"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: Din


🌹«ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን
/አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ።♥ https://t.me/Orthodoxtewahdoc

ሐምሌ 3 በ2014 ዓ°ም ተከፈተ።
📌እግዚአብሔር ቢፈቅድ የቅዱሳኑን ታሪክ እንመማርበታለን ብለን ከፈትነው ቅዱስ እግዚአብሔር ይፍቀድልን አሜን‼
❤የእመ ብርሃን ልጅ🤗

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
Din
Statistika
Postlar filtri


✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
✍️"የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ከመከራም ሥጋት ያርፋል"📖ምሳ 1፥33☦📚
        
✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
📗ስንክሳር ዘወርኃ የካቲት ፪/2/

ወለተ ሥላሴ ብላችሁ በጸሎታችሁ አስቡኝ
https://t.me/Orthodoxtewahdoc
🌹የያዕቆብ ሌሊት ይሁንልን🕊




ትልቁ መሳሪያችን ፀሎት ነው
እስካሁን ያላነው በአባቶች ፀሎት ልመና፣ በእናቱ በድንግል ማርያም፣ በፃድቃን መላእክት አማላጅነት ነውና
አሁንም የአባቶች ፀሎት ይጠብቀን🙏
የድንግል ማርያም፣ ፃድቃን መላእክት አማላጅነት የልጇ የወዳጇ ይቅር ባይነት አይለየን🙏


ባለ ጦር በጦሩ ይተማመናል።
ባለ ጡንቻው በጡንቻው ይመካል።
ጦር እና ጡንቻ ከፈጣሪ ዘንድ ናቸው።
የሚልካቸውም፣ የሚያጠፋቸውም እሱ ነው።
እግዚአብሔርን በቅንነት የያዘ ለድል አይጓጓም።
በሶምሶን እና በዳዊት ላይ አድሮ ድልን በምሳሌ ያስተማረን የድንግል ማሪያም ልጅ ብቻ ነው።
ቅረቡኝ ልቀራባችሁ፣ ጥሩኝ ወደ ድል ተራራ ላውጣችሁ እያለ ነው።
አምላከ ቅዱሳን ሲረሳ መከራ አምጥቶ እንዲታወስ ያደርጋል።
ጥበቡ ረቂቅ ነው። እንደ ምድር ነገሥስታት በአፈ ቀላጤዎች የማይወደስ።
በዲዳዎች የሚወደስ፣ ጸጋው የማይለካ፣ ቸርነቱ የማይመዘን፣ ትዕግስቱ የማይወሰን።
እግዚአብሔር ሲወድ ጅቡን ሰው፣ እግዚአብሔር ሲጠላ ሰውን ጅብ " የሚያደርገው
የዓለም ፈጣሪ ሥሉስ ቅዱስ ነው። በስሙ ላደሩት ሰይጣን አቅም የለውም።
ሲያስታውሱት የሚያስታውስ፣ ሲረሱት የሚታገዝ ፣ ጊዜ የሚሰጥ።
ከእሳት መካከል ገለባን የሚያተርፍ።
ከውሀ መካከል ገለባን የሚያወድም።
አመጣጡ የማይገመት ፣ ለቀረቡት የሚገለጥ።
የቅዱሳን አመላክ ፣ ፀሐይ የምስራቋ የእመብርሃን ልጅ።
በከብቶች ማደሪያ የተወለደ፣ የትህትና አባት።
በእንጨት መስቀል የተሰቀለ የመከራ አባት።
በፈጠረው ዓለም የተሰደደ የስደተኞች አባት።
ሕዝቡን ለመማር የወረደ የምህረት አባት።
ሁሉንም እንደ ስራው የሚከፍል የፍትህ አባት።
በጭንቀት መካከል የሚደርስ፣ በጥጋብም መካከል የማይጠፋ።
ጉልበታሙን የሚያመክን፣ ጭቁኑን የሚያነግሥ።
ሁልጊዜ በንስሀ መንገድ ለሚሄዱት ወዳጆቹ የሚከሰት።
ስጋ ደሙን ለጠጡት ወዳጆቹ የቀረበ።
ለሚለግሱ ድልን የሚለግስ ደግ።
ለሚራሩ ርህራሄውን የሚሰጥ ሩህሩህ።
በአፍ መመጻደቅ ውስጥ የሌለ፣ በድዳዎቹ በየዋሆቹ ውስጥ ያለ።
ፍቅር መግቦ ፍቅር የሚቀበል።
ትህትና ሰጥቶ ትህትና የሚቀበል።
ደግነትን ሰጥቶ ደግነትን የሚቀበል።
መከራንም ሰጥቶ መከረኞችን የሚቀበል።
ስደትን ሰጥቶ ስደትን የሚቀበል።
መገረፍን ሰጥቶ መገረፍን የሚቀበል።
የተገፉት አባት ፣ አምላከ ኢትዮጵያ  ማራናታ ቶሎ ና
አምላከ ኢትዮጵያ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ አድነን።
አምላከ ቅዱሳን ኤልሻዳይ አለሁ በለን። ያለፈው በደል በንስሐ ታጥቦ እንደ ገና ንጹህ ካልሆን ጩኸታችን የተኩላ ነው የቀበሮ ጸሎት።

🌷ሰናይ ምሽት✝


ወር በገባ በ2 የእመቤታችን ወዳጅ የቅዳሴ ማርያም ደራሲ የአባ ሕርያቆስ ወርሐዊ መታሰቢያው ነው፡፡

ወቶ ከመቅረት ካልታሰበ አደጋ ይሰውረን።🙏❤


"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒 dan repost
🌹#አባ_ሕርያቆስ 🌹

☞ወር በገባ በ2 የእመቤታችን ወዳጅ የቅዳሴ ማርያም ደራሲ የአባ ሕርያቆስ ወርሐዊ መታሰቢያው ነው፡፡ ሕርያቆስ ማለት ኅሩይ ረቂቅ ፀሓይ ብርሃን ማለት ነው፡፡ሀገሩ በብህንሳ ነው፡፡ በ10'000 መነኮሳት ላይ ተሹሟል፡፡ግብረ ገብ ነውናሥርዐት ያጸናባቸዋል፡፡ ነገር ግን ያልተማረ ነውና ይንቁታል፡፡ እሱ ግን እንደ ጠሉኝልጥላቸው እንደ ናቁኝ ልናቃቸው ሳይል በፍቅር በትሕትና ጸንቶ ያስተምራቸውጀመረ፡

☞ከዕለታት አንድ ቀን በምን ምክንያት እንሻረው ብለው መከሩ፡፡ ቅዳሴ ቀድሰኽ
አቁረበን ብለን የሚያስቸግር ቅዳሴ ሰጥተን በዚህ ምክንያት እንሽረዋለን ብለው
ወሰኑ፡፡
☞እሱ ግን እንደ ቅዱስ ኤፍሬም የእመቤቴ ምስጋና እንደ ባሕር አሸዋ በዝቶልኝ
እንደ ልብስ ለብሼው እንደ ምግብ ተመግቤዎ እንደ ውሃ ጠጥቼው እያለ ይመኝ
ነበርና ሥርዐቱን ጨርሶ ፍሬ ቅዳሴ ሲደርስ ከሊቃውንት የሚያስቸግር እያሉ
ሲያወጡ ሲያወርዱ ጉሥዐ ልብየ ቃለ ሠናየ ብሎ ወይእዜኒ ንስብሖ እስከ
ሚለው ድረስ ሰተት አድርጎ ተናግሮታል፡፡
☞የሚጠሉትና የሚንቁት የነገሩትን አከናውኖ መናገር የማይችል ዛሬስ እንግዳ
ድርሰት እደርሳለኹ ብሎ እንዳገኘ ይቀባጥራል ብለው አቃለሉበት፡፡
☞የሚወዱትና የሚያከብሩት ደግሞ ከመንፈስ ቅዱስ ካልኾነ ከዕሩቅ ብእሲ
እንዲኽ ያለ ምስጢር አይገኝም በማለት ጽፈው ደጉሰው ከውሃ ቢጥሉትብራናው
ሳይፋቅ ከእሳትቢጥሉት ሳይቃጠል ወጣ፡፡ ከሕሙማን ላይ ቢጥሉት ድውይ
ፈወሰ፡፡ የበለጠ ደግሞ ሙት አስነሳ፡፡
☞ይህስ ደግ ድርሰት ነው ብለው ከቅዳሴ ድረስት መካከል 14ኛ አድርገው
ጠርዘውታል፡፡፡፡
☞አባ ሕርያቆስ ተሹሞ ሳለ ብዙ ድርሰት ብዘ ተግሣፅ ጽፏል፡፡ ከብዙም ቅዳሴ
ማርያምና ላሐ ማርያም ተጠቃሽ ናቸው፡፡
☞እመቤታችን ቅዱስ ኤፍሬምን ከሶርያ አንተ ውዳሴዬን አባ ሕርያቆስን ከብሕንሳ በደመና ነጥቃ  አንተ ቅዳሴን ንገሩት ብላ ቅዱስ ያሬድ በዜማ ደረሶላቸዋል፡፡
☞የቅዱስ አባ ሕርያቆስ ድርሰት የሆነው ከ14
ቅዳሴ አንዱ የሆነው" ቅዳሴ ማርያም" ብለው ሰየሙት፡፡
☞(ከመድብለ ታሪክ መጻሐፍ የተወሰደ)
☞ለአባ ሕርያቆስ፤ለቅዱስ ኤፍሬም፤ለቅዱስ ያሬድ፤ለአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
የተመነች ለእኛም ትለመነን፡፡ ማስተዋሉን ታድለን፡
☞ሲራክ ተክለጻዲቅ የተዋህዶ ልጅ

https://t.me/Orthodoxtewahdoc




"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒 dan repost
#ወር በገባ በ2 ፃድቁ አባ ጉባ ከዘጠኙ ቅዱሳን አንድ ናቸው🙏
🌹#አባ ጉባ🌹

♨••• ጻድቁ የተወለዱት ታሕሳስ 29 ቀን በ336 ዓ/ም በመንፈቀ ሌሊት ነው:: አባታቸው ጌርሎስ : እናታቸው ቴዎዶክስያ ደጐች ነበሩ::

አባ ጉባ ("ባ" ጠብቆ ይነበብ) በተወለዱ ቀን ጌታችን ከመላእክቱ ጋር በመውረዱ ቤታቸው ለ7 ቀናት በብርሃን ተሞልቶ ነበር:: ሕጻኑ ጉባም ፈጣሪያቸውን "ሃሌ ሉያ" ብለው አመስግነዋል::

በልጅነታቸው መጻሕፍትን አጥንተው : ወደ ገዳመ አስቄጥስ ገብተው መንነዋል:: ለበርካታ ዓመታት ከተጋደሉ በኋላ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል "ወደ ቅድስት ሃገር ኢትዮዽያ ሒድ" ብሏቸው ከ8ቱ ቅዱሳን ጋር ወደ ሃገራችን መጥተዋል:: በወቅቱ ዕድሜአቸው ከ140 በላይ ነበር::

ጻድቁ አባ ጉባ እንደመሰሎቻቸው በስብከተ ወንጌል : መጻሕፍትን በመተርጐም : ገዳማትን በማስፋፋትና አብያተ ክርስቲያናትን በማነጽ ቆይተዋል:: በተለይ ራማ ኪዳነ ምሕረት የእርሳቸው ናት ይባላል::

ጻድቁ ቅዳሴ ሲቀድሱ ከመሬት ከፍ ብለው ነበር:: ብዙ ጠበሎችን አፍልቀው ድውያንን ፈውሰዋል:: ሙታንንም አንስተዋል:: እመቤታችንም የብርሃን መስቀል ሰጥታቸዋለች:: ጻድቁ ከበርካታ የቅድስና ዘመናት በኋላ በዚህች ቀን ዐርፈው በገዳማቸው ተቀብረዋል::

በዘመኑ ትኩረት ካጡ ታላላቅ ገዳማት አንዱ ይሔው ትግራይ ውስጥ የሚገኘው የአባ ጉባ ገዳም ነው::

(በነገራችን ላይ "ጉባ" ማለት "አፈ-መዐር : ጥዑመ-ልሳን" ማለት ነው)

††† ቸሩ መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ የጻድቃኑን በረከት ያድለን:: በጸሎታቸውም በደላችንን ይቅር ይበለን::


"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒 dan repost
የካቲት ፪ ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
፩.ቅዱስ አባ ጳውሊ ገዳማዊ (የባሕታውያን ሁሉ አባት)
፪.ቅዱስ አባ ለንጊኖስ ሊቀ ምኔት (ደብረ ዝጋግ)
፫.ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ
††† ወርኀዊ በዓላት
፩.ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት
፪.ቅዱስ ታዴዎስ ሐዋርያ
፫.ቅዱስ ሳዊሮስ ዘአንጾኪያ (የሃይማኖት
ጠበቃ)
፬.ቅዱስ ኢዮብ ጻድቅ
፭.ቅዱስ አቤል ጻድቅ
፮.አባ ሕርያቆስ ዘሐገረ ብሕንሳ

††† "የሚበልጠውን ትንሣኤ እንዲያገኙ እስከ ሞት ድረስ ተደበደቡ። ሌሎችም መዘበቻ በመሆንና በመገረፍ ከዚህም በላይ በእስራትና በወኅኒ ተፈተኑ። በድንጋይ ተወግረው ሞቱ። ተፈተኑ፤ በመጋዝ ተሰነጠቁ፤ በሰይፍ ተገድለው ሞቱ። ሁሉን እያጡ፣ መከራን እየተቀበሉ፣ እየተጨነቁ የበግና የፍየል ሌጦ ለብሰው ዞሩ። ዓለም አልተገባቸውምና በምድረ በዳና በተራራ በዋሻና በምድር ጉድጓድ ተቅበዘበዙ።" †††
(ዕብ ፲፩፥፴፭-፴፰)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††

Dn Yordanos Abebe




"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒 dan repost
†††✝ እንኳን ለታላቁ ገዳማዊ አባ ጳውሊ እና ለጻድቁ አባ ለንጊኖስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††✝

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† ታላቁ ቅዱስ ጳውሊ †††

††† በቤተ ክርስቲያን አስተምሕሮ "ታላቁ /ዐቢይ/ THE GREAT" የሚል ስም የሚሰጣቸው አባቶች የተለዩ ናቸው። አንድም እጅግ ብዙ ትሩፋቶችን የሠሩ ናቸው። በሌላ በኩል ደግሞ በተመሳሳይ ስም ከሚጠሩ ሌሎች ቅዱሳን እንለይበታለን።

ገዳማዊ ሕይወት ጥንቱ ብሉይ ኪዳን ነው። በቀዳሚነትም በደብር ቅዱስ አካባቢ ይኖሩ የነበሩ ደቂቀ ሴት እንደ ጀመሩት ይታመናል። ሕይወቱ በጐላ በተረዳ መንገድ የታየው ግን በታላቁ ጻድቅ ሄኖክ ከዚያም በቅዱሱ ካህን መልከ ጼዴቅ አማካኝነት ነው።

ቀጥሎም እነ ቅዱስ ኤልያስ ነቢይ እነ ኤልሳዕ ደቀ መዝሙሩ ኑረውበታል። በሐዲስ ኪዳን ደግሞ ሙሉ ሕይወቱን በገዳም (በበርሃ) ያሳለፈው መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ቅድሚያውን ይይዛል።

ለስም አጠራሩ ስግደት ይሁንና መድኃኒታችን ክርስቶስ በገዳመ ቆረንቶስ ለአርባ ቀናት በትሕርምት ኑሮ ገዳማዊ ሕይወትን ቀድሷል፤ አስተምሯል። በዘመነ ስብከቱም ያድርባት የነበረችው የደብረ ዘይቷ በዓቱ (ኤሌዎን ዋሻ) በራሷ ለዚህ ሕይወት ትልቅ ማሳያ ናት።

ከጌታ ዕርገት በኋላም ክርስቲያኖቹ የዓለም ሁካታ ሲሰለቻቸው አንድም በንጹሕና በተሸከፈ ልቡና ለፈጣሪያቸው መገዛትን ሲሹ ከከተማ ወጣ እያሉ ይኖሩ እንደ ነበር የታሪክ መዛግብት ያሳያሉ። አኗኗራቸውም በቡድንም በነጠላም ሊሆን ይችላል። ዋናው ነገር ግን በጾምና በጸሎት መትጋታቸው ነው። ይህም ሲያያዝ እስከ ሦስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ደረሰ። በዚህ ዘመን ግን አባ ጳውሊ የሚባል ንጹሕ ክርስቲያን ይህንን ሕይወት ወደ ሌላ ደረጃ ከፍ አደረገው። ለሰማንያ ዓመታት ሰው ሳያይ ተጋድሎ "የባሕታውያን አባት" ተባለ። ደንብ ያለው ተባሕትዎም ጀመረ።

ይህ ከሆነ ከሃያ ዓመታት በኋላ ደግሞ አባ እንጦንስ የሚባሉ ደግ ክርስቲያን ይህንን ገዳማዊ ሕይወት በሌላ መንገድ አጣፈጡት። በቅዱስ ሚካኤል አመንኳሽነት ገዳማዊ ሕይወት በምንኩስና ተቃኘ። ስለዚህም አባ እንጦንስ የመነኮሳት አባት ተባሉ።

እርሳቸውም ሕይወቱን ለማስፋፋት ከተለያዩ አሕጉር ደቀ መዛሙርትን እየተቀበሉ አመንኩሰዋል። ቅዱሳን የአባ እንጦንስ ልጆችም ወደየ ሃገራቸው ተመልሰው ሕይወቱን በተግባር አሳይተው ገዳማዊነትን አስፋፍተዋል።

አንድ ቀን ቅዱስ እንጦንስ (የመነኮሳት ሁሉ አባት) እንዲህ ሲል አሰበ። "በውኑ በበርሃ ለበርካታ ዘመናት በመኖር ከእኔ የሚቀድም (የሚበልጥ) ሰው ይኖር ይሆን?"
ይህንን ሃሳቡን ገና ሳይጨርሰው ቅዱስ ሚካኤል ወደ እርሱ ዘንድ ደረሰ።

"እንጦንስ ሆይ! ከእኔ የሚቀድም የበርሃ ሰው ይኖር ይሆን ብለህ አስበሃል። በእርግጥም ከአንተ ሃያ ዓመታትን ቀድሞ ወደ በርሃ የገባ፣ በቅድስናው ፈጣሪውን ያስደሰተ፣ ዓለም ከነ ክብሯ የእግሩን መረገጫ ያህል እንኳ የማትመጥነው በጸሎቱና በምልጇው ዓለም የምትጠበቅለት ሞገስን የተሞላ አንድ ሰው በበርሃ ስላለ ሒድና ተመልከተው።" ብሎት ተሠወረው።

ቅዱስ እንጦንስም ከሰማው ነገር የተነሳ እየተደነቀ ተነሳ። እርሱ ካለበት በርሃ በራቀ መንገድም ለቀናት ተጉዞ አንድ በዓት (ዋሻ) በር ላይ ደረሰ። በበሩ አካባቢ የሰውና የአራዊት ኮቴ ተመልክቶ በሩን ጸፋ (ቆፈቆፈ)። በውስጥ ያለው አረጋዊ ሰው ግን ትልቅ ድንጋይ ገልብጦ በሩን አጠበቀው። ለሰማንያ ዓመታት ሰውን አይቶ አያውቅምና ሰይጣን ሊያታልለኝ መጥቷል ብሎ አስቧል። ቅዱስ እንጦንስ ግን "ኃሠሥኩ እርከብ ጐድጐድኩ ይትረኃው ሊተ - ሽቻለሁና ላግኝ፤ ደጅ መትቻለሁና ይከፈትልኝ።" ሲል አሰምቶ ተናገረ።

ቅዱሱ ገዳማዊም ሰው መሆኑን ሲያውቅ በሩን ከፈተለትና ወደ ዋሻው አስገባው። መንፈሳዊ ሰላምታንም ተለዋወጡ። ሲመሽም ቅዱስ እንጦንስ ሽማግሌውን ገዳማዊ "ስምህ ማን ነው?" ቢለው "ስሜን ካላወክ ለምን መጣህ?" ሲል መለሰለት።

ያን ጊዜ ቅዱስ እንጦንስ ቀና ብሎ ሰማይን ሲመለከት ምሥጢር ተገለጠለትና "ቅዱስ ጳውሊ ሆይ! ከአንተ ጋር ያገናኘኝ ፈጣሪ ይክበር፤ ይመስገን።" ሲል ፈጣሪውን ባረከ። ቅዱስ ጳውሊም መልሶ (በጸጋ አውቆት) "አባ እንጦንስ ሆይ! እንኳን ደህና መጣህ።" አለው። ሁለቱም ደስ ብሏቸው ፈጣሪያቸውን እያመሰገኑ ተጨዋወቱ።

ቤተ ክርስቲያን ለሁሉም ዓይነት የቅድስና ሕይወት የመጀመሪያ የምትላቸው አላት። ለምሳሌ፦
የመጀመሪያው ሐዋርያ ቅዱስ እንድርያስ፣
የመጀመሪያው ሰማዕት ቅዱስ እስጢፋኖስ፣
የመጀመሪያው ባሕታዊ (ገዳማዊ) ቅዱስ ጳውሊ እና የመጀመሪያው መነኮስ ቅዱስ እንጦንስን ማንሳት እንችላለን።

ቅዱስ ጳውሊ የተወለደው በሰሜናዊ ግብጽ በእስክንድርያ ከተማ ሲሆን ዘመኑም ሦስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ ነው። ወላጆቹ ባለጸጐች ነበሩ። ቅዱሱንና ታላቅ ወንድሙን አባ ጴጥሮስን ወልደዋል። ሁለቱ ክርስቲያን ወንድማማቾች ገና ወጣት ሳሉ ወላጆቻቸው ሞቱባቸው። ሃዘናቸውን ፈጽመው ሃብት ሲካፈሉ ግን መስማማት አልቻሉም።

ምክንያቱ ደግሞ ትልቁ ጴጥሮስ ደህና ደህናውን እቃ ወስዶ መናኛ መናኛውን ለትንሹ ለጳውሎስ (ጳውሊ) መስጠቱ ነበር። ስለዚህ ነገር ተካሰው ወደ ፍርድ ቤት ሲሔዱ ግን መንገድ ላይ አንድ ባለጸጋ ሙቶ ደረሱ።

ቆመው ሳሉም ቅዱስ መልአክ ሰው መስሎ ጳውሊን "ይህ ሰው ባለጸጋ ነው። በገንዘቡ የሰጠውን ፈጣሪ ሲበድልበት ኑሮ እነሆ ተሸኘ። በሰማይም አስጨናቂ ፍርድ ይጠብቀዋል።" ሲል ነገረው።

በዚያች ቅጽበት የወጣቱ ጳውሊ ሐሳብ ተለወጠ። ወደ ወንድሙ ተመልሶ "ወንድሜ ሆይ! ሁሉ ንብረት ያንተ ይሁን።" ብሎት ከአካባቢው ጠፋ። በመቃብር ሥፍራ ለሦስት ቀናት ያለ ምግብ ጸልዮ የእግዚአብሔር መልአክ ሰው ወደ ማይደርስበት በርሃ ወሰደው።

በዚያም ምንጭ ፈለቀችለት። እየጾመ ይጸልይ ይሰግድ ገባ። ሁሌ ማታ ግማሽ ሕብስት ከሰማይ እየወረደለት ቅዳሜና እሑድ መላእክት እያቆረቡት ለሰማንያ ዓመታት ኖረ። (አንዳንድ ምንጮች ግን ለዘጠና ዓመታት ይላሉ።) ከቅዱስ እንጦንስ ጋር የተገናኙትም ከዚህ በኋላ ነው።

ከቅዱስ እንጦንስ ጋር በነበራቸው የሁለት ቀናት ቆይታም ቅዱስ ጳውሊ ብዙ ትንቢቶችን ተናግሯል። በዚህች ቀን ሲያርፍም መቃብሩን አናብስቱ ቆፍረዋል። ቅዱስ እንጦንስም በክብር ቀብሮታል። ለሰማንያ ዓመታት የለበሳት የዘንባባ ልብሱም ሙት አስነስታለች።

††† ጻድቅ፣ ቡሩክ፣ ቀዳሚው ገዳማዊ፣ መላእክትን የመሰለና የባሕታውያን ሁሉ አባት ለተባለ ለቅዱስ ጳውሊ ክብር ይገባል!

††† አባ ለንጊኖስ †††

††† ጻድቁ ከኪልቅያ እስከ ሶርያ ከሶርያ እስከ ግብጽ ድረስ በተጋድሎ የተጓዙ አባት ናቸው። በአምስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን አጋማሽም የደብረ ዝጋግ (ግብጽ፤ እስክንድርያ) አበ ምኔት ሆነው አገልግለዋል።

ሙታንን አስነስተው ሃይማኖታቸውን ጠብቀው ብዙ ተአምራትን ሠርተው በዚህች ቀን ዐርፈዋል። ከድንቅ ነገራቸው ሰይጣን የእርሳቸውን የምንኩስና ቆብ ዐይቶ ደንግጦ መሸሹን እንጠቅሳለን።
"ኀበ ኢኀሎከ ሶበ ቆብዓከ ርዕየ
ሰይጣን ተኃፊሮ እፎኑመ ጐየ።" እንዲል።
(አርኬ)

††† አምላክ በበረከታቸው ይባርከን።


ዮም ፍስሓ ኮነ/፫/
በእንተ ልደታ ለማርያም

እልልልልልልልልልል👏🌸🌷👏🌷🌸🌷👏🌷🌸🌷👏🌷🌸🌷🌸🌷


ድንግል ሆይ
በድካሜ ጊዜ ኀይል አደረኩሽ
የኤፍራታ ርግብ ማርያም ሆይ ነፍሴ ብቻዋን እንዳትኖር ከሕይወትሽ ጋራ አንድ አድርጊኝ። የሰላምና የፍቅር ንግሥት ድንግል ማርያም ሆይ ለክብርሽ ምስጋናን አነሣለሁ፤ ለስምሽ ምስጋናን በማቀርብበት ጊዜ ከበሮን አነሣለሁ። የሽቱ ሙዳይ ድንግል ማርያም ሆይ በውዳሴ ቃል አመሰግንሽ ዘንድ የአንደበቴን አልጫነት በጨው አጣፍጪ። የነዳያንን ልመና የምትሰሚ ማርያም ሆይ ጠላት በእኔ ላይ እንዳይበረታ ሰይፍሽን አንሺ።
ከሽቱ ይልቅ የምትሸቺ አበባ ማርያም ሆይ አንበሳ አራዊትን ሁሉ እንደሚያሸንፍ ያንቺም ጽድቅ የእኔን አበሳ ያሸንፈው።
ለእግዚአብሔር እናት የሆንሽ ማርያም ሆይ የተጠማች ምድር ዝናምን ተስፋ እንደምታደርግ በፊትሽ ቆሜ ምሕረትሽን ተስፋ አድርጋለሁ።
የሕይወት ፍሬ ክርስቶስን የተሸከምሽ ማርያም ሆይ የእግዚአብሔርን ቃል ወልደሽልናልና፤ በምደኸይበት ጊዜ ብልፅግናን፤ በድካሜ ጊዜ ኀይል አደረኩሽ። የጉባኤ መመኪያ ድንግል ማርያም ሆይ በውድቀቴ ጊዜ ረዳት ባጣሁ ጊዜ ባንቺ ቃል ትንሣኤን ተስፋ አደርጋለሁ።
ሙሴ በደብረ ሲና ያየሽ የማስተዋልና የጥበብ ዕፅ አንቺ ነሽ በቅድስና ፈጽሞ የተጐናጸፍሽ እመቤቴ ማርያም ሆይ ጥፋትን እንዳላይ ብርሃናዊ መጽሐፍንና የተሰወረ መናን ስጪኝ።
ሕያውና ማኅያዊ የሚሆን ጌታ ካንቺ የተወለደ የሰማያዊ ንጉሥ እርሻ አንቺ ነሽ፤ የሌዊና የይሁዳ ልጅ ድንግል ማርያም ሆይ በምልጃሽ የችግርን በር ዝጊ የምሕረትሽንም በር ክፈቺ።
የመላእክት ተድላ ደስታቸው የጌታ እናት ማርያም ሆይ ደስ ይበልሽ የነቢያት ዜና ትንቢታቸው ማርያም ሆይ ደስ ይበልሽ ፈጽሞ የተመሰገንሽ ማርያም ሆይ ከምርጦችሽ አትለይኝ ንግሥት ሆይ በሕይወቴም በሞቴም አትተይኝ (አትለይኝ)። ፈቃድን የምትፈጽሚ ድንግል ማርያም ሆይ የስምሽ መታሰቢያ ለሕሙማን ፈውስን ለተራቆቱት ልብስን ሰጣቸው።
ድንግል ሆይ ልዕልናሽ በመናገርም በመተርጐምም ሊነገር አይቻልም፤ የእግዚአብሔር ማደሪያው የሆንሽ ማርያም ሆይ የዓለምን ፍቅር እንዳልከተል ከዕውቀትሽ ዕውቀትን አድይኝ።
ከረጅም ተራራ የሰው እጅ ሳይነካው የተፈነቀለው ይህ ድንጋይ አንድ ልጅሽ ነው፤ ማለሟልነትሽ የበዛ ድንግል ማርያም ሆይ ከቀዳማዊና ከደኀራዊ ትውልድ ሁሉ ለስምሽ አጠራር ስግደት ይገባል።
የአባቶቻችን የቅዱሳን የጸናች የቀናች ሃይማኖታቸው እመቤታችን ሆይ የሕይወት አጽቅ አንቺ ነሽ፤ በዘመናችን ነፍሳችን ምስጋናን ይዛ ለልደትሽ ቊርባንን ታገባለች (ታቀርባለች)።
የታላቅ ብርሃን እናቱ አንቺ ነሽ ይኸውም ለዐይን የሚታይ ቃል ነው፤ ተስፋ ለቆረጡት ተስፋቸው የሆንሽ ድንግል ማርያም ሆይ ባርኪኝ፤ እንደ ለብሐዊ ምእመን (ቅዱስ ፍሬም) ከወይን ይልቅ በሚያስደስቱ ከናፍሮችሽ ባርኪኝ።
ጭንቅን የምታቃልዪ ድንግል ማርያም ሆይ በየዋሕነትሽ በርግብ ተመሰልሽ፤ በንጽሕናሽም ጥበበኛ ድንግል ተባልሽ።
እናትነትን ከአገልጋይነት አስተባብረሽ የያዝሽ ማርያም ሆይ ደስ ይበልሽ፤ በእቅፍሽ የያዝሽውን ጌታ መላእክት ያመሰገኑታል፤ ንጽሕትና የተባረክሽ ማርያም ሆይ በንጉሥ ቀኝ የምትቆሚ ንግሥት ሆይ ስላንቺ ዳዊት ዘመረ እኔም እዘምርልሻለሁ።
(መልክአ ውዳሴ)


#ድንግል_ሆይ_ዝም_አትበይ🙏🙏😢😢
ጨለማችን ጨልሟል ውስጣችን ቃል በሌለው ኃዘን ውስጥ ወድቋል ። አሰገራሚው መድኃኒት በውስጥሸ የተገኘ ፡ ምድርን የሸፈነ ፀሐይ የተገለጠብሽ የዳዊት ልጅ እናታችን ማርያም ሆይ ዝም አትበይ በእውነት ዝም አትበይ ። ትላንት ልመናሽ እንደጋረደን ዛሬም ቃል ኪዳንሽ ጥላ ይሁነን ።
ድንግል ሆይ....የመጣብንን እሳት ፡ከፊታችን
የቆመውን ደንቃራ በቃህ እንዲለው በልጅሽ ፈት ቁሚልን ።
እናታችን ሆይ ...አለማችን የዶኪማስን ቤት ሆኗል ፡ ሠርጉ ወደ ሙሾ ጠጁም ወደ መርዝነት ተቀይሯልና ....እንደ ልማድሽ ልጄ ሆይ በይልን ።
ከቀኝ ከግራ የሌለው የቃል ኪዳን ሕዝብሽን ሞት እንዳይበላው መድኃኒት ተብሎ ከተጠራው ልጅሽ ለምኚልን ። አንቺ በሥላሴ ፊት ሞገስ ያለሽ ሙሽራ ማርያም ሆይ ሠዓሊ ለነ እያልን በፊትሽ የመረረ እንባችንን እናፈሳላን ። ሚረዳን የልጅሽ እጅ ሚፈውሰንም እርሱ ብቻ ነውና ዝም አትበይ ።
ኢየሩሳሌምን ስለ ዳዊት የጋረድካት ጌታ ሆይ ስለ እናትህ ብለህ የሚሮጠውን መልአከ ሞት ያዘው።
ደምህ ይጋርደን ኃጢዓታችንን አታስብብን🙏🙏


"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒 dan repost
🌷መልክአ ቅዱስ ራጉኤል📗

አቤቱ የሊቀ መላእክት ቅዱስ ራጉኤል አምላክ ሆይ ! እኔን ባሪያህን .ወለተ ሥላሴ...ይልቁን ሙሉ ህዝበ ክርስቲያንን ከመከራ ስጋ ከመከራ ነፍስ ዘወትር በየጊዜውና በየሰአቱ አድነን ጠብቀንም ለዘለዓለሙ አሜን።


"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒 dan repost
🌷መልክአ ቅድስት ልደታ ለማርያም📗

እመቤቴ ማርያም ሆይ እኔ ኃጢዓተኛ ልጅሽን ወለተ ሥላሴን ለመንግሥተ ሰማያት እንድታበቂኝ በዚህ ዓለምም ከክፉ ነገር ኹሉ እንድትሰውሪኝ ዕለተ ልደትሽ ተስፋና አለኝታ አድርጌ እማፀንሻለሁና በፊት በኋላዬ ከእኔ ሳትለዪ ጠብቂኝ ዛሬም ነገም ዘወትርም ለዘለዓለሙ አሜን።🤲


✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
✍️"የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ከመከራም ሥጋት ያርፋል"📖ምሳ 1፥33☦📚
        
✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
📗ስንክሳር ዘወርኃ የካቲት ፩/1

ወለተ ሥላሴ ብላችሁ በጸሎታችሁ አስቡኝ
https://t.me/Orthodoxtewahdoc
🌹የያዕቆብ ሌሊት ይሁንልን🕊




አንቺን የያዘ ሰዉ ምን ይጎልበታል በምልጃሽ በረከት ቤቱ ሞልቶለታል።

🌷እመብርሃን ትጠብቃችሁ🌹🤲


እግዚአብሔር ይመስገን
እንሆ ወርኅ ጥር በእግዚአብሔር ቸርነት ተፈፀመ!ወርኅ የካቲትን የተባረከ መልካም ፍሬ የምናፈራበት ወደ ንስሃ የምንቀርብበት ያድረግልን!ሰይጣይ ከሸመቀው እኛ ከማናውቀው እግዚአብሔር ከሚያውቀው ክፉ ነገር ሁሉ ይሰውረን ይጠብቀን አሜን 🤲🌸

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.