Tea'mir Communication


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: ko‘rsatilmagan


This is the official Telegram account of Teamir Coomunication

Связанные каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri






BBC News Hour ላይ በሰጠው ቃለ መጠይቅ ላይ ግን፦ 'ችንፈታችን በዋናነት የጦር ሜዳ ሳይሆን የፖለቲክ እና የዲፕሎማሲ ነው። የፖለቲካው ክንፍ ነው ለዚህ ሃላፊነት ሊወስድ ሚገባው' የሚል አነጋጋሪና ህወሃትን የከፋፈለ ቃለ መጠይቅ በትግርኛ ሠጠ። 'ለኛ ችንፈት ተጠያቂዋ TPLF ናት' አለ።

And again TPLF Failed Tsadkan.

¤

[ፍረድ እንግዲህ]

¤

የሰባ አንድ አመቱ አረጋዊ። የሁለት ማስተርስ ባለቤት። የቀድሞው ኢታማዦር ሹም - ወ - ኢንቨስተር - ወ - TDF Strategist የህይወት ዘመን ጠላት ታዲያ፣ ከቶ ማን ነውን?

ሻእቢያ?

ደርግ?

ብልፅግና?

ወይንስ ህወሃት?


ነገረ ወዲ ገብረ ትንሳኤ

(እዮብ ምህረተአብ)

∞ ∞ ∞ ∞ ∞ ∞

ወደ ገደለው ስንሄድ፦ የራያው ልጅ ፃድቃን ገብረ ትንሳኤ አራት ኪሎ የባዮሎጂ ተማሪ ነበረ። ከዛም ትግል ስታይሌ ነው አለና ደደቢት በረሃ ወረደ።

[ውጊያ ተለማመደ]

ወያኔ ከደርግ ጋራ ስትዋጋ ከጦር ፊታውራሪዎች አንዱ ሆነ፤ ፃድቃን ገብረትንሳኤ። ከገቡም በኋላ ለአስር አመታት ያህል፣ በሌተና ጀነራል ማዕረግ፣ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የጦር ኤታማዦር ሹም (Chief of Staff) ነበረ።

ፃድቃን ቀጥተኛ፣ ቅን እና ሆደ ቡቡ ነው ይሉታል የሚያውቁት።

¤

[አንዴ]

የካህሳይ አብርሃን 'የአሲምባ ፍቅር' መፅሃፍን ካነበብክ፣ ያኔ ኢህአሠ አሲምባ እንደገባ በብሄር ፌድራሊዝም ጉዳይ ኢህአፓና ህወሃት ሲከራከሩ፣ ''የብሄር ፌዴራሊዝም የታክቲክ ጉዳይ ነው። #ማታገያ ነው እንጂ End አይደለም'' ብሎ የሞገተ ነው። ''የትግራይ ገባር የመሬት ላራሹ ጥያቄው ስለተመለሰለት፣ አሁን መደብ ምናምን ከምንለው ጨቋኝ የአማራ መንግስት መጣብህ፣ ነፍስህን ለማዳን ተዋጋ ብንለው ይሰማናል፣ ለዛ ነው ብሄር ፌዴራሊዝምን የምናራምደው'' አላቸው። ገራገሩ ፃድቃን። (ቀጥታ አማርኛው ሳይሆን አሳቡን ነው አስታውሼ የጻፍሁልህ)

[ሌላ ጊዜ ደግሞ]

ታስታውስ ከሆነ፣ 'የዘመናት የህዝባችን ብሶት የወለደው ጅግናው የኢህአዴግ ሠራዊት' ሸገርን ሲቆጣጠር - ኦፕሬሽኑን በተሳካ ሁኔታ የመራው ፃድቃን ነው።

ፃድቃን አዲስ አበባን ሲይዝ እነ መለስ ለንደን ነበሩ። ከደርጉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር፣ ዶክተር ይግለጡ አሻግሬ ጋራ ድርድር ላይ ነበሩ።

እናም ፃድቃን በለንደኑ ጉባኤ መሃል ላይ ለመለስ ደውሎ፣ 'አዲስ አበባን ገባን እኮ' ይለዋል።
መለስም 'እና ቤተመንግስት ገባችሁ ወይ?' ይለዋል
'አይ አልገባንም' ይለዋል።
መለስም ለምን አልገባችሁም?' ይላል።
ፃድቃንም፣ 'አይ ህዝቡ ስልጣን ፈልገን የመጣን እንዳይመስለው ብዬ ነው' ይላል።
መለስም፣ 'እና ምን ልንሰራ አዲስ አበባ ገባን?' ብሎት ስቆ ስልኩን ይዘጋበታል።

[እንዲህ አይነት ሰው ነው፣ ፃድቃን ገብረትንሳኤ]

¤

[ተመልከትኝ እንግዲህ]

በሶስት የጦርነት ኩርባዎች ላይ ፊታውራሪ የነበረው ፃድቃን፣ ህወሃት ሶስቴ ክዳዋለች። አዋርዳዋለች። . . . They Failed Him Big.

(1)

ኢትዮ ኤርትራ ጦርነት።

እንደዛ ፆሮና ግንባርን አቋርጦ፣ ሰንአፈን አልፎ አስመራ ካልገባው ያለው ጄኔራል ውጊያ ላይ እያለ፣ አሜሪካኖች መለስን 'ተመለስ፣ ካልተመለስክ ኤርትራም ብትገባ ሌላ ሱማሌ ነው የምትፈጥረው፣ የመሃል አገር ስልጣንህ አይረጋም። እኛም ማእቀብ እንጥልብሃለን' ብለው አዘዙት። መለስም ፃድቃንን 'ተመለስ' ብሎ አዘዘው። ፃድቃንም አኩርፎ ተመለሰ።

ሸገር ሲመለስ ህወሃት ተጣላችው። ከስራ ተባረረ። ብርና ጥቅማ ጥቅም ተነፈገ። በደህንነቱ ክንፈ አስተባባሪነት የህወሃት ሰው በሙሉ ራቀው፣ ሸሸው። እናም ያ ጉምቱ ኢታማዦር ሹም የሚቀመስ ሁላ አጥቶ ቸሰተ።

አዲስ አድማስ ላይ በሰጠው ቃለመጠይቅ፣ 'ያ ሁሉ አጃቢና ኮብራዎች የነበሩኝ ሰውዬ፣ ልጄን ከትምህርት ቤት ላወጣ ሴንጆሴፍ ትምህርት ቤት ለመጀመሪያ ጊዜ በታክሲ ሄድኩ። ልጄን አወጣሁትና ታክሲ ስጠብቅ ወረፋው አደነጋገረኝ። ህፃኑ ልጄም ፀሃይ ሲመታውና ግፊያ ሲያስደነግጠው፣ ''አባዬ ምን በድለን ነው ህወሃት የምትቀጣን?'' አለኝ። ይሄ አባባል ልቤን ያደማው። እስከ ዘልአለም ቅስሜን የሰበረው መጥፎ ትዝታዬ ነው' አለ።

Yes, TPLF Betrayed Him.

(2)

ከኢታማዦር ሹምነት የተባረረው ፃድቃን፣ የUN ሰላም አስከባሪ ሃይል ደቡብ ሱዳን ላይ ሃላፊ አድርጎ ቀጠረው - በጨቅ ደሞዝ። የደቡብ ሱዳን መንግስት ሲመሠረትም የጦር አማካሪያቸው ሆኖ በዶላር ሸቀለ። ሸገር ተመለሰ። ሸገር ላይ በት በት አለ። Lion Bank እና ራያ ቢራን አቋቋመ። የአራት የመንግስት የልማት ድርጅቶች የቦርድ ሰብሳቢ ሆነ። ራያ ላይ፣ ጋምቤላ ላይ ግብርና ጀመረ። ቦሌ መድሃኒያለም ሁለት ህንፃ ገነባ።

[ከበረ። ቻፒስት ሆነ]

በመሃል መለስ ዜናዊ ሞተ። መለስ ሲሞት ህወሃት በዝርፊያና በኔትዎርክ ሽቀላ በከተች። ገለማች። አረጀች። አፈጀች። አፈላች። ከስልጣን ተባረረች። . . . መቀሌ ገባች።

¤

ድኅረ ህወሃት ያለው አካሄድ ያስፈራው ፃድቃን፣ መቀሌና አዲስ እየተመላለሰ አብይንና ህወሃትን ለማስታረቅ ሞከረ፣ አልተሳካለትም። አብይን 'ከኛ ጋራ ከተዋጋህ አትችለንም፣ ጥይት የጥርስ መፋቂያችን ነው፣ እረፍ' ስለው፦ 'በStick and Carrot የማይገዛ ሕዝብ ዓለም ላይ የለም' አለኝ። ያኔ ተስፋ ቆረጥኩ' አለ አንዱ ቃለ መጠይቅ ላይ። ነገር ሲከርር፣ ፃድቃን ሸገር ቁጭ ብሎ ሻእቢያ እንደማይለቀው፣ የያኔውን አስቦ እንደ ሚበቀለው ተረዳ። ልክ ሃጫሉ የሞተ እለት በሌሊት ከ ጀነራል አበበ ተእለሃይማኖት (ጆቤ) ጋራ በሌሊት በአፋር በኩል ሲነዱ አድረው መቀሌ ገቡ።

የቀድሞው ኢታማዦር ሹም፣ የአሁኑ ኢንቨስተር ሌፍተናንት ጄነራል ፃድቃን ገብረትንሳኤ፤ በህወሃት ዝቅጠትና ቅሌት ሃብት ንብረቱን፣ የተረጋጋ ህይወቱን አጣ።

Again, TPLF Failed Him.

(3)

ሂዊ መቀሌ ከሸሸች በኋላ የትግራይ Central Military Command ተቋቋመ። ከነ ወዲ ወረደ ጋራ ወታደራዊ አመራር ሆነ። አዋጊ ፊታውራሪ ሆነ።

ከሰሜን እዝ መመታት በኋላ ሻእቢያ ከላይ፣ መከላከያ ከታች፣ ፋኖ ከጎን፣ ድሮን ከሰማይ ሲያሯሩጧቸው ተቸነፉ። ያ ሁሉ ሎጂስቲክስ ደባየ። ያ የተከማቸ ያጭርና የመካከለኛ ርቀት ሚሳኤል እንዳይሰራ ሆነ። እነ ፃድቃንም ሸሽተው ተንቤን ዋሻ ገቡ።

[ከዛ]

አለ አለና አመትም ሳይቆዩ መከላከያም ሻእቢያም ከትግራይ ለቀቁ። ህወሃት መቀሌ ተመለሰች። የነሱ ሚሊታሪ ኮማንድ ሃይሉን አሰባስቦ ከመቀሌ ወጣ። በምእራብ በወልቃይት ሞከረ፣ ተቸነፈ። በምስራቅ በሚሌ ሞከረ፣ ተቸነፈ። ቁልቁል በደቡብ በራያ መስመር ሞከረ፣ አቸነፈ።

[ነኩት ወደታች]

እስከ ደብረሲና ከቆሰቆሱት በኋላ ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አራት ኪሎን ለደመቀ መኮንን አደራ ብለው ከጦር ሜዳ ወረዱ። ይሄም ለጦሩ ከፍተኛ ሞራል ሆነው። እንደ ጀነራል አበባው ቃልም፣ መከላከያ ያሰለጠናቸው ምልምል ወታደሮችም ለአቅመ ውጊያ ደረሱ። ሪፐብሊካን ጋርድም ጦሩን በሙሉ አቅሙ ተቀላቀለ። ፋኖም፣ 'ደጀን ተራራንና ደብረታቦርን አሲዤማ አልተኛም' ብሎ አንገት ላንገት ተናነቀ። በላዩ ላይ የቻይናው Long Range Drone፣ በላይ ነሽ አመዴ ከቻሳ አለች።

¤

TDFም ተመታ። ተረታ። ተንገላታ። የህወሃት ጦር - 'ምን ይዤ ልመለስ ወደ እናቴ ቤት' የሚለውን ዘፈን እያንጎራጎረ U Turn ሠርቶ ሸከሸከው - ወደ መቀሌ።

[ሌፍተናንት ጀነራል ፃድቃን ገብረ ትንሳኤ ተቸነፈ]

ፃድቃን ግን መሸነፉን አላመነበትም። The Elephant ሜጋዚን ላይ 'ዓዱኒያ ብላሽ ናት። ዓለም ከዳን፤ የLip Service፣ ምፅ ምፅ ብቻ ነው ያለን። . . . 'we got words, they got weapons' ብሎ ኢሪሪ ብሎ ፃፈ። ኢሳያስንም የአፍሪቃ ቀንድ ሚካኤል ስሁል፣ The King Maker ብሎ ከሠሠ።

[በሌላ ቃለ መጠይቅ ደግሞ]




The talented Ethiopian photographer who won the 2022 World Press Photo Contest

Amanuel Sileshi, an Ethiopian photographer based in Addis Ababa and who works for Agence France-Presse, became a winner of the 2022 World Press Photo Contest with his photography project documenting the war in Tigray. Besides winning in the 2022 World Press Photo Contest, the jury decided to award an honorable mention to the photographer to highlight his bravery and determination in covering different angles of the Tigray conflict.


ኤልያስ መልካ "ወርቃማው" የሙዚቃ ዘመን ነው !

በዘመናዊ የሙዚቃ መሣሪያ ታጅቦ እና ዓለማቀፍ የምት ዘሮችን ተንተርሶ ቺግቺጋ፣ ፖፕ፣ ትዝታ/ዋልዝ እና ሬጌን የመሳሰሉትን ቅንብሮች ከአገርኛ ቅኝቶች ጋራ ደባልቆ ከአንድ ክ/ዘ በላይ በተጓዘው የአገሩ "ዘመናዊ" ሙዚቃ "ወርቃማው የሙዚቃ" ዘመን እይተባለ በስፋት ሲሞካሽ የምንሰማው የዕለት ተዕለት ትርክት ነው። ይህ ትክክል ነው፤ ትክክል አይደለም የሚለው አግባብ የሆነው ጥያቄ ለባለሙያዎቹ ተከድኖ ይቀመጥና፤ አንድ ትክክለኛ ቁምነገርን ግን እናስታውስ።

ለመሆኑ እንዲያው በጥቅሉ "ወርቃማ" የሚል ምክንያትነቱ አጠያያቂ የሆነ ስያሜ ያገኘው የ"1950" ዎቹ እና ቀጥሎም የመጣው እና እስከ "1980" የተቀነቀነው ሙዚቃ ምን ያህል በጥልቀት እና ዓለማቀፋዊ ባህሪያትን በተላበሰ የባለሙያዎች ጥናት እና ህዝባዊ ተሳትፎ ተተንትኖ ይሆን እንደ ደብተራ መፅሐፍ ሚስጥር ሆኖ በታመነበት ስያሜው እንዲፀና የተደረገው? አንድንስ ሙዚቃ ወይም የሙዚቃ ዘመን ምርጥ ወይም "ወርቃማ" የሚያሰኘው ባህሪይቱ ምን ምን ናቸው?...ለመሆኑ ሙዚቃ እንደ ሌሎቹ የስነጥበባት የዘር ሃረጉ ምርጥነቱ ወይም ውጤቱ የሚለካው በተደራሲያኑ ላይ በሚፈጥረው ሁለንተናዊ ተፅዕኖ ነው ወይስ በደራሲያኑ እና ባለሙያዎቹ ብቃት ነው?...እነዚህ እና ሌሎች በርካታ ጥያቄዎች ተንሸራሽረው እና ዓለማቀፍ ምጣኔ ያለው ጥናት እና ምርምር ተካሂዶ ቁርጥ ውስኔ ላይ እስካልተደረሰ "ሾላ በድፍኑ" የመሰለ ትርክት ከትርክትነቱ አያልፍም።

በርካታ የሙዚቃ ባለሙያዎች እና አድማጮች "ያሁኑ ሙዚቃ ይሻላል፤ የድሮ ሙዚቃ?" ወይም ደግሞ የድሮውን ሙዚቃ "ወርቃማ" ያሰኘው ምክንያት ምንድን ነው? በሚል ለሚቀርብላቸው የተሳከር ጥያቄ የሚሰነዝሩት የተሳከረ መልስ በዋናነት በሁለት መሰረታዊ ጽንሰ-ሃሳቦች ላይ የቸነከሩ ሆነው ይገኛሉ፦ አንድም የፈረደበት "ባንድ" ሌላው ደግሞ ስንፍና እና አቅመቢስነት የሚያጠቃውና የድምጻውያኑ ለገንዘብ የሚሰጡት ቦታ። እንግዲህ የየቀድሞውን እና ያሁኑን ሙዚቃ አስመልክቶ ለሚቀሰቀሰው ስሜታዊ ክርክር ከየአቅጣጫው የሚሰነዘሩት አስተያየቶች ዋናዋናዎቹ እነኚህ ሁልቱ ከሆኑ "ተከራካሪዎች ሆይ በከንቱ አተከራከሩ፤ ይልቁን ጉንጭ አልፋ ክርክራችሁን ወዲያ አሸቀንጥሩና ኤልያስ መልካ የተባለን የዘመኑን የሙዚቃ ፈላስፋ በሰላ ጆር፣ በተረጋጋ ልብ እና በሚያሰላስል አዕምሮ ተዘጋጅታችሁ አድምጡ ትባላላችሁ !

ኤልያስ መልካ በጠባብ ክፍል ውስጥ አንድ ኪቦርድ ይዞ ሙዚቃን በማቀናበር የመጀመሪያው አይደለም፣ ከመጀመሪያዎቹ ግን አንዱ ነው። ከሱም በፊት ከሱም በኋላ የመጡት ግን የሙዚቃ እውቀት እና የመሳሪያዎች ጥራት ካልከፋፈሏቸው በስተቀር በመሰርታዊ የመሽን ቅንብር አንዱን ካንዱ ለመለየት በሚያስቸግር መልኩ ተመሳሳይ እና አሰልቺ ናቸው። ኤልያስን ታዲያ ምን ለየው?...

ኤልያስ ወደ ሙዚቃ የገባው ቦክስ ጊታር በመጫወት ነው። እሱ ቦክስ ጊታር (የክር መሣሪያ) በሚጫወትበት የልጅነት እድሜ ደግሞ የአገሩ ሙዚቃ በጡሩንባ የታጀበ (ብራስ ባንድ) ነበር። የሙዚቀኛን ጆር ብቻ ሳይሆን የአድማጭንም ጆሮ የታደለው ኤልያስ መልካ ከልጅነት ዘመኑ ገናና የነበረውን "ሮሃ" የተሰኘ የአንጋፋዎችን ባንድ ሙዚቃ ሲያዳምጥ ይማረክበት የነበረው ድምጽ ሠላም ሥዩም ከሚያናግራት ጊታር የሚወጣው እንጂ ከሌሎቹ አልነበረም። ስለዚህ የኢትዮጵያ "ዘመናዊ" ሙዚቃ የምት አንድነት እና ተደጋጋሚነት የሚያጠላበት እንደሆነ በመረዳት አዲስ ድምጽ እንደሚያስፈልገው በመገንዘብ ወደ ሙዚቃ ቅንብሩ "ሀ" ብሎ ሲገባ በጡሩንባ የተደበደበውን ሙዚቃ በክር አክሞ ማስታመም ነበር ተቀዳሚው ሥራ።

ከዚህም በላይ የትውልዱን የባህር ማዶ ሙዚቃ መላመድ በጥበባዊ አይኖቹ አሻግሮ የተመለከተው ወጣት አሰልቺ እና ድግግሞሽ የሚስተዋልበትን "ቺግቺጋ" የተሰኘውን የአገሩን የሙዚቃ ሥልት እንደ ሞገደኛ ምሁር ፈነቃቅሎ ሳያፈራርሰው በዘዴ እና በጥበብ ከ ባህርማዶዎቹ "ሬጌ"፣ "ሮክ ኤን ሮል" እና "ፖፕ" ሙዚቃ ስልቶች ጋራ ተጣጥሞ የሚሄድበትን መንገድ እንደ አንዳንዶቹ ተስፈኞች ባሕር ማዶ መሻገር ሳያስፈልገው ደጁን ቆልፎ በመለማመድ እና ተፈጥሮ ያደለችውን የሙዚቃ ምትሃት እንደዛር በላዩ ላይ እና በተከታዮቹ ላይ በማውረድ ላለፉት ሃያ ዓመት በመደነቅ ስሜት ውስጥ የሰማናቸውን ጊዜ አይሽሬ ሙዚቃዎች አበርክቶልናል።

የአብነት አጎናፈር ሁለት ቀደምት ሥራዎች፣ የሚካኤል በላይነህ ሁልተኛ አልበም፣ የትዕግስት በቀለ "ተረታሁ"፣ የዘሪቱ ከበደ "ዘሪቱ" እና የሚኪያ በኃይሉን "ሸማመተው"ን ለአብነት መጥቀስ ብቻ በቂ ነው።

ከዚህ ባሻገር ኤልያስ እንደ አብዛኞቹ አንድዬ አቀናባሪዎች ኪቦርድ ላይ በተሞላ መሣሪያ በመጫወት "የትም ፍጪው ..." አይነት ንዝላልነት ፈጽሞ የሌለበት ሙሉ ሙዚቀኛ መሆኑን ለመመስከር "ኦሮማይ" በተሰኘው የእንዳሌ አድምቄ ሁልተኛ አልበም፣ "አንተ ጎዳና"በተሰኘው የሚካኤል በላይነህ ሁልተኛ አልበምና በሌሎችም ጥቂት የማይባሉ ቅንብሮቹ ውስጥ "ሙሉ" ሊባል የሚችል የባንድ ስብስብ ተጥቅሞ የግሉን ችሎታ በባንድ ልክ የፈተሸ የግለሰብ ባንድ ነው። ለነገሩ በያሬድ የሙዚቃ ት/ቤት ተማሪ እያለ ከመምህራኖቹ ጋራ መድረክ ተጋርቶ ሙዚቃ በመጫወት በእሱ ሰበብ አብሮት የድሉ ተጠቃሚ ከነበረው አብሮ አደጉ ቢንያም በድሩ ካልሆነ የትኛው ተጠቃሽ ሙዚቀኛ ሊጠራበት እንደሚችል እርግጠኛ አይደለሁም።

ከ"መዲና" አንስቶ "ስሪ ኤም" እና "ሚሊኒየም"አንቱ የተባሉ አንጋፋዎቹ የአገሪቱ ሙዚቀኞች ጋራ እኩል ተሰልፎ ሙዚቃን በግል ስቱዲዮ ብቻ ሳይሆን ብርቱ ጥረት በሚጠይቀው የአደባባይ ፈተናም ተዋውቋታል።ይህ ልምዱም መሬት ከሆነው ግለሰባዊ ማንነቱ እና ትህትናው ጋራ ተዳምሮ ከአንድም ሁልት ሦስት ጊዜ ጓደኞቹን በማሰባሰብ ተወዳጅ ባንዶችን ለማቋቋም በቅቷል። "አፍሮ ሳውንድ"፣ "ዜማ ላስታስ" እና "ኢትዮ ግሩቨስ" ተጠቃሾች ናቸው። ሥለዚህ የድሮ ሙዚቃ ወርቃማነቱ በባንድ መታጀቡ ከነበር የአንድ ሰው ጭንቅላት የሰራው የማይመስለውን እና አንድ ሆኖ ባንድ መሆን በቻለው ኤልያስ መልካ የተቀናበሩ ሙዚቃዎችን አብሮ መጥራት ተገቢ ይሆናል ማለት ነው።

ሁለተኛውም አመክንዮ ከዚህ የተለየ አይደለም። "የድሮ ሙዚቀኞች ካሴት ሲሰሩ ብዙ አመታት ይወስድባቸው ነበር፣ በዛ ላይ ለገንዘብ አልነበረም የሚሰሩት፤ ለጥበብ ነበር።" ከተባለም በዘመናችን ይህን ሲያደርግ ያየነው አንድ ሰው እሱ ኤልያስ መልካ ብቻ ነው። አንድን ድምጻዊ በሰለጠነ የመብት ውል አስማምቶ ስለ ካሴት ሥራ እና ውጤቱ ሙሉ ማብራሪያ ሰጥቶ ሲየበቃ ከ4 ዓመት እስከ 7 ዓመት በሚፈጅ የጊዜ ሰሌዳ ለትውልድ የሚተርፍ አልበም እሚደሰኩሩ ያደረጋቸው ድምጻውያን እሱ አርቆ ያስቀመጣቸው የዝና ማማ ላይ ሆነው ካልጠመሙ በቀር መናገር ይችላሉ።

ከኢዮብ መኮንን፣ እስከ ጌቴ አንለይ ያሉትን በርካታ ድምጻውያንን የቀድሞ ማንነት እና ሙዚቃዊ መረዳት በማጠያየቅ ከኤልያስ ጋራ ከተወዳጁ በኋላ ስለመጣው አዲስ ማንነት ምሥክር መስጠት ይቻላል።

እንደ እኔ አይነቱ እድለኛ አድማጭ ደግሞ ኤልያስ መልካን ደጅ ሳይጠና እና እነኛን ሁሉ የመልካም ሙዚቃ አሰራር ውጣ ውረድ ሳያይ ቤቱ ቁጭ ብሎ የእጆቹ አሻራ ያረፈባቸውን ሥራዎቹን በመኮምኮም የነብስም የሥጋም ድኅነትን አግኝቷል።

ከዕሜዪ ይቀጥልልህ ወዳጄ !!!

(በሄኖክ)


የትውልዱን የባህር ማዶ ሙዚቃ መላመድ በጥበባዊ አይኖቹ አሻግሮ የተመለከተው ወጣት አሰልቺ እና ድግግሞሽ የሚስተዋልበትን "ቺግቺጋ" የተሰኘውን የአገሩን የሙዚቃ ሥልት እንደ ሞገደኛ ምሁር ፈነቃቅሎ ሳያፈራርሰው በዘዴ እና በጥበብ ከ ባህርማዶዎቹ "ሬጌ"፣ "ሮክ ኤን ሮል" እና "ፖፕ" ሙዚቃ ስልቶች ጋራ ተጣጥሞ የሚሄድበትን መንገድ እንደ አንዳንዶቹ ተስፈኞች ባሕር ማዶ መሻገር ሳያስፈልገው ደጁን ቆልፎ በመለማመድ እና ተፈጥሮ ያደለችውን የሙዚቃ ምትሃት እንደዛር በላዩ ላይ እና በተከታዮቹ ላይ በማውረድ ላለፉት ሃያ ዓመት በመደነቅ ስሜት ውስጥ የሰማናቸውን ጊዜ አይሽሬ ሙዚቃዎች አበርክቶልናል።


መልአከ ሞት፥ አደራህን ተናገር
--
ጌታቸውን ፈዞና ናወዞ ሳይሆን አትሮንስ ስር ብራና ሲያገላብጥ እንዳገኘኸው ተናገር፡፡
--
በ1756 ዓ.ም. የጎንደር ካይላ ሜዳ ጉባኤ በነበረው የነገረ ክርስቶስ ላይ የነበሩትን ዐረብኛና ግእዝ ምንጮች እያመሳከረ ለኅትመት ሊያበቃ በዝግጅት ላይ ሳለ ማግኘትህን ተናገር፡፡
--
በ89 ዓመቱ 700 ገጽ የሚወጣው መጽሐፍ ጽፎና አሳትሞ ለዳግም ኅትመትና አርትዖት ሲላጋ ሲንከላወስ የነበረ ብርቱ መምህር እንጂ መንፈሱ የዛለ ድኩም አረጋዊ አለማግኘትህን ተናገር፡፡
--
በቅርብ ወራት የነግሕ ጸሎቱ ‹‹ይእዜ ትስእሮ ለገብርከ - ባሪያህን አሰናብተው›› ማለቱ በጥቂት ሕማም ‹አንሱኝ ጣሉኝ› ማለቱን ኩሩ መንፈሱ ተጸይፎ እንጂ የሚሠራውን አጥቶ አረጋውያን መዋያ ውሰዱኝ የሚል ቦዝ ሽማግሌ አለማግኝትህን ተናገር፡፡
--
60 ዓመት ከሞላው ወዲህ ወደ አማርኛ ኅትመት መጥቶ እስከ 90 ዓመቱ በተከታታይ 8 መጻሕፍትን በሚደንቅና በአምሳያ አልባ አርትዖት የጻፈ አረጋዊ እንጂ ጭራ ይዞ ከልጅ ልጆቹ ጋራ ለመጫወት ሰፊ ጊዜ የነበረው አባት አለማግኘትህን ተናገር፡፡
--
ስለሚወዳት አገሩና ስለ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ልዕልና ሲል የደም ዋጋ ከፍሎ ተተኩሶበት አጥንቱ እስኪፈለጥ በወታደር ጥይት ተመትቶ በተገፍኦ ቢወጣም ለእናት አገሩ ያለው ፍቅር እስከ መጨረሻዋ ህቅታ ድረስ አለመጓደሉን፣ ስሟ በተነሣ ቁጥር ከርቀት ሆኖ እንደ ነቢዩ ዕዝራ በዐይነ ሕሊና እያያት እየተሳለማት እያለቀሳለት ሳለ፣ ዕንባው ሳይቆም ማግኘትህን ተናገር
--
ተናገር! በአረጋዊነቱ የመጨረሻ ሰዓታት ከመጽሐፉ ኅትመት ያገኘውን ገንዘብ በስውር ለነዳያን ሲያከፋፍል እንዳገኘኸው ተናገር! ክርስትናውን ትሩፋቱን አትደብቅ! ለራሱ ጋሪ ላይ ሆኖ ደክሞ ከሕማሙ ታግሎ ያገኘውን ገንዘብ ሙሉ ለሙሉ መልሶ በስውር ለነዳያን መመጽወቱን፣ እየሞተ ማኖሩን አትሰውር!
--
እንደ ደሴተ ፍጥሞው ቅዱስ ዮሐንስ፣ እንደ ጋ(ን)ግራ ደሴቱ ዲዮስቆርዮስ በተገፍኦ በሄደበት አንገቱን ደፍቶ ከሰው መንጋ ተከልሎ በተባሕትዎ ከመጻሕፍት ሲነጋገር እንዳገኘኸው ተናገር፡፡
--
መሰቀቁን ተናገር! ያ የአፍርንጅ ሊቃውንት ወረፋ ይዘው የሚያገኙት ሊቅ በአገራዊ ቋንቋ በጻፈ ቁጥር ‹ሊቃውንቱ ምኑ ይሉ፣ የዚያ ብሔር የዚህ ሃይማኖት ምን ሊቀጽሉልኝ ይሆን› እያለ መስጋት መሰቀቁን ተናገር! በየጊዜው በገዛ ወገኖቹ በሚነዛ አሉባልታ፣ ከዐውድ በወጣ የጽሑፉ ትርጓሜ ያለአጽናኝ መተከዙን፣ ትካዜውን ለማባረር አትሮንስ ስር መደፋቱን አትደብቅ!
--
ትሕትናውን አትደብቅ! በቅጽል በውዳሴ ስንጠራው ተሰቅቆ መሸሹን ተናገር! የቈጣጠርንለትን ቅኔ ለከንቱ ውዳሴ ሳይሆን ከልባችን ፍቅሩ አገብሮን መሆኑን ለመግለጽ ለማሳመን አቅቶን በእመቤታችን ስም እስከ መማል ደርሰን ‹‹የእርሷን ስም ከጠራችሁብኝማ የት እደርሳለሁ!›› የሚል ሽጉብ በራሱ ላይ የሰሰተ ምስኪን ሊቅ መሆኑን መስክር!
--
ሁቦ ሉዶልፍ አባ ጎርጎርዮስን ቃለ መጠይቅ አድርጎ በሠራው ሥራ በስሙ የጥናት ማዕከል በቆመባት ምድር አቀርቅሮ ምዕራባዊው የኢትዮጵያ ሥዕለ ሕሊና ላይ የማይቀለበስ መፈንቅል ያደረገው ሊቅ በስሙ የ1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ላይብረሪ ሊሰየምለት መሆኑ በመስማቱ ብቻ በሕይወት ያቆየውን አምላክ ሲያመሰገን መታየቱን፣ ብሔራዊ ተገፍዖውን መስክር!
--
መልአከ ሞት ሆይ፡- መንበረ ጸባዖት ይዘኸው ስትቀርብ ፈጣሪያችንን እንዲህ በልልን፡- ዛሬ አንድ ግለሰብ፣ ምሁር፣ ሊቅ ፣ አስተማሪ፣ አጥኚ.፣ መልካም ባልና የልጆች አባት፣ የሴማውያን ልሳናት ተጠሪ፣ የቲዎሎጂ ምሩቅ፣ የሊቀ ሊቃውንት መሓሪ ትርፌ (ኋላ አቡነ ጴጥሮስ) የሐዲሳት ትርጓሜ ደቀ መዝሙር ሳይሆን ግዙፍ ሕያው ተቋም ከነአዕማዱ ይዤ መጣሁ በል! ተናገር!
--
ለእኛም ንገርልን! በዓለም ሥጋ ሳለ በዘወትር ጸሎት ‹‹..ለሣህለ ማርያም ይዕቀቦ…›› እያልን የምንጠራውን አባት በዓለመ ነፍስ አስቦ ‹‹…ለነፍሰ ሣህለ ማርያም ያድኅና…›› ብሎ ንባብ ቀይሮ ለመጸለይ አንደበታችን መያያዙን፣ ዳዊታችን በዕንባ መርጠቡን፣ የዕጓለ ማውታ ስሜት ውስጥ መሆናችንን፣ መዋዕለ ፍጻሜውን በሙሽራ መንፈስ ለማድረግ ስንመኝ ተነጥቀን የመዘረፍ ስሜት ውስጥ መግባታችንን፣ ደግሶ ሙሽራው የቀረበት ባለወግ ማዕረግ የሚሰማው ስሜት ውስጥ መግባታችንን ንገርልን! በእርሱ መጠራት ድኩማን የመንፈስ ልጆቹ የጎደልንን የጎደለብን ንገርልን!

~ በአማን ነጸረ




ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ
(ግንቦት 24፣ 1924 - ሰኔ 4 ፣ 2013)

በአንድ ቃለመጠይቃቸው ላይ "ሰዎች በሕይወት ዘመኖ ሲኖሩ በምን ዓይነት መልኩ ቢያስታውሶት ይሻሉ" ቢሏቸው?

"ከሞትኩ በኋላ ሰው ላይ ክፋት የማይሠራ ሰው ብለው ቢያስቡኝ ይበቃኛል። እኔ ለልጆቼ የማስተምራቸው ነገር ሰው እንዳትጎዱ በሰው ላይ ምንም አይነት ክፋት እንዳይኖራችሁ ነው የምላቸው ። እግዚአብሔርንም ታሳዝናላችሁ ነው የምላቸው በዚህ መንገድ ነው ሰው እንዲያስታውሰኝ የምፈልገው።"

ዕረፍተ ነፍስን ይስጥልን ጋሼ!!!


"It is Art because it is alive. It proves that, if you and I are to create at all, we must create with today and let all the Art schools and Medicis in the universe go hang themselves with yesterday’s rope. It teaches us that we have made a profound error in trying to learn Art, since whatever Art stands for is whatever cannot be learned. Indeed, the Artist is no other than he who unlearns what he has learned, in order to know himself; and the agony of the Artist, far from being the result of the world’s failure to discover and appreciate him, arises from his own personal struggle to discover, to appreciate and finally to express himself.

The thing of course, is to make yourself alive. Most people remain all of their lives in a stupor. The point of being an artist is that you may live.”

-E E. Cummings


"An artist is a sort of emotional or spiritual historian. His role is to make you realize the doom and glory of knowing who you are and what you are. He has to tell, because nobody else in the world can tell, what it is like to be alive. All I’ve ever wanted to do is tell that, I’m not trying to solve anybody’s problems, not even my own. I’m just trying to outline what the problems are.

I want to be stretched, shook up, to overreach myself, and to make you feel that way too.

In this country … if you’re an artist, you’re guilty of a crime: not that you’re aware, which is bad enough, but that you see things other people don’t admit are there."

-James Baldwin


"I can try." then they were in the car, driving. some son of a bitch hit his throttle and tried to ram them as they made a left turn. "baby, why do people try to hit us with their cars?" "well, mama, it's because they are unhappy and unhappy people like to hurt things." "aren't there any happy people?" "there are many people who pretend that they are happy." "why?" "because they are ashamed and frightened and don't have the guts to admit it." "are you frightened?" "I only have the guts to admit it to you — I'm so god damned scared, mama, that I think I'm going to die any minute." "baby, do you want your bottle?" "yes, mama, but let's wait until we get home." they drove along, turned right on Normandie. it was harder for them to hit you when you were turning right."

~Charles Bukowski


It is man's intelligence that makes him so often behave more stupidly than the beasts. ~Aldous Huxley


“Another way to be prepared is to think negatively. Yes, I'm a great optimist but, when trying to make a decision, I often think of the worst case scenario. I call it 'the eaten by wolves factor.' If I do something, what's the most terrible thing that could happen? Would I be eaten by wolves? One thing that makes it possible to be an optimist, is if you have a contingency plan for when all hell breaks loose. There are a lot of things I don't worry about, because I have a plan in place if they do.” ~Randy Pausch (Book: The Last Lecture


“My thought is me: that's why I can't stop. I exist because I think . . . and I can't stop myself from thinking. At this very moment, it's frightful, if I exist, it is because I am horrified at existing. I am the one who pulls myself from the nothingness to which I aspire: the hatred, the disgust of existing, there are as many ways to make myself exist, to thrust myself into existence. Thoughts are born at the back of me, like sudden giddiness, I feel them being born behind my head... if I yield, they're going to come round in front of me, between my eyes, and I always yield, the thought grows and grows and there it is, immense, filling me completely and renewing my existence.” ~Jean Paul Satre


People become neurotic when they content themselves with inadequate or wrong answers to the questions of life. They seek position, marriage, reputation, outward success of money, and remain unhappy and neurotic even when they have attained what they were seeking. ~Carl Jung


I can bear any pain as long as it has meaning. ~Haruki Murakami


Put your principles into practice – now. Stop the excuses and the procrastination. This is your life! You aren’t a child anymore. The sooner you set yourself to your spiritual program, the happier you will be. Separate yourself from the mob. Decide to be extraordinary and do what you need to do – now. ~Epictetus

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.

568

obunachilar
Kanal statistikasi
Kanalda mashhur