ፕሮቴስታንት መዝሙር ll Protestant Song


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: Din


💁በዚህ channel ውስጥ
🎧አዳዲስ መዝሙሮች
🎤አዳዲስ ስብከቶች
📆የ ኮንፍራን ፕሮግራሞች
📖የመፅሀፍ ቅዱስ ጥቅሶች
📝መንፈሳዊ ግጥሞችን ያገኛሉ
💒በወንጌል አናፍርም💒
ለማስታወቂያ ስራ 👉 @EYOSII ያናግሩ
@protestantmezemur

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
Din
Statistika
Postlar filtri


"ዝምታህ"
ዘማሪት አስቴር አበበ

ሐሳብህ ጥልቅ ዕቅድህ የተለቀ
ከሰፈሬ ርቆ ከሰማይ የላቀ
ይሁን ያልከው ብዬ በዚያ ደምድሜአለሁ
በጎ ስለሆነ ለኔ የምታስበው

ከአንተ ተከራክሮ ከሺህ ነገር አንዱን መመለስ የቻለ
ሊያወራ ጀምሮ አንገቱን ቀና አድርጎ ቆሞ የቀጠለ
ሊያርምህ የዳዳው ሊያስተካክልህ
እኮ የቱ አዋቂ ነው ተው በዚህ ነው የሚልህ

#1 ) በዝቶ ካለው ጩኸት ሸተተኝ ሰላሙ
ከጨለማው መሃል ታየኝ ወጋገኑ
ከድፍርሱ መሃል ኩልል ያለ ነገር
ይታየኝ ጀመረ በቃልህ ስታመን

የሃሳብህ ጥልቀት ባይገባኝ ድምድሙ
ጅማሬ ላይ ቆሜ ቢበዛ ለምኑ
የፍርስራሽ ክምር ግራ ቢያሳስበኝ
ማዶን አሻግሬ ለማየት ሲያቅተኝ
ጎራ ስል ወደ ቃልህ ነገረኝ ነገሩን
የዛሬው ትርምስ ነገ ላይ ማማሩን
ለአይን የሚመች ነገር ባያዩም አይኖቼ
ግን በስራ ላይ ነህ ልቀመጥ ረግቼ (2)

#2 ) የለም ከሰው ሰፈር የፈቃድህ ምክር
ፍጥረትን ሰብስበህ አትቆም ለድርድር
ለዝብርቅርቁ ቅርጽ መልክ ላጣው ውበት
ሰተት ብሎ ይገባል አሜን ባለ አንደበት

ዝምታህ መልስ ሆነኝ አሃ አሃ  ዝምታህ መልስ ሆነኝ (2)
እየሰራህ እንዳለህ ጨለማው ነገረኝ
ዝምታህ መልስ ሆነኝ (2)
በስራ ላይ እንዳለህ ድፍርሱ ነገረኝ
ዝምታህ መልስ ሆነኝ (2)

ዝምታህ መልስ ሆነኝ አሃ አሃ  ዝምታህ መልስ ሆነኝ (2)
ለዚህ ነው ባትለኝ ድፍርሱ ነገረኝ
ዝምታህ መልስ ሆነኝ (2)
በስራ ላይ እንዳለህ ሁኔታው ነገረኝ
ዝምታህ መልስ ሆነኝ (2)
share♻️share♻️share♻️
ድንቅ ዝማሬዎችን ከፈለጉ
ይህን link⬇️ተጭነው ይቀላቀሉ

🎼🎼  𝙟𝙤𝙞𝙣 & 𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚  🎼🎼
@Protestantmezemur
@Protestantmezemur
─── ❖ ──  ✦ ── ❖ ───


"እራስህ አስተማርከኝ"
ዘማሪት አስቴር አበበ

ስንፍና ላይ እንዳልከርም እንዳልቆይ በዝለት
ሁሉ ከአቅም በልጦ ከልክ ያለፈ ዕለት
ሳላመልክህ እንዳልቀር ከልምዴ እንዳልጎድል
ሸክሜን ለአንተ አራግፌ መዘመር እንድቀጥል
ከጣራዬ በታች ያለው እንዳይዘኝ
ወጣ/እልፍ ብሎ ማምለክን እራስህ አስተማርከኝ

ለአምላክነትህ ስግደቴ ይኸው
ጥያቄ የለኝም ፊትህ የማቀርበው
አይኔን የሚሰርቅ በልጦ ከፍቅርህ
ልቤን የሚያሸፍት ገኖ ከሃሳብህ
ጉዳይ የለኝም ከአንተ የሚያጎድለኝ
ቁም ነገሬ ነህ ሌላ ምን አለኝ

አገኘሁህ ከሚነደው እሳት መሃል
እንዳልችለው አውቀህ ፈጥነህ ተገኝተሃል
የፍርሃቱን ሽታ የእሳቱን ግለት
ቀድመህ በህልውናህ ስታሳጣው ጉልበት
ቀርቶ የሞት ዜና ሲወራ መኖሬ
ኧረ እንዴት አልጨምር በላይ በላይ ቅኔ

ለአምላክነትህ ስግደቴ ይኸው
ጥያቄ የለኝም ፊትህ የማቀርበው
አይኔን የሚሰርቅ በልጦ ከፍቅርህ
ልቤን የሚያሸፍት ገኖ ከሃሳብህ
ጉዳይ የለኝም ከአንተ የሚያጎድለኝ
ቁም ነገሬ ነህ ሌላ ምን አለኝ
share♻️share♻️share♻️
ድንቅ ዝማሬዎችን ከፈለጉ
ይህን link⬇️ተጭነው ይቀላቀሉ

🎼🎼  𝙟𝙤𝙞𝙣 & 𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚  🎼🎼
@Protestantmezemur
@Protestantmezemur
─── ❖ ──  ✦ ── ❖ ───


"ሳሙኤልን እንካ"
ዘማሪት አስቴር አበበ

በፊትህ እስክጥለው የኔ ነበረ በትሩ
ፈቃዴን ማድረጊያ ያልታየኝ አቅሙ
ከምርኩዝ የማያልፍ የማይዘል ከማገጃ
በእጄ የከረመ ድጋፍ መወጣጫ
ያን እለት ገብቶኛል ትኩረቴን ስትስበው
በሚነድ ቁጥቋጦ እግሬን ስታፈጥነው የሰጠኝን መልሼ በጥል ከእግሮችህ ስር
እንደ ምሰራበት ባንተው እጅ እንዲያምር አውቂያለሁኝ

እንካ ጊዜዬን ተጠቀምበት
በልብህ እንዳለ አከናውንበት
እንካ ያለኝን ወርቅ እና ብር
እኔጋር ሆኖ ጓዳ እንዳይቀር

#1 ) ሁለት አሳና አምስት እንጀራ
ከኔ አያልፍም በሰው ሲሰላ
ለራሴ ነበር ሰንቄ የያዝኩት
ረሀቡ ሲጠና ብጎርሰው ያልኩት
ያንተ ግምት ከኔ ካለፈ
ብዙ ልታጠግብ ከእጄ ወስደህ
እንቢ አልልም ስስት ለቆኛል
ከእኔ ቢወጣ እልፍን ይሸኛል

አስደምሞኛል ተደንቄያለሁ
ጥቂት ነበረ በእጄ ላይ ሳየው
ይለፍ ካንቺ ካልክ አገር ሊያበላ
ይውጣልኝ ከእጄ ይሁን የሌላ
ይለፍ ካንተ/ቺ ካልክ አገር ሊያበላ
ይውጣልኝ ከእጄ ይሁን የሌላ

#2 ) ምን ክፋት አለው ቢያገለግለኝ
አገር ሁሉ ያውቃል እንደሰጠኸኝ
እንደተቀበልኩት በለቅሶ በእንባ
በስለት ክምር ቤቴ እንደገባ
ከሚሆን የራሴ እኔ ጋር ቀርቶ
መልሼ ልስጥህ ልይ ሌላውን በቅቶ
ስስት ሳይዘኝ እንዴ ሳልል
ይኸው አኖርኩት ከእግሮችህ ስር

አሜን ይሁና ሳሙኤልን እንካ
ትርፍም አይኖረኝ እሱን ሚተካ
አይቆይ ካንቺ/ተ ጋር ካልክ አምጪው ለኔ
ለትውልድ ይሁን ይለፈ እኔን

ሽታውን ሳልጠግበው የልጅነቱን
ነግቶልኝ ሳላይ ጨዋታ ሳቁን
ጥቂት ቆይቶ ሳያባብለኝ
እንካ በማለዳ ተቀበለኝ

አሜን ይሁና....
share♻️share♻️share♻️
ድንቅ ዝማሬዎችን ከፈለጉ
ይህን link⬇️ተጭነው ይቀላቀሉ

🎼🎼  𝙟𝙤𝙞𝙣 & 𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚  🎼🎼
@Protestantmezemur
@Protestantmezemur
─── ❖ ──  ✦ ── ❖ ───


"ኢየሱስ"
ዘማሪት አስቴር አበበ

ላውራው ልዘምረው
ልናገር ልተርከው
ልጥራው ልደጋግመው
ልመርኮዝ ልደገፈው

ስሙ ከፊደል ያለፈ ነው
ስሙ ከአንድ ቃል ያለፈ ነው
ስሙ ከስሞች ያለፈ ነው
ስሙ ከምለው ያለፈ ነው

ስምህን ስጠራው ጥሜ ይረካልኛል
ስምህን ስጠራው ከረሃቤ እጠግባለሁኝ
ስምህን ስጠራው ጥሜ ይረካልኛል
ስምህን ስጠራው ከረሃቤ እጠግባለሁኝ
ለዚህ ነው ሲነጋ ኢየሱስ የምለው
ለዚህ ነው በቀትር ኢየሱስ የምለው
ለዚህ ነው ሲመሽም ኢየሱስ የምለው
ለዚህ ነው በሌሊት ኢየሱስ የምለው

በምን አጎደልከኝ መች ጠናሁ የሰው ደጅ
ከጫፍ ጫፍ ሙላቴ የምትደላ የምትመች
ሰው እንኳን የሚያልፈውን ይሄ አለኝ ይላል
አንድ ሁለት ሶስት ብሎ ለሚያይ ያስቆጥራል
የማታልፍ የማታልቅ የማትደክም ትምክህቴ
የማልቀይርህ መዝሙር እስካለሁ በህይወቴ
ለልጅ ልጅ ትምህርት ርስትም ያለኸኝ
ለሚያዩኝ ሁሉ እዩልኝ የሚያስብለኝ


እዩልኝ እዩልኝ
ደግነቱን እዩልኝ
እዩልኝ እዩልኝ
ምህረቱን እዩልኝ
እዩልኝ እዩልኝ
ደግነቱን እዩልኝ
እዩልኝ እዩልኝ
ምህረቱን እዩልኝ

ከማይደረስበት ከቅድስናው ጥግ በሞቱ አድርሶኝ
ፀድቀሻል አለኝ እዩልኝ
ከአለሁበት ሸለቆ ህያው ቃሉን ልኮ ዳግም ሰው አድርጎኝ
አንቺ ብርቱ አለኝ እዩልኝ

እዩልኝ እዩልኝ
ደግነቱን እዩልኝ
እዩልኝ እዩልኝ
ምህረቱን እዩልኝ
እዩልኝ እዩልኝ
ደግነቱን እዩልኝ
እዩልኝ እዩልኝ
ምህረቱን እዩልኝ
share♻️share♻️share♻️
ድንቅ ዝማሬዎችን ከፈለጉ
ይህን link⬇️ተጭነው ይቀላቀሉ

🎼🎼  𝙟𝙤𝙞𝙣 & 𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚  🎼🎼
@Protestantmezemur
@Protestantmezemur
─── ❖ ──  ✦ ── ❖ ───


"ከሙሴ የሚልቅ"
ዘማሪት አስቴር አበበ

በአመፅ ተፀንሶ ኃጢአት ሆና እናቱ ሞት ለሆነ አለሙ
ሲኦል መደምደሚያው እንዲሆን ለታጨ ታይቶህ መባዘኑ
ሩቅ ለነበረ ህዝብ ወደ ግዛት መጥሪያ አቁመህ ምልክት
ከምድር ዳርቻ ጠራህ በፉጨትህ ያላወቀህን ትውልድ
እየተጣደፍን በፍጥነት መጥተናል
ድካም ድንዛዜን ፍርሃት ጨለማን ከኛ ላይ ሰብረሃል
የተናቅነውን ምርጥ የተጣልነውን ቅዱስ ልትለን ያላፈርህ
የጸጋ ሁሉ አምላክ የሆንህ እግዚአብሄር ክቡር ስምህ ይባረክ

ምህረት ለወደደ ለሮጠም አይደለ
መማርን በምታውቅ በአንተ ለኛ ሆነ
ለፍቅርህ ማሳያ ህዝብ ብለህ መረጥከን
ለጥፋት ለሆንን የቁጣ እቃዎች ትዕግስትህ ቻለን

#1 ) የህግ መሰጠት የመቅደስ ስርዓት
ኪዳን ላልነበረን ውብ የተስፋ ቃላት
የጥሉ ግድግዳ ከማዶ ላረገን
ዕውር ለስርአትህ አህዛብ ለተባልን

ላክልን ለነፍሳችን መልህቅ
ሊቀ ካህን ከሙሴ የሚልቅ
ላክልን ለነፍሳችን መልህቅ
ሊቀ ካህን ከአሮን የሚልቅ

#2 ) የህልውናህን ስፍራ እንዳያይ አይናችን
ሆኖን መጋረጃ ከልሎ ሃጥያታችን
ይዞን እንዲገባ ከማዶ እንዳንቀር
ስለ እኛ ቀደመ ገባ በመካከል

ተልኮልን ለነፍሳችን መልህቅ
ሊቀ ካህን ከአሮን የሚልቅ
ላክልን ለነፍሳችን መልህቅ
ሊቀ ካህን ከሙሴ የሚልቅ

#3 ) የእንቅፋት ድንጋይ ማሰናከያ አለት
አኑሮ በፂዮን አምነው እንዲድኑበት
በስብከት ሞኝነት የሚያምኑትን ሊያድን
ቅን ፈቃዱ ሆኖ ጥንት ተወስኖልን

ተልኮልን ለነፍሳችን መልህቅ
ሊቀ ካህን ከአሮን የሚልቅ
ላክልን ለነፍሳችን መልህቅ
ሊቀ ካህን ከሙሴ የሚልቅ

ተልኮልን.....
share♻️share♻️share♻️
ድንቅ ዝማሬዎችን ከፈለጉ
ይህን link⬇️ተጭነው ይቀላቀሉ

🎼🎼  𝙟𝙤𝙞𝙣 & 𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚  🎼🎼
@Protestantmezemur
@Protestantmezemur
─── ❖ ──  ✦ ── ❖ ───


እንኳን ደስ አላችሁ !

ሚሽነሪ ዩኒቨርሲቲ ከዘመኑ ጋር አብሮ የዘመነ የቦታ ርቀት ሳይገድቦት የእጅ ስልኮን  አልያም ኮምፒውተሮን በመጠቀም በኦንላይ በቤቶ ሆነው ትምህርቶን መማር እንዲችሉ እድሉን አመቻችቱዋል። ሙሉ እውቅና ባገኘባቸው የትምህርት ዘርፎች በዲፕሎማ ፣ በመጀመሪያ ዲግሪና በማስተርስ ፕሮግራሞች  በካውንስሊንግ ሳይኮሎጂ፣ በስነ መለኮት፣ በክርስቲያን ሊደርሽፕ፣ በቢዝነስ ማኔጅመንት፣ በፕሮጀክት ማኔጅመንት፣ በሶሻል ወርክና ኮሚኒቲ ደቬሎፕመንት በክርስቲያን አውድ  ፤ ተማሪዎችን  ተቀብለን መመዝገብ መጀመራችንን እንገልጻለን!

ልዩ የሚያደርገን
1. የተቀላጠፈ የ24/7 አገልግሎት መስጠታችን
2. በተመጣጣኝ ክፍያ ማስተማራችን
3. ጥራት ያለው ትምህርት መስጠታችን

📚www.missionaryuniversity.org

አሁኑኑ ይመዝገቡ👉 https://missionaryuniverisityweb.com/my/student/register

ለበለጠ መረጃ @musupport

📞+251960840001

ቴሌግራም ቻናል
👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/+8s0AlnmXwBwzZTNk


"ወደ ተራራ ጫፍ"
ዘማሪት አስቴር አበበ

#1 ) ከህልውናህ ሰፈር ከምትገኝበት
ንግግር ጸሎቴ አንተው ከሆንክበት
ጠንቀቅ ካላልኩኝ ካልጠበቅኩ እግሮቼን
እልፍ የሚለይ ጉዳይ ከቦኛል ዙሪያዬን
በገለባ ናፍቆት በጠፊ ፍለጋ
አይለቅብኝ ቀኔ አርቆኝ ከአንተጋ
ወደ ተራራው ጫፍ ሳበኝ ወደራስህ
ነፍሴም ድና እንድትቀር አቅልጣት በክብርህ

መባዘን አይደለም መዋል ከአንተ ጋራ
ስለ ላዩ ምክርህ ነፍሴን ስታዋራ
ሰብሰብ ብሎዋል ቀኔ አልተዝረከረከም
የማይወሰድ እድል ከዚህ በላይ የለም

#2 ) አንተን ብቻ ይሁን የማይበት አይኔ
ልቤ ሄዶ ይቅር ከላዩ ሰፈሬ
ጆሮዬም ይቀሰር ከላይኛው ሃገር
አጥፋኝ  ከምድሩ ፍለጋዬ ይሰወር
አንገቴን አስግጌ በመናፈቅ ህይወት
ለአፍታ ጎንበስ ሳልል አንዳች ከሌለበት
እጅ ሰጥቶ ለአንተ ውስጥና ውጪዬ
ስንቄ ሆኖ ፍቅርህ ይጠቅለል እድሜዬ

ጥሜ ረሃቤ ናፍቆቴ መሻቴ
ጉጉቴ ፍላጎቴ ሩጫዬ መገስገሴ
አንተን ለማግኘት ነው

በቃ እፈልግሃለሁ በቃ ተርቤሃለሁ
በቃ በጣም ጠምተኸኛል በቃ አይኖቼ ናፍቀውሃል
በቃ ናፍቄሃለሁ በቃ ደጅ ደጅ አያለሁ
በቃ የውስጤ ጥም ነህ በምንም የማልለውጥህ

አንተን የተራበ የሚጠግበው አንተን ነው
አንተን የተጠማ የሚረካው አንተን ነው
ፊትህን የፈለገ ሲያገኝህ ያርፋል
ፈልጎ ክብርህን በእጅህ መች ይረካል
አይደለሁም ሰነፍ ተመከርኩ በቃልህ
የውስጤን ረሃብ አይደፍነውም የእጅህ
ነፍሴን የምታረካ ሙላት ነህ የልቤ
የኑሮዬ ፍሰሃ የዕድሜ ልክ ሃሳቤ
share♻️share♻️share♻️
ድንቅ ዝማሬዎችን ከፈለጉ
ይህን link⬇️ተጭነው ይቀላቀሉ

🎼🎼  𝙟𝙤𝙞𝙣 & 𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚  🎼🎼
@Protestantmezemur
@Protestantmezemur
─── ❖ ──  ✦ ── ❖ ───


"መኖር አልችልም"
ዘማሪት አስቴር አበበ

የኔ ጌታ የኔ ውበት
የኔ ፍቅር የኔ ናፍቆት
የኔ ወዳጅ የኔ ውበት
የኔ ፍቅር የኔ ናፍቆት
መኖር አልችልም ያላንተ (2) እፈራለሁ
ሁሉም ክድንድን ያለ ነው
መኖር አልችልም ያላንተ (2) እፈራለሁ
ሁሉም ጭልምልም ያለ ነው

አሁንም እላለሁ ጥማኝ አሁንም እላለሁ ራበኝ
አሁንም እላለሁ ናፍቀኝ
አሁንም እላለሁ ጥማኝ አሁንም እላለሁ ራበኝ
አሁንም እላለሁ ናፍቀኝ በማንነትህ ልክ

#1 ) የረሃቤ ቁመቱ ይላቅ ከከበበኝ
አይስረቅ እይታዬን ዘልቆ ላያዘልቀኝ
ከጎደለኝ ነገር ከምለው ይህ ቀረ
ይሁንልኝ ረሃቤ ለአንተ ያጋደለ

አሁንም እላለሁ...

አንተን ማጣት ነው ብቸኝነት
መጸለይ ማቆም ነው ድርቀት
መንፈስህን መተው ነው ክስረት
ውሎ ማደር አንተ በሌለህበት
ቃልህን መርሳት ነው ጎዶሎነት
ሳይሰሙህ መውጣት ነው ዙረት
ያለ ድምጽህ ማውራት ነው ቅዠት
ውሎ ማደር አንተ በሌለህበት

መኖር አልችልም ያላንተ....

#2 ) አንተን ተከትዬ ቤቴ ወና ይቅር
ከአፈር የሆነው ይቅርብኝ በጅምር
በአንተ ብቻ ልመር ላጊጥ በሃሳብህ
ይልቀቀኝ የምድሩ ሳበኝ በፈቃድህ

አሁንም እላለሁ....

በተጨመረልኝ ዕድሜ በተቀጠሉልኝ ቀናት
ነፍሴን ዝም ጸጥ አሰኝቼ ከጌታ ውጭ ላልሰጣት
ነጥቄአት ከሌላው ጎዳና ትዋል ኮቴህ በሚረግጥበት
ልቤን እንዲህ አስፋልኝ እና ላጊጥ በፈቃድህ ውበት

#3 ) ልመረቅ በእጆችህ ለማዶው ሽልማት
ፍለጋህ እንድከተል ጸጋህን ስጠኝ በብዛት
ትሁን ነፍሴ እንዳልካት ደስታህ ሃይሌ ነው
የሰማዩን ፈቃድህን በምድር ስኖረው

አሁንም እላለሁ....
share♻️share♻️share♻️
ድንቅ ዝማሬዎችን ከፈለጉ
ይህን link⬇️ተጭነው ይቀላቀሉ

🎼🎼  𝙟𝙤𝙞𝙣 & 𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚  🎼🎼
@Protestantmezemur
@Protestantmezemur
─── ❖ ──  ✦ ── ❖ ───


"ብዛልኝ"
ዘማሪት አስቴር አበበ

አንተየሌለህበት
ቦታለምኔ ሃገር ለምኔ ከፍታ ለምኔ አንተ የሌለህበት
ህብረት ለምኔ መዝሙር ለምኔ ወሬ ለምኔ አንተ የሌለህበት
ቦታ ለምኔሃገር ለምኔ ከፍታ ለምኔ አንተ የሌለህበት
ህብረት ለምኔ መዝሙር ለምኔ ወሬ ለምኔ

አስጠጋኝ ወደ ዕቅድህ
ወዳየህልኝ ወደ ሃሳብህ
ኧረ አስጠጋኝ ወደ እቅድህ
ወዳየህልኝ ወደሃሳብህ
የእግሮቼን ጉዞ መትርልኝ
የአንደበቴን ቃል ስፈርልኝ
ለፈቃዴ ገደብን አብጅለት
ሞገደኛው ልቤ ይወቅ ለከት
አስተምረኝ ምን ትላለህ ማለት
የእግሮቼን ጉዞ መትርልኝ
የአንደበቴን ቃል ስፈርልኝ
ለፈቃዴ ገደብን አብጅለት
ሞገደኛው ልቤ ይወቅ ለከት
አስተምረኝ ምን ትላለህ ማለት

አይኖቼ እያዩ ቅጥቅጧን ሸንበቆ ደግፈህ ስታቆመኝ
እያወቀ ልቤ የምጤሰውን ጧፍ ቀርበህ ስታበራኝ
ጆሮዬ እየሰማ ለራስ የማልበቃውን ስታተርፈኝ ለሃገር
በቀረልኝ እድሜ ከአንተ ሌላ ውጪ አፌ ምን ይናገር
አሁንም ብዛልኝ እንዲረዝም እድሜዬ
አብልጬ ልጠጋህ እንዲደምቅ ማታዬ
ሁነኝ መዋያዬ በቀረልኝ ዘመን
መንገዴ እየነጋ እስኪሆን ሙሉቀን

ውሎ ከአንተ ጋራ አድሮና ሰንብቶ
ማን በትናንት ቀረ ከአንተ ብዙ ቀድቶ የለውጥ ጅማሬ ነህ የህይወት ማጣፈጫ
የተጠጉህ ሁሉ ወጥተዋል በብልጫ

ሰሞነኛ እንዳልሆን አድሮ እንዳልሰለች
ጉልበቴን ላስጠጋ ወደ ቃሎችህ ደጅ
ዘመንን ዘላቂ እንዲሆን ነገሬ
ዙረቴን አቁሜ ልፈልግህ ዛሬ

share♻️share♻️share♻️
ድንቅ ዝማሬዎችን ከፈለጉ
ይህን link⬇️ተጭነው ይቀላቀሉ

🎼🎼  𝙟𝙤𝙞𝙣 & 𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚  🎼🎼
@Protestantmezemur
@Protestantmezemur
─── ❖ ──  ✦ ── ❖ ───


"እረዳሻለው"
ዘማሪት አስቴር አበበ

ውጪ ብሎ አስወጥቶኝ ከኖርኩበት ቀዬ ሰፈር
ሊሰራብኝ ገንዘብ ሊያደርገኝ ለእርሱ ስራ ለእርሱ  ክብር
ከዳር ማድረስ ሳይችል ቀርቶ ጥሎኝ አይሄድ በበረሃ
ያመንኩትን አውቀዋለው አይቼዋለሁኝ ትላንትና

አይቼዋለሁኝ ትናንትና አይቼዋለሁኝ ትናንትና
ለነገም አመንኩት ልቤ በእርሱ ፀና
አይቼዋለሁኝ ትናንትና አይቼዋለሁኝ ትናንትና
ለነገም አመንኩት ልቤ በእርሱ ፀና
ልቤ እርሱ ጋር ፀና
ልቤ እርሱ ጋር ፀና
ትናንት ሲደግፈኝ አይቻለሁና
ልቤ እርሱ ጋር ፀና

ያለኝ እውነት ሆኖ እያለ
መልካምነቱንም ፍጥረት እያወቀ
እንደተረሳሁ እንደተወኝ
እንደማያየኝ እንደጣለኝ
ያ ክፉ ጠላቴ ብዙ ብዙ ዋሽቶኛል
እውነታውን ግን ቃሉ ነግሮኛል

እረዳሻለው አግዝሻለው
በጸናች ክንዴ ደግፍሻለው
ልብሽ ቤቴ ነው የኔ የአንቺ ነው
ለአንቺ ያለኝ ፍቅር ጥልቅ ነው
ሁኔታ የሚለው ሌላ ሌላ ነው
ቃሉ ያለኝ ግን አይዞሽ ነው
ሁኔታ የሚለው ሌላ ሌላ ነው
ቃሉ ያለኝ ግን በርቺ ነው

እረዳሻለው....
ጠላቴ ያለው ሁሉ ውሸት ነው
ጌታ ያለኝ ግን እውነት ነው
ጠላቴ ያለው ሁሉ ውሸት ነው
ቃሉ ያለኝ ግን እውነት ነው
እቀጥላለው ገና ሄዳለው
እጁ ይዞኛል ምን እሆናለው

ብዙ ብዙ መልካም ነገር ብዙ ብዙ በጎ ነገር
ብዙ ብዙ ጥሩ ነገር ትላንቴ ላይ አድርጎልኛል
ብዙ ብዙ መልካም ነገር ብዙ ብዙ በጎ ነገር
ብዙ ብዙ ጥሩ ነገር ትላንቴ ላይ አድርጎልኛል

አመሰግነዋለው (8)

ቅኔዬ አልሻገተ ትውልድ አላለፈው
ገና በልጅነት በልቤ ያኖረው
ከአፉ በወጣው ቃል የተጻፈ ነገር
እርጅና አያውቀው ይህ ሰማይ ይናገር

አይቼዋለሁኝ...

ድንቅ ዝማሬዎችን ከፈለጉ
ይህን link⬇️ተጭነው ይቀላቀሉ

🎼🎼  𝙟𝙤𝙞𝙣 & 𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚  🎼🎼
@Protestantmezemur
@Protestantmezemur
─── ❖ ──  ✦ ── ❖ ───


"አመልክሃለው"
ዘማሪት አስቴር ከበበ

እረሳሁት ጥያቄዬን
የከበበኝን በዙሪያዬ
ስቀርብ ፊትህ ለማመስገን
ቀሎ ታየኝ ሁሉም ነገር (2)

ሳላመልክህ ጊዜው አይለፍ
የሚገባህን ምስጋና ሳላቀርብ
ሞልቶ ላይሞላ የምድሩ ነገር
ካልክልኝ አልጎድልም ለጭንቅ ውሎ ማደር ርቋል ከኔ ሰፈር (2)

አመልክሃለው (3)
በማደሪያዎችህ መካከል ቆሜ

ለተራራው ቁመት እያልኩኝ ትልቅ ነህ ለሸለቆው ጥልቀት እያልኩኝ ሙላት ነህ ለሞገዱ ብርታት እያልኩኝ ሰላም ነህ ለጨለማው ርዝመት እያልኩኝ ብርሃን ነህ

አመልክሃለው (3)
በማደሪያዎችህ መካከል ቆሜ

ብዙ ጊዜ ታገልኩ ከቃላቶች ጋራ
ስላንተ ማንነት በዝርዝር ላወራ
አንሰው ተገኙብኝ ያለኝ ሁሉ አላረካኝ
እንደገባኝ መጠን እንኳን ልገልጽህ አቃተኝ (2)

ማንንም እንደሚልህአይደለህም ከመታወቅ ታልፋለህ እግዚአብሔርትልቅ(2)

ትልቅነህ (2) እግዚአብሔር ትልቅ ነህ(4)

ካነበብኩት አይደል ከሰው የሰማሁት
ዛሬ በዚህ ሰዓት ፊትህ ያመጣሁት
ከነፍሴ ምስጋና ከውስጠቷ የሆነ
አፌን ምልቶ የሚፈስ አዲስ ቅኔ አለ (2)

ያላነሰ ያላጠረ
ከላይ ከላይ ያልሆነ
ለእኔፍቅር ለኢየሱሴ አለኝ ምስጋና ከነፍሴ(2)

አለኝ ምስጋና
share♻️share♻️share♻️
ድንቅ ዝማሬዎችን ከፈለጉ
ይህን link⬇️ተጭነው ይቀላቀሉ

🎼🎼  𝙟𝙤𝙞𝙣 & 𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚  🎼🎼
@Protestantmezemur
@Protestantmezemur
─── ❖ ──  ✦ ── ❖ ───


"ፍለጋው አ'ረገኝ"
ዘማሪት አስቴር አበበ

እንደገናን ባያውቅ ዳግም ዕድል ባይሰጥ
ማን ይችል ነበረ የጌታ ደጅ ሊረግጥ
እየተደገፈ በማይሰፈር ፀጋው
እንደኔ የቆመ ስንቱን ቤት ይቁጠረው
ስንቱን ቤት ይቁጠረው

ደጋግሞ የተፈተነ እምነቴ
እንዳይንኮታኮት አልቆለት እንዳይወድቅ
እንደስንዴ ሊያበጥረኝ የወጣውን ፈታኝ በ "አይቻልም" ሲሰድ

የአንደበቴን ሳይሆን ያወቀ የልቤን
እንደተመኘሁት ልሆን ያለመቻሌን
እስኪቆሙ እግሮቼ በብዙ አገዘኝ
ሃይልን እስክቀበል አይዞሽ በርቺ እያለኝ
ያለቀልኝ መስሎት ለሳቀብኝ ጠላት
ማልዶ ማለደልኝ ጉልበቴን አጸናት

ክህደት መሃላዬን አላውቀውም ማለቴን
ዶሮ ሶስቴ እስኪጮህ አልፎ መጨመሬን
ከትንሳኤው ማግስት ብርቱዎች እያሉ
ከሰነፎች ተርታ እንደኔ ያልዋሉ
ፍልጋው አ'ረገኝ መጣ ወዳለሁበት
ሊቀጥለኝ ዳግም ከተቆረጥኩበት

በማይጠቅሙት መጠቀም ልማዱ ለሆነው
በማለዳ ምስጋናዬ ይኸው
ለተቤዠኝ 
ሳላቋርጥ

በትንሿ አዕምሮዬ ስላሰብኩት ነገር
ብዕሬን ይዣለው ቃላትን ቀምሬ በዜማ ልናገር
አልችልም ልደብቅ የውስጥ ደስታዬን
እሱ በኔ ሆኖ ነውሬን አስወግዶ ከሰው መቆጠሬን
ዝም ይባላል እንዴ ደግሞስ ያስችላል ወይ
አትረፍርፎ አድርጎልኝ ረድኤቱን ከላይ
የቃላትን ድንበር ጥሶ ያለፈ መውደድ
አንድ ልጁን ሰጥቶ የራሱ የሚያደርግ

አጽናንቶኛል ባድማ ህይወቴን በመልካምነቱ ሞልቶ
አስደሰተኝ በረሃ ህይወቴን እንደ ኤደን አድርጎ
ተድላ አደለኝ የደስታ የቅኔ ድምጽ ወጣ ከቤቴ
መራቄ ቀርቶ ቀርቤአለሁ አብ ሆኖኝ አባቴ

share♻️share♻️share♻️
ድንቅ ዝማሬዎችን ከፈለጉ
ይህን link⬇️ተጭነው ይቀላቀሉ

🎼🎼  𝙟𝙤𝙞𝙣 & 𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚  🎼🎼
@Protestantmezemur
@Protestantmezemur
─── ❖ ──  ✦ ── ❖ ───


"በቃኝ የማልለው"
ዘማሪት አስቴር አበበ

እንደገና ረሃብ እንደገና ጥማት
ትናንት ምንም እንዳላየ
እንደገና ናፍቆት እንደገና ጉጉት
አንተ ወዳለህበት

ጥቂት አንተን ቀምሶ እንደ ጠገበ ሰው
መሆን የጤና አይደለም ረሃቤን ፈውሰው
እለት እለት ባዶ ትሁን እና ነፍሴ
በመገኘትህ ውስጥ ይረስርስ መንፈሴ
እለት እለት ባዶ ትሁን እና ነፍሴ
በመገኘትህ ውስጥ ይረስርስ መንፈሴ

በቃኝ የማልለው ይለፈኝ የማልለው
ሰለቸኝ የማልለው ያንተ ህልውናህ
ደስታዬ ያለበት ያለፈ ሰላሜ
መገኘትህ ነው መዋያ ማደሪያዬ

ናና እስኪ አጠጣኝ
ናና እስኪ አጉርሰኝ
የእጅህን ሳይሆን ክብር መልክህን
የምድሩን ሳይሆን ህልውናህን
ሌላውን ሳይሆን አንተው እራስህን

ናና እስኪ አጠጣኝ
ናና እስኪ አጉርሰኝ
የእጅህን ሳይሆን ክብር መልክህን
የምድሩን ሳይሆን በላይ ያለውን
ሌላውን ሳይሆን አንተው እራስህን

የፊትህን ሳይሆን ፈልጎ የእጅህን
ባትገባም ከቤቴ ላክ ብቻ ቃልህን
የእምነቱን ቁመት አድንቀህ እንዳለፍከው
አንተን በደጅ ትቶ ፈውሱን ብቻ እንዳለው

አይደል መገስገሴ ፊትህን ማለቴ
ማድጋዬን ልሞላ ላሰማምር ቤቴን
ይሁን ሁሉ እንዳለ ከነ ዝብርቅርቁ
ከአንተ ካልከተመኝ ካቆመኝ በሩቁ
ሳበኝ በእጆችህ ወደ ክብርህ ጥልቅ
አስገባኝ ከእልፍኝህ ጅምሩም ባያልቅ

በቃኝ የማልለው ይለፈኝ የማልለው
ሰለቸኝ የማልለው ያንተ ህልውናህ
ደስታዬ ያለበት ያለፈ ሰላሜ
መገኘትህ ነው መዋያ ማደሪያዬ

share♻️share♻️share♻️
ድንቅ ዝማሬዎችን ከፈለጉ
ይህን link⬇️ተጭነው ይቀላቀሉ

🎼🎼  𝙟𝙤𝙞𝙣 & 𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚  🎼🎼
@Protestantmezemur
@Protestantmezemur
─── ❖ ──  ✦ ── ❖ ───


"ሀሌሉያ"
ዘማሪት አስቴር አበበ

በሰላሙ ብዛት ቀለለ ችግሩ
አደገ ቁመቴ እያለ ነገሩ
ቀረ መዋከቤ በጠራኸኝ ሳርፍ
ተምራልኝ ነፍሴ አንተ ላይ ማራገፍ
ድምጿ ቀየረ ተለወጠ ቃሏ
እዬዬን በእሰየው ያንተ በመሆኗ
እህህን በእልልታ ለምኑን በአሜን
ለለወጥከው ኢየሱስ እንካ ዘለዓለሜን

ተባረክ እልሃለው (*8)

ተንበርክኬ አሸነፍኩኝ
እጅ ሰጥቼ ድል ነሳሁኝ
በጩኸቴ መዳን ሆነ
አበሳዬ ተከደነ
          ተከትዬ ከፊት ቀደምኩ
          ያንተን ብዬ ከምን ጎደልኩ
            ስፈልግህ ፀኑ እግሮቼ
            ሀይሌ ሆነኝ ተሙዋጋቼ
በመጨነቅ ስርዓትን
በመማፀን መጓደድ
በር በመዝጋት ክፉን ማምለጥ
እርዳኝ ብዬ ሁሉን መብለጥ
ካንተ ሰምቶ የውስጥ ውበት
አቤት ብዬ አለኝ ማለት
ካንተ  ዘግኖ ሞልቶ ማደር
ሆኖልኛል ስምህ ይክበር

ስኬቴ ባንተ መታመኔ
ከፍታዬ እግርህ ስር መሆኔ
ውበቴ አንተን መጠጋቴ
ድምቀቴ ምህረትህ ነው ለኔ

አሃ ሀሌሉያ ሀሌሉያ
ሀሌሉያ ሀሌሉያ
እላለሁ ሀሌሉያ

በማለዳ ሀሌሉያ በቀትርም ሀሌሉያ
በምሽትም ሀሌሉያ በለሊትም ሀሌሉያ
ሁሉ እንዳለ ሆኖ ሀሌሉያ ሳይቀየር ሀሌሉያ
እላለሁ ሀሌሉያ አሃሃ....ሃ ሀሌሉያ
ሀሌሉያ....

share♻️share♻️share♻️
ድንቅ ዝማሬዎችን ከፈለጉ
ይህን link⬇️ተጭነው ይቀላቀሉ

🎼🎼  𝙟𝙤𝙞𝙣 & 𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚  🎼🎼
@Protestantmezemur
@Protestantmezemur
─── ❖ ──  ✦ ── ❖ ───


"ጉዳዬ"
ዘማሪት አስቴር አበበ

ለሚያወራህ ውበት ለሚለብስህ ጌጥ
ሮጦ ለተጠጋህ የማምለጫ አለት
ህይወት ከሞት ወዲያ እርስቱ ላረገህ
ለአፍታ እንኩዋን የማትጎድል ለሰው ሙላቱ ነህ
አንተን ነው እንጂ ጥብቅ አድርጎ መያዝ ያዘኝ እያሉ
ማልዶ በጠዋት በአንተው እጅ ደምቆ መዋል ደጅ እየጠኑ
አንተን ነው እንጂ ጥብቅ አድርጎ መያዝ ያዘኝ እያሉ
ማልዶ በጠዋት በአንተው እጅ ነቅቶ መዋል ደጅ እየጠኑ

አይኔን ጉዳዬ ላይ ማድረግ
ፍለጋዬን እድሜ ልክ መፈለግ
ናፍቆቴን ሳላርፍ መናፈቅ
ጉጉቴን ሳልደክም መፈለግ
እንዲሆንልኝ ይብዛልኝ ጸጋህ
ጊዜው ደርሶ እስክደርስ አንተ ጋ
ገባ ወጣ እግሬ ሳይልብኝ
ፍለጋዬ ሳትጎድል ብዛልኝ

በድነቴ ጠዋት በገባኸኝ ማግስት
ጨዋታ ወሬዬ መወደዴን ማድነቅ
ዘምሬህ አልጠግብ አውርቼህ አልረካ
ይቺህ ትንሽ ልቤ ለፍቅርህ ሸፍታ

አልደግ አንተላይ እራሴን አልቻል
አጓጉል ነው ሁሉም ያላንተ መች ያምራል
መጠበቂያ አጥሬ መሰንበቻዬ ነህ
ልኑር እንደፈዘዝኩ አይኔ አንተን እያለ

ጉዳዬ አንተው ነህ
መናፈቄ መምጣትህን
ጉጉቴ አይኔ እስከሚያይህ

ሁሌ ሁሌ ሁሌ ሁሌ አንተን ብቻ
እስከ እድሜዬ መቋጫ
ሁሌ ሁሌ ሁሌ ኢየሱስን ብቻ
እስከ ዕድሜዬ መቋጫ

share♻️share♻️share♻️
ድንቅ ዝማሬዎችን ከፈለጉ
ይህን link⬇️ተጭነው ይቀላቀሉ

🎼🎼  𝙟𝙤𝙞𝙣 & 𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚  🎼🎼
@Protestantmezemur
@Protestantmezemur
─── ❖ ──  ✦ ── ❖ ───


"ፈራ ፍርሃቴ"
ዘማሪት አስቴር አበበ

ደረበልኝ በላይ አለበሰኝ ጸጋ
እንዲሆነኝ አቅም እስክደርስ እሱ ጋ
በአቅመኞች ጉልበት በብርቱዎች ማደም
ማትገፈፍ ልብሴ ለኔ እንዳንተ የለም

1-   በህብሮች ቀለም በተንቆጠቆጠች
      ከወንድሞች መሃል ለዮሴፍ ለተባለች
      ቢውልባት ደምቆ ለብሶ ቢያምርበት
      ቢያሳብቅ ሞገሱ አይንህ እንዳረፈበት
      ዛቻ ሲጠብቀው መልካም እያሰበ
      እንጀራ አቀብሎ ጉድጓድ ለተቸረ
      ለሰው ሃገር ሰዉ ጠብቀህ ዘመንን
      በአንተው እጅ ለበሰ የማይገፈፈውን

2-  የንጉስ ልብ ከፍቶ ጦርን ሲወረውር
     የተቀባው ቅባት ሲያስነሳ ስደትን
     በእባብ ጊንጥ መኖሪያ በአዶላም ዋሻ
     ስንቱን አስጀገነ ሆነኸው ድል መንሻ
     መጠጊያ ለሌለው ማስገቢያ ለአንገቱ
     ስንቱ ተማምኖብህ ተረፈ ለስንቱ
     ሸለቆው ጠገበ በጠልህ ረስርሶ
     ቀን እስኪወጣለት አንተን ተንተርሶ


ፈራ ፍርሃቴ ቃልህን ስትናገር
ሸሸ ጨለማዬ ነጋ በኔ መንደር
ጥንካሬ አገኘኝ ፊትህን በማየት
ደመቀ ህይወቴ ከአንተ በመቆየት(2)

ከላይ ከውሽንፍር ጥላ ከሃሩሩ
የጸናልኝ ቤቴ መርከብ በማዕበሉ
የማይደፈር አጥር ለጎመጀኝ አውሬ
ትልቁን ወግድ ባይ የማይነቀነቅ በሬ (2)
አዎ ስምህ ነው አዎ (4)

ምን ይሆናል ለጸጋው ታልፎ የተሰጠ
መንገድ ጎዳናውን ለእግዚአብሔር ይኸውልህ ያለ
ያየህለት እንጂ የሚያልፍ የሚያገድመው አያገኘው
ቃሉ እንዳለ እንደተጻፈለት ነው የሚኖረው
አዎ ስምህ ነው አዎ(4)

share♻️share♻️share♻️
ድንቅ ዝማሬዎችን ከፈለጉ
ይህን link⬇️ተጭነው ይቀላቀሉ

🎼🎼  𝙟𝙤𝙞𝙣 & 𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚  🎼🎼
@Protestantmezemur
@Protestantmezemur
─── ❖ ──  ✦ ── ❖ ───

2k 0 34 1 22

``ደህና ነኝ´´
ዘማሪት ቃልኪዳን ጥላሁን ሊሊ

የሕይወቴን መጸሃፍ የጻፈው እግዚአብሔር
ደራሲው እርሱ ነው ተራኪዋ እኔ ነኝ (2x)
የመጨረሻውን ምዕራፉን ሳነበው
ደህና ነሽ በሎኛል ደህና ነኝ እላለው (2x)

አዝ፦ ደህና ደህና ነኝ እግዚአብሔር ይመስገን (5x)
ደህና ደህና ነኝ እግዚአብሔር ይመስገን (5x)

ሳለ መድሃኒያለም በዙፋኑ ላይ
በቀኝም በግራም ሠላም አይደል ወይ (2x)
እግዚአብሔር ይመስገን እፎይ ብያለሁ
በአገሪቱ ላይ ተዘ. (1) . (2x)

አዝ፦ ደህና ደህና ነኝ እግዚአብሔር ይመስገን (5x)
ደህና ደህና ነኝ እግዚአብሔር ይመስገን (5x)

እግዚአብሔር አምላኬ ደህንነት ሆነልኝ
እግዚአብሔር አምላኬ እፎይታ ሆነልኝ
እግዚአብሔር አምላኬ ጸጥታ ሆነልኝ
እግዚአብሔር አምላኬ ሠላሜ ሆነልኝ

አዝ፦ ደህና ደህና ነኝ እግዚአብሔር ይመስገን (5x)
ደህና ደህና ነኝ እግዚአብሔር ይመስገን (5x)

ምሥጋና የሚገባው አምልኮ የሚገባው
ዝማሬ የሚገባው እግዚአብሔር አምላኬ ነው (2x)

አምልኮ የሚገባው እግዚአብሔር አምላኬ ነው
መምስገን የሚገባው እግዚአብሔር አምላኬ ነው
መወደድ የሚገባው እግዚአብሔር አምላኬ ነው
መከብር የሚገባው እግዚአብሔር አምላኬ ነው

እግዚአብሔር አምላኬ ነው (4x)

share♻️share♻️share♻️
ድንቅ ዝማሬዎችን ከፈለጉ
ይህን link⬇️ተጭነው ይቀላቀሉ

🎼🎼  𝙟𝙤𝙞𝙣 & 𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚  🎼🎼
@Protestantmezemur
@Protestantmezemur
─── ❖ ──  ✦ ── ❖ ───


ዛሬ 2 ነገሮችን እንድታደርጉ እጠይቃቹሃለው

1,ቻናሉን #UNMUTE ካደረጋቹት እንዳላቹሁም ስለማይቆጠር❎
እዚው ቻናል ላይ እንዳሉ ከታች ልክ
#MUTE የሚል ካለ ምንም አትንኩት
 ግን    
#UNMUTE❗️ የሚል ካለ  አንድ ጊዜ ብቻ በመጫን  MUTE ✅ ላይ በማድረግ  ለቻናላችን ያላቹሁን ድጋፍ ያሳዩ🙏

2, share react እንድታደርጉ ነው።
ከዚህ በዋላ በርካታ አለበሞችን ጨምሮ ዝማሬዎችን ከነ ግጥማቸው እናደርሳቹሃለን። ስለዚህ ሌሎች ጋርም እንዲደርስ share ማድረግ አትርሱ እንዲሁም react በማድረግ አበረታቱን።

ተባረኩ❤️


የዘማሪት አስቴር አበበ "ሀሌሉያ" የተሰኘውን ድንቅ የመዝሙር አልበም💽 ከነ ሙሉ ግጥም(lyrics) እሁድ ከቸርች መልስ (7:00) እናደርሳቹሃለን።

ይህን መልዕክት ለወዳጆ share በማድረግ በዝማሬው እንዲባረኩ ይጋብዙ🎁።
 ❤️ react ማድረግ አትርሱ      
     💐ተባረኩ💐
        🪅መልካም ቀን
🪅
       🎼 𝙟𝙤𝙞𝙣👇 𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚  🎼
     @Protestantmezemur
     @Protestantmezemur
  ❖ ─────  ✦ ───── ❖


እንኳን ደስ አላችሁ !

ሚሽነሪ ዩኒቨርሲቲ ከዘመኑ ጋር አብሮ የዘመነ የቦታ ርቀት ሳይገድቦት የእጅ ስልኮን  አልያም ኮምፒውተሮን በመጠቀም በኦንላይ በቤቶ ሆነው ትምህርቶን መማር እንዲችሉ እድሉን አመቻችቱዋል። ሙሉ እውቅና ባገኘባቸው የትምህርት ዘርፎች በዲፕሎማ ፣ በመጀመሪያ ዲግሪና በማስተርስ ፕሮግራሞች  በካውንስሊንግ ሳይኮሎጂ፣ በስነ መለኮት፣ በክርስቲያን ሊደርሽፕ፣ በቢዝነስ ማኔጅመንት፣ በፕሮጀክት ማኔጅመንት፣ በሶሻል ወርክና ኮሚኒቲ ደቬሎፕመንት በክርስቲያን አውድ  ፤ ተማሪዎችን  ተቀብለን መመዝገብ መጀመራችንን እንገልጻለን!

ልዩ የሚያደርገን
1. የተቀላጠፈ የ24/7 አገልግሎት መስጠታችን
2. በተመጣጣኝ ክፍያ ማስተማራችን
3. ጥራት ያለው ትምህርት መስጠታችን

📚www.missionaryuniversity.org

አሁኑኑ ይመዝገቡ👉 https://missionaryuniverisityweb.com/my/student/register

ለበለጠ መረጃ @musupport

📞+251960840001

ቴሌግራም ቻናል
👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/+8s0AlnmXwBwzZTNk

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.