መሪጌታ አምደብርሃን የባህል ህክምና መስጫ ማዕከል 🌿🌿🌿


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha


☑ ከጥንት አባቶቻች በተቸረን ሰሎሞናዊ ጥበብ ተፈጥሮ ያበቃላቸው የእፅዋት መድሀኒቶችን በመጠቀም ክፉ ዓይነ ጥላ ፣ በቤተሰብ ወይም በዘር የሚተላለፉ መናፍስት መፍትሔዎቻቸው ይተነተናሉ።
☑ አድራሻ ቁጥር 1 ምዕራብ ጎጃም ቡሬ ቁጥር 2 አ/አ እንዲሁም በተለያዩ የክልል ከተሞች እንልካለን
📞#0918834904
📞#0915310455
መልዕክት ካለዎት @merigetaamedeberhan

Связанные каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Statistika
Postlar filtri


🌱🌱ዕፀ አንግሥ ምንድነው🌿🌿

📖#እፀ_አንግሥ የሚደገመው በእጽዋት ለይ ሲሆን ....
🪴ከባህላዊ ህክምና ውጪ ማለትም እፅዋቶች በእራሳቸው ከሚሰጡት ተፈጥሮአዊ ጥቅም በተጨማሪ ሌላ መንፈሳዊ ሀይልን እንዲቀናጁ በእጽዋቶች ላይ የሚደገመው #እፀ_አንግሥ ይባላል ።
👉 ይህ ፀሎት እፅዋቱን ከመቁረጣችን በፊት ለፈለግነው አላማ እንዲውል #ለዚህ_ሁነኝ ብሎ #እፀ_አንግሡን ደግሞ መቁረጥ ነው ።
👉በ #እፀ_አንግሥ የሚቆረጡ #እፅዋቶች ጥቂት ናቸው ።
👉ብዙ ቦታም በቅለው አይገኙም
👉በርሀማ ቦታ ላይ / ተራራማ ቦታ / በወንዝ ዳርቻ / በገደላ ገደል ቦታ ብዛት በቅለው የሚገኙ ሲሆን
ለሰዎች ለመኖር በማይመች / ሰዎች በማይኖሩበት ቦታ ለይ በጥቅጥቅ ጫካ በቅለው ይገኛሉ ።
👉 የሚሰጡት ጥቅምም እረቂቅ እና አስማታዊ ጥበብን ያካተተ ነው ።
👉እነዚህ #እፅዋቶች ጥቂት ከመሆናቸውም ባሻገር ከስራቸው ጠባቂ መልአክ አላቸው ተብሎ ይታመናል !!!
ለዚህም ነው አንዳንድ ዕፅዋቶች ዝም ተብለው የማይቆረጡት
👉በቅድሚያ ከስራቸው ካሉ ጠባቂ መልአክ ጋር መዋረስ / መወዳጀት / መወሐድ ያስፈልጋል ።
👉ይሄን ለማድረግ የተለያዩ ቅድመ ዝግጅቶች ያሉት ሲሆን በዝግጅቱ ላይ የሚያስፈልጉ ነገሮች አሉ እነሱም #ጢሶች #እጣን #ከርቤ #ሉባንጃ እያጤሱ
#የኑግ #የቆሎ ዓይነት ... የመጠጥ አይነት አቅርቦ ማርና ወተት ከእፅዋቱ ስር አፍስሶ ,,, አንቺ እፅ ,,, በተጠጉሽ ,, በሚጠብቁሽ ,, በፈጠረሽ ,, #አምላክ ይሁንብሽ !!! ፍቃዴን ፈፅሚልኝ ?
እየተባለ ወይም የ #እፀ_መላክ #እፀ_አንግስ ደግመህ ማንገሻውን ፀሎቱ ለይ የሚጠይቀውን ግብር አቅርበህ ....
,,, ግብርህ እሄውልህ ,,
ለኔም በዚህ እፅዋት ስም ጉዳዬን ፈጽምልኝ / አድርግልኝ እየተባለ ደጋግሞ መቁረጥና ለተባለው ነገር መሞከር ነው ።
👉ከዚህ ውጪ በድፍረት እፅዋቱን ካለምንም ነገር ካለገቢር ለመቁረጥ ቢሞክሩ አልያም ቢቆርጡት ሁለት ነገሮችን ያስከስታል።
1 . እፅዋቱ ለታሰበው አላማ ሳይውል ይቀራል የመስራት እድል አይኖረውም
👉ምክንያቱም ከላይ እንደገለፅኩት የእፅዋቶች የበላይ ጠባቂ ስላላቸው የእነሱን ፍቃድ በ #ገቢሩ ወይንም #እፀ_አንግሡ መሰረት መጠየቅ አለባችሁ
2 . እፅዋቶች በበላይ ጠባቂ ስለሚጠበቁ ለመቁረጥ አደለም ለመንካትም የሚያሰጉ እፆች ይገኛሉ ።
ስለዚህ በድፍረት ቢነኩዋቸው ሆነ ቢቆርጡአቸው ,, አምእሮን የመንሳት ,, ነውነትን ሽባ የማድረግ ,, ቡዳ ያደርጋሉ ,,መጋኛ ያስመታሉ ,, በመናፍስት ያስጠቃሉ ,,,,,,
መጠንቀቁ የሚበጅ ይመስለኛል ።
👉ሌላው በአንድ ጊዜ በአንድ ቀን ገብሬ #እፀ_አንግስ ደግሜ ያሰብኩትን እሆናለሁ / አሳካለሁ ማለት አይቻልም ።
በአንድ ቀን የመምህርን የዶክተርን ሞያ አውቄ አደርጋለሁ ማለት እስካልቻለ ድረስ
ለእፅም ባንድ ቀን ለምን አልሰራም ብሎ ተስፋ መቁረጥ የለም ።
መለማመድ ወይም የሚፈልጉትን ነገር እስከሚያገኙ ድረስ ከጠበብት ሊቃውንት አባቶች በማማከር ውጤት ይገኛል ።

,,, ለክፉም ለደጉም ይሆናል ብዬ ለእናተ ለጥበብ ወዳጆች አካፍዬአችኃለው።

,,, ጥበብ በራሱ ክፋት የለውም ጥሩም መጥፎም የሚያደርገው የደጋሚው እና የአስደጋሚው ሀሳብ ነው


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish


፯ቱ፤7ቱ፤ሰብዓቱ፤ሰባቱ፤ የቅመም ዓይነቶች ለጨጓራ መፍትሔ ሲውሉ!!!

♦ትህትና ለኢትዮጵያ ልጆች!
♦መዋደድ ለመላው የዓለም ህዝብ!
♦አንድነት ለኢትዮጵያ ህዝብ!

#ከሊቅ እስከ ደቂቅ ብዙ ጊዜ ከአንደበታችን የማይለይ የጨጓራ በሽታ ተጠቂ ኖት?

♥የጨጓራ ባክቴሪያ ወይም ሄሊኮባክተር ፓይሎሪ(♥

📌የጨጓራ ባክቴርያ የባክቴሪያ አባል ሲሆን ወደ ሰውነታችን በመግባት በምግብ ጉዞ መንገድና ጨጓራ ውስጥ መኖር የሚችል ነው፡፡

የጨጓራ ባክቴርያ የሚከተሉት ምልክቶች ሊታዩ ይችላሉ፡-
📌 የሆድ መነፋት፣
📌ግሳት፣
📌የረሃብ ስሜት አለመሰማት፣
📌ማቅለሽለሽ፣
📌ማስመለስ፣
  📌ያለምክንያት ክብደት መቀነስ ሊታዩ ይችላሉ፡፡

✔️በጨጓራ ውስጥ የሚያጋጥም ቁስለት ደም ወደ ከርሳችንና አንጀታችን እንዲፈስ ሊያደርግ ይችላል፤ ከባድ የሚባል የጤና ችግርም ሊፈጥርብን ይችላል፡፡ በመሆኑም የሚከተሉት ምልክቶች ከታዩን ወደ ሕክምና በመሆድ የምንገኝበትን ሁኔታ መመርመር አለብን፡፡
📌የሰገራ መጥቆርና ደም መቀላቀል ካለ፣
📌ለመተንፈስ መቸገር ካጋጠመን፣
📌ያለስራ የመልፈስፈስና የድካም ስሜት ከተጫነን፣
📌የቆዳ መገርጣትና ራስን የመሳት ሁኔታ ከታየብን፣
📌የተፈጨ ቡና የመሰለ ነገር የሚያስመልሰን ከሆነ፣
📌 ከባድ የሆድ ህመም ካለን የጨጓራ ባክቴሪያ ሊሆን ስለሚችል መታየት አለብን፡፡

✔️አልፎ አልፎ ደግሞ የጨጓራ ባክቴሪያ የጨጓራ ካንሰር ሊያስከትል ይችላል፤ እንዲያ ሲሆን በመጀመሪያ አንዳንድ ምልክቶች ሊያሳይ ይችላል፤ ለምሳሌ ማቃር ሊበዛን ይችላል፡፡ በመቀጠል ግን የሆድ ሕመምና ማበጥ፣ ማቅለሽለሽ፣ ያለመራብ ስሜት፣ ትንሽ ከተመገብን በኋላ በጣም የጠገብን የሚመስለን ስሜት መሰማት፣ ማስመለስና ምክንያቱ ያልታወቀ የክብደት መቀነስ ሊታይብን ይችላል፡፡

🙏ምክር
የጨጓራ ባክቴሪያን ለመከላከል የምንወስደው እርምጃ ሌሎች ጀርሞችን ለመከላከል ከምንወስደው የጥንቃቄ እርምጃ ጋር ተመሳሳይ ነው፤ ይኸውም እጅን በሳሙና ከምግብ በፊትና ከመፀዳጃ ቤት መልስ በደንብ መታጠብ፣ በፅዱ ሁኔታ ያልተዘጋጀ ወይም የቀረበ ምግብና መጠጥ አለመጠቀም፣ ያልበሰሉ ምግቦችን አለመጠቀም ናቸው፡፡ እንዲሁም ጭንቀትና ውጥረት፣
♦ቅመም የበዛባቸው ምግቦችና♦
ሲጋራ ማጨስ ለጨጓራ ቁስለት የማይዳርጉን ቢሆንም ሁኔታውን ግን ሊያባብሱ ስለሚችሉ ቢያንስ ከቁስለት እስከምንድን ድረስ መጠቀም ወይም ማድረግ የለብንም፡፡
❓ልብ በሉ ቅመም የጨጓራ ህመም እንደሚያባብስ ሁላ ቅመማቅመም የጨጓራ መዳኛ ሲሆኑም እናያለን።

✅የጨጓራ ባክቴርያ፣አሲድ የመርጨት ችግር፣መፍትሔዎቻቸው✅

🌿የጥቁር አዝሙድ ፍሬ
🌿የኮረሪማ ፍሬ
🌿የጤና አዳም ፍሬ
🌿የሰሊጥ ፍሬ
🌿የእንስላል ፍሬ
🌿የፌጦ ፍሬ
🌿የቁንዶ በርበሬ ፍሬ

✅እነዚህ የቅመም ዝርያዎች ከምግብነት ማጣፈጫ አልፈው ለየቅልም ቢሆኑ እጅግ ፍቱን እና ውስብስብ ያሉ ችግሮችን የመፍታት ዓቅም ያላቸው አሁን ደግሞ በሕብረት ሁነው የጨጓራ በሽታን ለማከም በሰፊው የጥበብ ድህረገጻችን በኔ ጋባዥነት ብቅ ብለዋል።

✅የቅመሞቹ አዘገጃጀት እና አጠቃቀም!
በቅድምያ በንጽሕና ለየብቻ እንዲደርቁ ማድረግ የደረቀ ከገዛንም ለየብቻ  በንጽህና መፍጨት።

✅ከዛ በመቀጠል ንፁህ ሩብ ኪሎ ማር ማዘጋጀት ለስኳር ታማሚዋችም ይሆናል።የስኳሩ መጠኑ ቅመሞቹ ስለሚያቀዘቅዙት አትስጉ!

#ከላይ ያስቀመጥናቸው የቅመም ዓይነቶች ግማሽ ግማሽ የስኳር ማንኪያ ከ ሰባቱም ቅመማቶች በመለካት ወደ ተዘጋጀው ሩብ ኪሎ ማር ማቀላቀል።

#በመቀጠል አንድ ላይ በንጽህና በደንብ አድርገው ማዋሃድ!
ይህ የቅመሞች ውህድ ጧት ጧት አንድ አንድ የስኳር ማንኪያ በመለካት በባዶ ሆድ መብላት።

#መድኃኒቱ ከወሰዱ ከ አንድ ሰዓት በኃላ የሚስማማዎት ምግብ መመገብ ይችላሉ።

#ይህ መፍትሔ ልዩ ከመሆኑ የተነሳ በጨጓራ ምክንያት ለዓስርት ዓመታት የሚያቃጥሉ ነገር፤ስጋ፣ዶሮ ወጥ፤ስንዴ ነክ፣ መብላት የማይችሉትን ማከም የቻለ ልዩ ውህድ ነው።

#ፍቱን ነው።
📌መፍትሔውን ተጠቅመው ምስክር ይሁኑ፡፡

#ውድ የዚህ ድህረገጽ ቤተሰቦች ስለ ሰባቱ ቅመማት ሌላ እና ልዩ ምስጢራቸው በሌላ ጊዜ የማጋራችሁ ይሆናል።

#ይህ ማለት አንድ የጮጓራ በሽተኛ ታደጋችሁ ማለት ነው።
✅SHARE✅ እናድርግ የሰከንድ ስራ ናትና!

❤️ሕይወትን ለመታደግ ንቁ ትውልድን እንፍጠር።
❤️መልካምነት ግዴታችን ነው።
❤️ተፈጥሮን በጥበብ እንቃኛት።

✅የቀደምት አባቶቻችንን እውቀት እና ጥበብ ሳይበረዝ እንደወረደ ይቀርባል። የአያቶቻችን የእጽዋት ጥበብ፣ በህይወትዎ ላይ ለሚያጋጥሙ ችግሮችና መፍትሔዎቻቸው፣ ክፉ መናፍስትን እንዴት ማራቅ እንደምንችል፣ የብራና መጽሐፍት እና ጥቅማቸው በዚ ይዳሰሳሉ።








👆👆🌿🌿አዝዋሪት አዙር አዙሪት አሸሺ🌿🌿
/ሽዋሺውይት ነፋስ/ ሸውሻውይት አደናግር ጀብር የሚባል ስም አሉት ሲነኩዋቸው አእምሮ የሚያስረሱና የሚያፈዙ እፅዋቶች ብዙ አይነቶች ናቸው ።
ነገር ግን ከነዚህ እግዚአብሔር ለሰው ልጅ በሰጣት የተፈጥሮ ባህሪይ ጥበብ የምታገለግለውን እፅ እፅፋለሁ ።
ከእነርሱም አንዷ ባለሀረግ ስትሆን ሁለተኛዋ ግን ድቃቃ ቅጠል ያላት ሆና ከስርዋ ድንች የመሰለ እንደእንዝርት ክብ ሁኖ አዝዋሪት የአለው ነው ።
በመጀመሪያ በእፀ እስክንድር /ወንዴው ምስርች/ ለበቅእኔ ቀደምኩሽ ሳትቀድሚኝ ብለህ ንካት ከዚያ በፈለከው ነገር ለዚህ ሁኝኝ ብለህ ነጭ ቄብ ዶሮ አርደህ ቁረጥ ከቆረጥክበት ቦታ ዶሮውን ቀብረህ ስሩን ይዘህ ሂድ ።
ገቢሩ....
1.ለመፍዝዝ በጥቁር ዶሮ ቆርጠህ ስሩዋን ያዝ
2.#ለገንዘብ ከሳጥን ውስጥ ማስቀመጥ
3.#ለገበያ ከገቢያ መሃል ቀብሮ ገበያው ሲሞቅ አውጥቶ ከሚሸጡበት ማስቀመጥ
4.#ለመሰውር ከጥቁር ድመት አንግሰህ ቆርጠህ በግራ ጎንህ ያዝ
5.#ለእጣ አርብ ቀን ነቅለህ ከእጣን ጋር አጥነህ ያዝ
6.#ለመስተባርር እገሌን የእገሌን ልጅ ከዚህ አገር ነቅለህ አብረው ብለህ ነቅለህ በጥቁር ድንጋይ ወቅጠህ በጥቁር ዶሮ ጉበት ነስንሰህ ለጥቁር አሞራ ስጥ
7.#ለመንድግ+ለምህሳበ_ንዋይ  የገበሎና የእስስት እራስ ጊንጥ እንዳለች የእፀልባዊት  የእሺኮኮ ጎመን የአዝዋሪት  /አዙሪት/ ስር በጥቁር ዶሮ ደም ለውሶ አድርቆ በጥቁር ፍየል ቆዳ ቦርሳ አሰፍቶ በውስጡ አድርጎ መያዝ ።
8.#ለግርማ_ሞገስ ‛‛ሜኤል አላልኤል’’ 99 ጊዜ ደግመህ ለዚህ ነገር ሁነኝ ብለህ ቁረጥና ከቀጠጥና ከእፀአንበሳ ስር ጋር ደቁሰህ ግማሹን በነጭ ማር ብላ፡ ግማሹን በነጭ ዶሮ ደም ለውሰህ ያዝ ።
9. #የተመኘህው_ነገር_እንዲሳካ ሻኤል 3 ሸማልዳ 3 አሻማሺል 11 ጊዜ በስሯ ደግሞ ቀጥቅጦ በውሀ ዘፍዝፎ ፊትን ታጥቦ መሄድ ነው ።
10. #ገንዘብ_ለማግኘት ‛‛አጂማን 99፡ አጁማን 49፡ አላጁማን 51’’ ጊዜ በፀደል ቀበሮ ብራና ጽፎ በሳጥን ከስርዋ ጋር ማስቀመጥ ነው ።
11. #ለመፍትሄ_ሀብት ለሲሳይ የገዴ እንቁላል ወይም ልብና ጥፍሩዋን ስርዋን በጥጥፍሬና ጥጥ ሸፍነህ በበላዩ በወርቀ ዘቦ ግምጃ ጠምጥመህ ያዝ ።
12. #ለመስተፋቅር የጎርጎሮ ተቀጽላ የከልብ አፈ ማህፀን ከስርዋ ጋር ደቁሶ ለሴት ከጭንዋ ለወንድ ከክንዱ መቅበር ነው ።
13. #ለምህሳበ ንዋይ የጭላት ወይም የጭልፊት ልብ የእፀ ልባዊትና የአዝዋሪት ስር የወርቅ የብር ሙራጂ ጋር ከኪስ ወይም ከሳጥን ውስጥ ማስቀመጥ ነው ።
አዝዋሪት ከዚህ በላይ ለተጻፉትና ያልተጻፉ ከ 70 በላይ ገቢሮችን ለመስራት በመጀመሪያ ከስርዋ ጠባቂ መልአክ ጋር መለማመድ እና መዋረስ ማለት መወሀድ ያአስፈልጋል ይሄም ማለት የተለያዩ ጢሶች እጣን ከርቤ ሉባንጃ አሰያጤሱ የኑግ የቆሎ ዓይነት የመጠጥ አይነት አቅርቦ ማርና ወተት ከስርዋ አፍስሶ አንቺ እፅ በተጠጉሽ በሚጠብቁሽ በፈጠረሽ አምላክ ይሁንብሽ ፈቃዴን ፈጽሚልኝ እየተባለ ወይም የእፅ መላክ የእፅ ንጉስ ምሰህ ግብርህ ይሄውልህ ለእኔም በዚህ እንጨት ስም ጉዳዬን ፈጽምልኝ አድርግልኝ እየተባለ ደጋግሞ መቁረጥና ለተባለው ነገር መሞከር ነው ።
በአንድ ጊዜ በአንድ ቀን ገብሬ እሆናለሁ ወይም በአንድ ቀን የመምህርን የዶክተርን ሞያ አውቄ አድርጋለሁ ማለት እስከ አልተቻለ ድረስ ለእፅም በአንድ ቀን ለምን አልሰራም ብሎ ተስፋ መቁረጥ የለም ።
መለማመድ ወይም ለፈለጉት ነገር ለዚህ ሁነኝ ብሎ መቁረጥ ነው ።
ለክፉም ለደጉም ይሆናል ።

14. #ለምህሳበ_ንዋይ የጠላህ ሰው እንዳያይህ ስሩን ከእሬት ተቀጽላ ጋር በጥቁር ውርንጭላ አህያ በግራ ጆሮ ደም ለውሶ በግራ ኪስ መያዝ ነው ።
15. #ለአቃቤ_ህግ ስሩን በአሳ ሀሞት ለውሰህ ቀብተህ አውስብ

👉የቀደምት አባቶቻችንን እውቀት እና ጥበብ ሳይበረዝ እንደወረደ ይቀርባል። የአያቶቻችን የእጽዋት ጥበብ፣ በህይወትዎ ላይ ለሚያጋጥሙ ችግሮችና መፍትሔዎቻቸው፣ ክፉ መናፍስትን እንዴት ማራቅ እንደምንችል፣ የብራና መጽሐፍት እና ጥቅማቸው በዚ ይዳሰሳሉ።
መሪ አምደ ብርሃን !
ሌሎች መፍትሔዎች ለምትሹ በሙሉ
ለበለጠ መረጃ 0918834904 ብለው በስራ ሰዓት ይደውሉ።
✅ቴሌግራም መልክት የምቀበልበት
@merigetaamedeberhan




🌿ለማታ የማቀርብላችሁ እጅግ መልካም የመዝሙረ ዳዊት ከህቡዕ ስም ጋር በማወዳጀት የሚጸለይ ጥበብ እንዳለ ሁኖ ትንሽ ስለ መዝሙረ ዳዊት ግንዛቤ ይፈጥርልን ዘንዳ ነው ይህንን ማቅረቤ!🌿
👉ይነበብ👇
❤️የመዝሙረ ዳዊት ዓይነቶች እንዴት መለየት እንችላለን? መዝሙራት በምን ዓይነት ሁኔታ ይከፈላሉ? አመዳደባቸውስ እንዴት ነው?❤️

👉የመዝሙራት ዓይነቶች መለየት አስቸጋሪ ቢሆንም ቀጥሎ የተጻፈው መረጃ ሊመራን ይችላል፡፡
የምስጋና መዝሙሮች ፦

👉ሀ) የእግዚአብሔርን ስም የሚያመስግኑ(መዝ 8፤ 20፤30፤34፤65፤68፤75፤76፤83፤87፤88፤91፤95፤107፤136)፡፡
ለ) ከመከራ ማዳኑን የሚያወድሱ (መዝ 18፤30፤34፤65፤75፤115፤116፤118፤138)፡፡
እነዚህ መዝሙሮች ዋና ትኩረታቸው እግዚአብሔርን ማመስገንና ማወደስ ነው፡፡ የሚያመሰግኑትም እግዚአብሔር ለፍጥረት ሁሉ ስላደረገውና እያደረገው ስላለው ድንቅ ሥራ ነው፡፡

👉ኃጢአተኛ በኃጢአቱ የሚያዝንበት(መዝ 6፤ 32፤38፤51፤102፤130፤143)፡፡
የዚህኛው ክፍል ዋና ትኩረት የኃጢአተኛ ሰው መጸጸትና ወደ እግዚአብሔር የሚያቀርበው ልመና ነው፡፡ ኃጢአተኛው እግዚአብሔርን እንዳሳዘነ አምኖ በመገንዘብ ስሕተቱን ይቀበላል፤ ያዝናል፤ ይጸጸታል፤ ወደ እግዚአብሔር እየጸለየ ምሕረት ይለምናል፡፡
በመከራ ያለ ሰው የሚጸልይበት (የሚጽናናበት)(መዝ 3፤5፤7፤17፤20፤30፤31፤54፤59፤142)፡፡
በመከራ ውስጥ ያለ ሰው ስለደረሰበት መከራ ወደ እግዚአብሔር ይጮኻል፤ ይመጸናል፤ መከራውን ለእግዚአብሔር ይናገራል፤ መከራ እንዲደርስበት ያደረጉት ሰዎችን ይራገማል፤ በመከራ ውስጥ እያለ እግዚአብሔር ለምን ዝም እንዳለው ይጠይቃል፤ ከመከራው እንዲያወጣውም ይማጸናል፡፡

👉ዘማሪው እግዚአብሔርን ፣ ሕጉንና ቤቱን የሚናፍቅበት(መዝ 16፤ 17፤ 19፤ 40፤ 42፤ 45፤ 63፤ 73፤ 84፤ 119፤ 122፤ 128፤ 132)፡፡
እነዚህ መዝሙሮች የሚያተኩሩት በእግዚአብሔር ሕግ ፣ በቤተ መቅደስና በኢየሩሳሌም ከተማ ዙሪያ ላይ ነው፡፡ ቤተ መቅደስ እንደ የእግዚአብሔር ማደሪያ ቦታ የተጠቀሰበትም አለ፡፡ ስለዚህ ዘማሪው ወደ እግዚአብሔር ቤት ለመሄድ እንደሚናፍቅና እንደሚደሰት ይናገራል፡፡ ዘማሪው እግዚአብሔርን ለማየት እንደሚናፍቅ በተለያየ መልኩ ይገልጻል፤ ለምሳሌ ዋለያ የምንጭ ውሃ ለማግኘት እንደሚናፍቅ እኔም አንተን ለማየት እናፍቃለሁ ይላል(መዝ 42፡ 1)፡፡ እንዲሁም እግዚአብሔር ሆይ ! አንተ አምላኬ ነህ፤ አንተን ለማግኘት በብርቱ እናፍቃለሁ፤ ሁለንተናዬ አንተን ይመኛል፤ ውሃ በማጣት ደርቆ እንደተሰነጣጠቀ መሬት ነፍሴ አንተን ተጠማች ይላል(መዝ 63፡ 1)፡፡ በተመሳሳይ መልኩ የእግዚአብሔር ሕግ እንደ ብርሃን ሆኖ ሰዎች የሚመራ ስለሆነ መከበር እንዳለበትና የሚያከብሩትም በረከት እንደሚቀዳጁ የሚናገር ክፍል ነው፡፡ ለምሳሌ መዝሙር 128 ላይ እግዚአብሔር የሚያከብሩና ትእዛዛቱን በመጠበቅ የሚኖሩ ደስ ይበላቸው እያለ ይዘምራል(መዝ 128፡ 1)፡፡ በተጨማሪም ቃልህ እንደ መብራት ይመራኛል፤ ለመንገዴም ብርሃን ነው እያለ የእግዚአብሔር ሕግ ወደ እውነተኛው መንገድ እንደሚመራ ይናገራል(መዝ 119፡ 105)፡፡
ስለ መሲሕ የሚናገሩ(መዝ 2፤ 8፤ 16፤ 22፤ 40፤ 45፤ 69፤ 72፤ 110)፡፡
ይህ የሚያተኩረው እግዚአብሔር ስለሚልከው መሢሕና ስለዘሚያደርግለት ጥበቃና እንክብካቤ ላይ የሚናገር ነው፡፡ ይህ መሢሕ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ(መዝ 2፡ 7) ፣ በቀኙ እንደሚያስቀምጠውና(መዝ 110፡ 1) እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመት ለዘላለም ካህን እንደሆነ ይናገራል(መዝ 110፡ 4)፡፡
ለትምህርት የሚሆኑ (መዝ 37፤ 49፤ 50፤ 52-55፤ 60፤ 74፤ 78፤ 89፤ 104፤ 119፤ 127)፡፡
እነዚህ ምዕራፎች ውስጥ ብዙ ምክር አዘል አባባሎችና ትምህርቶች ተካተዋል፤ እነዚህም አባባሎችና ምክሮች መጽሐፈ ምሳሌ ውስጥ ከተገለጹት ጋር ተመሳሳይነት ያላቸው ናቸው፡፡ የሰዎች ትዕግሥት ፣ ታማኝነት ፣ ትሕትና ፣ በጎ ተግባራትና የመሳሰሉት ባሕርያት ወይም ክንውኖች ለሰው ልጅ መንፈሳዊ እርካታ እንደሚያሰጡና ከእግዚአብሔር ዘንድ ጸጋ እንደሚያቀደጁ ይናገራል፡፡ በአንጻሩ ደግሞ ክፉ ማድረግና የእግዚአብሔር ትእዛዝ መዘንጋት ወደ ጥፋት እንደሚመራና ከእግዚአብሔርም ጋር እንደሚያቈራርጥና መጨረሻውም እንደ በረሓ አበባ በፍጥነት መርገፍ እንደሆነ ያስተምራል(መዝ 37፡ 20)፡፡

👉ካህናት የቤተ መቅደስን ደረጃዎች ሲወጡ የሚዘምሩአቸው የመዐረግ መዝሙሮች (መዝ 120-134)፡፡
እነዚህ መዝሙሮች በተለያየ ጉዳይ ላይ የሚያተኩሩ ናቸው፡፡ የእነዚህ መዝሙሮች አብዛኛው ትኩረት የእግዚአብሔር ጠባቂነት ለማግኘት ቢሆንም ሌሎች አሳቦችም በመዝሙሮች ውስጥ በጸሎትና በልመና መልክ ተካተዋል፡፡
👉ሃሌሉያ ብለው የሚጀምሩት የሃሌል መዝሙሮች (የስብሐት መዝሙሮች) (መዝ 111-113፤ 146፤ 148-150)፡፡
እነዚህ መዝሙሮች ከሌላው ክፍል የሚለዩበት ዋናው ምክንያት ገና ከመዝሙሩ ጅማሬ እግዚአብሔርን ያመስግናል፡፡ መዝሙሮቹ ሲጀምሩ "እግዚአብሔር ይመስገን" ወይም "እግዚአብሔርን አመስግኑት" በማለት ይጀምራሉ፡፡ ስለዚህ መዝሙሮቹ የምስጋና መዝሙሮች ተብለው ይታወቃሉ፡፡

👉የቀደምት አባቶቻችንን እውቀት እና ጥበብ ሳይበረዝ እንደወረደ ይቀርባል። የአያቶቻችን የእጽዋት ጥበብ፣ በህይወትዎ ላይ ለሚያጋጥሙ ችግሮችና መፍትሔዎቻቸው፣ ክፉ መናፍስትን እንዴት ማራቅ እንደምንችል፣ የብራና መጽሐፍት እና ጥቅማቸው በዚ ይዳሰሳሉ።




Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
ሰንሰል፥ ስምዒዛ....ዕጸ ሥላሤ፦
ይህ ዕጽ ብዙ ሊቃውንት የወጡበት ዕጽ ነው።
ለልጆችም ይሰጣል
ዕጸ ሥላሤ በአንድ የግንድ ዘለላ ፫ ቅጠል በአንዴ ከበው ሲበቅሉ ዕጸ ሥላሤ ይባላሉ ልዩ የሆነ የትምህርት ገቢርም የሰራባቸዋል።
ለድርሰት
የተማሩትን ላለመርሳት
ለፈጠራ ባለሙያነት
ለንቃተ ህሊና...በአፍልሆ መልኩ
እናም ቅጠልዋ ላይ የተለያዩ አስማተ እግዚአብሔር በመጻፍ የሚከናወን ነው።
በተጨማሪም፦
በኢትዮጵያ፣ ሙሉ ተክሉ ለቁርባ ሕክምና ይጠቀማል። እንዲሁም ለሚያስቀምጥ መድኃኒት ይጠቀማል።
የሰንሰል ቅጠል ጭማቂ ለቁርባ ወይም ለወፍ በሽታይጠጣል።
የሰንሰልና የአኻያ ቅጠል ጭማቂ ለሰዎችም ሆነ ለእንስሶች ውሻ በሽታ ይሰጣል። የሰንሰል፣ የእምቧጮና የግራዋ ቅጠል ጭማቂ ለሆድ ቁርጠት ወይም ለወባ ይሰጣል።
ማስጠንቀቅያ አንድ መድኃኒት ያለ ባለሙያ ፈቃድ ው�ጭ
ወደአፍ ማስገባት አይቻልም።
መሪ አምደ ብርሃን !
ሌሎች መፍትሔዎች ለምትሹ በሙሉ
ለበለጠ መረጃ 0918834904 ብለው በስራ ሰዓት ይደውሉ።
✅ቴሌግራም መልክት የምቀበልበት
@merigetaamedeberhan


የእግዚአብሔር ምሕረት እና ቸርነት ከእናንተ ጋር ይሁን ።
            💚 ዝግባ 💚
ዝግባ እጅግ በጣም ውድ እና ብርቅየ ከሚባሉ እጽዋቶች አንዱ ሲሆን ቅጠሉ ቅርፊቱ ሥሩ እናም ሙጫው የየራሳቸው የሆነ ጥቅም ያለው መልካም  ዕጽ ነው።

ዛሬ ስለ ዝግባ ሙጫ እናውራ! ሙጫ ማለት  የአንድ ዛፍ ግንድ ቅርንጫፍ ሲቆረጥ ፣ሲሰነጠቅ ፣በስለት ነገር ሲወጋ፣ ከውስጥ የሚወጣ ዕዥ ወይንም ፈሳሽ ተሰብስቦ ሲደርቅ በምስሉ እንደምታዩት ሁኖ ሲገኝ ሙጫ ይባላል።

የዝግባ ሙጫ ጥቅም፦
🌿ለራእይ
🌿ለመፍትሔ-ሥራይ
🌿ለህዝብ ፍቅር
🌿ለስኳር በሽታ ተጨምሮ ይገባል!
🌿ለጠላት መፍዝዝ...እና የመሳሰሉት መፍትሔ ይሰጣል።

1ኛ, ለራእይ!
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ አምላክ ጸሎት በእንተ ራእይ ወምክስተ ምስጢር

ኦ መድሙጦስሙት አርእየኒ ግብረ ጸላእትየ ወግብረ ፈተውትየ
ኦ ሙርድያል ክስት ልየ ህቡዓተ ምስጢራተ ሰማይ ወምድር
ኦ አአትማይያል አርእየኒ ምስጢረ አዝማድየ ወአብያጽየ
ኦ አፍድክያል ክስት ልየ ስውራተ ወህቡዓተ ዘተኃለዩ እምላዕለ ነብስየ ወስጋየ
ኦ ሰምራካኤል አርእየኒ ሀብታተ ዕዮብ ወጥበበ ሰለሞን በዝንቱ ቃልከ አውሎግሶን
ኦ መቅጀሐቡር  ክስት ልየ በኅልም ወበገሀድ ዘተገብረ በላዕሌየ
ድማክል
ድማክል
ድማክል
ህልድጣኤል
ህልድጣኤል
ህልድጣኤል
ዝምራኤል
ዝምራኤል
ዝምራኤል
ድልካም
ድልካም
ድልካም
ኦ አጥዮንዮስ ክስት ምስጢራተ ዓለም በዛቲ ዕጽ ተመሲለከ ለለዕለቱ ወለለሰዓቱ በእንቲአየ እኩይ ነገር ዘይሔሊ ወዘይገብር አርእየኒ ወአስምዓኒ በእዝነ ልቡናየ ለገብርከ (ስም)

ገቢሩ፦የዝግባ ሙጫለ ፯ ቀን ማታ ማታ በመኝታ ሰዓት ታጥኖ  በንጽሕና መተኛት።
ቀድሞ የተደረገውን ለወደፊት የሚደረገውን በህልም ይታያል።
በተለይ መድኃኒት፣ ውለሽ ፣የሴት ዛር፣ሥራይ..በሰው ዘንድ ተደርጎብናል ብላቹ የምታስቡ በሙሉ በራእይ ሁሉም ነገር ይታያችኃል።
ይህ ጥበብ በምትሰሩበት ሰዓት ተራክቦ(ወሲብ) አይቻልም።

2ኛ,ለመፍትሔ ሥራይ
የዝግባ ሙጫ፤ ሥር ፤ቅጠል፤
የእንቧጮ ሥር፤ ቅጠል ፤ተቀጽላ
የሎሚ ሥር፤ ቅጠል፤ ተቀጽላ
የሴት ዕሬት ሥር ፤ግንድ
ከከርቤ ዕጣን ጋር ለሳምንት ያክል መታጠን ማንኛውም ሥራይ ውለሽ ዓይነጥላ ይለቃል።

3ኛ, ለህዝብ ፍቅር

የዝግባ ሙጫ
ቅብዓ ሜሮን
የ ጥርኝ  ሽቶ
ከቀዘው(አሞጭ) ሥር ጋር ለውሰው ለሳምንት ያክል በስሱ ሴት ልጅ ትኳል ወንድ ልጅ ግንባሩ በትእምርተ መስቀል ይቀባ።

4ኛ, ለስኳር በሽታ

የዝግባ ሙጫ ፤ቅጠል ቀንበጥ
የቁልቋል ቀንበጥ
የዶግ(ዕጸ ራምኖን) ቀንበጥ
የዕንጭብር ሥር
ከርቤ ዕጣን
የወርቅ በሜዳ ሥር በአንድ ላይ አልሞ ደቁሶ በጣዝማ ማር አዋህዶ በግማሽ የሾርባ ማንኪያ ከምግብ በኃላ ለ 21 ቀን መብላት ነው።
ፍቱን ነው። በተለይ ለኢንሱሊን መርፌ የማይወጉ ለውጡ ውጤታማ ነው።

5ኛ, ለጠላት ለሌባ መፍዝዝ

የዝግባ ሙጫ
የአበዘንጣ(የአሽኮኮ ጎመን ሥር
የዋርካ ተቀጽላ
የጠምበለል ተቀጽላ በአሽኮኮ ሓሞት አንግሰህ ከትበህ ያዝ ጠላትህ ደፍሮ አይናገርህም ሌባም ኪስህ ውስጥ አይገባም።

እነዚህ ጥበቦች ተፈትነው ተግባር ላይ የዋሉ ናቸው ማየትም ማመን ነውና !
ሞክረው ውጤቱን ይንገሩን።

መሪ አምደ ብርሃን !!!
ለበለጠ መረጃ 0918834904 ብለው በስራ ሰዓት ይደውሉ።
✅ቴሌግራም መልክት የምቀበልበት
@merigetaamedeberhan




ሌላው በልብሶቻችን ወዝ የሚመተተው መተት የሰውነታችንን ጠረን በከፋ ሁኔታ ያበላሻል፡፡ የመተት ጠባዩ አንዱ የሰውነትን ጠረን በማሽተት ከሰው እንዳንቀላቀል፣በክፉ ሽታ እንድንሰቃይ ማድረግ ነው፡፡ መተት ያለብን ሰዎች አፋችን፣ብብታችን የውስጥ ገላችን፣አንቀጸ ሥጋችን፣ማኅፀናች ጥሩ ባልሆነ ጠረን ይሸታል፡፡ በወዛችን መተት ተመተተ ማለት የሰውነታችን መዓዛ ይጠፋል፡፡ በዚህም ሰውነታችን በአስደንጋጭ ሁኔታ ይሸታል፡፡

ወዳጆቼ በአጠቃላይ በልብሳችን፣በቁሳችን ወዝ መተት ተመተተብን ማለት ብዙ እድላችንን እና ጤናችንን እናጣለን፡፡ እንዲሁም የሰውነታችን ጠረን እየሸተተ እንሰቃያለን፡፡ አጠቃላይ መፍትሔዎችን መጨረሻ ላይ ብመጣበትም በወዛችን አስመትተው እድላችንን ቀምተው የቁም እስረኛ እንዳያደርጉን ልብሶቻችን፣ቁሳቁሶቻችንን ለሰው ባናውስ እና በውጭ ባናሰጣ እመክራለሁ፡፡ እኛ ሰዎች በተንኮል ከአጋንንት እኩል እየሆንን ስለሆነ እየተጠነቀቁ በጸሎት መበርታቱ መልካም ነው፡፡

የአንድን ሰው ተሰጥኦ በምቀኞች በመተት አጋንንት ወደራሳቸው ማድረግ ልክ በእኛ ያለን የስልክ ካርድን ለሌላ ሰው ትራንፈስ እንደማድርግ የቀለለበት እኛም የቀለልንበት ዘመን ነው፡፡


〰   በወዝ የሚተት መተት

ብዙዎች ልብሳቸውን፣ጫማቸውን፣ደብተራቸውን፣ብዕራቸውን ወዘተ ጓደኛ ለተባሉ ጉደኛ በማዋስ እድላቸውን በመተት በመቀልበስባዶ አድርገዋቸዋል፡፡ በወዛችን መተት የሚመተተው እና እድላችን የሚወሰደው በሁለት መልኩ ነው፡፡ አንደኛው የራሳችን እና የቅርባችን ለምንላቸው ሰዎች ልብሳችንን፣የምንጠቀምበትን ቁስ በማዋስ ነው፡፡ ከእኛ የተዋሱትን ነገር አጋንንት ጎታች እና መተት መታች ጋር ይዘው በመሄድ በወዛችን ያስደግማሉ፡፡ ከዛማ የእኛ የሆነው ሁሉ በተዘዋዋሪ ሳይሆን በቀጥታ የእነሱ ይሆናል፡፡

ሁለተኛው የእኛ የምንላቸው እኛ በምቀኝነት እና በቅናት የሚያዩን፣በመልካም ነገሮቻችን፣በተሰጦአችን ዓይናቸው ደምየሚለብስ፣በቅናት የሚንከላወስ የቅርብ ሩቅ የሆኑ ሰዎች የእኛን ለምሳሌ ልብሳችንን፣ቁሳችንን በመስረቅ እና በሰው በማሰረቅ ያስመትቱብናል፡፡ እነዚህም ሰዎች ሁለት ገጽታ ነው ያላቸው፡፡ አንደኛው ቀርበውን ወዳጅ ሆነውን ጓዳ ጎድጓዳችን ካወቁ በኃላ በመጎራበት የእኛን ነገር በመስረቅ ወስደው ያስመትቱበታል፡፡ ሁለተኛው እኛን ሳይቀርቡን ለምሳሌ ያሰጣነውን ልብስ፣ያስቀመጥነውን ቁስ ወዘተ ከውጭ ሆነው በማሰረቅ ያስመትቱብናል፡፡

ወዳጆቼ ሆይ አንዳንዴ ከቤት ያስቀመጥነው ልብስ እና ቁሳቁስ እንዲሁም በውጭ ያሰጣነው ልብስ እንደ ዘበት የሚጠፋው ለመተት ተግባር ነው፡፡ እኛ ኢትዮጲያውያን ኑሮአችን፣ማህበራዊ መስተጋብራችን ለመጠላለፍ፣በመተት ለመጉዳዳት ይመቸናል፡፡ ምክንያቱም ጉርብትናችን እንደ ቤተሰብ፣አሰፋፈራችን እንደ ምላስ እና ጥርስ በአንድ ቦታ ስለሆነ ነው፡፡
እዚህ ላይ አጥርቼ ልለፍላችሁ፡፡ መቼም ‹‹እንዴት መተት በወዛችን ይመተትብናል?›› ማለታችን አይቀርም፡፡ ወዳጄ አሁን በረቀቀው ዓለም አንድ ሰው አንድን ሰው በጨለማ እና ሰው በሌለበት ቦታ ቢገድለው ለገዳይ ምስክር ላይኖር ይችላል፡፡ ለሟች ግን እውነተኛ እና ሐቀኛ ምስክር አለ፡፡ ይህም አሻራ የምንለው ነው፡፡ አሻራ ደግሞ በሟች ሰውነት ወይም ሟች በሞተበት መሣሪያ ላይ የሚታተመው በወዝ ነው፡፡ ሟች የሞተበት ማንኛው ነገር ላይ የገዳይ አሻራ በራሱ ወዝ ምስክር
ይሆንበታል፡፡ ይህ ማለት ወዝ ማንነት ነው፡፡ ወዝ የአንድን ሰው ሁለንተና ሊገልጽ ይችላል፡፡ ስለዚህ ወዳጅ ያልናቸው እና በቅናት በጠላትነት የሚነሱብን ሰዎች በልብሳችን እና በቁሳችን ሳይሆን እሱ ላይ ባለው ወዛችን መተት ያስመትቱብናል፡፡ ያኔ ከሕይወታችን የሚፈልጉትን መልካም እድላችንን ይነጥቁናል፡፡ በራሳችን ወዝ በመተት በማፍዘዝ በማደንዘዝ ከቆሙት በታች ከሞቱት በላይ፤ከመቃብር በላይ ከሕያዋን በታች ያደርጉናል፡፡

ያኔ ከእኛ ኃላ ያሉት ሰዎች በእኛ እድል ከእኛው ይቀድሙናል፡፡ ብንሮጥ አንደርስባቸውም፡፡ የእኛ የሆነ ነገር እነሱ ጋር ስላለ ምን ይዘን እንሮጣለን?  እኛ ውበት ከቁመናና እና ከመልካም ጠባይ ጋር ይዘን እነሱ ከእኛ በታች ሆነው በእኛው እድል ከእኛ በላይ ይሆናሉ፡፡ እነሱ ያገባሉ እኛ ቆመን እንቀራላን፡፡ እነሱ በእኛ እድል ይወልዳሉ እኛ የወላድ መካን እንሆናለን፡፡ እነሱ በእኛ እድል ሠርተው ሐብታም ይሆናሉ እኛ መሥራት እየቻልን እድላችንን ተነጥቀን በቤታችን ታስረን እንኖራለን፡፡ እኛ ተምረው የት ይደርሳሉ ለሰው እና ለሀገር ይተርፋሉ ተብለን ተስፋ የተጣለብን ተስፋ ቢስ ሆነን እውቀታችንን ተነጥቀን ያለ አንዳች ሥራ እንቀመጣለን እነሱ በእኛ እድል እና እውቀት ተምረው እንጀራችን እየበሉ ይኖራሉ፡፡

ብዙዎቻችን እንደ ቀልድ በለጋነት እድሜያችን ነገሮችን በፍጹም በማናውቃቸው ጊዜያት እድላችንን በወዛችን ተነጥቀናል፡፡ ለምሳሌ በትምህርት ዓለም እያለን አንዱ የትምህርት እድላችን፣እውቀታችን የሚሰለበው በመተት ቢሆንም የሚደገመው በወዛችን ነው፡፡ ይህም ደብተራችን፣ብዕራችን፣ልብሳችንን ተውሰው በወዙ አስደግመውበት ይመልሱልናል፡፡ እኛም በአስደንጋጭ ሁኔታ የትምህርት አቅማችን እየወረደ፣ትምህርት እያስጠላን በሂደት እንፈዛለን እንደነዝዛለን፡፡ እነሱ እያየናቸው እየተገላበጡ እየተለወጡ ይሄዳሉ በእኛ እድል ተምረው ሰው ይሆናሉ፡፡

እኛ ለወዳጅ ባዋስነው እኛ በተሰረቀብን ልብስ፣ቁስ በወዙ መተት ተመትቶበት ዕድላችንን ይወስዳሉ፡፡ በተለይ የትዳር፣የልጅ፣የሥራ ወዘተ ዕድላችን በወዛችን ተደግሞበት ብዙ ነገራችንን እናጣበታለን፡፡ ወዳጆቼ አጋንንት ረቀቅ ያለበት ጊዜ ስለሆነ መተት የሚመትቱትም እንኳን በቁሳችን በእጃችን ወዝ የመስለብ ሥራን ይሠራሉ፡፡ አንድ የማውቀው ማህበርተኛዬ አለ፡፡ ይህ ልጅ አሜሪካ እንደ ነገ ሊሄድ እንደ ዛሬ የሽኝት ፕሮግራም አዘጋጅቶ ጓደኞቹን ይጠራል፡፡ እሱ ይህንን ባዘጋጀ ጊዜ አንድ የሚያውቃቸው ትልቅ አባት ከሽሬ ከአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም ድረስ በመምጣት አግኝተውት ‹‹ልጄ እባክህ እንዲህ ዓይነት ሰው ጠበቅ አድርጎ እጅህን ጨብጦ ሰላም ይልሃል፡፡ ከቻልክ ጸሎተ ማርያምን እየጸለይክ አናግረው ግን ሰላም ባትለው ይሻላል›› ይሉታል፡፡ እሱም እንደ ቀልድ ለይስሙላ እሺ ይላቸዋል፡፡

ማታ ፕሮግራም ይጀመራል ወዳጅ የተባለ ሁሉ ይመጣል፡፡ ይበላል ይጠጣል፡፡ አንድ የሚያውቀው እና በነገሮች ሁሉ የሚቀናበት ስለ እሱ መልካም እድሎች በተደጋጋሚ ‹‹አንተማ ታድለህ፣አንተማ ያሰብከው ይሳካል›› እያለ የሚያሟርትበት ጓደኛ ተብዬው ግጥም አድርጉ ባልተለመደ ምልኩ ጨብጦ ሰላም ይለዋል፡፡ አጅሬም ከሆነ በኃላ የእኛ አባት ቃል ትዝ ይለውና በልቡ ‹‹ምናባቱ ምን ያመጣል›› ብሎ እንደ ዘበት አይቶ ያልፋል፡፡ ይሄ ልጅ አሜሪካ እንደ ገባ ከጥቂት ቀናት በኃላ እጄን ወጋኝ ጠዘጠዘን ማለት ጀመረ፡፡ እዛም በጥሩ ሁኔታ ታከመ ግን እየተሻለው ሳይሆን እየባሰበት ሄደ፡፡ በሚገርም ሁኔታ ቀኝ እጁ እንደ ለምጽ በመንደድ በሂደት እጁ ሰለለ፡፡ ዛሬ ቀኝ እጁ ምንም የማይሠራበት ሆኖ ከመስለሉ በተጨማሪ ሠርቶ አምድ አፋሽ ሆኗል፡፡ ጤናውን አጥቶ በመተት ተጎድቶ ይኖራል፡፡

ወዳጆቼ ከላይ በርዕሱ እንደነገርኳችሁ የመተት አንዱ ጦሱ ጤናችንን ማቃወሱ ነው፡፡ ስንቶች አሉ በልብሳቸው፣በቁሳቸው ወዝ መተት ተመትቶባቸው እድላቸውን ብቻ ሳይሆን ጤናቸውንም አጥተው የአልጋ ቁራኛ የደዌ ዳኛ ሆነው በየ ቤታቸው፣በየ ጸበሉ በየ ሐኪም ቤቱ ያሉ፡፡

እህት ወንድሞቼ ከቤታችሁ ያስቀመጣችሁት፣በውጭ ያሰጣችሁት የውስጥ ልብሶቻችሁ ለምሳሌ ፓንት፣ታይት፣ካልሲ፣የጡት ማስያዣ፣ጃፖኒ/ፓክ አውት/ በቀጥታ ከሰውነታች ጋር ስለሚገናኙ በወዝ ለሚመት መተት አንድ ግብአት ስለሆኑ ጠንቀቅ ብትሉባቸው አይከፋም፡፡ ‹‹ኢዲያ
ውሸት ነው እኔ ላይ አይሠራም›› ካላችሁ እዳው ገብስ ነውና ታገኙታላችሁ መልሳችሁ የማታገኙትን እድላችሁንም ታጣላችሁ፡፡

ወዳጆቼ ሆይ በልብሳችን ወዝ የሚመተተው መተት እድላችንን ከማኮላሸት በተጨማሪ መልካችንን ያበላሻል፡፡ አንዲት ሴት በወዝዋ ጓደኛዋ መተት ብታስመትትባት መልከኛዋ ለወንዶች መልከ ጥፉ ሆና ትታያለች፡፡ መልከ ቢስዋ ለወንዶች መልከኛ ሆና ትታያለች፡፡ በዚህም አስመታችዋ የመልከኛዋን የመልክ ወዝ ተላብሳ ቆንጆ መስላ ትታያለች፡፡ ለዚህም ነው መልከኞቹ ውበት ይዘው ሳያገዙ ይቀራሉ የእነሱ ጓደኛ መልከ ቢስ መተተኛዋ ቆንጆ ወንድ አግብታ ትኖራለች፡፡ ወዳጆቼ በወዝ የሚመተት መተት የመልክ ደም ግባታችንንም እንዲወሰድ ያደርግብናል፡፡ በብዛት በመልካቸው የወዝ ድግምት ተደግሞባቸው ያሉ ሰዎች ፊታቸው ባላወቁት ምክንያት ውበታችው ይጠፋል፣ፊታቸው በብጉር ይመታል፣ፊታቸው ይቆስላል፣ፊታቸው እየሻከረ እየወየበ ይሄዳል፣የማይጠፋ ጠባሳ መሰል ምልክት ይታይባቸዋል፡፡




〰️ ለዓይነ ጥላና ለገርጋሪ〰️
በስመ አብ በል ጸሎት በእንተ ዓይነ ጥላ ወገርጋሪ አስማተ እግዚእነ #ኢየሱስ_ክርስቶስ ራፎን ፫ ጊዜ ራኮን ፫ ጊዜ ጰስአፍሊስ ፫ ጊዜ መልዮስ ፫ ጊዜ አናኤል ፫ ጊዜ ጽራኤል ፯ ጊዜ ሕናኤል ፫ ጊዜ ናፎስ ናሮስ ኮሮስ ፫ ጊዜ ፌሎስ ፫ ጊዜ ቢናር ፫ ጊዜ ሊናስ ፫ ጊዜ ሊኖስ ፫ ጊዜ ሊፍሎራኖስ ፫ ፓፓሮስ ፫ ኢሮስ ፫ አኖሮስ ፫ ኢሮን ፫ ጊዜ ብርስባሔል ፫ ጊዜ ድማሄል ፫ ጊዜ በኃይለ ዝንቱ አስማቲከ አድኀነኒ እምኩሉ ዓይነ ጥላ ወዓይነ ባርያ ስድዶሙ ለአጋንንት ዕቀበኒ ወአድኀነኒ ሊተ ለገብርከ #የክርስትና_ሥም
#ገቢሩ የቀጠጥና አበባ የፅጌ ረዳ አበባ የቀጋ አበባ ዕፀ ሳቤቅ ሞይደር እነዚህን አንድ ላይ ቀምመህ ለ ፯ ቀን ማታ ማታ ታጠን የማያዳግም መፍትሔ ይሰጣል ።

         ❤️የሕዝብ_መስተፋቅር ❤️
ጸሎተ ተሳልሞ ወተፋቅሮ ነገሥት ወመኳንንት ዘኩሎሙ ፍጥረታቲከ አከለወጅ ፱ ጊዜ ሰማይጅጅ ወአርሞንሂ መጅጅ በሴቅምንጅ ከርወነጅጅ ከንጅጅ ሰያሜከራጅ በእሉ ቃላቲከ አስተፋቅረኒ ወአስተጻምረኒ ምስለ ኩሎሙ ወሉደ አዳም ወሔዋን ነች ምስለ ኩሎሙ ነችች ወረስየኒ ፍቁረ በኀበ ኩሉ እግዚእ ወአጋዕዝት ኦ #እግዚአብሔር መፍቅሬ ሰብእ ጸግወኒ ፍቅረ ወሰላመ በከንቱ የሀቡኒ ወርቀ ወብሩረ ኦሆ ኦሆ ኦሆ ይብሉኒ ኩሎሙ ሰብእ ወይፌጽሙ ፈቃደ ልብየ ሊተ ለገብርከ ዕገሌ #የክርስትና_ሥም
#ገቢሩ በ፯ ኮረሪማና እፍኝ ስንዴ አንድነት ፈጭተህ ጋግረህ ፵፱ ጊዜ ደግመህበት ብላ ወለፍቅር ይከውነከ ።

                〰️ለመንሥኤ_እስኪት〰️
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ጸሎት በእንተ ንአጽዖተ እስኪት ጢፍራን ፯ ጊዜ ወዱን አንቅዕ እስኪቶ ያንቅሖ ያንቅሕ ፯ ጊዜ ለገብረ ዕገሌ ዶር ፯ አኽያ ፯ ሽራኽያ መሸያ ፍታህ ዮፍታሔ ብሂል  ፍታሕ ተፈታሕ አንቀሕ አንቀሕ ወእለ ነቅሐ ያንቅሐ እስኪቶ ለከብርከ ዕገሌ: ፍርኑ ፍርናኤል ሱሱራኤል ሲሲሳኤል አጽንዕ እስኪቶ ከመሐጺን ማዕሠረ እስኪቱ ለገብርከ ዕገሌ ገቢር በአሞሌ ጨው በ፵፱ ቁንዶ በርበሬ ደግመህ ብላ ።

          〰️ለፈተና_የሚሆን〰️
ዋይ ዘጭላት ቁርአን ቁርአንከ በይንከ በይነጁና ሰረተኪላሂ መስተሐቢረ ወቀውዝረ ቀሊናታም በእሉ አስማተ ፍታሕ ማእሰረ ሥራዮሙ ለኩሎሙ መሠርያን እምላእለ ገብርከ ዕገሌ#የክርስትና_ስም
#ገቢር የቧጮ ተቀጽላ የሎሚ ተቀፅላ የዋርካ ተቀፅላ በእለት ውሀ አስማቱን ፯ ጊዜ ደግመህ ለ ፯ ቀን ታጠን ።




፵፪ #ለአስም የቀጠጥናውን ስር ከዕፀ መናሂ ከስረ ብዙ ከእንጭብር ከአሜራ ከጥቁር የደጋ እንጆሪ ጋር አልመህ ስራቸውን በጠጅ ጥለህ ጠጣ ።
፵፫ #ሰውነቱ_ለሚመነምን ህፃንና ለማንኛውም ሰው የቀጠጥናውን ስር የምድር እንቧይ ስር የብሳና ቅርፊት የጤና አዳም ፍሬ በአንድነት ደቁሰህ ለህፃን ልጅ በወተት አጠጣ ለአዋቂ ሰው በቡና በሸክላ ስኒ አጠጣ
፵፬ #ለህገ_ጠብቅ  የቀጠጥናውን ስርና የወይን የምድር እንቧይ የሴት ቀስት ስራቸውን ደቁሰህ በአዲስ ጠላ አቀላቅለህ ጠጥተህ ተራከብ ምስለ ብእሲትከ ኢይክል አውስቦታ ካልዕ ብእሲ
፵፭ #ለጀርባ_ህመም የቀጠጥናውን ስርና የአቱች ስሩንም ቅጠሉንም አድቀህ በአንድነት በአጓት ዘፍዝፈህ ጠጣ ።
፵፮ #ለቡዳ የቀጠጥና ስሩንና ጊዜዋ አልቴት ጤና አዳም ጭቁኝ ነጭ ሽንኩርት የአስተናግርት ፍሬ መሬንዝ ዕፅ ፋርስ የጅብ አርና ገበት ቀምሞ ማጠን ነው ፡ በግራ እጅህም ይዘህ ካለበት ቤት ወይም ቦታ ስትገባ ይለፈልፋል ።
፵፯ #ለሾተላይ የቀጠጥና ስር የምድር እንቧይ ስር የቀበርቾ የአቱች የፍየል ፈጅ የዝግጣ የአጋም ስራቸውን የባህር ጤፍ ፍሬውን ከሰሊጥ ጋር አልሞ ወቅጦ በማር መዋጥ አሰራሩ ከአስር ላይ አድበልብሎ በመጀመሪያ ባልየው ፩ዱን ይዋጥ ሚስትየዋ ፱ን ከ፪ ላይ ከፍላ ፫ ቀን ፫ ፫ እየዋጠች ትጨርስ ።
፵፰ #ለደም_ብዛት የቀጠጥናውን ስር በወይራ አንካሴ ምሰህ በትንሽ ጣትህ እየለካህ ስጥ ይቆርጥም ነገር ግን ደሙ እንዳያልቅ ደሙን እየተለካ ነው በመጠኑ ካልሆነ ደም ይጨርሳል


🌿🌿🌿 ቀጠጥና(ዕፀ ደብተራ)🌿🌿🌿
             #የቀጠጥና_ገቢር

፩ #ለጨብጥ  ከ ፫ ላይ በወይራ አንካሴ ምሶ በትክል ድንጋይ ላይ ቀጥቅጦ ፫ ቀን በውሀ አፍልቶ ማጠጣት
፪ #በምጥ_ለታመመች_ሴት የቀጠጥናውን ስር በወይራ ፍም ማህፀንን ማጠን ነው ።
፫ #ለሁሉ_መስተፋቅር ስሩን አልሞ ደቁሶ በቅቤ ለውሶ መዝሙረ ዳዊት ከመያፈቅርን ፯ ጊዜ ደግሞ እራሱን ቀብቶ ወደ አደባባይ ቢወጣ ኩሉ ያፈቅሮ ።
፬ #በድንገት_ሆነ_በተለያየ_ምክንያት_እግሩ_ላበጠ
በቀጠጥናው ቅጠል በእሳት ሞቅ እያደረጉ መተኮስ ነው ።
፭ #የጠላት_ሙግት_በተነሳብህ_ግዜ በጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ቤተ ልሄም አመድ ከቀጠጥናው እንጨት ጋር የጊዮርጊስን መልከአ ደግመህ አመዱን በ፬ቱ ማዕዘን ለነፋስ ስጥ ዕፁን መፋቂያ አድርገህ እየፋቅህ ወደ ችሎቱ ሂድ ።
፮ #ጉሮሮው_ላበጠ_ሰው የቀጠጥናውን ስር በትክል ድንጋይ አልሞ በማር ህፃን ልጅ እንዲያዋህድላችሁ በማድረግ የታመመውን ሰው እህል ሳይቀምስ ጧት ጧት ለ፭ ቀን አቅምስ ።
፯ #ዘኢያወርድ #ለስንፈተ_ወሲብ የቀጠጥናና የጠንበለል የቀጋ አበባቸውን አልሞ በማር ለውሶ በ፫ በ፫ ቀን ፫ ጊዜ ይዋጥ
፰ #ለችፌ የቀጠጥናውን ስር ከጥፍሬና ከምድር እንቧይ ስር ጋር ህፃን ልጅ ደቁሶ በማር ለውሶ ከበሽተኛው ቁስል ለይ ማሰር እስከሚድን ድርስ አይፈታም ።
፱ #ተስቦ_ከቤት_እንዳይገባ የቀጠጥናው ስሩንም ቅጠሉንም እየዘፈዘፉ ጧት ጧት ቤቱን የቤቱን ቅፅረ ግቢ እርጭ ።
፲ #ብልቱ_ለደከመ ከጅብራ ስር ጋራ የቀጠጥናውን ስር ህፃን ልጅ ደቁሶ መዝሙረ ዳዊት እግዚአብሔርን ቆመን ፯ ጊዜ ደግመህ በጉሽ ጠላ ጠጣ ።
፲፩ #ትክሻው_ላበጠ_በሬ የቀጠጥናውን ስር ከእሬት ስር ጋር በእሳት አቃጥለህ በቅቤ ለውሰህ ቅባ ።
፲፪ #ለስራይ የቀጠጥናውን ስር ከቁንዶ በርበሬ ከ፯ ዘቢብ ጋር የአሞሌ ጨው ቀላቅለህ አብላው
፲፫ #ቅንቅን_በጆሮው_ለገባበት_ሰው የቀጠጥናውን ስር እየጨመቅህ ከጆሮው ጨምርበት ።
፲፬ #ለነስር የቀጠጥናውን ስር ከምድር እንቧይ ስር ጋር ህፃን ልጅ ደቁሶ በአዲስ ጨርቅ ቋጥሮ በግራ አፍንጫው ወትፍ ።
፲፭ #ትዳር_ላጣች_ሴት የቀጠጥናውን ስር ከምስረች ስር ጋራ ርእሰ አሌፋትን (ታውን) በነጭ ወረቀት ጽፈህ አሳርረህ ስሩንም ገበያ አዙራ በልህኩት ትጠጣው ።
፲፮ #ለሳል የቀጠጥናውን ስር ከጉመሮ ስር ጋር ቀቅሎ ጧት ጧት ፩  ፩ ፍንጃል ስተይ ።
፲፯ #ለራስ_ነቀርሳ ለቆሰለበት የቀጠጥናውን አበባ ከጽጌ ረዳ አበባ ጋር በፍየል ቅቤ አንጥሮ በአፍንጫው ግበር ።
፲፰ #ሆዱ_ለሚጮህ_እና_ለሚያቃጥለው የቀጠጥናውን ስርና የቄስ በደጄ ስሩን ቀቅሎ አልሞ ደቁሶ በማር ማብላት ነው
፲፱ #ሲበላ_ወደላይ_ለሚለውና_ለሚያቅለሸልሸው
በዕለት ውሀ ዘቢቡን ጨምቶ የቀጠጥናውን ቅጠል አልሞ ደቁሶ ከዘቢቡ ውሀ ጋር አዋህዶ በዋንጫ ይጠጣ ።
፳ #ለጥላ_ወጊ መከላከያ የቀጠጥናውን ስር በወይራ አንካሴ ምሶ እፀ አንግስን እየደገሙ ፫ ጊዜ ደግሞ መሄድ ነው ።
፳፩ #እንስሶችህን_አውሬ_እንዳይበላቸው የቀጠጥና ስሩንና ቅጠሉን በዕለት ውሀ ጨምቀህ ዘየሀድርን ፯ ጊዜ ደግሞ በየወሩ በረቱን እርጭ
፳፪ #በመብልና_በመጠጥ_ስራይ_ለተደረገበት የቀጠጥና ቅጠሉን ከምድር እንቧይና ከእንጭብር ቅጠል ጋራ አልሞ ደቁሶ በማር ለውሶ ጧት ጧት በልክ በልኩ መብላት ነው ።
፳፫ #ለስራይ_መከላከያ በመንፈቀ ሌሊት ፵ ክንድ ርቆ ልብስን አውልቆ በወይራ አንካሴ ቆፍሮ መቃብያንን ደግሞ የቀጠጥናውን ስር ነቅሎ ከአቱች ጋራ ሰፍቶ ቢይዙት የአቅብ ኩለሄ ።
፳፬ #መስተፍቅር  ለተደረገበት ሰው የቀጠጥና ስሩን አልሞ ደቁሶ ከዝንጀሮ ኩስ ጋራ ፍትሀ ዘወልድን ደግሞ በጠላ ማጠጣት ነው ።
፳፭ #ለገበያ የቀጠጥና ስሩን ከነጭ ዕጣን ጋር አምጽኡን ደግመህ ታጠን ።
፳፮ #ቁስሉ_አልድንም ሲልና መግሉን ለማድረቅ የቀጠጥና ቅጠሉን አልሞ መነስነስ ነው ።
፳፮ #ከብትና_በግ_ፍየል_ሲከሱ የቀጠጥና ስርና ቅጠሉን አድርቆ  በጨው አብላ ።
፳፯ #መስተባርር ለተደረገበት ሰው ቀጠጥናውን ረቡዕ ቀን ቆፍሮ በስሩ ላይ ፯ ቀን በትክል ዕብን ላይ ቀሞ ፍትሀ ዘወልድንና ጠቢበ ጠቢባንን ደግሞ በጣዝማ ማር ለውሶ መብላት ነው ።
፳፰ #ለሙግት የቀጠጥና ስሩን ነቅለህ ከቤትህ ደጃፍ አኑረህ ሌሊት ከመኝታህ ተነስተህ ጧፍ አብርተህ ስሩን በግራ እግርህ እረግጠህ ፍካሬን ትጠፍዕ ላይ እያጠፋህ ፯ ጊዜ ደግመህ በነጋታው ይዘህ ወደ ችሎት ሂድ ።
፳፱ #ለልጅ_አገረድ_መፍትሄ_ሀብት ባል ላጣች ሴት
የቀጠጥና ስሩን 3 ቦታ በወይራ አንካሴ ቆፍረህ ወፍ ባልቀመሰው ውሀ ዘፍዝፈህ እግዚኦ ሚበዝሀኑ ፯ ጊዜ ደግመህ ፫ ቀን የደጅ ማይ ትውጣበት ገላዋንም ትታጠብበት ግማሹን ትታጠብ፡ ዓዲ ለዘፀልኣ ምታ የቀጠጥና ስሩን በእሳት አቃጥሎ ዓይኗን ትኳል ።
#፴ #ለማንኛውም_አስፈላጊ_ነገር የቀጠጥና ስሩን ከ፫ ቦታ በወይራ አንካሴ ቆፍረህ ከትክል ድንጋይ ላይ ቀጥቅጠህ ከጽጌ ረዳ ጋር አዋህደህ ታጥነህ ተኛ
፴፩ #ለትምህርት የቀጠጥና አበባውን ከጠንበለልና ከጽጌ ረዳ አበባ ጋር በትክል ድንጋይ ደቁሰህ በብርጭቆ ከ፫ ዕብን ላይ ከፀሀይ ላይ አድርገህ መልክአ ኢየሱስን እየደገምክ አፍልተህ ስተይ ።
፴፪ #ማንኛውም_ክፉ_ነገር_እንዳይደስስብህ የቀጠጥናውን ከ፫ ቦታ ለይ በቀንድ ቢለዋ ምሰህ ስሩን ቆርጠህ የጥቁር ጤፍ ቂጣ ብር የምታህል ጋግረህ ቂጣውን ከተማሰው ጉድጓድ ውስጥ አድርገህ አፈሩን መልስበት የቀጠጥናውን ስር ቀጥቅጠህ አድርቀህ በብረት ምጣድ አሳርረህ ተነቀስ ዕድሜህ ድረስ ክፉ መከራ አያገኝህም ፡ ነገር ግን ስትቆርጥ ጥላህ እንዳያገኘው ተጠንቀቅ
፴፫ #ለመስተሀምምና_ለዛር_ውላጅ_ለጥላ_ወጊ
መጠበቂ የቀጠጥና ስሩን ከአንድ ቦታ ቆፍረህ ውሀ ባልነካው ቅቤ ዋጥ ።
፴፬ #ለሌባ የቀጠጥና ስር ከ፫ ቦታ በወይራ አንካሴ ምሰህ በግራ ፈትል ወስላታ መስክ ሰላቢ ከመቅብዕ ይቅለፁ ወከመ ሰም ይብረዱ በሎ ወቅትሎ ጥናክኤል ፯ ጊዜ አድራኤል ፯ ቃምናኤል ፯ በዝ ቃል ስትዞር እደር ተያዝ ዕደር አለህ ቃለ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ወቃለ እግዚአብሔር ይህን በዕፁ ላይ ፯ ጊዜ ደግመህ ፫ ጊዜ ቤቱን አዙረህ ከቤትህ ውስጥ ቅበር ።
፴፭ #ለመድፍነ_ፀር ቢስሚላሂ፡ሮሂማን፡ሮሂም፡ወሱሬቹ፡በሸናኤል፡ፈቸቸኤል፡ህያው፡ሆር፡ማሹ፡አሴር፡ሴኮ፡ጀመጀረ፡ሴሬ፡ጉሬ፡ወሬን፡በሬን፡ሀናቁፎ፡ጭጭኤል፡ናችር፡አልማችር፡በከመ፡ደፈንክ፡ልቦ፡ለዲያብሎስ፡ከማሁ፡ድፍን፡ልቦሙ፡ለፀርየ፡ወለጸላእትየ ... ብለህ ስርና ቅጠሉን ደቁሰህ አስማቱን በቀይ ቀለም ጽፈህ ከ፫ ላይ በእሳት አቃጥለህ በጥቁር ጤፍ ቂጣ ጋግረህ ለጸሊም ከልብ አብላ ።
፴፮ #ለወገብ_እና_ለጀርባ_ህመም የቀጠጥና ስርና ቅጠል ከአቱች ስር ጋራ ደቁሰህ አልመህ በአጓት ጠጣ
፴፯ #ለዓቃቤ_ርእስ የቀጠጥናውን አበባ ከትክል ዕብን ላይ ሰልቀህ ውሀ ባልነካው ቅቤ ለውሰህ ገጽህን ተቀባ እስከ ዓመት ከፀር የአቅበከ ።
፴፰ #ለመፍትሔ_ሀብት የቀጠጥናውን አበባ (አሉማ) የአመራሮ ፍሬ አደይ አበባ አንድነት ቀምመህ አምጽኡን ወይከስት አእዋመ ድረስ ፵፱  ጊዜ ደግመህ በአምሳያ ቅቤ ለውሰህ ራስህን ተቀባ ለሹመትም ይከውን ።
፴፱ #አልሸጥ_ላለ_ከብትና_ለማንኛውም_ንብረት የቀጠጥናውን ስር ነቅለህ በግራ እጅህ ይዘህ ሂድ ይሸጣል ።
፵ #ለገበያ የቀጠጥናውን ስርና የዘረጭ እንባይ የጭቁኝና የአስተናግር ስራቸውን ታጠን ።
፵፩ #ጆሮው_ለደነቆረ የቀጠጥና ፍሬውን ደቁሶ ከሰሊጥ ጋር አንጥሮ በትንሽ በትንሹ በጀሮው ይክተት

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.