ከአመት በላይ በጦርነት ውስጥ የሚገኘው አማራ ክልል አዲስ የፖሊስ ምልመላ ጥሪ ማቅረቡን ተመልክተናል።
" ወጣቶች የተከፈተዉን የስራ ዕድል በመጠቀም ህዝብን የማገልገል ክብር መገለጫ ወደሆነው የፖሊስነት ሙያ ኑ" በማለት ተከታዩን የምልመላ መስፈርት አስቀምጧል።
1. ዜግነቱ ኢትዮጲያዊ የሆነ/ች
2. ለፌዴራሉና ለክልሉ ሕገ-መንግስንቱና ሕገ-መንግስቱን መሰረት አድርገው ለወጡ ሕጎች ተገዥና ታማኝ የሆነ/ች፣
3. ቢያንስ 10/12ኛ ያጠናቀቀ/ች፤ ያላገባ/ች፣ያልወለደ/ች
4. ከማናቸውም ደባል ሱሶች የፀዳ/ች፣ መልካም ስነ ምግባር ያለው/ት
5. ከሚኖርበት ቀበሌ አስተዳደር የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል/የምትችል፣
6. ለፖሊስነት የሚያበቃ ሙሉ ጤናማ መሆኑ/ኗ በህክምና የተረጋገጠ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል ወይም የምትችል፣
7.ዕድሜው/ዋ ከ18 እስከ 25 ዓመት፣
8. የማነኛውም የፖለቲካ ድርጅት አባል ያልሆነ/ች፣
9. ቁመት ለወንድ 1.65 ሜትር በላይ የሆነ፣ ለሴት 1.60 ሜትር በላይ የሆነች፣
10. ክብደት ለወንድ 50-70 ኪ.ግ፤ ለሴት 45-65 ኪ.ግ
11. የ7 ዓመት የሥራ ውል ግዴታ በመግባት ሥልጠናው ሲጠናቀቅ በየትኛውም የክልሉ አካባቢ ተመድቦ/ድባ ለመሥራት ፈቃደኛ የሆነ/ች፣
12. ከአሁን በፊት በወንጀል ተከሶ/ተከሳ ያልተቀጣ/ች ወይም የወንጀል ክስ የሌለበት ወይም የሌለባት፣
13. ከአሁን በፊት በማንኛውም የፖሊስ እና የመከላከያ ሰራዊት ተቋም ሥልጠና ያልወሰደ/ሰደች፤ አባል ሆኖ/ና የማያወቅ ወይም የማታውቅ፤
14. ያላገባ እና ያልወለደ ወይም ያላገባች እና ያልወለደች፣
15. ደሞዝ 5,283 የቀለብ አበል 2200 ቀድምሩ 7,483 ተቋሙ ነፃ ህክምና ያመቻቻል፤
ማሳሰቢያ፦
ማንኛውም ዕጩ ተመልማይ በምዝገባ ወቅት ከላይ ከተገለፁት መመዘኛዎች በተጨማሪ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች ይዞ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
1. የትምህርት ማስረጃ ዋናውንና የማይመለስ 1 ፎቶኮፒ፣
2. ከ2 ዓመት በላይ ነዋርነትን የሚያመለክት የቀበሌ ነዋሪነት መታወቂያ ካርድ ይዞ መቅረብና መመዝገብ ይጠበቅበታል፣
3. ምዝገባው በሥራ ቀንና በሥራ ሰዓት በክልሉ በሚገኙ የወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤትና ጣቢያዎች ይሆናል፤
https://www.facebook.com/profile.php?id=61569879454961&mibextid=ZbWKwLቤተሰብ❤ በቅንነት ሰብስክራይብ በማድረግ ተባበሩ 👇
https://www.youtube.com/channel/UCrdWHrcXNEhMfbp1ucgxd1gአዳዲስ መረጃዎች እንዲደርስዎ Join አድርገው👇በዚህ ይከታተሉ
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4💎ጥቆማና ማስታወቂያ 👇መቀበያ
https://t.me/wasumohammed