«ታይፕ አደራረግሽ ነዋ! ፊደሎቹን እያፈላለግሽ ነው የምትጫኝያቸው… አያቴ ነበር እንደዚህ የሚፅፈው . . . ይገርማልኮ አሁን አንች የተማርሽ ዘመናዊ ታዋቂ የፊልም ተዋናይ ነሽ! ታይፕ ማድረግ እንኳን በወጉ አትችይም! ይመስለኛል ታይፕ አደራረግ ወደፊት ማስተማር ሳይኖርብኝ አይቀርም!
ፊደል በስጨት አለች « አሁን የጀመርነውን እንጨርስ ወይስ ልተኛ ?» አለቻት በቁጣ !
«አትቆጭ ፊደል! ኢትዯጵያዊያን አለመቻላችሁ ሳይሆን አትችሉም መባላችሁ ያበሳጫችኋል! ቀኑን ሙሉ ስልክና ኮምፒውተር ላይ አቀርቅረሽ እየዋልሽ ታይፕ ማድረግ እንኳን በስርዓት አለመቻልሽ ሊያስቆጭሽ ነበርኮ የሚገባው!
ትልቅ እውቀት መሆኑ ነው? አለች ፊደል
ነውና! እኔ በአስራሁለት ዓመቴ ነው ጥንቅቅ አድርጌ ኪቦርድ አጠቃቀም የቻልኩት
«የራስሽ ጉዳይ ወሬ አለብሽ. . . በነገራችን ላይ እየረዳሁሽ መሆኑን አትርሽ »
«ሂሂሂሂሂ ሂጅ ካሜራ ማኖችሽን ጥሪና "ኒላን እየረዳኋት" ብለሽ ነገ ለአድናቂዎችሽ እዩልኝ በይ! . . . እሽ እያሳደድሽ የአባቴን ስም ፃፊ!
እንዲህ እያሉ ለኒላ አዲስ አካውንት ከፈቱ! በመጨረሻም ኒላ በምትነግራት መሰረት የኒላን ቤተሰቦች አካውንት ከፈቱ ! ኒላ መጀመሪያ ያየችው የወንድሟን አካውንት ነበር . . . እንደነፍሷ የምትወደውን ወንድሟን ! ፕሮፋይሉ ላይ «ውቧ እህቴን ካጣኋት ሁለት ዓመት ሆነ እንወድሻለን» ከሚል የእንግሊዝኛ ፅሁፍ ስር እጅግ ውብ የሆነች ሴት ፎቶ ይታያል!
ፊደል ልቧ ስንጥቅ አለ! ካሰበቻት በላይ ቆንጆ ሴት ነበረች ! ፀጉሯ በቀኝ ትከሸዋ በኩል አልፎ ፊት ለፊት እየተዘናፈለ ይወርድና ተፋዋ አካባቢ ድረስ ቁልቁል ወርዷል! ፈገግታዋ ሲበዛ ውብ ፊቷን የበለጠ አስውቦታል! የለበሰችው ደማቅ ቀይ የህንድ ባህላዊ ልብስ ድምቀቷን አጉልቶት ፎቶ ሳይሆን ህያው ስጋና ደም ያላት ፍጥረት አስመስሏታል!
«አንች ነሽ ? » አለች ፊደል ! ኒላ ግን ማልቀስ ጀምራ ነበር!
ፊደል በዝምታ ቆየች! ኒላ ለቅሶዋን አቁማ ሌላ ስም ነገረቻት! ፊደል ስሙን አስገብታ ስትከፍተው አንድ መልከመልካም ወጣት ከአንዲት ሴት ጋር በባህላዊ የሰርግ ልብስ አምሮ የሚታይበት የሰርግ ፎቶ ስክሪኑን ሞላው! ከጎኑ ቆንጆ ሚስቱ በፈገግታ ቁማለች!
ኒላ « ይሄ ቀልድ ወይም ህልም መሆን አለበት » አለች በቀስታ ! ከዚያም ድንገት «ውሻ የውሻ ልጅ » ብላ ጮኸች በጩኸቱ የፊደል ሰውነት ተናወጠ!
«ምንድነው ኒላ ?» አለች በፍርሃት ! «ፍቅረኛየ፣ ባቡር ላይ አብረን ሞትን ያልኩሽ ፍቅረኛየ ! ገና ከሞትኩ በሁለት ዓመቴ ጓደኛየን አግብቶ ነዋ! ይሄው አይታይሽም ይች ውሻ ጓደኛየ ናት . . . ጓደኛየ ! የራሴ ጓደኛ »
ፊደል ግራ ገባት « ቆይ ባቡሩ ላይ ሞተ አላልሽኝመረ . . .? »
«እኔጃ እኔ ስለሞትኩ የሞተ ነው የመሰለኝ ! አላውቅም . . . ምናልባትም ውሻ ቶሎ አይሞትም » ኒላ ዝም አለች ! ረዥም ዝምታ !
ኒላ አለች ፊደል የምታደረገው ግራ ገብቷት መልስ የለም . . . ኒላ ትሰሚኛለሽ ? ዝምታ ! በቀስታ ላፕቶፑን ዘግታ ወደምኝተዋ ሄደች! ዝምታው ያስፈራ ነበር።
ይቀጥላል!
@wegoch@wegoch@paappii