"ከአማራ ክልል ተማሪዎች 60 በመቶ የሚጠጉት ከትምህርት ገበታ ውጭ ናቸው።" - የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር
በአማራ ክልል ከሚገኙ ተማሪዎች ውስጥ 59.8 በመቶ የሚሆኑት፤ በዘንድሮው የትምህርት ዘመን “ከትምህርት ገበታ ውጭ” መሆናቸውን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ገልፀዋል።
በክልሉ ከሚገኙ ትምህርት ቤቶች መካከል 32 በመቶ የሚሆኑት ከመማር ማስተማር ተልዕኮዋቸው መስተጓጎላቸውንም በክልሉ ም/ቤት መደበኛ ጉባኤ ላይ የግማሽ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ያቀረቡት ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ ተናግረዋል።
በክልሉ በአሁኑ ወቅት “በተጨባጭ በመማር ማስተማር ሂደት እየተሳተፉ” የሚገኙ ተማሪዎች ብዛት 2.78 ሚሊዮን እንደሆኑ ጠቅሰዋል።
በአማራ ክልል በዘንድሮው በጀት ዓመት ለመመዝገብ ታቅዶ የነበረው አጠቃላይ የተማሪዎች ብዛት 7.1 ሚሊዮን እንደሆነ የክልሉ ትምህርት ቢሮ መረጃ ያመላክታል።
በአማራ ክልል በ2017 በጀት ዓመት መደበኛ የመማር ማስተማር ተግባራቸውን ያከናወኑ ትምህርት ቤቶች ብዛት 7,444 መሆኑን ርዕሰ መስተዳድሩ በሪፖርታቸው ጠቅሰዋል።
በአማራ ክልል ያሉት ትምህርት ቤቶች ብዛት 10,983 ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 32 በመቶ በሚሆኑት ትምህርት ቤቶች ከመማር ማስተማር ተልዕኳቸው ተስተጓጉለው መቆየታቸው ተገልጿል። #ኢትዮጵያ_ኢንሳይደር
ትምህርት ሚኒስቴር ✅
✅ ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ
🔻
https://t.me/Tmhrt_Ministers🔻
https://t.me/Tmhrt_Ministers