ምናል ብታስተምረኝ | ዘማሪት ሲስተር ሕይወት ተፈሪበክብር በሞገስ በመወደስ ፈንታ
መቀመጥ እንድችል ከመዋረድ ተርታ
ስድብን እየሰማሁ ያላንዳች ሁካታ
ለመቆም እንድችል ልቤ ሳይረታ
ምናል ብታስተምረኝ/2/
ብታስችለኝ ጌታ/2/
አዝ
ለኔም አስተምረኝ ባላጠፋት ጥፋት
በጸጋ መቀበል የአይሁድን ጥፋት
እንዴት እንደሚቻል ሳያጉረመርሙ
ንገረኝ ጌታዬ ይረዳኝ ትርጉሙ
ምናል ብታስተምረኝ/2/
ብታስችለኝ ጌታ/2/
አዝ
የመናቅን ጥበብ የውርደትን ዘዴ
እባክህ አስረዳኝ አስተምረኝ አንዴ
ብኤል ዜቡል ተብለህ ያልተበሳጨኸው
የሀጢያተኞች ወዳጅ መባል ያልጠላኸው
ጋኔን ይዞታልን የሰማህ በጸጋ
ለኔም አስተምረኝ /2/
በቂም አልዋጋ/2/
አዝ
አልወጋ እባክህ በመራርነት ጦር
በቁጣ ጥላቻ ነፍሴ አትሰበር
እንዴት ነበር ያኔ የይሁዳን እግር
ዝቅ ብለህ ያጠብከው ስታውቅ ሁሉን ነገር
ለእኔም አስተምረኝ/2/
ብዙ ሳልናገር/2/
አዝ
በችንካር ተጣብቀህ ከመስቀሉ ጋራ
የደምህ ነጠብጣብ ገና ሳያባራ
አያውቁትምና የሚያደርጉትን
ይቅርታ የለመንክ ላጠጡህ ሐሞትን
ምናል ብታስተምረኝ/2/
እንዲህ ያለ ሕይወትን/2/
አዝ
አሁን ምንቸገረህ ብትሰጠኝ ለአንድ አፍታ
የትህትናን ቀሚስ የትዕግስትን ጉታ
እያየህ አይደል ወይ ነፍሴ እንዲ ተራቁታ
የመሰደብን ዘውድ የመናቅን ካባ
ምናለ ብትኖር/2/ ይህቺ ልቤ ደርባ/2/
አዝ
ትዕቢት ለተሞላው ላትንኩኝ ባይ ልቤ
ለክብሩ ለሚኖር ለኮርማው ሀሳቤ
ምናል ብትቀባው የትህትናን ሽቶ
እንደዚህ ከሚኖር ሸቶ ተበላሽቶ
ኧረ እኔስ አልቻልኩም አቅቶኛል በጣም
ስድብንም መቀበል ሀሜትንም ማጣጣም
ስተርከው እንጂ ስኖረው አቃተኝ
ይህን መራር ኑሮ
አንተው ይዘህ ጋተኝ/2/
@Orthodox_Mezmur_For_All@Orthodox_Mezmur_For_All