምነት እራሳቸውን ደብቀው በጤናም ሆነ በእድገት የሰውን ልጅ ህይወት ምስቅልቅ ውስጥ ከተውት ይኖራሉ

👉የዛር መናፍስቶች ህፃን አዋቂ ሽማግሌ አይመርጡም ሁሉንም ያሰቃሉ።

👉የዛር መናፍስት በተለያዩ መንገዶች ካልተወገዱና ካልተገሰፁ እስከ ሰባት ትውልድ ድረስ የመውረድ አቅም እንዳላቸው ምሁራን ያትታሉ።

👉የዛር መናፍስቶች መልካምና ጥሩ ነገር በመምሰል ከላይ ወደታችኛው ትውልድ በመውረድ ለአካላዊና ስነልቦናዊ ችግር የሚዳርጉ መናፍስት ናቸው።

⏩#የዛር መንፈስ #በሴቶች ላይ
✅ ትዳር ይገረግራል
✅ በሰው ዘንድ እንዲጠሉ ያደርጋል
✅ ተስፋ ማስቆረጥ
✅ የገንዘብ አለመበርከት
✅ የፊንጢጣ ኪንታሮት

👉 የወገብ ሕመም ይፈጥራል
👉 የራስ ሕመም (ማይግሪን)
👉 መጥፎ የሰውነት ጠረን 
👉 መጥፎ የአፍ ጠረን
👉 ቁርጥማት ያመጣል
👉 እግር ሰብስቦ ይይዛል

☑ጓደኝነት ጀምሮ ምክንያት አልባ መለያየት
☑እራስን ዝቅ ማድረግየበታችነት ስሜት
☑ተስፋ መቁረጥ
☑ፀባይ መቀያየር
☑ወንድ ልጅን ለማውራት መቸገር
☑ህልመ ሌሊት
☑ሱሰኛ መሆን
☑የእድል መዘጋጋት

✅የወር አበባ መዛባት (መብዛት )
✅ማስለቀስ፣መጨናነቅ
✅ቤተሰብ ማስጠላት
✅ሥራ ማስጠላት
✅ከፍተኛ የራስ ህመም
✅ተኝቶ መቃዥት
✅ፍርሐት
✅ከፍተኛ ላብ
✅የሰውነት ጠረን መቀየር
✅መጥፎ የአፍ ጠረን
✅በሰው መሐል ሐሳብን መግለፅ አለመቻል
✅#ከሥራ ባልደረባ ጋር አለመስማማት

✳ ህልመ ለሊት ያመጣል
✳ የትዳር ማስጠላት  
✳ ለተለያዩ ሱሶች ይዳርጋል
✳ ሥራ ሲሰሩ ሲያነቡ ማዛጋት መደበት
✳ ሆድ መጮህ መገላበጥ መንፋት ጋዝ መብዛት

⏩የበታችነት ስሜት መሰማት
⏩የምግብ ፍላጎት መዝጋት
⏩ማክሳት ማቅጨጭ
⏩ጥርስን ማንቀራጨጭ በህልም ማሽናት
⏩ለጨጓራ በሽታ መዳረግ
⏩ስኳር ፣ ደም ግፊት ፣ አስም ፣ ኩላሊት
ማምጣት 

🔀#ወንዶች ላይ የዛር መንፈስ፦
🔶ህልመ ሌሊት
🔶ድክመተ ወሲብ
🔶ከፍተኛ ፍርሐት
🔶ትዳር ማጣትን
🔶የሥራ ዕድል መዝጋት
🔶መካን ማድረግ
በጣም የባሰ እንደሆነ የአልጋ ቁራኛ አድርገው ማሰቀመጥ የመሳሰሉት ችግሮች የመፍጠር ኃይል አላቸው።

የዛር መናፍስትን እንዴት ማራቅ ይቻላል ?
የማያዳግም መፍትሔውን በመውሰድ
ሀሉም በሃይማኖቱ መበርታት
#መፍትሔ
መፍትሔ
👉የአንፋር ተቀጽላ
👉የቡና ተቀጽላ
👉የሎሚ ተቀጽላ
👉የእጸ ሳቤቅ ሥርና ቅጠል
👉የሎል ሥሩን

እነዚህን ዕፀዋቶች በንጽሕና በማዘጋጀት አድርቆ ሸርከት አድርጎ በመፍጨት ከሁሉም ለ ፳፩(21) ቀን ሚሆን እኩል እኩል መጠን ጨምሮ ማዋሃድ ከተዋሀደ በኃላ በንፅህና ሆኖ ከአልኮል መጠጥ ከሴት ተከልክሎ ማታ ማታ ፳፩ ቀን በስኳር ማንኪያዋ አንዳድ እየጨመሩ ታጥኖ መተኛት።

⏩#የሚከለክሉ ነገሮች
⏯አልኮል
⏯ተልባ
⏩ግንኙነት


#አድራሻችን_ቁ/1 ምዕራብ ጎጃም ቡሬ ከ አደባባይ ወደ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን መሄጃ...

#አድራሻችን_ቁ/2 አ/አ ከ አየር ጤና ወደ አለም ባንክ መሄጃ በ ቤተል መገንጠያ በኩል ኪዳነምህረት ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት  እንገኛለን

👉 የስራ ሰአት ከሰኞ -ቅዳሜ ከ2:30 እስከ 11:00 ሰአት  ለበለጠ መረጃ (ለሐሳብ አስተያየተዎ )
☎️#0918487073  ወይም
📞#0920253444 ይደውሉልን

✅ቴሌግራም መልክት @mergetaam

✅ቴሌ ግራም ቻናላችን
https://t.me/+cBvwauvLhQAxNWE8

✅ቴሌ ግራም ቻናላችን
https://t.me/+yYkKb77I1kw1NTM0

✅የቴሌ ግራም ቻናላችን
https://t.me/mergeta_amdebrhan

✳️የቲክቶክ ቻናላችን
@mergetaamdebrhan' rel='nofollow'>http://tiktok.com/@mergetaamdebrhan

✅YouTube ገፃችን
https://www.youtube.com/@merigetaa

የምንሰጣቸው አገልግሎቶች
1, ለስንፈተ ወሲብ
2, ለኪንታሮት
3, ለዓይነ ጥላ
4, ለስኳር
5, ለእጀሰብ/ድግምት
6, ለኩላሊት ጠጠር
7, ለመፍትሔ ሥራይ
8, ለጭርት/ቋቁቻ
9, ለሆድ ውስጥ ሥራይ
10, ለቆዳ/ለለምጥ
11, ለወር አበባ መዛባት
12, ለወፍ/ጉበት
13, ለነስር
14, ለጫማ ሽታ
15, ለአፍ ለሰውነት ጠረን
16, ለሱስ ለማንኛውም እኒህና መሰል ችግሮች ካሉ መፍትሔ አግኝተው ይመለሳሉ።

👉 ❗️❗️እውቀቱ ሳይኖራቸው በተመሳሳይ ፅሁፍ ኮፒ እያደረጉ ከሚያጭበረብሩ ሌቦች ተጠንቀቁ ሌባው በዝቷል ❗️❗️




⏩#የሴት ልጅ ዓይነ ጥላ ምልክትና #መፍትሔ አጠር አድርጌ እንደሚከተለው አቀረብንላችሁ
✅ ትዳር ይገረግራል ፣ ያፈርሳል ይዘጋል
✅ ቤተሰብን ያስጠላል፣ከቤተሰብ ያርቃል
✅ በሰው ዘንድ እንዲጠሉ ያደርጋል
✅ ተስፋ ማስቆረጥ ህይወትን ባዶ ያደርጋል
✅ የገንዘብ አለመበርከት ፣ መገርገር
✅ የፊንጢጣ ኪንታሮት ያመጣል
✅ የወር አበባ ያዛባል (ይዘጋል)

👉 የወገብ ሕመም ይፈጥራል
👉 የአጥንት መገጣጠሚያ ህመም
👉 የራስ ሕመም (ማይግሪን)
👉 መጥፎ የሰውነት ጠረን 
👉 መጥፎ የአፍ ጠረን
👉 ቁርጥማት ያመጣል
👉 እግር ሰብስቦ ይይዛል
👉 ለሰው ጥሩ ሰርተው አለመመስገን

☑#ጓደኝነት ጀምሮ ምክንያት አልባ መለያየት
☑#እራስን ዝቅ ማድረግ
☑#ተስፋ መቁረጥ
☑#ፀባይ መቀያየር
☑#ወንድ ልጅን ለማውራት መቸገር
☑#ባል እየመጣ መመለስ
☑#ህልመ ሌሊት
☑#እራስን መደበቅ/ከቤት አለመውጣት
☑#ሱሰኛ መሆን
☑#የእድል መዘጋጋት

✅#ማስለቀስ፣መጨናነቅ
✅#ቤተሰብ ማስጠላት
✅#ሥራ ማስጠላት
✅#ከፍተኛ የራስ ህመም
✅#ተኝቶ መቃዥት
✅#ፍርሐት
✅#ከፍተኛ ላብ
✅#በሰው መሐል ሐሳብን መግለፅ አለመቻል
✅#ከሥራ መባረር
✅#ከሥራ ባልደረባ ጋር አለመስማማት

✳ ሕልመ ሌሊት ያመጣል
✳ የትዳር ማስጠላት 
✳ ለፍቅር አጋር ስሜት አለመኖር
✳ ለተለያዩ ሱሶች ይዳርጋል
✳ ቤት ማስጠላት ውጭ ማምሸት
✳ ሥራ ሲሰሩ ሲያነቡ ማዛጋት መደበት
✳ ሆድ መጮህ መገላበጥ መንፋት ጋዝ መብዛት
✳ በሚሰሩት ሥራ ደስተኛ አለመሆን

⏩የበታችነት ስሜት መሰማት
⏩ሀገር ለሀገር ማዞር
⏩የምግብ ፍላጎት መዝጋት
⏩ማክሳት/ማቅጨጭ
⏩ጭንቀት ፣ ድብርት
⏩ሌሊት ማቃዠት ፣ ማስጮህ
⏩በሕልም ማስጨነቅ
⏩ጥርስን ማንቀራጨጭ በሕልም ማሽናት
⏩ለጨጓራ በሽታ መዳረግ
⏩ስኳር ፣ ደም ግፊት ፣ አስም ፣ ኩላሊት
ማምጣት 

⏩#የጭንቀት_መንፈስ_ችግር ያስከትልባታል
🔶ተስፋ መቁረጥ
🔶ፍርሃት ፍርሃት ማለት
🔶የበታችነት ስሜት መሰማት
🔶በራስ አለመተማመን
🔶ሐሳብን በነፃነት አለመግለፅ
🔶ከፍተኛ ላብ መፍጠር
🔶ሰላም ማሳጣት መረበሽ
🔶እራስን አጥፋ አጥፋ ማለት

⏩#የወንድ ዛር ሴቶች ላይ ያለው ተፅኖ
❇️ትዳር መገርገር
❇️ከትዳር አጋር ማለያየት
❇️መነጫነጭ መበሳጨት
❇️ወንዶች እየቀረቡ መሸሸት
❇️ፍቅር ጀምረው መጥፋት
❇️የፆታዊ ግንኝነት ላይ ስሜትን ማጥፋት
❇️በግንኙነት ጊዜ ደስተኛ አለማድረግ
❇️የወር አበባ መዛብት መብዛት/ማነስ

         ⏩#መፍትሔ
⏯#የጠንበለል ሥሩን
⏯#የግሞሮ ሥሩን
⏯#የግሞሮ ሥር
⏩#የምስርች ሥር

እነዚህን እጸዋቶች ሥራቸውን ቅጠላቸውን በማድረቅ እና በማላም ከሁሉም ለ21 ቀን በስኳር ማንኪያዋ ሚሆን አዘጋጅቶ ማታ ማታ ከ14-21 ቀን ቢታጠኑት ከላይ የዘረዘርኳቸውን ችግሮች ያስወግዳል

#አድራሻችን_ቁ/1 ምዕራብ ጎጃም ቡሬ ከ አደባባይ ወደ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን መሄጃ...

#አድራሻችን_ቁ/2 አ/አ ከ አየር ጤና ወደ አለም ባንክ መሄጃ በ ቤተል መገንጠያ በኩል ኪዳነምህረት ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት  እንገኛለን

👉 የስራ ሰአት ከሰኞ -ቅዳሜ ከ2:30 እስከ 11:00 ሰአት  ለበለጠ መረጃ (ለሐሳብ አስተያየተዎ )
☎️#0918487073  ወይም
📞#0920253444 ይደውሉልን

✅ቴሌግራም መልክት @mergetaam

✅ቴሌ ግራም ቻናላችን
https://t.me/+cBvwauvLhQAxNWE8

✅ቴሌ ግራም ቻናላችን
https://t.me/+yYkKb77I1kw1NTM0

✅የቴሌ ግራም ቻናላችን
https://t.me/mergeta_amdebrhan

✳️የቲክቶክ ቻናላችን
@mergetaamdebrhan' rel='nofollow'>http://tiktok.com/@mergetaamdebrhan

✅YouTube ገፃችን
https://www.youtube.com/@merigetaa

የምንሰጣቸው አገልግሎቶች
1, ለስንፈተ ወሲብ
2, ለኪንታሮት
3, ለዓይነ ጥላ
4, ለስኳር
5, ለእጀሰብ/ድግምት
6, ለኩላሊት ጠጠር
7, ለመፍትሔ ሥራይ
8, ለጭርት/ቋቁቻ
9, ለሆድ ውስጥ ሥራይ
10, ለቆዳ/ለለምጥ
11, ለወር አበባ መዛባት
12, ለወፍ/ጉበት
13, ለነስር
14, ለጫማ ሽታ
15, ለአፍ ለሰውነት ጠረን
16, ለሱስ ለማንኛውም እኒህና መሰል ችግሮች ካሉ መፍትሔ አግኝተው ይመለሳሉ።

ቡዙዎቻችሁ በጽሁፍ መመሳሰል የዘመኑ ሰለባ እንዳይሆኑ አድራሻ ያለው በመንግስት ደረጃ ፍቃድ መሰጠቱን አረጋግጠው ይጠቀሙ። እናመሰግናለን


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
መዝሙረ ዳዊት በውስጡ ያዛቸው ጥበቦች
✳️የቲክቶክ ቻናላችን
@mergetaamdebrhan' rel='nofollow'>http://tiktok.com/@mergetaamdebrhan





16 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.