🔖የጁምዓ ሰላት ሸሪዓዊ ብይኑና ማስረጃዎቹ🔖
🌂የጁምዓ ሰላት በያንዳንዱ ሙስሊም በሆነ ወንድ ላይ ግዴታ ነው፡፡
አላህ እንዲህ ይላል፡-
‹‹እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በዐርብ ቀን ለስግደት ጥሪ በተደረገ ጊዜ ወደ አላህ ማውሳት ኺዱ፡፡ መሸጥንም ተዉ፡፡›› ጁምዓ 9
ነብዩም (ﷺ) እንዲህ ብለዋል
‹‹አቅመ አዳም በደረሰ በያንዳንዱ ሰው ጁምዓ ግዴታ (ዋጂብ) ነው››[ነሳኢይ 1371]
በሌላም ሐዲስ ነብዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል
‹‹ሠዎች ጁምዓን ከመተው የማይታቀቡ ከሆነ አላህ ልቦናቸውን ያሽግና ዝንጉዎች ይሆናሉ››[ሙስሊም 865]
☄ጁምዓ ግዴታ የሚሆንባቸው ሰዎች☄
ጁምዓ በእያንዳንዱ ወንድ፣ ከባርነት ነፃ በሆነ፣ አቅመ አዳም በደረሰ፣ የአእምሮ ጤነኛ በሆነና ወደ ጁምዓ የመምጣት ችሎታ ባለው ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው፡፡ በአንፃሩ በባሪያ፣ ሴት ልጅ፣ ያልደረሰ ልጅ፣እብድ፣ህመምተኛና መንገደኛ ላይ ግዴታ አይደለም፡፡ ነብዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል
‹‹ጁምዓን በህብረት መስገድ ከአራት ሰዎች በስተቀር በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው፡- ባሪያ፣ ሴት ልጅ፣ ህፃንና ህመምተኛ››[አቡዳውድ 1ዐ54]
መንገደኛ የሆነ ሰው ላይ ጁምዓ ግዴታ አይደለም፡፡ ምክንያቱም ነብዩ (ﷺ) ባደረጓቸው ጉዞዎች ላይ አንድም ቀን ጁምዓ አልሰገዱም:: ነብዩ (ﷺ) ባደረጉት የመሰናበቻ ሐጅ ላይ ጁምዓ ገጥሟቸው ነበር ነገር ግን የሰገዱት ዙህርና ዓስርን በማቆራኘት እንጂ ጁምዓን አልነበረም፡፡ ይሁንና አንድ መንገደኛ ሙስሊምች ጁምዓ የሚሰግዱበት ቦታ ላይ በአጋጣሚ ቢገኝ ከነሱ ጋር አብሮ ጀምዓ መስገድ አለበት፡፡ ባሪያ፣ ሴት፣ልጅ፣ህፃን፣ህመምተኛ ወይም መንገደኛ ጁምዓ ተገኝተው ከሰገዱ ዙህርን መስገድ አይጠበቅባቸውም::
የጁምዓ ወቅት🌤
የጁምዓ ሰላት ወቅት ልክ እንደ ዙህር ፀሀይ ወደ ምዕራብ ዘንበል ካለችበት ወቅት አንስቶ የአንድ ነገር ከፀሐይ የሚያገኘው ጥላ በቁመቱ ልክ እስከሚሆን ድረስ ነው፡፡ አነስ ኢንብ ማሊክ እንዳሉት
‹‹ነብዩ (ﷺ) ጁምዓ የሚሰግዱት ፀሐይ ዘንበል ስትል ነበር››[ቡኻሪ 9ዐ4]
✔በዚህ ወቅት ጁምዓ መስገድ የሰሃቦች የተለመደ ተግባር እንደነበርም ተዘግቧል፡፡ በዚህ መሰረት ወቅቱ ከማብቃቱ በፊት አንድ ረከዓ የመስገጃ ያህል ጊዜ ላይ የደረሰ ጁምዓን ይሰግዳል፡፡ ወቅቱ ያለፈበት ከሆነ ግን መስገድ ያለበት ዙህርን ነው፡፡
📔የጁምዓ ኹጥባ📚
ኹጥባ ነብዩ (ﷺ) በሰገዷቸው ጁምዓዎች ሁሉ የፈፀሙትና ትተውት የማያውቁ በመሆኑን የጁምዓ መሰረት ነው፡፡ ስለዚህ ጁምዓ ያለ ኹጥባ መሰረተቢስ ነው:: በጁምዓ የሚደረጉት ኹጥባዎች ሁሉት ኹጥባዎች(ሁለት ኹጥባዎች የሚባሉት ኢማሙ አንደኛውን ኹጥባ ካደረገ በኋላ በመሃል ተቀምጦ ለሁለተኛ ጊዜ ቆሞ የሚያደርጋቸው ናቸው)ሲሆኑ መስፈርቱም ከሰላት አስቀድሞ ማድረግ ነው፡፡
🔖የኹጥባ ሱናዎች🔖
ለሙስሊሞች ዱንያዊና ሀይማኖታዊ ጉዳዮች መስተካከልና ለመሪዎች ዱዓ ማድረግ የተወደደ ነው፡፡ ነብዩ (ﷺ) የጁምዓ ዕለት ኹጥባ ሲያደርጉ በጣታቸው ወደ ላይ እየጠቆሙ ዱዓ ሲያደርጉ ሰዎችም አሚን ይሉ ነበር፡፡
ኹጥባና ሰላት በአንድ ሰው ቢፈፀሙ ይወደዳል፤ ኹጥባ አድራጊው በተቻለ አቅም ድምፁን ከፍ ቢያደርግ የተወደደ ነው፤ ኹጥባን ቆሞ ማድረግ የተወደደ ነው፡፡
ጃቢር ኢብን ሰሙራ እንዳሉት
‹‹ነብዩ (ﷺ) ቆመው ኹጥባ ካደረጉ በኋላ በመሀል ተቀምጠው ከዚያ እንደገና ቆመው ያደርጉ ነበር››[ሙስሊም 862]
ኹጥባን አጠር ማድረግና የሁለተኘውን ኹጥባ ከመጀመሪያው ይበልጥ አጠር ማድረግ፡፡ ዓማር ባስተላለፉት ሀዲስ ነብዩ (ﷺ) እንዲህ ይላሉ
‹‹የአንድ ሰው ኹጥባ አጠር ማለቱና ሰላቱን ረዘም ማድረጉ የአዋቂነቱ ምልክት ነው፡፡ ሰላትን አስረዝሙ ኹጥባን አሳጥሩ››[ሙስሊም 869]
ኹጥባ አድራጊው ወደ ህዝቦች ዞር ብሎ ሠላምታን ማቅረብ፡- ጃቢር እንዳሉት
‹‹ ነብዩ (ﷺ) ሚንበር[የኹጥባው መድረክ (ምኹራብ)] ላይ ሲወጡ ሠላምታ ያቀርቡ ነበር”
አዛን አድራጊው አዛኑን እስኪያጠናቅቅ ሚንበር ላይ መቀመጥ ኢብን ዑመር እንዳሉት ‹‹ነብዩ (ﷺ) በሚንበር ላይ ወጥተው አዛን አድራጊው አዛኑን እስኪጨርስ ሚንበር ላይ ይቀመጡና ሲጨርስ ተነስተው ኹጥባ ያደርጉ ነበር››
🔊በጁምዓ ክልክል የሆኑ ተግባራት🔊
✔ ኢማሙ ኹጥባ እያደረገ መናገር አይፈቀድም፡፡ ነብዩ (ﷺ) እንዲህ ይላሉ
‹‹በጁምዓ ቀን ኢማሙ ኹጥባ እያደረገ የተናገረ መፅሐፍ እንደተሸከመ አህያ ነው››[አህመድ 1/23ዐ]
በሌላም ሀዲስ እንዲህ ብለዋል
🌈‹‹ኢማሙ ኹጥባ እያደረገ ለጓደኛህ ዝም በል ካልክ ከንቱ ንግግር ተናገርኽ››
🌈በተቀመጡ ሰዎች ትከሻ በኩል በመሸጋገር መተላለፍ :
✔ ነብዩ (ﷺ) የሰዎችን ትከሻ እየተሸጋገረ ሲያልፍ ለተመለከቱት ሰው ‹‹ተቀመጥ ሰውን አስቸገርክ›› ብለውታል:: በዚህ ተግባር ሰውን ማስቸገርና ኹጥባን የሚያደምጥን ማዘናጋትም ይፈጠራል:: ኢማሙ ግን የሠዎችን ትከሻ እየተሸጋገረ ካልሆነ ወደ ቦታው የሚደርስበት ሌላ አማራጭ ከሌለው ይህን ሊፈፅም ይችላል፡፡
ሁለት ሰዎችን በመለየት በመካከላቸው መቀመጥም አይፈቀድም፡፡ ነብዩ(ﷺ) እንዲህ ብለዋል
✔የጁምዓ ሰላት ገላውን ታጥቦ በጊዜ ወደ ጁምዓ የሄደ ከዚያ በኋላ በሰዎች መካከል ሳይለይ አላህ የወሰነለትን የሰገደ በዕለቱና በሚቀጥለው ጁምዓ መካከል የሚፈፀሙ ኃጢአቶች አላህ ይቅር ይለዋል።
[ቡኻሪ 91ዐ]
🔖ጁምዓ ላይ መድረስ የሚቻለው በምንድን ነው?
💡ከኢማሙ ጋር አንድ ረከዓ ከደረሰ ጁምዓን በማግኘቱ የቀረውን አንድ ረከዓ ይጠበቅበታል:: ነብዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል ‹‹ከጁምዓ አንድ ረከዓን የደረሰ ሰላት ላይ ደርሷል›› ኢማሙ ላይ የደረሰው ግን ከአንድ ረከዓ ባነሰ ከሆነ መሙላት ያለበት ዙህር ሰላትን ነው፡፡
💡የጁምዓ ሱና ሰላት💡
✔ከጁምዓ በፊት የሚሰገድ መደበኛ ሱና የለም፡፡ ነገር ግን ወቅቱ ከመድረሱ በፊት መደበኛ ያልሆነ ሱና ቢሰግድ ምንም ችግር የለውም ምክንያቱም ነብዩ (ﷺ) በጥቅሉ ሱና መስገድን አበረታተዋል፡፡ ከጁምዓ በኋላ ግን መደበኛ የሆኑ ሁለት፣ አራት ረከዓ ወይም ስድስት ረከዓ ሱናዎችን እንደሁኔታው ሊሰገድ ይችላል፡፡ ቡኻሪና ሙስሊም ባስተላለፉት ሀዲስ
‹‹ነብዩ (ﷺ) ከጁምዓ በኋላ ሁለት ረከዓ ይሰግዱ ነበር››[ቡኻሪ 937 ሙስሊም 882]
በሌላ ሀዲስ ደግሞ ነብዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል
‹‹ ከጁምዓ በኋላ አራት ረከዓ ሱናዎችን ስገዱ››[ሙስሊም 881]
ኢብን ዑመርም ከጁምዓ በኋላ ስድስት ረከዓዎችን ይሰግዱ እንደነበር ‹‹ነብዩ ይፈፅሙት ነበር››[አቡዳውድ 113ዐ]
✔እንዳሉ አቡዳውድ ዘግበዋል፡፡ በዚህ መሰረት ከጁምዓ በኋላ የሚሰገድ መደበኛ ሱና ከፍተኛው ስድስት አነስተኛው ሁለት መሆኑን እንረዳለን::
🔖የጁምዓ ሰላት አሰጋገድ🔖
🎯የጁምዓ ሰላት ድምፅ ከፍ በመደረግ የሚሰገዱ ሁለት ረከዓዎች እንደሆኑ በነብዩ (ﷺ) ተግባርና በዑለማዎች ስምምነት የተረጋገጠ ነው፡፡ በመጀመሪያው ረከዓ ከፋቲሃ በኋላ ሱረቱል ጁምዓ በሁለተኛው ረከዓ ደግሞ ሱረቱል ሙናፊቁን[ሙስሊም 877] ወይም በመጀመሪያው ረከዓ ከፋቲሃ በኋላ ሱረቱል አዕላ በሁለተኛው ሱረቱል ጋሺያ እንደሚነበብም ነብዩ (ﷺ) በተግባር አስተምረዋል፡፡[ሙስሊም 878]
@yasin_nuru @yasin_nuru