ታህሳስ ፮ ቅድስት አርሴማ
በዚችም ቀን የድንግሊቱ አርሴማ ቤተ ክርስቲያኗ የከበረችበትና የሥጋዋ ፍልሰት የሆነበት ከእርሷ ጋር የተገደሉ የሃያ ሰባት ደናግልም የሥጋቸው ፍልሰት የሆነበት ነው ።
ይችንም ቅድስት አርሴማን ንጉሥ ድርጣድስ ይህን ያህል ታላቅ ክብር ካለው ከእኛ ጋር መኖርን እምቢያልሽ ልብ የለሽምን አላት እርሷም በሰማያት ያለው ይበልጣል እጅግም ይሻላል አለችው ወደ ጎን ወስደው ልብሷን ገፈው አንገቷን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘ የደናግሉንም ሁሉ አንገት እንዲቆርጡ አዘዘና ተቆረጡ ።
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በደናግል ጸሎት ይማረን አሜን ።
" ገድሏን በስቃይ የፈጸመች ለቅድስት አርሴማ ሰላምታ ይገባል: በመንግስተ ስማይም ስሟ ታላቅ ነው ::"
አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ