⚡️መለኮታዊ ጉብኝት ለኢትዮጲያ በሚል መሪ ቃል በመስቀል አደባባይ የወንጌል መርሃግብር ሊካሄድ ነዉ፡፡
የዝማሬ፣ የአምልኮ እና የወንጌል መርሀግብር የካቲት 29 እና 30 በመስቀል አደባባይ ከቀኑ 7 ሰዓት ጀምሮ እንደሚደረግ የቢሊ ግራሃም የወንጌል ማህበር አስታወቀ፡፡
የቢሊ ግራሃም የወንጌል ማኅበር በመስቀል አደባባይ ለሚያደርገው የሁለት ቀናት መርሐ ግብር መጋቢ ፍራንክሊን ግራሃም ወደ አዲስ አበባ መምጣታቸዉ ተገልጿል፡፡
ሰማሪታንስ ፐርስ ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ ከ3 ሚሊየን ለሚበልጡ ሰዎች የምግብ እርዳታ ማቅረቡን እና ከ5 መቶሺህ ለሚበልጡ ሰዎች የህክምና እርዳታ መስጠቱ ተነስቷል፡፡
በተጨማሪም ከ2መቶ60ሺህ ለሚበልጡ ሰዎች ንጹህ ውሃ፣ የንጽህና መጠበቂያ ግብዓቶች እና አገልግሎቶች እንዳበረከተም ነዉ የተገለጸዉ፡፡
ሰማሪታንስ ፐርስ በትግራይ፣ አፋር እና አማራ ክልሎች ውስጥ ለሚገኙ 3መቶሺህ ስደተኞች እና ተፈናቃዮች ምግብ እያቀረበ እንደሚገኝም ተገልጿል፡፡
በትግራይ እና አማራ ክልሎች ውስጥ ከ52 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ተንቀሳቃሽ የሕክምና አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝም በመግለጫዉ ወቅት ተነስቷል፡፡
ድርጅቱ ከኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን ጋር በመተባበር በአዲስ አበባ ከተማ በቆሼ የቆሻሻ ማጠራቀሚያ ቦታ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ለሚኖሩ ሰዎች የሚደረግ ድጋፍ መኖሩም በመግለጫው ወቅት ተገልጿል፡፡
@seledadotio@seledadotio