12ኛውን ሰዓት እየጠበቅን ነው!"አንድ አማራዊ ተቋም ልንመሰርት 11ኛው ሰዓት ላይ ደርሰናል። መተዳደሪያ ደንቦችን፤ አዋጆችን፤ አርማና ስም መርጠን ጨርሰናል። በቅርቡ በአጭር ቀናት አንድነቱን እናበስራለን!" ይህ የአርበኛ አስረስ ማረ ንግግር የፋኖ አንድነት ምን ያህል እንደተቃረበ የሚያሳይ ብስራት ነው። 11ኛው ሰዓት ለንጋት 12 ሰዓት መድረስ አግባቡን ጠብቆ እንዲሄድ እያመለከትን፣ 12ኛውን ሰዓት በተስፋ እየጠበቅን ነው!
ይህ 12ኛው ሰዓት ግን ከቃላትና ከምኞት የዘለለ ነገር የሚፈልግበት ሰዓት ነው። ለረጅም ጊዜ ስንጠብቀው የነበረው የአንድነት ብስራት እውን የሚሆነው በቃል ብቻ ሳይሆን በተግባር ሲረጋገጥ ነው። ቃላት ኃይል አላቸው፣ ነገር ግን ተግባር ከቃላት እጅግ የላቀ ኃይል አለው።
አሁን ላይ፣ የፋኖ በአንድ ቤት ሥር መሰባሰብ ከምን ጊዜውም በላይ እጅግ ወሳኝና ግዴታም ጭምር ነው። ጊዜውም የዘገየ ቢሆንም፣ የአንድነቱ ብስራት እውን የሚሆነው ሁሉም ፋኖዎች ለአንድ ዓላማ ሲቆሙና ሲሰለፉ ብቻ ነውና ሁሉንም ያማከለ ድርጅት እንጠብቃለን። አሁን የምንጠብቀው አንድነት በቃል ብቻ ሳይሆን በተግባር የሚታይ አንድነት ነው።
ለዚህ ጉዳይ መሳካት ደከመኝ፣ ሰለቸኝ፣ ታከተኝ፣ አቃተኝ፣ ሳትሉ በብዙ ተስፋ አስቆራጭ ሁኔታዎች ውስጥ ሁናችሁ እየሰራችሁ ላላችሁ ክብራችን ከፍ ያለ ነው።
ታጋይ አምሓራ
ነፃነት በትግል እንጂ በልመና አይገኝም!