ይህም ባህሌ ነው
ከሃያ ስድስት አመት በፊት፣ ገና ወደ ሆላንድ እንደመጣሁ ጓደኞቼ 'አምስተርዳም ውስጥ የምናሳይሽ ድንቅ ነገር አለ' ብለው ይዘውኝ ሄዱ። ከሮተርዳም በባቡር የ45 ደቂቃ መንገድ ተጉዘን እስክንደርስ ድረስ እነዚህ በሰው በሰው ያወቅኳቸው ሃበሻ ጓደኞቼ “የነጮቹን ጉድ ታያለሽ---” እያሉ እስክንደርስ ድረስ ልቤን በጉጉት ሰቀሉት። አይደረስ አይቀር Red light destrict የሚባል ቦታ ደረስን። ሴተኛ አዳሪዎች በተገለጠ መስታዎት ውስጥ ጡት ማስያዢያ እና የውስጥ ሱሪ ብቻ ለብሰው ሰው በሚያማልል አኳኋን ተቀምጠው ሚውዝየም እንደሚታይ እንሰሳ ወይም ዕቃ በጎብኚዎች ይታያሉ። አየሁ፣ ዞር ዞር ብዬ የሚያይዋቸውንም ቃኘሁ፣ የነጭ ገላ እንዲህ ተገላልጦ ሳይ የመጀመሪያዬ በመሆኑ በመጠኑ ተገረምኩ። ነገር ግን ጓደኞቼ እንደጠበቁት በጣም አልተደመምኩም። አለመደንገጤ ወይም በስመአብ ብዬ አማትቤ አገሬ መልሱኝ አለማለቴ አወዛገባቸው። ከጎኔ እየተራመደች ስትመራኝ የነበረችው ጠይሟ ፍንጭት ልጅ “ከባህላችን ጋር ስለማይሄድ ብዙ ሃበሾች ይደነግጣሉ” አለችና መልስ ፍለጋ ትቃኝኝ ጀመር። ነገሩን አይቼ አለማጋነኔ ያበሳጫት ትመስል ነበር። አልፈረድኩባትም። ግን ምን ልበላት?
አኔ፣ ትግስት፣ የቤት ስሜ ሚሚ፣ የአቶ ሳሙኤል ማቴዎስ በቀለ ልጅ፣ መርካቶ ከፍተኛ 5 ቀበሌ 17 የቤት ቁጥር 475 ነበር መኖሪያዬ ልበላት? ከሰፈሬ አንድ አስፋልት ከፍ ብሎ የነበረው የሴተኛ አዳሪዎች ሰፈር ቀበሌ 12 ይባል ነበር ልበላት? ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቴን ያጠናቀቅኩት አዲስ ከተማ ትምህርት ቤት ነው ልበላት? ከቤቴ ወደ ትምህርት ቤቴ ለመድረስ በ12 ቀበሌ ሰፈር ውስጥ ውስጡን ስጓዝ ያልተሳለምኩት ሴተኛ አዳሪ አልነበረም ልበላት? አንዷ በጉርድ ቀሚስ፣ አንዷ በቀይ ጫማ፣ አንዷ በውሰጥ ልብስ፣ አንዷ ስትታጠብ፣ አንዷ ስትቀባ፣ አንዷ ስታማልል ጠባብ ሱሪ አጥልቃ፣ አንዷ በጠዋቱ፣ አንዷ በከሰአት፣ አንዷ አመሻሽ ላይ፣ በነጻነት ቆመው ሁሉን አይቻለሁ ልበላት? የትዬ እንትና ባል፣ ያ ጠጅ አዘውታሪው፣ 3 ቀን ሙሉ ተፈልጎ ጠፋ። ሚስቲቱ ሰክሮ ቦይ ውስጥ ወድቆ ሞቷል ብላ ተንሰቅስቃ አለቀሰች። የሰፈሩ ሰው ተገልብጦ ወጥቶ ባልየው ሲፈለግ፣ የ12 ቀበሌዋ ሴተኛ አዳሪ ስላጽ “አኔ ጋር ነው ግን አልከፈለኝም” ብላ ያሳበቀች ዕለት፣ ሰውዬው ተጎትቶ ከቤቷ ሲወጣ፣ እኔም እዛ ነበርኩ ልበላት?
አባቴ የአትዮጵያ አየር መንገድ ይሰራ ስለነበር የተለያዩ አገሮች ለስራ ሲጓዝ የሚሸጡ አልባሳትና ጫማዎች ያመጣ ነበር። አንድ ጊዜ ከታይላንድ ሲመለስ ብዙ የሚሸጡ ቦርሳዎች አምጥቶ ለእናቴ እና ለእህቶቹ ሸጠው አንዲያተርፉ አከፋፈላቸው። በጣም የምወዳት አክስቴ አራት ቦርሳ አስይዛኝ ወደ ሴተኛ አዳሪዎቹ ሰፈር ላከችኝ። ትጠብቅሻለች የተባልኩት ስሟን በቅጡ የማላስታውሰው ቀይ ዳማዋ ሴተኛ አዳሪ ቤት ስደርስ ከደንበኛዋ ጋር ነበረች። በጣም ያረጀ፣ አውራ ጣቱ ጫፍ ተበላልቶ የተቀደደ፣ ቡናማ የወንድ ቆዳ ጫማ አልጋው ስር ይታያል። ከንፈሩ ሳይሳም ከሚያድር ቢታረዝ የሚመርጥ ሰውዬ አልጋዋ ላይ እደነበረ ከጫማው ገምቼ ነበር። በመጋረጃ ከተከለለው አልጋዋ ተስፈንጥራ ወጥታ ይዤ የነበረውን አራቱንም ቦርሳዎች አንድ በአንድ ቃኝቻቸው። ከመጋረጃው ጀርባ ሰውዬው በስሱ ያስላል። የቱን እንደምትመርጥ ዓይንአዋጅ ሆነባት መሰለኝ በርጩማ ላይ አስቀምጣኝ ትንሽ እንድጠብቃት አዝዛኝ ወደ ደንበኛዋ ተመለሰች።
ታዲያ የአምስተርዳም አስጎብኚዬን ምን ልበላት? እኔ ትግስት፣ የአቶ ሳሙኤል ማቴዎስ በቀለ ልጅ፣ አንዲት የቀይ ዳማ ሴተኛ አዳሪ በመጋረጃ ተከልላ ከደንበኛዋ ጋር አንሶላ ስትጋፈፍ አኔም እዛው ክፍል ነበርሁ ልበላት? አራት ከታይላንድ የመጡ ቦርሳዎች አቅፌ፣ እሱ ዚፑን ሲከፍት፣ የአልጋ ላይ ግብግብ፣ አሷ ስታቃስት፣ እሱ ሲያለከልክ፣ እንዳልተቃኝ ማሲንቆ የሽቦ አልጋዋ ሲያለቅስ ሰምቻለሁ ልበላት? በኋላም ሰውዬው ከመጋረጃ ጀርባ ሲለባብስ፣ ከፍሎ ሲወጣ ትዝ የሚለኝ ጀርባው ነበር። ደርዙ የተተረተረ ሱሪው .... ልበላት? አጠገቤ መጥታ እንደገና ቦርሳ ስትመርጥ፣ የሩካቤ ምርቃናዋ ሳይበርድ፣ ላብ ያዘፈቀውን ሰውነቷን አይቻለሁ ልበላት? ይህም ባህሌ ነው ልበላት?
By ትግስት ሳሙኤል
@wegoch
@wegoch
@paappii