TIKVAH-SPORT


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: Sport


ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ስፖርት ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የስፖርታዊ መረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
በዚህ ቻናል ሀገራዊ እና አለም አቀፋዊ የስፖርት መረጃዎች ይዳሰሱበታል።
ለመረጃ እና ማስታወቂያ +251926797469

Bog‘liq kanallar  |  O‘xshash kanallar

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
Sport
Statistika
Postlar filtri


አርጀንቲና ከቡርኪናፋሶ ቅሬታ ቀረበባት !

አርጀንቲና ትላንት ሌሊት ከቡርኪናፋሶ ያደረገችውን የወዳጅነት ጨዋታ 7ለ0 በሆነ ውጤት አሸንፋለች።

አርጀንቲና ለቡርኪናፋሶ ተጨዋቾች ሙሉ የጉዞ ወጪ ብትሸፍንም ዝቅተኛ ክፍያ እና ከደረጃ በታች ያለው በረራ መሆኑ ተጨዋቾቹን አላስደሰተም።

በዚህ ምክንያት የቡርኪናፋሶ ተጨዋቾች ወደ አርጀንቲና አንጓዝም በሚል ሊቀሩ ችለዋል።

የቡርኪናፋሶ ብሔራዊ ቡድንም ለጨዋታው በይበልጥ ከ 23አመት በታች ቡድኑን ልኳል።

ተጨዋቾቹ አርጀንቲና የደረሱት ከጨዋታው ሶስት ሰዓት ቀደም ብለው ሲሆን ያለ እረፍት ጨዋታውን ማድረጋቸው ተገልጿል።

የቡርኪናፋሶ መገናኛ ብዙሃን ጨዋታውን የወዳጅነት ሳይሆን የውርደት ነው ሲሉ በዘገባዎቻቸው ገልፀውታል።

የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሊዮኔል ስካሎኒ ጨዋታው ተመጣጣኝ እንዳልሆነ እንደተሰማቸው ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe


“ ለሮናልዶ የተለየ ክብር ነው ያለኝ ” ዚነዲን ዚዳን

የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ዚነዲን ዚዳን ለክርስቲያኖ ሮናልዶ የተለየ ክብር እንዳላቸው ገልጸዋል።

“ ሮናልዶ አስደናቂ ዋንጫዎችን እንዳሸንፍ አድርጎኛል “ ያሉት ዚዳን “ ለአንተ ኮፍያዬን ዝቅ አደርጋለሁ " ሲሉ ተናግረዋል።

አክሎም “ እሱ ለነበረው ታላቅ የእግር ኳስ ህይወት ምስጋና ማቅረብ አለብን ከእኔ ጋር ስለነበር እድለኛ ነበርኩ "ብሏል።

“ ለሁሉም ተጨዋቾች በተለይ ለክርስቲያኖ ሮናልዶ የተለየ አክብሮት ነው ያለኝ ” ዚነዲን ዚዳን.

@tikvahethsport     @kidusyoftahe


“ ቤሊንግሀም ከምንጊዜም ምርጥ ተጨዋቾች አንዱ ይሆናል ” ሮይ ኪን

የቀድሞ የማንችስተር ዩናይትድ ተጨዋች ሮይ ኪን ጁድ ቤሊንግሀም ትልቅ ደረጃ ያለው ተጨዋች ነው በማለት ተናግሯል።

“ ቤሊንግሀም ከፍተኛ ደረጃ ላይ ያለ ተጨዋች ነው “ ያለው ሮይ ኪን “ እሱ አቻ የማይገኝለት ጥንካሬ ፣ በራስ መተማመን ይዟል ” ብሏል።

አክሎም “ እሱ ከምንግዜውም ምርጥ ተጨዋቾች መካከል አንዱ ይሆናል ብዬ አስባለሁ "ሲል ገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe

23k 0 1 2 217

ስፔን በአሸናፊነቷ ቀጥላለች !

በአውሮፓ ኔሽንስ ሊግ ስፔን ከቼክ ሪፐብሊክ ጋር ያደረገችውን ጨዋታ 3ለ1 በሆነ ውጤት አሸንፋለች።

የስፔንን የድል ግቦች ላሚን ያማል ፣ ሮድሪ እና ሚኬል ሜሪኖ ከመረብ ሲያሳርፉ ለቼክ ጂሪ ስላማ አስቆጥሯል።

ስፔን ሶስት የምድብ ጨዋታዎችን በማሸነፍ በዘጠኝ ነጥብ ምድቡን እየመራች ትገኛለች።

የስፔን ብሔራዊ ቡድን ያለፉትን ተከታታይ 41 ጨዋታዎች አልተሸነፈም።

በሌሎች ጨዋታዎች

- ስኮትላንድ ሰሜን መቄዶንያን 2ለ0
- ስዊዘርላንድ ስሎቬኒያን 2ለ1 ማሸነፍ ችለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe


ሶስቱ አናብስት በሰፊ የግብ ልዩነት አሸነፉ !

እንግሊዝ ከክሮሽያ ጋር ያደረገችውን የኔሽንስ ሊግ ጨዋታ 7ለ0 በሆነ ሰፊ ውጤት ማሸነፍ ችላለች።

ለሶስቱ አናብስት የድል ግቦችን ሀሪ ኬን 2x ፣ ቡካዩ ሳካ 2x ፣ ቤሊንግሀም ፣ ጎርደን እና ሮጀርስ አስቆጥረዋል።

ጁድ ቤሊንግሀም በጨዋታው ሶስት ለግብ የሆነ ኳስ አመቻችቶ ሲያቀብል አንድ ግብ ከመረብ አሳርፏል።

ሀሪ ኬን ለእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን 89ኛ ጎሉን ማስቆጠር ችሏል።

ሀሪ ኬን ከ 1948 በኋላ በ 6 ተከታታይ የሜዳ ውጪ ጨዋታዎች ግብ ያስቆጠረ ቀዳሚው እንግሊዛዊ ተጨዋች ሆኗል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe


“ ሮናልዶ የፖርቹጋል ትልቁ ምልክት ነው ” ፈርናንዴዝ

ፖርቹጋላዊው አማካይ ብሩኖ ፈርናንዴዝ ክርስቲያኖ ሮናልዶ የብሔራዊ ቡድኑ መልክት ነው ሲል ተናግሯል።

“ ሮናልዶ ሁልጊዜም የብሔራዊ ቡድኑ ትልቁ ምልክት ይሆናል “ ያለው ፈርናንዴዝ “ እሱ የአለም እግርኳስ ተምሳሌት ነው "ብሏል።

አክሎም “ እሱ የሁሉም ፖርቹጋላዊ አክብሮት ይገባዋል ፤ ምንም ቢፈጠር ትልቁ ምልክታችን መሆኑ እንደማይቀየር ነግሬዋለሁ “ ሲል ገልጿል።

ብሩኖ ፈርናንዴዝ አያይዘውም በብሔራዊ ቡድኑ ውስጥ መከፋፈል እንዳይኖር ሁለቱም ወገኖች ነገሮችን በጥሩ ሁኔታ እንዲፈቱ ጠይቋል።

“ ሮናልዶ በእርግጠኝነት በታሪክ ከታዩ ታላቅ ተጨዋቾች መካከል እና ፖርቹጋላዊያን ልብ ውስጥ የተረጋገጠ ቦታ አለው “ ፈርናንዴዝ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe


WANAW SPORT WEAR dan repost
🌿✨Baga Ayyaana Irreechaa Nagaan Geessan!✨🌿
እንኳን ለኢሬቻ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

🔗ማህበራዊ ገጾቻችን🔗
Instagram|Facebook |TikTok |X|Youtube
⭐️| #WanawSportwear |🇪🇹በኢትዩጵያ የተመረተ


“ ስለ ሮናልዶ ከጨዋታው በኋላ እንነጋገራለን ” ጆርጅ ጄሱስ

“ ሮናልዶ የፖርቹጋል ምልክት ነው "

የፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ጆርጅ ጄሱስ ከነገው የኖርዌይ ጨዋታ በፊት ከጋዜጠኞች ጋር ቆይታ እያደረጉ ይገኛሉ።

ከሮናልዶ ጋር ችግራቸውን ለመፍታት ዝግጁ ስለመሆናቸው የተጠየቁት አሰልጣኙ “ አሁን ትኩረቴ ጨዋታው ላይ ነው “ ብለዋል።

“ ነገርግን ይሄን ስል የክርስቲያኖ ሮናልዶን ጉዳይ ወደጎን እያደረግኩ ነው ማለት አይደለም “ ሲሉ ተናግረዋል።

“ ሮናልዶ የብሔራዊ ቡድኑ እና የፖርቹጋል ምልክት ነው ” ያሉት አሰልጣኙ " ከጨዋታው በኋላ ስለዚህ ጉዳይ ለመነጋገር ጊዜ ይኖረናል "ብለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe


ቡርኪናፋሶ በወጣት ቡድኗ ትጫወታለች !

አፍሪካዊቷ ሀገር ቡርኪናፋሶ ዛሬ ሌሊት ከአርጀንቲና ጋር የወዳጅነት ጨዋታዋን ታደርጋለች።

ይሁን እንጂ የብሔራዊ ቡድኑ ተጨዋች ባላቸው የፋይናንስ ጥያቄ ምክንያት ስብስቡን ለቀው እንደሄዱ ተገልጿል።

በዚህም ምክንያት ቡርኪናፋሶ ለጨዋታው ከ 23ዓመት በታች ቡድኗን ለመላክ ማሰቧ ተነግሯል።

ወጣት ብሔራዊ ቡድኑ በጨዋታው ዕለት ዛሬ ወደ አርጀንቲና ያመራል ተብሎ ይጠበቃል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe

47k 0 0 3 216

ሉሲዎቹ በሰፊ የግብ ልዩነት አሸነፉ !

የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ከሲሼልስ ጋር ያደረገውን ሁለተኛ የወዳጅነት ጨዋታ 10ለ0 በሆነ ሰፊ ውጤት አሸነፈ።

በጨዋታው ዳግማዊት ሰለሞን ሶስት ግቦችን በማስቆጠር ሀትሪክ ሰርታለች።

ቀሪዎቹን የሉሲዎቹ ግቦች እሙሽ ዳንኤል 2x ፣ ቤተልሔም መንተሎ ፣ ቱሪስት ለማ ፣ ቤተልሄም በቀለ ፣ ረድኤት አስረሳኸኝ እና አሻንታ ማሪ (ራሷ ላይ) አስቆጥረዋል።

ብሔራዊ ቡድኑ ከሲሼልስ ያደረጋቸውን ሁለት የወዳጅነት ጨዋታዎች 26ለ0 ማሸነፍ ችሏል።

ሉሲዎቹ በቀጣይ የ 2028 ኦሊምፒክ ሴቶች እግር ኳስ ማጣርያ ጨዋታቸውን ከሩዋንዳ ጋር ያደርጋሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe


በአየር ላንድ ጋዜጣዊ መግለጫ ምን ተፈጠረ ?

አየር ላንድ ነገ ከእስራኤል ጋር ከምታደርገው ጨዋታ በፊት በነበረ መግለጫ ላይ አለመግባባት ተፈጥሮ ነበር።

በመግለጫ ወቅት በአየርላንድ እና እስራኤል ጋዜጠኞች መካከል አለመግባባት ተፈጥሯል።

አንድ የእስራኤል ጋዜጠኛ የአየርላንድ ተጨዋቾች ተጨዋቾቻችንን ' ዝንጀሮ ' በማለት የዘረኝነት ጥቃት አድርሰውባቸዋል ሲሉ ጠይቋል።

የአየርላንድ እግርኳስ ፌዴሬሽን እውነት አይደለም ሲል ውድቀ በማድረግ ጋዜጠኛው ንግግሩን እንዲያቋርጥ አድርጓል።

ቀጥሎም በተፈጠረው ሁከት ምክንያት ጋዜጣዊ መግለጫው እንዲቋረጥ ተድርጓል።

የብሔራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ የሀገሪቱ ጋዜጠኞች ብቻ በተገኙበት መግለጫ ለመስጠት ወደ ሌላ ቦታ መሄዳቸው ተገልጿል።.

@tikvahethsport     @kidusyoftahe


“ የባሎን ዶር እጩ መሆን አይገባኝም ” ቮዚንሀ

የኬፕ ቨርዴ ብሔራዊ ቡድን ግብ ጠባቂ ቪዚንሀ የያሲን ትሮፊ እጩ መሆኑ አይገባኝም ሲል ገልጿል።

“ ብዙዎች ፍትሀዊ አይደለም ሲሉ ሰምቻለሁ እኔም እሱ ተሰምቶኛል “ ሲል ቮዚንሀ ተናግሯል።

" ዜናውን ሳይ ቀልድ መስሎኝ ነበር " ያለው ቮዚንሀ “ ምክንያቱም በትልቅ ሊግ ስለሚጫወቱ ጥሩ ግብ ጠባቂዎች ክብር አለኝ "ብሏል።

" በዚህ እድሜዬ ይህ መፈጠሩ ከዩኒቨርስ የመጣ ስጦታ ነው ፣ የመረጡኝን አመሰግናለሁ “ሲል ጨምሮ ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe


“ በባርሴሎና ጫማ መስቀል እፈልጋለሁ ” ጋቪ

የባርሴሎናው የመሐል ሜዳ ተሰላፊ ጋቪ የእግርኳስ ህይወቱን በአንድ ክለብ ማጠናቀቅ እንደሚፈልግ ገልጿል።

“ በባርሴሎና ጫማዬን መስቀል እፈልጋለሁ በአንድ ክለብ ማጠናቀቅ እፈልጋለሁ ” ሲል ጋቪ ተናግሯል።

አክሎም “ ለእኔ ስኬት ማለት በባርሴሎና ለረጅም አመት መጫወት ያለኝን ሁሉ መስጠት መቻል ነው "ብሏል።

ጋቪ አያይዞም የገጠመው ተደጋጋሚ ጉዳት የማሰቢያ ጊዜ እንደሰጠው እና አሁን ትንሽ የተረጋጋ እንዲሆን እንደረዳው ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe


Baga Ayyaanaa #Irreechaa geessan !

Ayyaana Gaari !  Happy Irreechaa !

#Irreechaa2019

#TikvahEthiopiaFamily

@tikvahethiopia


“ ጃክዌት ደፋር ተከላካይ ነው ” ዚነዲን ዚዳን

የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ዚነዲን ዚዳን ጄርሚ ጃክዌት ትላንት ምሽት ያሳየውን አቋም አድንቀዋል።

“ ያሳየው ደረጃ አስደናቂ ነበር ” ያሉት ዚነዲን ዚዳን “ በጣም ደፋር ተጨዋች ነው ሲሉ ገልፀውታል።

አክለውም " ወደፊት መውጣት እና ከአካባቢው መራቅን ፈፅሞ አይፈራም በአንድ ለአንድ ግንኙነትም ጠንካራ ነበር " ብለዋል።

በአጠቃላይ “ እሱ ሌላ አስደናቂ አቋሙን ነበር ያስመለከተን “ ሲሉ ለሊቨርፑሉ ተከላካይ ጃክዌት ያላቸውን አድናቆት ገልጸዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe


#NationsLeague

በኔሽንስ ሊግ መርሐ ግብር ቤልጂየም ቱርኪዬን 3ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችላለች።

የቤልጂየምን የማሸነፊያ ግቦች ኬቨን ዴ ብሮይን 2x እና ሮሜሎ ሉካኩ አስቆጥረዋል።

ፈረንሳይ ከጣልያን ያደረጉት ተጠባቂ ጨዋታ 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቋል።

የፈረንሳይን ግብ ኦሊሴ ሲያስቆጥር አሌሳንድሮ ባስቶኒ ጣልያንን አቻ አድርጓል።

በሌላ ጨዋታ ስዊድን ከ ቦስኒያ ጋር 1ለ1 ሲለያዩ ፖላንድ ሮማንያን 6ለ0 በሆነ ሰፊ ውጤት አሸንፋለች።

ቪክቶር ዮኬሬሽ ለብሔራዊ ቡድኑ ባደረጋቸው ያለፉት ሶስት ጨዋታዎች ሶስት ግቦችን አስቆጥሯል።

ሮበርት ሌዋንዶውስኪ ለፖላንድ ሶስት ግቦችን አስቆጥሮ ሀትሪክ መስራት ችሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe


ራፊና የወሩ ምርጥ ሽልማት አሸንፏል !

የባርሴሎና የፊት መስመር ተሰላፊ ራፊና የመስከረም ወር የስፔን ላሊጋ ምርጥ ተጨዋች በመባል ተመርጧል።

ራፊና በተከታታይ ወር የወሩ ምርጥ ተጨዋች ሽልማት አሸንፏል።

ጥሩ የውድድር አመት እያሳለፈ የሚገኘው ራፊና በመስከረም ወር ባደረጋቸው የሊግ ጨዋታዎች :-

⏩ ሰባት ግቦችን አስቆጥሮ
⏩ ሁለት ለግብ የሆነ ኳስ አመቻችቶ አቀብሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe


ሮናልዶ እና ኤሪክ ቴን ሀግ ለምን ተጋጩ ?

ከአመታት በፊት በክርስቲያኖ ሮናልዶ እና አሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሀግ መካከል አለመግባባት ነበር።

በወቅቱ አሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሀግ ሮናልዶን ተጠባባቂ ያደረጉ ሲሆን በኋላም ክለቡን እንዲለቅ ምክንያት ሆኗል።

አሁን ላይ ፍሬድ በሰጠው አስተያየት በሁለቱ መካከል የነበረው አለመግባባት የአጨዋወት እንደነበር ገልጿል።

ፀቡ ቀላል ነበር ያለው ፍሬድ “ ሮናልዶ ለማጥቃት አይሮጥም ነበር በዚህ ምክንያት እሱን አላጫወተውም ተጠባባቂ አድርጎታል " ብሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe


“ ቴንሀግ ተጨዋች አያያዝ ላይ ደካማ ነበር ” ፍሬድ

የቀድሞ የማንችስተር ዩናይትድ አማካይ ፍሬድ አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ ከተጨዋቾች ጋር ስምምነት እንዳልነበራቸው ተናግሯል።

ፍሬድ ቴን ሀግ የማንችስተር ዩናይትድን ተጨዋቾች የመሩበትን መንገድ “ በጣም ደካማ "ሲል ገልፆታል።

“ እሱ ከሁሉም ጋር መነታረክ ይወድ ነበር “ ያለው ፍሬድ " ከእኔ ፣ ሮናልዶ ፣ ካሴሚሮ ፣ ራሽፎርድ ጋር ይጨቃጨቅ ነበር "ብሏል።

አክሎም “ ኔዘርላንዳዊ ተጨዋቾች ብቻ ነበሩ የመጫወት እድል የሚያገኙት " ሲል ተናግሯል።

ከተጨዋቾች አያያዝ ውጪ ቴን ሀግ “ በታክቲክ ካሰለጠኑኝ ምርጥ አሰልጣኞች አንዱ ነው "ሲል አወድሷል።

“ እሱ የሚያመጣው ተጨዋች ኔዘርላንዳዊ ፣ የአያክስ እና ከራሱ ወኪል ነበር እንግዳ ነገር ነበር “ ፍሬድ

@tikvahethsport          @YisakAH


የዩናይትድ ተጨዋቾች ከሲቲ ካሳ ይፈልጋሉ !

ማንችስተር ዩናይትድ ማንችስተር ሲቲ ደንብ በመጣሱ ምክንያት የደረሰበትን የኢኮኖሚ ኪሳራ ገምግሟል።

ክለቡ ማንችስተር ሲቲ ጥፋተኛ መባሉን ተከትሎ በውስጥ የደረሰበትን ተፅዕኖ ሲገመግም ቆይቷል።

የማንችስተር ዩናይትድ ተጨዋቾች በበኩላቸው ካሳ ሊጠይቁ እንደሚችሉ ተገልጿል።

ተጨዋቾቹ ማንችስተር ዩናይትድ ሻምፒየንስ ሊግ አለመግባቱን ተከትሎ ደሞዛቸው በ 25% ቀንሶ ነበር።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.