ነህምያ ስለ ሕዝቡ መከራና ስለ ኢየሩሳሌም ጥፋት በሰማ ጊዜ እጅግ አዘነ። ያዘነውም ለእግዚአብሔር ሕዝብ እጅግ ስለሚያዝን እና በጸሎት ሀይል እጅግ ስለሚያምን ነው።
ሀዘኑም ደግሞ አጭር አልነበርም ለአያሌ ቀናት ነበር።ከማዘን ይልቅ
በሰማይ አምላክ ፊት ጾምና ጸለየ ወደ እግዚአብሔርም ተመለሰ። ጾም እና ጸሎት በእግዚአብሔር ላይ የመታመን ምልክት እንደሆነም ገብቶታልና!
ዛሬ አንተም ምንም አይነት ነገር ቢገጥምህ በእግዚአብሔር ፊት ብትጾምና ብትጸልይ መፍትሄ ከእርሱ ይሆንልሀል!
ነህምያ 1:4፤ ይህንም ቃል በሰማሁ ጊዜ ተቀምጬ አለቀስሁ፥ አያሌ ቀንም አዝን ነበር፤ በሰማይም አምላክ ፊት እጾምና እጸልይ ነበር፥
#tesfa #hope
Follow Tesfa on:
Instagram |
Facebook |
Telegram |
TikTok |
Youtube |
Threads |
Pinterest