ሰማያዊ አመለካከትባለፈው ፖስቴ፣
“የታደሰ አእምሮ” በሚል ርእስ ስር ትምህርት እንደምጀምር በመግለጽ መግቢያውን ሰጥቻችኋለሁ፡፡ ባለፈው የሰጠኋችሁ note በ pdf በመሆኑ እንዳስቸገራችሁ ብዙዎቻችሁ በገለጸችሁት መሰረት ጽሑፉን ብቻ አሰፍራለችኋለሁ፡፡
የዚህን ትምህርት የመጀመሪያ ክፍል፣ “ሰማያዊ አመለካከት” የተሰኘ ሲሆን፣ በዚህ ክፍል የምንመለከታቸው አምስቱ ሃሳቦች የሚከተሉት ናቸው፡፡
“ከላይ የሚመጣው ከሁሉ በላይ ነው፤ ከምድር የሚሆነው የምድር ነው የምድሩንም ይናገራል። ከሰማይ የሚመጣው ከሁሉ በላይ ነው” (ዮሐ. 3፡31)፡፡
አንድ ሰው በምድራዊው ሃሳብና አመለካከት ብቻ ሲጠመድ የሚናገረውም ሆነ የሚተገብረው ምድራዊውን ነው፤ ፍሬውም እንዲሁ፡፡
ሰማያዊው አመለካከት ሁል ጊዜ ከምድራዊው እንደላቀ ይኖራል፡፡ ራሱ እግዚአብሔር እንዲህ ብሎናል፡- “ሰማይ ከምድር ከፍ እንደሚል፥ እንዲሁ መንገዴ ከመንገዳችሁ አሳቤም ከአሳባችሁ ከፍ ያለነው” (ኢሳ. 55፡9)፡፡
“ከሰማያዊው ጥሪ ተካፋዮች” (ዕብ. 3፡1) ሆነን ሳለን በምድራዊው አሳብ ተይዘንን እንዳንቀር የታደሰ አእምሮ ያስፈልገናል፡፡
በምድር ካለው ተራ ነገር ለመውጣት ደግሞ የላቀውን ሰማያዊ አመለካከት ማዳበር የግድ ነው፡፡ የታደሰ አመለካከት የሚጀምረው ምድራዊውን ሃሳብ በመጸየፍና ሰማያዊውን ሃሳብ በማስተናገድ ነው፡፡
ይህንን ለማድረግ ደግሞ ቃሉ በዚህ ጉዳይ ላይ ምን እንደሚል ጠለቅ ብለን መመልከት ይገባናል፡፡
የዚህ ክፍል አላማ አንድ አማኝ ስለ ሰማያዊ አመለካከት ሊያውቃቸው የሚገባውን መሰረታዊ እውነታዎች መግለጽ ነው፡፡ በዚህ ክፍል ውስጥ የምናጠናቸው
አምስት ዋና ዋና እውነታዎች የሚከተሉት ናቸው፡-1. ሰማያዊ የአስተሳሰብ ዘይቤ“በላይ ያለውን አስቡ እንጂ በምድር ያለውን አይደለም” (ቆላ 3፡1)፡፡
2. ሰማያዊ የንግግር ዘይቤ“መንፈሳዊውን ነገር ከመንፈሳዊው ነገር ጋር አስተያይተን መንፈስ በሚያስተምረን ቃል ይህን ደግሞ እንናገራለን” (1ቆሮ. 2፡13)፡፡
3. ሰማያዊ የሕይወት ዘይቤ“ከእንግዲህ ወዲህ በሥጋ ልትኖሩ በቀረላችሁ ዘመን እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ እንጂ እንደ ሰው ምኞት እንዳትኖሩ” (1ጴጥ. 4፡1)፡፡
4. ሰማያዊ የውጊያ ዘይቤ“በሰው ልማድ ምንም እንኳ የምንመላለስ ብንሆን፥ እንደ ሰው ልማድ አንዋጋም” (2ቆሮ. 10፡3)፡፡
5. ሰማያዊ የጥበብ ዘይቤ“ላይኛይቱ ጥበብ ግን በመጀመሪያ ንጽሕት ናት፥ በኋላም ታራቂ፥ ገር፥ እሺ ባይ ምሕረትና በጎ ፍሬ የሞላባት፥ ጥርጥርና ግብዝነት የሌለባት ናት” (ያዕ. 3፡17)፡፡
የመጀመሪያውን ሃሳብ (ሰማያዊ የአስተሳሰብ ዘይቤ) ነገ ጠዋት ጠብቁ፡፡
የጌታን በረከት ተመኘሁላችሁ!
@revealjesus