Remedial HUB


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: Ta’lim


👩‍🏫በ2017 ሬሚዲያል(ማካካሻ) ትምህርት ለሚወስዱ ተማሪዎች ተበሎ የተከፈተ ቻናል!

Buy ads: https://telega.io/c/Remedial_Hub

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Statistika
Postlar filtri


#DebreTaborUniversity

በ2017 ዓ.ም ለአቅም ማሻሻያ ትምህርት (Remedial Program) ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ቀናት ጥር 29 እና 30/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➫ የ8-12ኛ ክፍል የትምህርት ማስረጃዎች ዋናውና ኮፒው፣
➫ 3×4 የሆነ አራት ጉርድ ፎቶግራፍ፣
➫ ብርድ ልብስ፣ አንሶላ የትራስ ልብስ፡፡

@Remedial_Hub

3.2k 0 13 10 17

#AksumUniversity

በ2017 ዓ.ም ለአቅም ማሻሻያ ትምህርት (Remedial Program) አክሱም ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ቀናት ጥር 15 እና 16/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

የምዝገባ ቦታ፦
በዩኒቨርሲቲው ዋና ግቢ፣ አክሱም ከተማ

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➫ የ8ኛ ክፍል ፈተና የወሰዳችሁበት ማስረጃ ዋናውና ኮፒው፣
➫ የ12ኛ ክፍል ፈተና የወሰዳችሁበት ማስረጃ ዋናውና ኮፒው፣
➫ የ2ኛ ደረጃ የትምህርት ማስረጃዎች ዋናውና ኮፒው፣
➫ 3×4 የሆነ ስድስት ጉርድ ፎቶግራፍ፣
➫ የመኝታ አልባሳት እና የስፖርት ትጥቅ፣
➫ ማንነታቸሁ የሚገልፅ የታደሰ መታወቂያ፡፡

@Remedial_Hub

4.8k 0 17 10 20

ለአዲስ ተማሪዎች ምዝገባ እንደቀጠለ ነው!🥰

💥በጥርጣሬ ጊዜ ሳንገድል ከሚፈጠረው ጭንቀት ዛሬውን በመመዝገብ የRemedial HUB ቤተሰብ ይሁኑ🤝


❓ስለትምህርት አሰጣጡና የክፍያ ሂደቱ መረጃ ለማግኘት ይህን ሊንክ በመንካት ይመልከቱ! 😊👇

https://t.me/Remedial_Hub/804

📌ለመመዝገብ ይህንን ይጠቀሙ 👇 @RemedialHubBot


⭕️ Announcement  😊

የሁለተኛ ዙር ምዝገባ በዛሬዉ እለት ተጀምሯል!

የRemedial Hub spacial Class የመጀመሪያ ዙር ምዝገባ በይፋ ተጠናቋ! በመጀመሪያዉ ዙር ምዝገባ ብዙዎች ተመዝግበዉ ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ ይገኛሉ።

📮እርሶም ይህንን እድል በመጠቀም የሪሜዲያል ትምህርቶን በጥሩ ዉጤት እንዲጨርሱ ዛሬ ነገ ሳይሉ አሁኑኑ ተመዝግበዉ ትምህርቶን ይጀምሩ።

❓ስለትምህርት አሰጣጡና የክፍያ ሂደቱ መረጃ ለማግኘት ይህን ሊንክ በመንካት ይመልከቱ! 😊👇

https://t.me/Remedial_Hub/804

📌ለመመዝገብ ይህንን ይጠቀሙ 👇 @RemedialHubBot


#AssosaUniversity

በ2017 ዓ.ም አሶሳ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች ወደ ተቋሙ የመግቢያ ጊዜ ጥር 22 እና 23/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

- ከ8-12ኛ ክፍል ሰርፍትኬት እና ትራንስክፕሪት ዋናውና ኮፒው፣
- 3x4 ጉርድ ፎቶግራፍ፣
- አንሶላ፣ ብርድ ልብስ እና ትራስ ልብስ።

@Remedial_Hub


MaddaWalabuUniversity
#የጥሪ_ማስታወቂያ

በ2017 ዓ.ም በመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ለተመደባችሁ የሪሜዲያል (የአቅም ማሻሻያ ፕሮግራም) ተማሪዎች በሙሉ፡፡

መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ በ2017 ዓ.ም የተመደቡ የሪሜዲያል (የአቅም _ ማሻሻያ ፕሮግራም) ተማሪዎችን የሚቀበልበት የመግቢያ ቀን ጥር 19 እና 20/2017 ዓ.ም በመሆኑ በተጠቀሰው ቀናት ብቻ በዩኒቨርሲቲው ዋና ሬጅስትራር በአካል በመገኘት እንድትመዘገቡ ጥሪ እያደረገ ከተጠቀሰው ቀን ቀድሞ ወይም ዘግይቶ የሚመጣን ተማሪ ዩኒቨርሲቲው የማያስተናግድ መሆኑን አሳውቋል፡፡

@Remedial_hub


#RayaUniversity

በ2017 ዓ.ም ራያ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ የአቅም ማሻሻያ ትምህርት (Remedial Program) ተማሪዎች የምዝገባ ቀናት ጥር 15 እና 16 /2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሔዱ ከ8ኛ-12ኛ ክፍል ሰርቲፊኬት እና ትራንስክሪፕት ከማይመለስ ኮፒ ጋር እንዲሁም ብርድ ልብስ፣ አንሶላ እና ትራስ ልብስ መያዝ ይኖርናችኋል ተብሏል፡፡

@Remedial_hub


Remedial Hub Is Back.🥰


#HaramayaUniversity #Remedial

በ2017 ዓ.ም. በሀረማያ ዩኒቨርሲቲ በሪሜዲያል ፕሮግራም ለተመደባችሁ ተማሪዎች በሙሉ በ2017 ዓ.ም. ትምህርት ዘመን በሪሜዲያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን በሀረማያ ዩኒቨርሲቲ እንድትከታተሉ የተመደባችሁ ተማሪዎች በጥር 02፣ 03 እና 04፣ 2017 ዓ.ም. ሀረማያ በሚገኘው የዩኒቨርሲቲው ግቢ በአካል ተተኝታችሁ ሪፖርት እንድታደርጉ ዩንቨርሲቲው ገልጿል።

#ማሳሰቢያ
1ኛ. የህብረተሰብ ሳይንስ ተማሪዎች በቨተርነሪ (Veterinary) ካምፓስ እንዲሁም የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በቴክኖሎጂ (Technology) ካምፓስ ሪፖርት የምታደርጉ መሆኑን እናሳውቃለን።

2ኛ. ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትመጡ የ8ኛ ክፍል ካርድ፣ ከ9ኛ አስከ 12ኛ ትምህርት ያጠናቀቃቸሁበትን ትራንስክሪፕት እና የ12ኛ ከፍል ሰርትፍኬት ዋናውን እና ፎቶ ኮፒ 4 ፓስፖርት መጠን ያላቸው ጉርድ ፎቶ እንዲሁም በማስታወቂያው የተጠቀሱ የግል መጠቀሚያ ቁሳቁሶችን ይዛቹህ እንድትሄዱ ዩንቨርሲቲው ጨምሮ አሳስቧል።

ተማሪዎች የዶርም ምደባችሁን ከዩንቨርሲቲው ዌብሳይት (www.haramaya.edu.et) ላይ በመግባት መለያ ቁጥራችሁን ተጠቅማቹህ መመልከት ትችላላቹህ።

@Remedial_hub


#WachemoUniversity

በ2017 ዓ.ም ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ መደበኛ የሪሚዲያል ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ታህሳስ 21 እና 22/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

በቅጣት ምዝገባ ታህሳስ 23/2017 ዓ.ም የሚከናወን ሲሆን፤ ትምህርት ታህሳስ 23/2017 ዓ.ም ይጀምራል ተብሏል።

በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ በግል የሪሚዲያል ትምህርት ለመማር የተመዘገባችሁ ተማሪዎች ትምህርት ታህሳስ 25/2017 ዓ.ም እንደሚጀምር ተገልጿል።

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➫ የ8ኛ ክፍል ካርድ ዋናውና አንድ ኮፒ፣
➫ ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት፣
➫ ስምንት 3×4 ጉርድ ፎቶግራፍ፣
➫ ትራስ ጨርቅ፣ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ።

የካምፓስ ምደባ፦

► የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ስማችሁ ከ A-G የሚጀምር በዱራሜ ካምፓስ፥ ዱራሜ
► የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ስማችሁ ከ H-Z የሚጀምር በዋናው ግቢ፥ ሆሳዕና
► የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ስማችሁ ከ A-J የሚጀምር በዱራሜ ካምፓስ፥ ዱራሜ
► የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ስማችሁ ከ K-Z የሚጀምር በዋናው ግቢ፥ ሆሳዕና

@tikvahuniversity


#JinkaUniversity

ጂንካ ዩኒቨርሲቲ ለ2017 ዓ.ም ሪሚዲያል ተማሪዎች ጥሪ አላደረገም።

"ዩኒቨርሲቲው ለ2017 ዓ.ም ሪሚዲያል ተማሪዎች ለታህሳስ 11 እና 12/2017 ዓ.ም እንደጠራ" ተደርጎ በማኅበራዊ ሚዲያ የተሰራጨው መረጃ ሐሰት መሆኑን ተቋሙ ገልጿል።

ለጊዜው ምንም አይነት ጥሪ አለመተተላለፉን አውቃችሁ፣ በይፋ ጥሪ እስከሚደረግ ድረስ ተማሪዎች በትዕግስት እንዲጠብቁ ዩኒቨርሲቲው ጠይቋል።

@Remedial_hub


#OdaBultumUniversity

በ2017 ዓ.ም ለሪሚዲያል ፕሮግራም በኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ታህሳስ 7 እና 8/2017 ዓ.ም ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
- የ8ኛ ክፍል ስርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
- የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ዋናውና ኮፒው፣
- ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
- አራት ፓስፖርት መጠን ፎቶግራፍ፣
- አንሶላ፣ ትራስ ጨርቅ፣ ብርድ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ።

የምዝገባ ቦታ፦
ጭሮ ከተማ በሚገኘው የዩኒቨርሲቲው አዲሱ ካምፓስ

@Remedial_hub


#BuleHoraUniversity

በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ሀገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ በ2017 ዓ.ም ለሪሚዲያል ፕሮግራም ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ ተማሪዎች ሪፖርት ማድረጊያ ቀናት ታህሳስ 7 እና 8/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
- ከ8ኛ-12ኛ ክፍል የትምህርት ማስረጃዎች ዋናውና ኮፒው፣
- ስምንት 3X4 ጉርድ ፎቶግራፍ፣
- ትራስ ጨርቅ፣ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ፡፡

@Remedial_hub


#DillaUniversity

በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ሀገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ ለሪሚዲያል ፕሮግራም ውጤት አምጥታችሁ ዲላ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ ተማሪዎች ሪፖርት ማድረጊያ ቀናት ታህሳስ 14 እና 15/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

የምዝገባ ቦታ፦
ኦዳያኣ ግቢ ሬጂስትራር ጽ/ቤት

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
- ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
- የ8ኛ ክፍል ካርድ ዋናውና ኮፒው፣
- አራት 3X4 ጉርድ ፎቶግራፍ፣
- ትራስ ጨርቅ፣ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ፡፡

@Remedial_hub


አክሱም ዩኒቨርሲቲ በ2017 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርት ለመማር ለተመደቡ አዲስ ተማሪዎች አድርጎት የነበረውን ጥሪ አራዝሟል።

ዩኒቨርሲቲው የ2017 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም አዲስ ገቢ ተማሪዎች የመግቢያ ቀናት ታህሳስ 1 እና 2/2017 ዓ.ም ብሎ የነበረ ቢሆንም፤ የመግቢያ ቀናት ላልተወሰነ ጊዜ የተራዘመ መሆኑን አሳውቋል።

@Remedial_hub


#MizanTepiUniversity

በ2017 ዓ.ም ለሪሚዲያል ፕሮግራም ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁና ከዚህ በፊት በተላለፈው የጥሪ ጊዜ በተለያዩ ምክንያቶች መመዝገብ ያልቻላችሁ ተማሪዎች ህዳር 30 እና ታህሳስ 1/2017 ዓ.ም በአካል በመገኘት መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡

የምዝገባ ቦታ፦
- የማኅበራዊ ሳይንስ መስክ ተማሪዎች ሚዛን አማን ከተማ በሚገኘው ዋናው ግቢ፣
- የተፈጥሮ ሳይንስ መስክ ተማሪዎች ቴፒ ከተማ በሚገኘው ቴፒ ግቢ፡፡

ለምዝገባ ስትሐየዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
- የ12ኛ ብሑራዊ ፈተና ውጤት፣
- ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
- ዘጠኝ የቅርብ ጊዜ 3x4 ጉርድ ፎቶግራፍ፣
- ብርድ ልብስ፣ አንሶላ፣ ትራስ ጨርቅ እና የስፖርት ትጥቅ፡፡

@Remedial_hub


መቱ ዩኒቨርሲቲ ለ2017 ዓ.ም ሪሚዲያል ተማሪዎች ጥሪ አላደረገም።

"ዩኒቨርሲቲው ለ2017 ዓ.ም ሪሚዲያል ተማሪዎች ለታህሳስ 7 እና 8/2017 ዓ.ም እንደጠራ" ተደርጎ በማኅበራዊ ሚዲያ የተሰራጨው መረጃ ሐሰት መሆኑን ተቋሙ ገልጿል።

በይፋ ጥሪ እስከሚደረግ ድረስ ተማሪዎች በትዕግስት እንዲጠብቁ ዩኒቨርሲቲው ጠይቋል።

@Remedial_hub


ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በ2017 አዲስ ለተመደቡ የአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም ተማሪዎች ጥሪ አላደረገም።

"በ2017 ዓ.ም ከትምህርት ሚኒስቴር ወደ ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደቡ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ህዳር 30 እና ታህሳስ 1/2017 ዓ.ም እንደሆነ" የሚገልፅ በማኅበራዊ ትስስር ገጾች የሚዘዋወረው መረጃ #ሐሰተኛ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

በ2017 ዓ.ም አዲስ የተመደቡ የሪሚዲያል ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜን ወደፊት የሚያሳውቅ መሆኑን የገለፀው ዩኒቨርሲቲው፤ ጥሪ እስከሚደረግ ተማሪዎች በትዕግስት እንዲጠብቁ ጠይቋል።

@Remedial_hub


በ2017 ዓ.ም በአክሱም ዩኒቨርሲቲ በሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርት ለመማር የተመደባችሁ አዲስ ተማሪዎች የመግቢያ ቀናት ታህሳስ 1 እና 2/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
- የ8ኛ፣ የ10ኛ እና የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
- ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
- የቅርብ ጊዜ አራት ጉርድ ፎቶግራፍ፣
- አንሶላ፣ የትራስ ጨርቅ፣ ብርድ ልብስ፡፡

@Remedial_hub


#ArbaMinchUniversity

በ2017 የትምህርት ዘመን አዲስ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ለተመደባችሁ የአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም ተማሪዎች የመግቢያ ጥሪ ማስታወቂያ

በ2017 የትምህርት ዘመን አዲስ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ለተመደባችሁ የአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም ተማሪዎች ቅበላ ረቡዕ ታህሳስ 2 ቀን 2017 ዓ.ም፣ ምዝገባ ሐሙስና ዓርብ ታህሳስ 3 እና 4 ቀን 2017 ዓ.ም፣ ትምህርት የሚጀመረው ሰኞ ታህሳስ 7 ቀን 2017 ዓ.ም እንዲሆን ተወስኗል፡፡

በዚህ መሠረት የተፈጥሮ ሳይንስ (Natural Science) የአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም ተማሪዎች በአርባ ምንጭ ከተማ በሚገኘው አባያ ካምፓስ፣

የስማችሁ የመጀመሪያ ፊደል ከ A እስከ R የሆናችሁ የማህበራዊ ሳይንስ (Social Science) የአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም ተማሪዎች በአርባ ምንጭ ከተማ በሚገኘው ጫሞ ካምፓስ፣

እንዲሁም የስማችሁ የመጀመሪያ ፊደል ከ S እስከ Z የሆናችሁ የማህበራዊ ሳይንስ (Social Science) የአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም ተማሪዎች በጎፋ ዞን ሳውላ ከተማ በሚገኘው ሳውላ ካምፓስ ሬጅስትራር ማስተባበሪያ ጽ/ቤቶች በአካል እየቀረባችሁ በተጠቀሰው ቀን ሪፖርት እንድታደርጉ፣ ምዝገባ እንድትፈጽሙ እና ትምህርት እንድትጀምሩ እናሳውቃለን፡፡

ማሳሰቢያ፡-
1ኛ) ሁሉም ተማሪዎች ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕትና የ12ኛ ክፍል ሰርተፍኬት ኦርጂናልና የማይመለስ ሁለት ኮፒ እንዲሁም አንሶላ፣ የትራስ ጨርቅ እና የስፖርት ትጥቅ በመያዝ መምጣት ይጠበቅባቸዋል፡፡

2ኛ) ከተጠቀሰው ቀን ቀድሞም ሆነ ዘግይቶ የሚመጣ ተማሪን ዩኒቨርሲቲው አያስተናግድም፡፡፡

[የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሬጂስትራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት]

@Remedial_hub

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.