telebirr

Kanal geosi va tili: Efiopiya, Inglizcha

The first mobile money platform in Ethiopia

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Inglizcha
Statistika
Postlar filtri

በትዊተር ገጾቻችን ላይ ባደረግነው የ9ተኛ ዙር የ#ንቁ_ተሳታፊዎች ውድድር የ 10 ጊ.ባ ወርኃዊ የኢንተርኔት ጥቅል አሸናፊዎች እንኳን ደስ አላችሁ!

አሁንም የኢትዮ ቴሌኮም https://x.com/ethiotelecom?s=21 እና የቴሌብር https://twitter.com/telebirr ገጾቻችንን መከተል፣ ልጥፎቻችንን መውደድ፣ ማጋራት እና ኮሜንት ማድረግ ያሸልማል!

እድለኞች በትዊተር ገጾቻችን በውስጥ መልዕክት እየሰራ ያለ (Active) የስልክ ቁጥር በ 24 ሰዓት ውስጥ እንድትልኩልን እንጠይቃለን።

ደንብና ሁኔታዎች ተፈፃሚ ይሆናሉ

#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia

9.5k 0 12 17 37

በቀድሞው ጅማ ክፍለ ሃገር በሻይ ከተማ አዲስ የቴሌፎን ጣቢያ በይፋ በከፈትንበት ወቅት!

#ትውስታ #throwbackthursday
#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia

የፊታችን እሁድ መነሻና መድረሻውን በመስቀል አደባባይ አድርጎ የሚካሄደውን ኢትዮጵያ ታምርት የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ የመሮጫ ቲሸርትዎን በቀላሉ በቴሌብር ይግዙ!

የቴሌብር ሱፐርአፕ መተግበሪያ ላይ ክፍያ የሚለው አማራጭ ውስጥ በመግባት ዝግጅት እና ትኬቶች የሚለው ዝርዝር ውስጥ ያገኙታል!
ቴሌብር ሱፐርአፕን በቀጣዩ ማስፈንጠሪያ http://onelink.to/fpgu4m አውርደው፤ ኑሮዎን ይቅልሉ!

ቴሌብር - እጅግ ቀላል፣ ፈጣን፣ ምቹ እና አስተማማኝ!

#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia

በነፃ ማውጋት፣ በቴሌብር ሱፐርአፕ ተችሏል!

በዘመነው ቴሌብር ሱፐርአፕ ከግብይት፣ ገንዘብ እና የአየር ሰዓት መላላክ ባሻገር ቪዲዮ፣ ድምጽ፣ ፎቶ፣ ጽሁፍ እና ፋይሎችን በነጻ በመጋራት ማህበራዊ ግንኙነትዎን ያጠናክሩ፤ ቢዝነስዎን ያቀላጥፉ!

በቴሌብር ኢንጌጅ፣ የዲጂታል ህይወትዎን ያቅልሉ!

መተግበሪያውን ለማዘመን ወይም ለመጫን http://onelink.to/fpgu4m ይጠቀሙ፡፡

#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia

15.1k 0 24 47 104

የኩባንያችንን አገልግሎቶች በተመለከተ መረጃ ወይም እገዛ ሲያስፈልግዎ የደንበኞች አገልግሎት ማዕከላችንን 8994 ላይ አጭር መልእክት በመላክ በቀጥታ ያግኙ!

ሙሉ ሐሳብዎን አጠር አድርገው ይጻፉልን🙏

እንደ ቋንቋ ምርጫዎ 24 ሰዓት ልናገለግልዎ ዝግጁ ነን!

#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia

የመደበኛ ባለገመድ ኢንተርኔት (ዋይፋይ) በመኖርያ ቤትዎ አስገብተው ወሩን ሙሉ ዘና ብለው ኢንተርኔት ይጠቀሙ!

በወር ከ605 ብር ጀምሮ ከቀረቡት አማራጮች ውስጥ መርጠው አሁኑኑ የፈጣን ኢንተርኔት ተጠቃሚ ይሁኑ!

አገልግሎቱን ለማግኘት አቅራቢያዎ ወደሚገኝ የአገልግሎት መስጫ ማዕከሎቻችን ጎራ ይበሉ!

#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia

ሚያዝያን ለመቄዶንያ!

በዚህ ወር በማኅበራዊ ትስስር ገፆቻችን በሚቀላቀሉ አዲስ ተከታዮች (Followers) ብዛት ልክ 30 ብር እንዲሁም በሚጋሩ ልጥፎች (Share) ልክ 10 ብር ለመቄዶንያ አረጋዊያን እና ህሙማን መርጃ ማዕከል እንለግሳለን!

እርስዎም ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገፆቻችንን ይከተሉ፤ ፖስቶቻችንን ያጋሩ፤ ለወገን ድጋፍ ይተባበሩ!

ቴሌግራም | ፌስቡክ | ኢንስታግራም | ሊንክዲን |
ዩትዩብ | ቲክቶክ |

ዘላቂ የጋራ ማኅበራዊ ኃላፊነት ለወገን ብሩህ ተስፋ!

#MatchingFundForSustainableFuture
#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia

17k 0 6 14 43

ኩባንያችን አዲስና አካታች የዲጂታል ስነምህዳር ለመገንባት በሚያደርገው ጥረት ምርትና አገልግሎታቸውን በአጭር ጊዜ Time To Market (TTM) ተደራሽ ለማድረግ የሚፈልጉ አጋር ድርጅቶች ከቴሌብር ሱፐርአፕ ጋር ሲስተሞቻቸውን በፍጥነት ለማስተሳሰር (to integrate) የሲስተም ሙከራ የሚያከናውኑበት የዴቨሎፐርስ ፖርታል አዘጋጅቶ በይፋ አስጀመረ፡፡

የዴቨሎፐርስ ፖርታሉ በዋነኛነት የአጋር ድርጅቶች ሲስተም ወደ ዋናው ቴሌብር ሲስተም ከመተሳሰሩ በፊት በተለየ የሙከራ ቦታ ላይ (sandbox environment) የኢንተግሬሽን ሙከራ ለማከናወን ያስችላል፡፡ አገልግሎቱ ከሶፍትዌር ዴቨሎፕመንት፣ የሲስተም መፈተሻ እና የትግበራ ቦታ በተጨማሪ ለዴቨሎፐሮች ዶክመንቴሽኖች፣ መመሪያዎች፣ የቪዲዮ ቱቶሪያሎች፣ የኮድ ናሙናዎች፣ የኤፒአይ ማጣቀሻዎች እና ሌሎች አጋዥ መርጃ መሳሪያዎች ያካተተ ነው፡፡

ፖርታሉ ዴቨሎፐሮች ከኩባንያችን ሲስተሞች ጋር በፍጥነት እንዲላመዱ እና ክህሎት በመጋራት ደረጃቸውን የጠበቁ በርካታ ችግር ፈቺ የፈጠራ ስራዎች እንዲያፈልቁ ከማስቻሉ በተጨማሪ የኦንላይን ማህበረሰብ በመፍጠር የስነምህዳሩን ተደራሽነት ይጨምራል ብለን እናምናለን፡፡

የዴቨሎፐርስ ፖርታሉን ለማግኘት ማስፈንጠሪያውን https://developer.ethiotelecom.et ይጠቀሙ!

#telebirrEngage #telebirr #Ethiotelecom #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #SmartAfrica #Huawei #GSMA #ITU

15.5k 0 19 120 117

ኩባንያችን በዛሬው ዕለት የዲጂታል ሕይወትን በማቅለል እልፍ ጉዳይ በአንድ መተግበሪያ መከወን በሚያስችለው ቴሌብር ሱፐርአፕ ደንበኞች ከመገበያየት እና ገንዘብ ከማስተላለፍ ባሻገር መረጃን በነጻ በመለዋወጥ ማህበራዊ ግንኙነታቸውን እና ቢዝነሳቸውን የሚያጠናክሩበት ቴሌብር ኢንጌጅ የተሰኘ አገልግሎት አስጀመረ፡፡

አዲሱ ቴሌብር ኢንጌጅ የቢዝነስ እና ግለሰብ ደንበኞች ያለምንም ተጨማሪ የኢንተርኔት ክፍያ ለተናጠል ወይም ለጋራ የጽሁፍ፣ የፎቶ፣ ድምጽ፣ ቪዲዮ እና ፋይሎችን ለማጋራት የሚያስችል ሲሆን ከዚህም ባሻገር ለበዓል ወይም ለተለያዩ ማህበራዊ ሁነቶች የተናጠል ወይም የቡድን መልካም ምኞት መልእክት ከገንዘብ ስጦታ ጋር መላክ የሚያስችላቸውን አዲስ ገጽታ አካቷል፡፡ በተጨማሪም በጭውውቶች ወቅት ገንዘብ ለመጠየቅ፣ ለመላክ እና ለመቀበል፣ ቢል ለማጋራት እንዲሁም ጥቅል ወይም የአየር ሰዓት መግዛትን ጨምሮ በርካታ የዲጂታል አገልግሎቶችን በአንድ መተግበሪያ እንዲያከናውኑ ያስችላል፡፡

ኩባንያችን ለክቡራን ደንበኞቹ አዳዲስ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አማራጮችን በማስተዋወቅ የቢዝነስ ተሞክሮአቸው እና የዕለት ተዕለት ኑሮአቸው ላይ ተጨማሪ ምቾት እና ቅልጥፍና በመጨመር ለዲጂታል ኢትዮጵያ እውን መሆን ሁሉን አቀፍ ጥረት ማድረጉን አጠናክሮ ይቀጥላል፡፡

ለተጨማሪ ማስፈንጠሪያውን https://bit.ly/3W3291x ይጠቀሙ፡፡

#telebirrEngage
#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia

16.5k 0 21 42 136

በኦክሽን ኢትዮጵያ ድረገጽ http://auction-ethiopia.com/ የሚቀርቡ ጨረታዎችን ለመጫረት ወይም ማጫረት ሲያሻዎ ክፍያዎን በቴሌብር በቀላሉ ይፈጽሙ!

ቴሌብር - ቀላል፣ ፈጣን፣ ምቹ እና አስተማማኝ!

#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia

መልካም የሥራ ሳምንት !

#Monday
#MondayMotivation
#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia

መልካም የእረፍት ቀን!

ወዳጅ ዘመድዎን በ 35 ሳንቲም ብቻ ሃሎ ይበሉ !

#Sunday #StayConnected
#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia

የቴክኖሎጂ አጋራችን ሁዋዌ ቴክኖሎጂስ የአፍሪካ ክፍለ አህጉር ኃላፊዎች ልኡካን ቡድን በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም የሚገኘውን የኩባንያችንን የኤክስፒሪየንስ ማዕከል ጎበኘ፡፡

ልዑካን ቡድኑ በማዕከሉ የሀገራችንን የቴሌኮም ታሪካዊ ጉዞ አሁን እስከደረሰበት የእድገት ደረጃ የሚያመላክቱ ቴክኖሎጂዎችን የጎበኙ ሲሆን፣ የስማርት ግብርና፣ ትምህርት፣ ማዕድን ልማትን እና ቱሪዝም የመሳሰሉት የስማርት ሶሉሽኖች ለሀገራችን ዲጂታል ኢኮኖሚ ይዞት የሚመጣው ትሩፋት ላይ ገለጻ ተደርጎላቸዋል፡፡

የልዑካን ቡድኑ በኤክስፒሪየንስ ማዕከሉ በቀረቡት የዲጂታል ሶሉሽኖች እና በአመራሩ ብቃት መደነቃቸውን የገለጹ ሲሆን ኩባንያችን ለዲጂታል ኢትዮጵያ እውን መሆን እየተጫወተ ያለው ሚና ለሌሎች አፍሪካ ሀገራት አርአያ እንደሚሆን ገልጸዋል፡፡

#DigitalAfrica #DigitalEthiopia #SmartAfrica #Huawei #GSMA #ITU #Ethiotelecom #telebirr

17.8k 0 11 70 100

ሚያዝያን ለመቄዶንያ!

በዚህ ወር በማኅበራዊ ትስስር ገፆቻችን በሚቀላቀሉ አዲስ ተከታዮች (Followers) ብዛት ልክ 30 ብር እንዲሁም በሚጋሩ ልጥፎች (Share) ልክ 10 ብር ለመቄዶንያ አረጋዊያን እና ህሙማን መርጃ ማዕከል እንለግሳለን!

እርስዎም ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገፆቻችንን ይከተሉ፤ ፖስቶቻችንን ያጋሩ፤ ለወገን ድጋፍ ይተባበሩ!

ቴሌግራም | ፌስቡክ | ኢንስታግራም | ሊንክዲን |
ዩትዩብ | ቲክቶክ |

ዘላቂ የጋራ ማኅበራዊ ኃላፊነት ለወገን ብሩህ ተስፋ!

#MatchingFundForSustainableFuture
#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia

15 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.