ስሜትን በግጥም dan repost
...እየጠበኩት...እየጠበቀኝ...እያረፈደ...እየቸኮልኩኝ ብዙ ተጠባበቅን፤ ስለኔ እያዘነ...ስለሱ እያነባሁ...በጊዜዬ ከመጣ እያየሁ ካረፈደም እንዳያጣኝ በመናፈቅ የሌለሁ መስሎት ከደጅ እንዳይመለስ አንገቱን እንዳያቀረቅር ስንት ዘመን በራፌን ክፍት አድርጌ ጠበኩት።መሰነባበት የሌለው መለያየት ምንኛ ያማል? ደጄን ክፍት አድርጌ ስንት ተኩላዎች፣ ጅቦችና ውሾች ሲተናኮሉኝ ስመልሳቸው እንደኖርኩ ማን በነገረው...ብርቱ ክንዴ ሳይዝል ተስፋዬ ተስፋ በነበረው ሰአት ፤ አለመሸነፌ መሸነፍ ሳይሆን በፊት። አልቀረም በጊዜዬ ሳይሆን በጊዜው መጣ እንጂ...መቅረቱ አድኖኝ ማርፈድ ሲሆን ጎዳኝ። ለምን? ሌላ ሰው አገባኝ። ለምን? በአራተኛው ጣቴ ቀለበት ታሰረ። የሴት ልጅ እድሜ ቁማር ነው ወይ ትበላለች ወይ ትበላለች። ልክ እሱን እንዳየ እንዳቀረቀረ...ከመታሰር ላልድን መሄዴ ላልቀረ....መቅረቱ ማርፈድ እንዳይሆን እልፍ ጊዜ ፀልያለሁ፤ በሱ አያስችለኝም ባሌን ፈታዋለው። ዋጥ ፀጥ ረጭ ዝም...ግን እንደ እውነታው ጩኸት እንዲ አይጮህም...ምናለ በልጅነታችን ት/ቤት ስናረፍድ ካሁን ቡሀላ ተብለን ድጋሚ እድል እንደሚሰጠን ህይወትም ያን እድል ብትሰጠን...ምናለ ማርፈድ የስንፍና ምልክት ብቻ እንደሆነ ባይነግሩን...ራስን እንደሚያሳጣ ቢያስተምሩን...አንዳንድ ማርፈዶች ትልቅ ዋጋ ያስከፍላሉ።
✍ ተጻፈ በአብዱ የእሙዬ ልጅ
✍ ተጻፈ በአብዱ የእሙዬ ልጅ