ቁርአን የልብ መድኃኒት


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha


የአላህ መልክተኛ ﷺ እንዲህ አሉ፦ 📖
《 ቁርአንን አሳምሮ የሚቀራ እሱ ከነዛ ታላላቅ መላኢካዎች ይመደባል》
━══ ❁❁❁ ═══
አብደሏህ ኢብኑ መስዑድ እንዲህ ብለዋሉ፦

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Statistika
Postlar filtri


እነሆ እቅዳችሁ አንድ ወር አልፎታል እቅዳችሁን ጀመራችሁ? ከእቅዳችሁ ምን ያህል•\• አሳካችሁ? አላህ ያግዛችሁ🤲


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
ሸይኽ ፈውዛን (አላህ ይጠብቃቸውና) ቀላል አሳቁኝ መሰላችሁ!

ጠያቂ፦ ነቢዩላህ ዒሳ ኋላ በአኺረ ዘማን ሲመጣ አግብቶ ልጅ ይወልዳል የሚባለው ነገር እንደት ነው?

እርሳቸው፦ «ሰርጉን ከታደምንና ካየነው እንነግርሃለን!»።

ጠያቂ፦ «መለከል መውት "አርዛኢል" የሚባል ስም አለው?»

እርሳቸው «የለውም፤ ግን ይህን ስሙን ተወውና ነፍስህን ያዝ። ካልክ ደግሞ ታገስና ሲመጣ ታየዋለህ!»

ጠያቂ፦ «ሰው ሪከርድ የተደረገን ቁርኣን በማጫወቻ (ለምሳሌ፦ በስልክ፣ በሬዲዮ፣ በቲቪ…) እያዳመጠ ሳለ ቃሪኡ ሱጁድ ማድረጊያ ላይ ቢደርስ የሚያዳምጠው ሰው ሱጁድ ማድረግ አለበት?»

እርሳቸው «ያ የምታዳምጥበት ነገር ሱጁድ ካደረገ አንተም አድርግ።»

ኧረ! በአላህ!

ጠያቂ፦ «ካፊሮች ጨረቃ ረግጠናል፣ ወደ ጨረቃ ደርሰናል!» ብለው ይሞግታሉና እንመናቸው ወይንስ እንደ ኢስራኢሊያ ቆጥረው ውሸትም እውነትም አንበል?

እርሳቸው «ምን ይጎዳችኋል ከቻሉ ወደ ጨረቃ ቢሄዱ? እንዳውም ደህና ምድርን ይተውልናል!»

ኧረ! ሙሉውን አዳምጡት'ማ!


           ╭─•••─        ═••••••═      ─•••─╮
.          🌺የ25ቱ ነቢያት ስም ከነአመጣጡ 🌺     
.          ╰─•••─        ═••••••═      ─•••─╯


   🔗 ካነበባችሁ በኋላ ለሌሎች ማስተላለፍ አትርሱ 🔗

#1=አደም(ዐለይሂ ሰላም)፡- ይህ ስም በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ በ9 ሱራዎች በ25 አንቀጾች ውስጥ 25 ጊዜ ተጠቅሷል፡፡

#2=ኢድሪስ(ዐለይሂ ሰላም)፡- ይህ ስም በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ በ2 ሱራዎች በ2 አንቀጾች ውስጥ 2 ጊዜ ተጠቅሷል፡፡

#3=ኑሕ(ዐለይሂ ሰላም)፡- ይህ ስም በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ በ30 ሱራዎች በ50 አንቀጾች ውስጥ 50 ጊዜ ተጠቅሷል፡፡

#4=ኢብራሒም(ዐለይሂ ሰላም)፡- ይህ ስም በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ በ25 ሱራዎች በ63 አንቀጾች ውስጥ 69 ጊዜ ተጠቅሷል፡፡

#5=ሉጥ(ዐለይሂ ሰላም)፡- ይህ ስም በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ በ14 ሱራዎች በ27 አንቀጾች ውስጥ 27 ጊዜ ተጠቅሷል፡፡

#6=ኢስማዒል(ዐለይሂ ሰላም)፡- ይህ ስም በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ በ8 ሱራዎች በ12 አንቀጾች ውስጥ 12 ጊዜ ተጠቅሷል፡፡

#7=ኢስሐቅ(ዐለይሂ ሰላም)፡- ይህ ስም በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ በ12 ሱራዎች በ16 አንቀጾች ውስጥ 17 ጊዜ ተጠቅሷል፡፡

#8=የዕቁብ(ዐለይሂ ሰላም)፡- ይህ ስም በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ በ10 ሱራዎች በ10 አንቀጾች ውስጥ 16 ጊዜ ተጠቅሷል፡፡

#9=ሁድ(ዐለይሂ ሰላም)፡- ይህ ስም በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ 3 ሱራዎች በ7 አንቀጾች ውስጥ 7 ጊዜ ተጠቅሷል፡፡

#10=ሷሊሕ(ዐለይሂ ሰላም)፡- ይህ ስም በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ በ9 ሱራዎች በ25 አንቀጾች ውስጥ ለ 25 ጊዜ ተጠቅሷል፡፡

#11=ሹዐይብ(ዐለይሂ ሰላም)፡- ይህ ስም በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ በ4 ሱራዎች በ10 አንቀጾች ውስጥ 11 ጊዜ ተጠቅሷል፡፡

#12=ሙሳ(ዐለይሂ ሰላም)፡- ይህ ስም በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ በ34 ሱራዎች በ131 አንቀጾች ውስጥ 136 ጊዜ ተጠቅሷል፡፡

#13=ሀሩን(ዐለይሂ ሰላም)፡-  ስም በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ በ13 ሱራዎች በ20 አንቀጾች ውስጥ ለ 20 ጊዜ ተጠቅሷል፡፡

#14=ዳዉድ(ዐለይሂ ሰላም)፡- ይህ ስም በቅዱስ ቁርአን ውስጥ በ9 ሱራዎች 16 አንቀጾች ውስጥ ለ 16 ጊዜ ተጠቅሷል፡፡

#15=ሱለይማን(ዐለይሂ ሰላም)፡- ይህ ስም በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ በ7 ሱራዎች 16 አንቀጾች ውስጥ ለ 17 ጊዜ ተጠቅሷል፡፡

#16=ኢልያስ(ዐለይሂ ሰላም)፡- ይህ ስም በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ 1 ሱራ በ2 አንቀጾች ውስጥ ለ 2 ጊዜ ተጠቅሷል፡፡

#17=አዩብ( ሰላም)፡- ይህ ስም በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ በ4 ሱራዎች በ4 አንቀጾች ውስጥ ለ 4 ጊዜ ተጠቅሷል፡፡

#18=ዩኑስ(ዐለይሂ ሰላም)፡-  ስም በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ በ4 ሱራዎች በ4 አንቀጾች ውስጥ ለ 4 ጊዜ ተጠቅሷል፡፡

#19=ዩሱፍ(ዐለይሂ ሰላም)፡- ይህይህ ስም በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ 3 ሱራዎች በ26 አንቀጾች ውስጥ ለ 27 ጊዜ ተጠቅሷል፡፡

#20=በአል-የሰዕ(ዐለይሂ )፡- ይህ ስም በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ በ2 ሱራዎች በ2 አንቀጾች ውስጥ ለ 2 ጊዜ ተጠቅሷል፡፡

#21=ዙል-ኪፍል(ዐለይሂ ሰላም)፡- ይህ  በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ በ2 ሱራዎች በ2 አንቀጾች ውስጥ ለ ስም2 ጊዜ ተጠቅሷል፡፡

#22=ዘከሪያ(ዐለይሂ ሰላም)፡- ይህ ስም በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ በ4 ሱራዎች በ6  ውስጥ ለ 7 ጊዜ ተጠቅሷል፡፡

#23=የሕያ(ዐለይሂ ሰላም)፡- አንቀጾችይህ ስም በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ በ4 ሱራዎች በ5 አንቀጾች ውስጥ ለ 5 ጊዜ ተጠቅሷል፡፡

#24=ዒሳ(ዐለይሂ ሰላም)፡- ይህ ስም በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ በ11 ሱራዎች በ25 አንቀጾች ውስጥ ለ 25 ጊዜ ተጠቅሷል፡፡

#25=ሙሐመድ(ዐለይሂ ሶላቱ ወስ-ሰላም)፡- ይህ ስም በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ በ4 ሱራዎች በ4 አንቀጾች ውስጥ ለ 4 ጊዜ ተጠቅሷል ።

    በቀጣይ ደግሞ የነብያቱን ሀገር እናያለን
      


« وَاصْبِرْ عَلَىٰ مَا أَصَابَكَ ۖ  »
{ በሚያገኝህም መከራ ላይ ታገስ፡፡ }
መልዕክቱን ለሌሎችም ያጋሩ 👉
ቻናላችንን ለኡማው ያስተዋውቁ 👇
https://t.me/onlyquran11


ሰዎች ስለ ወንድሞቻቸው ማሰቡ (ዱዓ ማድረጉ) ቀርቶ ስለነሱ ዜና መስማት ሁሉ ማይፍልጉት ግዜ ላይ ደስረስን 😢 ነገ አላህ ፊት ምን እንል የሆን ? እንዴት ድዓ ማድረግ እራሱ አቃተን 😭


« فَبِأَيِّ آلَاءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ »

{ (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? }
መልዕክቱን ለሌሎችም ያጋሩ 👉
ቻናላችንን ለኡማው ያስተዋውቁ 👇
https://t.me/onlyquran11


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
ከለሊቱ 7 ሰዐት ላይ
አሁን እየደረ ያለው ጭፍጨፋ ከየትኛውም ጊዜ በላይ የከፋ ነው።


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
#ሰበር፡ ​​እስራኤል በራፋህ ላይ የሚደረገውን እንቅስቃሴ መጀመሩን በይፋ አስታውቃለች።

የእስራኤል ጦር ቃል አቀባይ በራፋህ ወታደራዊ ዘመቻ መጀመሩን አስታወቀ።

በአሁኑ ጊዜ ኃይለኛ እስራኤል የቦምብ ጥቃት ረፋህ በስተምስራቅ በኩል እየደረሰ ነው ።

በዱአቹ አትርሷቸው።
#BREAKING: ISRAEL OFFICIALLY ANNOUNCES THE BEGINNING OF OPERATIONS IN RAFAH.

ALL EYES ON RAFAH!


ይህ በደም በአጥንታችን የተገነባ የተባረከው የፍልስጥጤም ምድር ነው። መኖርያ ማረፊያችን ማደርያ መዋያችን እዚሁ ነው ይላል አንደበታቸው።


ባሌ ሰካራም ነው !
አልጀሪያዊት እንስት ነች። ከአድማጮቹ የሚቀርቡለትን
ጥያቄዎች በማስተናገድ ሐይማኖታዊ ብያኔ እየሰጠ ወዳለ
የቴሌቪዥን ጣቢያ ስልክ እየደወለች ነው። ብያኔውን እየሰጡ
ያሉት የ 83 ዓመት የዕድሜ ባለጸጋው እና ሞሪታኒያዊው ስመ
ጥር ሙፍቲ አብደላህ ቢን በየህ ይሰኛሉ። እንደ አውሮፓዊያን
የዘመን ቀመር በ2009 በጆርጅ ታውን ዩኒቨርስቲ አማካኝነት
በሙስሊሙ ዓለም ካሉ 50 ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች መካከል
አንዱ ሆነው ተመርጠዋል። ከጠያቂዋ ጋር ያደረጉትን የሐሳብ
ልውውጥ እንደሚከተለው አቅርበነዋል: -
.
.
እርሷ ሸይኽ፣ እኔ አልጀሪያዊት ሙስሊም ነኝ። ፈጣሪየን
በምችለው አቅም ሁሉ ለመታዘዝ ጥረት የማደርግ ሙዕሚን
ነኝ። ግና ባለቤቴ የአልኮል መጠጥ ሱሰኛ ነው። ትዳር
ስንመሰርት አስካሪ መጠጥ የሚባል ቀምሶ አያውቅም። ከሆነ
ጊዜ በኋላ ነው የጀመረው። ከዛሬ ነገ ይተዋል ብየ ብታገስ
ሊያቆም አልቻለም። በቅርቡ የፈጸመው ተግባር ትዕግስቴን
አሟጠጠው። በውድቅት ሌሊት መጣ። ቁርአን እየቀራሁ
አገኘኝ። ቁርአኑን ከእጄ ላይ በሐይል ነጠቀኝ። ቀዳደደው።
ወረወረው። ከዚህ ሰው ጋር በዚህ አኳኋን የትዳር አጋር ሆኖ
መቀጠል ይቻላል ወይስ ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በፍች
መለያየት አለብኝ ? ብያኔው ምንድን ነው?
ሸይኹ ከርሱ የወለድሻቸው ልጆች አሉሽን ?
እርሷ አዎ፣ አምስት ልጆች አሉኝ።
ሸይኹ ወላጆች አሉሽ ? የት ነው የሚኖሩት ?
እርሷ ወላጆች አሉኝ፣ ቢሆንም እኔ ከምኖርበት ከተማ
በጣም ይርቃሉ።
ሸይኹ ድጋፍና እገዛ የሚያደርግልሽ ሰው ይኖራልን ?
እርሷ ልጆቼ ሁሉም ህጻናት ናቸው። ቤተሰቦቼም ራሳቸውን
የቻሉ አይደሉም። በእርዳታ ነው የሚተዳደሩት። አይዞሽ የሚለኝ
ሁነኛ ዘመድ የለኝም።
ሸይኹ እንግዲህ ጉዳዩ እንዲያ ከሆነ በትዕግስት
ተቀመጪ። ፍችም አትጠይቂ። ከባለቤትሽ ጋር
የሚያጨቃጭቅሽን ነገር በዘዴ ለማስወገድ ሞክሪ።
እርሷ እንዴት ብየ ነው በዚህ ጉዳይ የምታገሰው? ጭራሽ
እንዲህ አይነት ብያኔ እንዴት ይሰጡኛል ?
ሸይኹ አየሽ ልጄ ፣ እርሱ ጋር በትዕግስት መቀመጥ
እየተሻለ ጥለሽው ብትሔጂ እየሰከሩ ቁርዓኑን የሚቀዱት
በድምሩ ስድስት ይሆናሉ። አምስቱ ልጆችሽ እና ጥለሽው
ለመሰናበት ያሰብሽው ባለቤትሽ ማለቴ ነው። ምክኒያቱም ልጆቹ
በርሱ ስር ያድጋሉ። በባህሪው ይቀረጻሉ። ቤትሽን ጥለሽ መሔድ
መፍትሔ አይሆንም። መታገሱ ውጤት ይኖረዋል። ያንቺ ሚና
ለልጆችሽ ትልቅ ድልድይ መሆን ነው። አማን ወደሆነው ዓለም
ያሻግራቸዋል። በይ የምመክርሽ ሌሊት እየተነሳሽ ለባለቤትሽ
ዱዓ እንድታደርጊለት ነው። ቀናውን መንገድ እንዲያመላክተው
ለፈጣሪሽ ተማጽኖ አሰሚ።
እርሷ እስኪ ኢንሻአላህ !!
ቀናት አለፉ ፤ ወራት ነጎዱ ፤ ዓመት ተተካ። ከዕለታት አንድ ቀን
ከላይ ስማቸውን የጠቀስናቸው ሸይኽ በተመሳሳይ ፕሮግራምና
የቴሌቪዥን ጣቢያ እንግዳ ሆነው ቀርበዋል። እንዳጋጣሚ ስልክ
ከሚደውሉት መካከል አንዷ ያቺ አልጀሪያዊት እንስት ነች።
እርሷ አሰላሙዓለይኩም ሸይኽ ?
ሸይኹ ወዓለይኩሙሰላም። እሺ ልጄ ጥያቄሽን ማቅረብ
ትችያለሽ።
እርሷ አላወቁኝም እንዴ ሸይኽ ?
ሸይኽ ኧረ አላወኩሽም፤ ራስሽን ልታስተዋውቂን
ትችያለሽ ?
እርሷ ከዓመት በፊት በአስካሪ መጠጥ ሱስ ስለተጠቃው
ባለቤቴ ጥያቄ ያቀረብኩት እና «እንዲህ እንዲህ» አይነት
ብያኔዎችን የሰጡኝ አልጀሪያዊት ነኝ።
ሸይኽ አዎ ፣ አስታወስኩኝ። ልጄ እስኪ መልካም ዜና
ንገሪኝ። እንዴት ነሽ አንቺ ?
እርሷ ወላሒ አሁን ባለቤቴ ለሌሊት ሶላት የሰፈሩን
መስጂድ እየከፈተ አዛን የሚያደርገው እርሱ ሆኗል። ቁርዓንም
በፍቅር ይቀራል። ግዴታና ሱና የሆኑ ሶላቶች አያመልጡትም።
እንዲሆን ስመኘው በነበረው ፍኖት ላይ አላህ መርቶታል።
እርሰዎንም አላህ ይባርከዎት።
.
.
በስልኩ የሚሰማው ድምጿ በደስታ የታጀበ እንባ ጋር ተደምሮ
ነበር። ፈታኙን ኬላ ያለፈች ታጋሽ እንስት ነች። ወደ አላህ
ተጠጋች። በጥረቷ ገፋች። ተስፋ ሰነቀች። በጽናቷ ከአላህ
ምንዳ ለማግኘት ታገለች። ንጹህ ልቧን አይቶ ችግሯን
ቀረፈው። አንድን ሰው ወደ ቀጥተኛው ጎዳና እንዲመለስ ሰበብ
ለመሆን የሚጠይቀው ትዕግስት የመጨረሻ ከባድ በመሆኑ
አላህም ዘንድ ሽልማቱ የገዘፈ ሆኗል።


الشوق حركني بغير تردد والشعر أبحر في غرام محمد

فاءذا مدحت محمدآ بقصيدتي فلقد مدحت قصيدتي بمحمد

شرف اللسان بذكر احمد سيدي فبذكره نكفي الهموم ونهتدي

وإلهنا أوصى فهيا رددوا يا رب صل على الحبيب محمد


ጁምኣን በሰለዋት
اللهم صلي على سيدنا محمد ❤️❤️❤️
ከነቢያችን ሙሀመድ ሰ,ዐ,ወ ምናቸውን ትወዳላችሁ? እየመለሳችሁ


እየተሳትፍን ጀመኣው😊👋


#ኢስላማዊ ጥያቄ 2 በቁርአን ውስጥ የተጠቀሱት ነቢያት ብዛታቸው ስንት ነው?
So‘rovnoma
  •   ሀ፡25
  •   ለ፡15
  •   ሐ፡14
  •   መ፡17
82 ta ovoz


#ኢስላማዊ ጥያቄዎች ይቀጥሉ?


#ኢስላማዊ ጥያቄ 1
የመጀመሪያው መልእክተኛ(ረሱል) ማነው?

መልሱ፡_ነብይ ኑህ(ዐሰ)_


ኢስላማዊ ጥያቄዎች #የመጀመሪያው መልእክተኛ(ረሱል)ማነው?
So‘rovnoma
  •   ሀ፡አደም(ዐሰ)
  •   ለ፡ሉጥ(ዐሰ)
  •   ሐ፡ኑሕ(ዐሰ)
  •   መ፡ዳውድ(ዐሰ)
114 ta ovoz


የሆነ ጊዜ አንድ ሰው ህይወት ያደክመውና ችግሮች በዝተውበት ወደ አንድ ጥበበኛ ሰው ዘንድ ይሄዳል ላለበት ችግር መፍትሄ ፈልጎ  ....

   ጥበባኛው ዘንድ ሂዶ ያለውን ነገር አስረዳው
ምንም መፍትሄ እንዳጣና አቅጣጫ አሳይኝ ሲል ጠየቀው ...  ጥበበኛው ሁለት ጥያቀውን እጠይቅሀለሁ መልስልኝ አለው ...?

    ጥበበኛውም ወደዚህ ዱንያ ስትመጣ ይህንን ሁሉ ችግር ይዘህ ነው የመጣሀው...?

    ሰውየውም አይደለም ሲል መለሰ!

ጥበበኛውም ይችን ዱንያ ትተህ ስትሄድ ይህንን ሁሉ ችግር ይዘህ ነው ወይ የምትሄደው ...?

    ሰውየውም ይዤ አልሄድም አለ!

ጥበበኛውም ይዘሀው ያልመጣሀው ነገር ይዘሀው የማትሄደው ነገር በዚህ ደረጃ ሊያሳስብህ አይገባም ትግስተኛ ሁን በዱንያ ነገራቶች ላይ መሬት ላይ ከምትመለከተው በላይ ሰማይ ላይ የምትመለከትበት ጊዜ ረጂም ይሁን የፈለከው ነገር እንዲሳካ ከፈለክ!

   ሰውየውም ደስ ብሎት ተስፈኛ ሁኖ ልብ ተጠግቦ ሄደ።


አስተማሪየሆነቂሷ

አንዲት እናት ለአንድ ሼኽ ልጆቼን ከበድ ያለ #እንቅልፍ ስለሚተኙ #ለሶላተል ፈጅር ማስነሳት አልቻልኩም ምን ይሻላል ብላ ትጠይቃችዋለች??

ሼኹም፦ አያርገውና ልጆችሽ ተኝተው ቤቱ ላይ #እሳት ቢነሳ ምን ታደርጊያለሽ አሏት ?

እናት፦ እቀሰቅሰቸዋለው.

ሼኹም፦ ከበድ ያለ እንቅልፍ ላይ ከሆኑስ?

እናት፦ወሏሂ በግድም ቢሆን አንገታቸውን ይዤ እቀሰቅሳቸዋለሁ

ሼኹም፦ #ከዱንያ እሳት ልታድኛቸው ይሄን ያህል ከታገልሽ #ከአኼራ ለማዳን ከዚህ በላይ መታገል አለብሽ አሏት ይባላል።

አሏሁ ተዓላ ከጀሀነም እሳት ይጠብቀን!


የሼህ እገሌን ልጅ ልንድርህ ነውና ሂድ እያት አሉት ወላጆቹ፡፡ ገና ሲያያት ግንባሩ
ከግንባሯ ገጠመ፡፡ ወደዳት፡፡ እናም በሌላ ቀን ፈቃደኝነቷን ሊጠይቃት ብሎ ሄደ፡፡
ስለ ሀሳባቸዉና ዓላማቸው አወሩ፡፡
“ቁርኣን ምን ያህል ሐፍዘሃል?” አለችው፡፡
“አይ ብዙ አላፈዝኩም፤ ምናልባት ካሁን በኋላ እሐፍዝ ይሆናል፡፡ ግን መልካም
የአላህ ባርያ የመሆን ጉጉት አለኝ፡፡” አላት፡፡ ጉጉቱን በቀልቧ ያዘችለት፡፡ ሲቪው
አማረለት ።
“አንቺስ ሐፍዘሻል?” አላት፡፡
“የዐምማን ጁዝ ሐፍዣለሁ፡፡” አለችው፡፡
እውነት የነገራት መሆኑን ባወቀች ጊዜ ቀልቧ ወደዳት፡፡ አሳዝኗትም ወዳዉም
ጥያቄዉን ተቀበለች፡፡
“ከተጋቡ በኋላ ቁርኣን እንዲአስሐፍዛት ጠየቀችው፡፡ ችግር የለዉም እሺ
እንተጋገዛለን፡፡” አላት፡፡
ከ “መርየም” ምዕራፍ አብረው ጀመሩ፡፡
ሒፍዙን ሳያቆሙ ቀጠሉ፡፡ በመጨረሻም ሁለቱም ቁርኣንን በቃል አኽትመው
የሒፍዝ ሰርተፊኬት አገኙ፡፡
አላረፈችም፡፡ አሁን ደግሞ ።"ሐዲሥ ለምን አንሐፍዝም?" አለችው፡፡ ቡኻሪን
አጥንተው ጨረሱ፡፡
፨፨
አንድ ቀን ለዚያራ ወደ ወላጆቿ ቤት ሄዱ፡፡
ባል “አንድ ያልነገርንዎት ነገር አለ አባ፡፡ አልሐምዱሊላህ ልጅዎ ቁርኣን
ሐፍዛለች፡፡” አላቸው ለአማቹ በኩራት ፡፡
አማቹ በግርምት አዩት፡፡ ወደ ጓዳ ገቡና የልጃቸዉን የተለያዩ የምስክር
ወረቀቶችን አመጡ፡፡ አማች ባየው ነገር ደነገጠ፡፡ ልጅት ሳታገባው በፊት
አስቀድማ ሐፊዛ ነበረች ለካ፡፡ ከቁርአን አልፋ ሱነኑ ሲታንም ጭምር የጨረሠች
ስለመሆኑ ማስረጃ አላት፡፡ ባል ተገረመና ዝም አለ፡፡
፨፨፨፨፨
ያኔ እንዲያ ያደረገችው የባሏ ሞራል እንዳይነካ ፈርታ ነበር፡፡ ዒልም የለህም፤
ቁርኣን አላፈዝክም ብላ አላጣጣለችዉም፤ በዕውቀቱ ደረጃ አልናቀችዉም፡፡ እሱ
እውነቱን በነገራት ጊዜ ከልቧ አስገባችው፤ ፈቀደችዉም፡፡ እንደሷ ቁርአን
እንዲሐፍዝም ስለፈለገች በዚያ መልኩ አስጀመረችው፡፡ ዐምማን ሐፍዣላሁ
ያለችውም እውነቷን ነበር አልዋሸችም፡፡ ዐምማ ከ30 የቁርኣን ጁዞች አንዱ
ነዉና፡፡

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.