🇪🇹🌱
ኢትዮጵያ ለስድስት ወራት የሚቆይ ፀረ-ብክለት ዘመቻ መጀመሯን የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን አስታወቀ
ለስድስት ወራት በሚቆየው የፀረ-ብክለት ዘመቻ የአረንጓዴ አካባቢ ግንዛቤን በህብረተሰቡ ዘንድ ለማስረጽ አቅዶ እየሰራ መሆኑን ባለስልጣኑ አስታውቋል። ለሁለተኛ ገዜ የሚካሄደው ይህ ዘመቻ "ጽዳትና አረንጓዴን የኢትዮጵያ ባህል ማድረግ" በሚል መሪ ቃል በቅርቡ ይጀመራል ሲሉ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሌሊሴ ነሜ ተናግረዋል።
የዘመቻው ዓላማ በአካባቢ ብክለት ዓይነቶች እና ቅድመ መከላከል እርምጃዎች ዙርያ የህብረተሰቡን ግንዛቤ ማሳደግና የማህበረሰቡን የተባበረ እርምጃ ወሳኝነት ማጉላት እንደሆነ የባለስልጣኑ ዳይሬክተር ጠቁመዋል።
♻️ ሌሊሴ አክለውም የፕላስቲክ ብክለት ሕጎችን በትክክል መተግበር፣ ደረቅ እና አደገኛ ቆሻሻዎችን በአግባቡ ማስወገድ እና ሁሉም ፕሮጀክቶቸ የአካባቢ እና የማህበራዊ ተፅእኖ ግምገማን እንዲያከብሩ ማድረግ አስፈላጊ እንደሆነ አጽንኦት ሰጥተው፤ ይኽንን በሚጥሱት ላይ ሕጋዊ ቅጣት ይጣላል ብለዋል።
📄 የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን በዘመቻው ላይ በጋራ መሥራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነት ከኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ጋር ባሳለፍነው ሳምንት ተፈራርሟል፡፡
በእንግሊዘኛ ያንብቡ📲 መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦
👉
APK ፋይል ሊንክ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ 👉
@sputnik_ethiopia