т н σ υ g н т°ρ α ι 𝔫 т ι и g 🎴


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha


B l a c k o u t ☔️

Связанные каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Statistika
Postlar filtri


Ernesto cheguevara


ቼጉቬራ በ20ኛው ክፍለ ዘመን በጣም ተደማጭነት ያላቸው እና አወዛጋቢ ከሆኑ ሰዎች አንዱ ነው። ብዙውን ጊዜ የነፃነት አርማ እና የማርክሲስት አብዮታዊ አራማጅ ተደርጎ ይቆጠራል።

ቼጉቬራ በላቲን አሜሪካ ባሉ ብዙ ሀገሮች ተጉዞ በድህነት እና በጭቆና የሚሰቃዩ ህዝቦችን አይቷል። ይህም ለአብዮታዊ እንቅስቃሴው መነሻ ሆነ። በተለያዩ ሀገራት እየዞረም የተጨቆኑትን ደግፏል ከነዚህም ውስጥ ኩባን ከፊደል ካስትሮና ከሌሎች አብዮተኞች ጋር በመሆን ነፃ አውጥቷታል። ኩባ ውስጥ ከፍተኛ ስልጣን ቢያገኝም አብዮተኞችን ለመደገፍ ወደተለያዩ ሀገራት ጉዞ ጀመሮ አፍሪካ ድረስ መጥቶ ነበር።

በመጨረሻም በቦሊቪያ አብዮት ለመጀመር ባደረገው ሙከራ ሊሳካለት ስላልቻለ በ 39 አመቱ በCIA ሊገደል ችሏል።
ከዛሬ 57 አመት በፊት የሞተ ቢሆንም አሁንም ድረስ የነፃነት ፋኖ ተደርጎ ይቆጠራል።


አንድም ወላጅ ደካማ ልጅ አይፈልግም፤ ማንኛዋም እህት ደካማ ወንድም አትፈልግም፤ የትኛውም ልጅ ደካማ አባት አይፈልግም፤ ሚስቶች በጠቅላላ ደካማ ባል አይፈለጉም።

ሁሉም ጠንካራ እና የበላይ እንድትሆን ይፈልጋሉ። በዚያን ጊዜ ብቻ ደስተኛ፣ ኩራት፣ የደህንነት ስሜት እና መብት ይሰማቸው ይጀምራል። ምክንያቱም ወንዶች የተፈጠሩት ለዚህ ነው።

ለጥቃት የተጋለጡ ሊሆኑ ይችላሉ፤ ofcourse ወንዶችም ሰዎች ናቸው። በባለቤትህ እና በልጆችህ ፊት አለማልቀስህን አረጋግጥ። መነጋገር ካለብህ ሂድ ከአባትህ ወይም ከወንድምህ ጋር ተነጋገር። ጠንካራ ሁን ሁሉም ካንተ እየጠበቀ ነው እንጂ ከፈጣሪ በቀር ብትወድቅ የሚያነሳ አንዳችም የለም!

             ፦Savage words


በህይወት ውስጥ አንድ ሰው ሁሉን ነገር ያጣል ጤና ገንዘብ ጓደኝነት ቤተሰብ ምንም ነገር አይቆይም ሁሉንም ነገር እስከ መጨረሻው አይሄድም።

ማይክ ታይሰን የቦክስ ጀግና ነው ሴት ልጁን በመኪና አደጋ በሞት አጥቷል። በአንዳንድ የህግ ጥሰት ጉዳዮች እዳ ተከማችቶበት ነበር። የገንዘብ ችግር በእርጅና እድሜው ወደ ወጣትነት ስራው እንዲመለስ አደረገው።

ምን አልባት ግጥሚያውን መሸነፍ በሱ መንገድ ላይ አስፈላጊ ላይሆን ይችላል። ነገር ግን ህይወቱን መልሶ ለመገንባት ብዙ ገንዘብ አግኝቷል።

ወድቀን መነሳት አለብን

ማይክ ታይሰን ጊዜ የሰው ልጅ እውነተኛ ጠላት መሆኑን አረጋግጥልን!

ግዜ የሰው ልጅ ጠላት ሲሆን የምታሸንፈውን ጦርነት እንደተሸነፍክ ታልፈዋለህ። በአንድ ዝረራ knackout የምታሶጣውን ውርጭላ ምላሱን እያወጣ ያፌዝብሃል!። ቢሆንም ራስህን ታውቀዋለህ..


“Say money bring bitches, bitches bring lies!”

                  -2PAC


ለ ሀጥያትም ይታነሳል?

እኚ በቀይ መብራት የተንቆጠቆጡ ጎዳናዎች ላይ በውድቅት ሌሊት በለጋነቴ ተፈራርቄባቸዋለሁ ፣ በወጣትነቴ ብዙ ሴሰኛ ወንዶች ቀሚሴ ላይ እጣ ተጣጥለውብኛል!

ዛሬ ላይ ወጣትነቴ ባክና ጉልምስና በተጫጫናቸው ጣቶቼ በ እኩለ ሌሊት ሲጋራዬን እየማግኹኝ በተገተርኩበት ጨረቃን ሸኝቼ አነጋግ ላይ በድካም የዛለ አካሌን ለማሳረፍ ወደ ቤቴ አዘግማለሁ... ለካ ለሀጥያትም ማነስ አለ!!!

የአፀደ


"Let me tell you something. There's no nobility in poverty. I've been a rich man and I've been a poor man. And I choose rich every f*cking time."

-The Wolf of Wall Street 📽️


ምግብ፣ ውሀ ፣መብራት ፣ ማገዶ የለም። ረሀብ ገብቷል። እፍኝ ጥሬ አሮአል። የቤት እቃ እየፈለጡ ማንደድ ተጀምሯል። ከተኩስ ሌላ የሚሰማ ሙዚቃ የለም ተኩሱ ለአንድ አፍታ ፀጥ ሲል አለም እንደሙታን መቃብር ፀጥ ይላል እና መልአከ ሞት መጥቶ በጆሮ ያንሾካሹካል አየሩ የሞት ጠረን ይዞ ይመጣል።

ህፃናት ተርበው ያለቅሳሉ። እናቶች ተጨንቀው ዋይታ ያሰማሉ ። ሽማግሌወች ከደጅ ቁጭ ብለው ይተክዛሉ። ፋብሪካወች ጢስ አይታይባቸውም ፣ማሳወች ፆም አድረዋል ። ገበያወች አይቆሙም። ቢቆሙም ባዶ ነበሩ የቁልቋል ገበያ ።   

✍️ አሮማይ


የመግቢያ ዋጋ
....
በአርሊንግተን ቴክሳስ ከጥቂት ሰአታት በኋላ በሚካሄደውና ከ 50 ዶላር ጀምሮ እስከ 350 ሺህ ዶላር የሚከፈልበት በዛሬው የታይሰንና የፓውል ቦክስ ግጥሚያ ፡ ሁሉም እንደኪሱ መጠን ገብቶ ማየት ይችላል ።
በዚህም መሰረት ከ50 ዶላር የመነሻ ትኬት ጀምሮ $ 70. ... $117 - $185. ..
ከፍ እያለም $200 እና ከዛም በላይ. ... እያለ እያለ ይሄድና ለጥቂትና ለሀብታም ሰወች ብቻ የተዘጋጀው ጥቂት ቦታ ይቀራል ።
......
ይህ ከቦክሱ ሪንግ በጣም ቀርቦ ፡ ምቾት ባለውና በተለየ ሁኔታ በተዘጋጀው በዚህ ቦታ ሆኖ ለመመልከት ግን 350 ,224 ዶላር መክፈል ግድ ነው ።
....
እና ይህን አውጥቶ የፕሪሚየም ትኬቱን የያዘ ሰው ፡ ገና ከበር ጀምሮ የመኪና ማቆሚያ ቦታ ይያዝለታል ። እዛ እንደደረሰም በክብር ወደተያዘለት ቦታ የሚወስዱት ሰወች ተመድበውለት ቦታውን ይይዛል ።
.....
ልክ የክብር ቦታውን ከያዘ በኋላ ፡ የሰለጠኑ አስተናጋጆች ቀርበው ፡ የምግብ ምርጫው ይጠየቃል ፡ የሚጠጣስ ምን ይሁንልህ ይባላል ።
.....
ጨዋታው እስኪጀምር ፡ ከለስላሳ መጠጥ ፡ እስከ አልኮል እንደምርጫው እየተጎነጨ ይቆያል ፡ በዚህ ቆይታው ወቅትም ፡ ከታዋቂ ሰወች ጋር ይገናኛል ፡ ምናልባትም ከማይክ ታይሰንና ከጃክ ፓውል ጋር ፎቶ የመነሳት እድል ይኖረዋል ።
...
ቦክሰኞቹ የፈረሙበት ካርድ ወይም የቦክስ ጓንትና ፡ ይህን እለት የሚያስታውሱ ሌሎች እቃዎች ይሰጠዋል ከዚህም ሌላ ብዙ የተለዩ እንክብካቤዎችን ያገኛል ።

ምክንያቱም. .........................
ይህ ሰው ብቻውን የከፈለው ፡
በሀምሳ ዶላር ሂሳብ ፡ ለሰባት ሺህ ሰወች ትኬት በሚገዛ ገንዘብ ነው ።


-Wasihun tesfaye


ብዙ መጠሪያ ስሞች ያሉት ማይክ ታይሰን የሚሉት ቡጢኛ መቼስ ጉደኛ ሰው ነው። በጉብዝናው ዓመታት ከ400 ሚሊየን ዶላር በላይ ከስፖርቱ አግኝቷል። እንደ Rolls-Royce እና ፌራሪን የመሳሰሉ ከመቶ በላይ ውድ መኪኖች፣ ስድስት ቅንጡ ቤቶች፣ በርካታ የዳይመንድ ጌጣጌጦችን ሲሰበሰብ ኖረዋል። ለልብስ ብቻ ከሶስት ሚሊየን ዶላር በላይ ያወጣ እንደነበር ይነገራል።
ሲዝናና እና ሲገዛ ለነገ አይልም። ከጓደኞቼ ጋር ዎክ እያረኩ ድንገት ወደሆነ መዝናኛ ቦታ እንሂድ ሲሉኝ ለሰከንድ ሳላቅማማ ወዲያው አዲስ መኪና ገዝቼ ይዣቸው ሄዳለሁ ይላል።

ብራዘር እኔ እኮ ገንዘብ አጠፋለሁ..አይበረክትልኝም አትበል። ማይክ ታይሰን አለልህ። ይበትናል ቢባል እንኳ አይገልጸውም። የሚስቱን ገላ መታጠቢያ ገንዳ በተለየ ሁኔታ ለማሰራት ያወጣውን ብትሰማ ታብዳለህ። ለልደቷ ድግስ ብቻ ከ400K ዶላር በላይ አውጥቷል። [ያውም በእነሱ 80'ዎቹ ውስጥ]። በስፖርቱ እጅግ ስኬታማ ነበር። ከ56 ግጥሚያዎች ውስጥ 50ውን አሸንፈዋል። ያውም 44ቱን በዝረራ።

የጉብዝና ወራቱ ሲያልፉ ጡረታ ወጣ። ቁጭ ብሎ ጥሪቱን መብላት ጀመረ። ሱስ አጧጧፈ። ከዕፅ ጋር ተመቸቸ። ቁማር አስከተለ። ዝነኛው ቡጢኛ በአጭር ጊዜ ቀውስ ላይ ቀውስ እየጨመረ ተቃወሰ። በዚህ ላይ አስገድዶ የመድፈር ክስ እና እስር። የሃብቱ ተራራ በፍጥነት ተናደ። የገላ መታጠቢያን በወርቅ ያሰራላት ሚስቱ 9 ሚሊየን ዶላር ወስዳ ተሸበለለች። ተለየችው። ሌላ አገባ። እሷም ሃብቱን ተካፍላ እብስ አለች። ቀሪ ሃብቱን ቁማር እና መጠጥ ቤቶች ተከፋፈሉት። ጭራሽ መኪኖቹን እና ቤቶቹን በሙሉ በመሸጥ ወደ ዕዳ ገባ። 400 ሚሊየን ዶላሩ ጨርሶ ከ30 ሚሊየን በላይ ዕዳ ተሸካሚ ሆነ። በብድር የተገዘችን መኪና ይዞ ለማደሪያ ጓደኛው ቤት በጥገኝነት ገባ።

በወቅቱ በሰጠው አንድ ቃለመጠይቅ እንዲህ አለ
[ ለሰላምታ የሚጠይቀኝ ሰው አልነበረም። የሚፈልጉኝ በሙሉ አበዳሪዎቼ ናቸው። እራሴን ጠላሁ። በጥልቀት መውደቄን አየሁ። የባከነ ሕይወት መምረጤን ተረዳሁ። እንደምንም በምንም ዋጋ ዕዳዬን ከፍዬ ከሰው ዓይን ዞር ማለት..ከአሜሪካ መራቅ ፈልግኩ ]

ዘመን አልፎ ዘመን ሲተካ አዲስ ፀሐይ ወጣች።
ከሱስ አገገመ። ከቁማር እና ዕፅ ራቀ።
በተቋማት ታግዞ ዕዳውን ለመክፈል ዳግም ወደ ቦክሱ ሪንግ ተመለሰ። በተለያዩ ስፖንሰሮችም ታገዘ። ዕዳውንም መክፈል ቻለ። እንዳውም አሁን እስከ 10 ሚሊየን ዶላር የተጣራ ሃብት አፈራ።

እነሆ...
ዛሬ ንጋት በ58 ዓመቱ ከወጣቱ ጄክ ፓውል ጋር ዳግም ቡጢ ይጋጠማል። በዚህም ተጨማሪ ሚሊየን ዶላሮችን ይዝቃል። 70 ሺህ ተመልካች ፊት የሚደረገውን የቡጢ ግጥሚያ Netflix ለ280 ሚሊየን ደንበኞቹ በቀጥታ ያስተላልፋል።

እኔ ጠብ፣ ጠበኞች፣ ቡጢ እና ቡጢኞችም አይመቹኝም። ሰው እንዴት በድብድብ እንደሚዝናና አይገባኝም። ሞሐመድ አሊ በፖለቲካዊ ሃሳቦቹ እና በቀጥተኝነቱ ደስ ይለኛል። በርግጥ ታይሰንም ፖለቲካዊ እሳቤዎቹን በንቅሳቶቹ ይነግረናል። ብዙ ንቅሳቶች አሉት።

[ አርቱር አሼ: በቴኒስ የገነነ ጥቁር
Spike Lee: ነጮች በፊልሞቻቸው ያሳነሳቸውን ጥቁር አሜሪካዊንን በፊልሞቹ ለማቃናት የተጋ
.
.
ማኦ ዜዶንግ
ቼ ጉቫራ
ፊቱ ላይ የ{Maori} ጎሳ ታጋይነት ምልክት ]
እነዚህ ነቅሳቶቹ Political statement ናቸው።

የሆነ ሆኖ...
በዚህኛው ግጥሚያ ግምቴ ለወጣቱ Jake Paul ነው። በመካከላቸው የ30 ዓመት የዕድሜ ልዩነት አለ። ታይሰን ነገሩ ከከበደው ከዚህ ቀደም የሆሊፊልድን ጆሮ ነክሶ ደም በደም እንዳረገው ታሪክ እራሱን ልደግም ይችላል። በተረፈ ማይክ ታይሰን ወድቆ የመነሳት ተምሳሌት ነው።


-ፀሐፊ ጥላዬ ያሚ

-Source mereja




አንዷ ናት አሉ ለምን ሀይማኖት ቀየርሽ ስትባል

" የሆነ ቀን ማታ ላይ ተኝቼ እያሰብኩ የሆነ ጥያቄ ተፈጠረብኝ ከዛ ጓደኛዬን ስጠይቃት መመለስ አልቻለችም ከዛን ቀየርኩ አለች አሉ😂

እና እኔም አሁን ስለ ኢትዮጵያ ታሪክ ከ አራተኛ ክፍል ያቋረጠ ጀለሴን ጠይቄው ሊመልስልኝ ስላልቻለ ዜግነት ልቀይር ነው😂


world giving index ranking (የ አለም ለጋስ ህዝቦች ደረጃ)

በ አለም ዙሪያ በ 142 ሀገሮች የተሰራ ጥናት ነው። ጥናቱ በዋናነት 3 ነገሮች ላይ ያተኮረ ነው። 1, ለተለያዩ ተቋሞች ገንዘብ መለገስ 2, የነፃ አገልግሎት መስጠት(volunteer) 3, የማያውቁትን ሰው በመርዳት ላይ ያደረገ ነው።

ታዲያ ሀገራችን ከ 142 ሀገሮች ውስጥ በ 38ተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች። Indonesia በአንደኝነት ስትመራ Kenya እና Singapore በሁለትና በ ሦስት ይከተላሉ።

ታዲያ ይሄን ነገር ለምን ዛሬ ለማውራት ፈለኩ መሰላቹ። በ አንድ ወቅት በ አዲስ አበባ በተደረገ ጥናት በ ቀን እስከ 2 ሚሊዮን ብር ለ የኔ ብጤ ይሰጣል። በወር ወደ 60 ሚሊዮን ብር ገደማ እንደማለት ነው። የተለያዩ በአላት በሚኖሩበት ጊዜ ደግሞ ንግስ ሲኖር እስከ 8 ሚሊዮን ብር ለ የኔ ብጤ ይሰጣል እንግዲህ ይሄ በ አዲሳባ ብቻ ነው ፣ አጠቃላይ እንደ ኢትዮጵያ ስንት ሊሰጥ እንደሚችል አስቡት?

ሀገራችን ላይ የጥገኝነት መጠን(Dependency rate) አንድ ሰው 7 ሰው ነው የሚያስተዳድረው። ይሄ አንድ ሰው ሲሞት ሰባት ሰው ጎዳና ይወጣል እንደማለት ነው።

ታዲያ አሁን ላይ ከ የትኛውም ወቅት በላይ ብዙ የኔ ብጤ ብዙ ተፈናቃይ በበዛበት ጊዜ ይሄ ሁሉ ሰው በሰው ምፅዋት በሚኖርበት ወቅት እንዴት እንደዚህ ደረጃችን ዝቅ አለ? ቀላል ነው መልሱ የነሱ መስጠት በተቋም ደረጃና በ ተቀናጀ መልኩ ነው የሚከናወነው ። መስጠታቸው መዋቅራዊና በሚታይ መልኩ ነው ቀኝ እጅህ ሲሰጥ ግራ እጅህ አይመልከት የሚል ነገር የለም በግልፅ ይረዳሉ ለተቋም ይለግሳሉ እና የኛም ተቋማዊ መስጠት ቢሆን ስንተኛ ልንሆን እንደምንችል ማሰብ ነው።

ምን ልል ፈልጌ ነው ያው ቸግሮኛል በግልፅ እርዱኝ ደረጃችን ከፍ ይበል😊

የ አፀደ


“አንድን ነገር ስታደርግ ጎበዝ ከሆንክ በፍጹም በነፃ እንዳታደርገው!”

 -Joker ፦The black Knight 📽️


This is how depression is felt by people. Yes it's the symptom of larger causes but what it isn't is just some random shit they go through.
Be kind, be open minded. 🖤

`` The true horror of existence is not the fear of death, but the fear of life. It is the fear of waking up each day to face the same struggles, the same disappointments, the same pain. It is the fear that nothing will ever change, that you are trapped in a cycle of suffering that you cannot escape. And in that fear, there is a desperation, a longing for something, anything, to break the monotony, to bring meaning to the endless repetition of days. ``


—Albert Camus/ The Fall📖


' ' one day we will all die. so lets enjoy the moments we have.. ' '

-Berlin
፦Money heist📽️


' ' Many men
many many many men
Wish death upon me
Lord I don’t cry no more ' '

🎶🤝🏼🥹

406 0 12 3 13

Repost 2022


ጥበብ ከጲላጦስ እስከ ቅፅ³ ድረስ the same chapter ነው ምን አልባት ምዕራፎችሁ ውስጥ የሚነሱት ሰዎችና አሳቦች ይለያዩ ይሆናል። ካልረሳውት ምዕራፎችሁ ሀሳብ ፡ እምነት : ሞት : ሴት : ውበት ነው።

ታድያ ከነዚህ ውስጥ "ውበት" የሚለው chapterን Define የሚያደርጉት ወንዶች ብቻ ናቸው። እና በስጨት ያደርገኛል በእውኑ አለም ስለ ውበት የሚጠበቡት ሴቶች ሆነው ሳለ ይህን ጥልቀት የሚተነትኑት ግን ወንዶች ናቸው። ከዛሬ 5-6 ወር በፊት መሸሸት ብሎ እኔም ከስራ ወደቤት እየገባው በነበረበት ሰዓት ከጀርባዬ ሁለት ሴቶች  እያወጉ ነበር። በርግጥ "ሁለት ሴቶች ተቀምጠው ሲያወጉ ምንም የረባ ነገር አይወጣቸውም" እንዳለው ካህሊል ውይይታቸውን ንቄ አላለፍኩትም ነበር።

እያወሩ ነው አንዷ ሴት ተለቅ ያለች ወደ 30 ዓመት እድሜ የምትጠጋ ነች አንዷ ደግሞ የገጠር ንጹህ ታዳጊ ልጃገረች ነች። ታዳጊዋ ገና ከገጠር እንደመጣችና ብዙም ከተማውን እንዳለመደችው አነጋገሯ ያስታውቃል። Like "origin woman" አዳም ረታ ``በማህፀኗ ዓየር ያላስገባች ድፍን ሴት`` ነች ማለት ይቀላል። እኔ ከፊት ከፊት ስሄድ እነርሱም ከዋላዬ እየተከተሉ ያወጋሉ።  ይህቺ የገጠር ንጹህ ሴት ተናዳ ታወራለች የምታወራው የወንድሟን የማብሸቂያ ስድብ እንዲያቆም ነግራው አለማቆሙን ነው።

ትልቋ ሴት ትጠይቃለች- "ቆይ ምን ልሁን ነው የምትይው?"

ልጅቷ-"በቃ አረጀሽ አስጠሊታ እየሆንሽ ነው ይለኛል"

  "እና ምን ችግር አለው"

"እንዴ ደጋግሞ 'አረጀሽ አረጀሽ' ይላል አትበለኝ ስለው ደግሞ ይብስበታል"

-"ወይኔ እውነቱን እኮ ነው አረጀሽ በቃ"

ስትላት ታዳጊዋ የማጉረምረምና የመከፋት ድምፆችን አሰማች። ለምን ግን¿ 🤔

እላይ በኑሮ ተሰቅላለች የምትባለው ሴት እና ሁሉንም የተረዳች አዋቂ የምትባል ሴት አልያም ምንም የማታውቀው ንጹህ ሴት፤ አንድ የሚያደርጋቸው ፍርሃት ቢኖር የማርጀት ወይንም የውበት መርገፍ ፍርሃት ነው። ይሄ profile ሲደበዝዝ ውብ የሆኑ ነገሮች የማብቂያ ጊዜያቸው እንደደረሰ የማመን አባዜ ተጠናውቷቸዋል። Money Heist የተሰኘው Movie ላይ በርሊን የሚባለው ገፀባህሪ ለአንድ ያልጠነከረ አዕምሮ ላለው ወጣት ምክር ቢጤ ይወረውርበታል። ልጁ አብራው በምዘርፈው ሴት ፍቅር ክንፍ ብሏል። ወላ ከእርሷ ጋር አግብቶ ልጅ ወልዶ መኖር አላማው አድርጎታል። እና በሁለቱ መኃከል ያለው ነገር የእውነት እንደሆነ እና ልጆች እንደሚያፈሩ ለበርሊን ይነግረዋል። በርሊንም ያለው ይሄን ነው። ቃል በቃል ባይሆንም የማስታውሰውን ማለት የፈለገውን ነው የጻፍኩት።

`` ከእርሷ ጋር አንድ ላይ ሆናችሁ የመጀመርያ ልጃችሁን አርግዛ መጣው መጣው ብሏት ሆስፒታል አልጋ ላይ በህመም እያማጠች ሳለ የምታስበባቸው የተወሰኑ ነገሮች ቢኖሩ ህመሟን እና የእርጅና መንገድ ላይ እንደሆነች ብቻ ነው። ታድያ የሚመጣው ልጅ የደስታ እሳቤ ቢሆንም ከሁለት ጭን እንደወጣ ኒኩለር ነው። ሁለምንም ነገር ከነበር ወደአልነበር ይለውጠዋል። ምክንያቱም ከእንግዲህ እንደበፊቱ እሆናለው የልጄ አባትም በድሮ ፍቅሩ ይቀጥላል የሚለው አሳብ እንደማይሆን በመገንዘብ ባሏን የማጣት ቀሽም የመክሸፍ ስሜታዊ ሀሳብ ይከባታል!``

በመጨረሻም ውበት ምንድነው ብዬ መጠየቅ የምፈልገው ሴትን ልጅ ነው። ስለ ውበት ከሴት በላይ የሚጠበብ የለም እንዴት ላምጣው እና እንዴት ይዘቱን ሳይለቅ ለዓመታት ላቆየው የሚለው የማሰብ ሂደት ለሴት ልጅ የተሰጠ የእግዜር ሰይጣን ነው። ቅዱስነቱ በእድሜ የታጠረ እርኩሰት እንደማለት ነው።


-እሺ ፕሮፌሰር ምን ምን ትምህርት ነው የምታስተምሪው?"

እ..History.. Ethics.. philosophy.. About sex..

-አዎ ስለ sex እሱ ዋነኛውና አሰፈላጊው ክፍል ይመስለኛል። ሁለቱንም ፆታ የሚያሳትፍ። ስለ Headache ቀልድ ሰምተሻል፤ አየሽ ቀልድ አስቂኝ እንዲሆን በውስጡ አንዳንድ እውነቶች ሊኖሩት ይገባል። ምን መሰለሽ በሚስቱ የራስ ምታት ህመም ምክንያት ወሲብ ካደረገ የቆየ ባል?"

      ራስምታት?

-አዎ ባል ነው አሉ ወደቤት ቀጥታ እንደገባ ሚስቱን፦
"ውዴ ቤት ነሽ? አንዳንድ አስፕሪንና ፓራስታሞል ይዤልሽ መጥቻለው።

ሚስት፡- ምን ሆነሃል ራስ ምታት አላመመኝም እኮ?

ባል፡- እንግዲያውስ እንለጣለጥ 😊


       (  Money Heist 📽️)




ግጥማቸው ትልቅ ሀሳብ ከያዙ ዘፈኖች መካከል ይካተታል አድምጡት...🎶

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.