''የኔ ከሀገር መውጣት የታቀደበት ወይም ሌሎቹ እንደሚሉት ጦርነቱን እየከበደ ስለመጣ የወሰድኩት የመጨረሻ ውሳኔ አልነበረም'' - ፕሬዝዳንት በሽር አላሳድ
ከአንድ ሳምንት በፊት ሀገር ጥለው ወደ ሩሲያ የኮበለሉት የሶሪያው ፕሬዝዳንት በሽር አላሳድ፤ ከሀገር ከወጡ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በሰጡት መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫቸው፣ "ታጣቂዎች ደማስቆ መግባት ሲጀምሩ እኔ ጦርነቱን መቀልበስ በሚቻልበት ሁኔታ ከሩሲያ አጋሮቼ ጋር ለመወያየት ወደ ላቲካ ተጉዣለሁ" ብለዋል።
"በሀሜም አየር ማረፊያ እንደደረስኩ የኛ ኃይሎች የጦር ቀጠናዎችን ጥለው እየወጡ ተመለከትኩ" ያሉት አላሳድ፤ እሳቸው የሄዱበት የሩሲያ ባህር ሀይል ሰፈር በድሮን ጥቃት መመታት እንደጀመረም ገልጸዋል፡፡
ጦሩ ሙሉ በሙሉ መደምሰሱን ተከትሎ የመንግስት ተቋማት መዳከማቸውን ሲያዩ በዚያ ቅጽበት ወደ ሞስኮ እንዲወጡ የሩሲያ ባለስልጣናት ሁኔታዎችን እንዳመቻቹላቸው አብራርተዋል፡፡
ፕሬዝዳንቱ ስልጣን የመልቀቅና ጥገኝነት የመጠየቅ እቅድ በግለሰብም ሆነ በፓርቲ ደረጃ ፈጽሞ አልነበረም ብለዋል፡፡
"ገና ጦርነት ሲቀሰቀስ 14 አመታትን በጦርነት ጨለማ የነበረ፣ የሀገሩን ሉዓላዊነት የህዝቡን ክብር ለማስጠበቅ ብዙ አመታትን እንደደከመ መሪ፣ ሀገሩን ከአሸባሪዎች ለመጠበቅ ከጦር ጀኔራሎች ጋር የቆመ መሪ፤ ድንገት ህዝቡንና ሀገሩን አሳልፎ አይሰጥም" ሲሉ ተናግረዋል።
''የኔ ከሀገር መውጣት የታቀደበት ወይም ሌሎቹ እንደሚሉት ጦርነቱን እየከበደ ስለመጣ የወሰድኩት የመጨረሻ ውሳኔ አልነበረም'' ነው ያሉት። #rtnews
@ThiqahEth