🌙 ባያቹት ጊዜ ጹሙ፣ ስታዩትም አፍጥሩ
✓ ጨረቃን በማየት የወሩ ማረጋገጫ ✓
✨በአቡ ሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዳስተላለፉት ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹ባያቹት ጊዜ ጹሙ፣ ባያችሁትም ጊዜ አፍጥሩ። ሙስሊም ዘግበውታል (2379)
✨ከአብደላህ ኢብኑ ዑመር (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዳስተላለፉት የአላህ መልእክተኛ (ሶ.ዐ.ወ) ረመዳንን ጠቅሰው እንዲህ አሉ፡- “ ጨረቃን እስክታዩ ድረስ አትጹሙ፣ ከተደበቀባችሁ (በደመና) ገምቱለት(30 ሙሉት) ቡኻሪ (1906) እና ሙስሊም (1080)።
✨ይህ ሀዲስ የረመዳን ፆም ግዴታ መሆኑን የሚያረጋግጥና ጨረቃ መታየቱ በእስልምና ህግ መሰረት ከተረጋገጠ ነው ። እንዲሁም የሸዋል ወር ጨረቃ በህጋዊ መንገድ መታየቱ ከተረጋገጠ ፆምን የመፍታት ግዴታ እንዳለበን እና ደመና ወይም መሰል የረመዷንን ጨረቃ ማየት ከከለከሉ ሸዕባንን ሰላሳ ቀን አድርጎ ማጠናቀቅ ግዴታ መሆኑን ያመለክታል።
✨እያንዳንዱ ሰው ጨረቃን ማየት ግዴታ አይደለም , ይልቁንም, አንድ ሰው ካየ (ታማኝ) ይበቃል።
@sebil_tube@sebil_tube