🫴የሰር ጂም ራትክሊፍ ቅነሳ የቀጠለ ሲሆን እስከ 200 የሚደርሱ ሰራተኞችን ሊያባርር ነው
ማንቸስተር ዩናይትድ በሰር ጂም ራትክሊፍ የቅርብ ጊዜ የወጪ ቅነሳ እንቅስቃሴ ላይ እስከ 200 የሚደርሱ ተጨማሪ ሰራተኞችን ሊቀንሱ ነው እንግሊዛዊው ቢሊየነር ባለፈው አመት ክለቡን 27.7 በመቶ 1 ቢሊዮን ፓውንድ ከፍሎ ገዝተዋል እናም ከራክትሊፍ ሹመት በኋላ በኦልድትራፎርድ ፋይናንስን ለማስተካከል ተስፋ አስቆራጭ እርምጃዎች መውሰድ ጀምረዋል
The Sun ከ100-200 የሚደርሱ ሰራተኞች በመጨረሻው ወጪን ለመቀነስ በሚደረገው ሂደት ከስራ እንደሚባረሩ መረጃን አግኝቻለው ይለናል በክለቡ ውስጥ ባሉ ሁሉም ክፍሎች ተጨማሪ የሰው ቁጥሮች ሲቀንስ የማየት አደጋ ከፈት አለ አንድ ምንጭ ለዘ ሰን ሲናገር “በመጨረሻ እግር ኳስ ንግድ ስራ ነው ነገር ግን በመቶዎች የሚቆጠሩ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ የሚሰሩ ሰዎች ከክለቡ ሊቀነሱ ነው ከሚቀነሱት ሰራተኞች ውስጥ ብዙዎቹ ክለቡን ለአመታት ያገለገሉ እና ከፍተኛ አስተዋፅዖ ያደረጉ ናቸው
"በማንችስተር ካለፈው ዓመት ጀምሮ የሥራ ማጣት ቀላል እየሆነ ነው ይህ ሌላ ትልቅ ውድቀትን ያመጣል በጁላይ ወር ራትክሊፍ ከ1,150 የሰው ሃይል ውስጥ 250 ያህሉን መቀነሱ ይታወሳል ማንችስተር ዩናይትድ ባለፉት ሶስት አመታት 300 ሚሊየን ፓውንድ አጥቷል እና ምንም እንኳን በIneos ስር የረጅም ጊዜ ተስፋ ቢኖርም አሁን ላይ ግን ከባድ እየሆነባቸው ነው
ራትክሊፍ ትላልቅ ቀናትን ወደ ክለቡ ለመመለስ ቆርጧል እና በሜዳ ላይ እና ከሜዳ ውጪ ነገሮችን ለመለወጥ ፍቃደኛ ነው ማን ዩናይትድ ገንዘብ ለመቆጠብ እና ገቢን ለመጨመር ማንኛውንም አማራጭ እየፈተሸ ነው አዲሶቹ ባለቤቶች ቀደም ሲል አወዛጋቢ በሆነ ሁኔታ የቲኬት ዋጋ ጨምረዋል ሰር አሌክስ ፈርጉሰንን ከአምባሳደርነት ሚና አስወግደዋል ቀጣዩ እርምጃም በቡድኑ ከባድ ተቃውሞን እንደሚያስነሳ ይገመታል.
#
@the_red_forever_mv