👆🏻የዲኔ ጉዳይ ያገባኛል👆🏾


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: ko‘rsatilmagan


በዚህ ቻናል
♦️#ተውሒድና_ሱና በሰለፎች አረዳድ ብቻ ከተለያዩ የሰለፊያ መሻይኾችና ኡስታዞች ትምህርት ይቀርባል።
♦ እንዲሁም ሙስሊሙን የተመለከቱ ወቅታዊ መረጃዎችን እናጋራለን ተቀላቀሉ
ولقد بعثنا في كل أمة رسولاً عن اعبد الله واجتنبوا الطاغوت
https://t.me/yedine_guday

ሀሳብ እስተያየቶን በ👇ያድርሱን
@Yedinegudaybot

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri


የነገው ቀጠሮ

በደመቀው ሳሎን - በተዋበው ማጀት
ብትቀማጠለው ከልጅ እስከ ማርጀት

ያሻህን ብትነዳ በዝቶ ተሽከርካሪ
አለምን ብታስስ በሰማይ በራሪ

ጉድጓድ ነው ማረፊያህ የነገ ቀጠሮ
አፈር ልብስህ ሊሆን ሱፍህን ቀይሮ

ታገል ወንድሜ ሆይ ሰንቅ ለአኺራ
ፀፀት ያኔ አይጠቅምም ዛሬ ካልተሰራ



https://t.me/Muhammedsirage


" ኑ በሙያችሁ 'ሙያዊ ሰደቃን አበርክቱ!' " - የፌደራል መጅሊስ

Kottaa ogummaa keessaniin , sadaqaa ogummaadhaa gumaachaa. ¡¡¡

Majlisa federala


كيف #تحفظ_المتون مثل حفظ الفاتحة..

العلامة محمد علي آدم الإتيوبي -رحمه الله رحمة واسعة-

👈 ويذكر طريقته في الحفظ..


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
☜ تلاوة جميل جدا

ቁርአን የልብ ብርሀን የዱኒያ የአሄራን ህይወት የሚያቀና የማይጠገብ ውብ የአላህ ቃል ነው።


https://t.me/yedine_guday


የደዕዋ ድግስ በደሴ ከተማ ወሎ ባህል አምባ አዳራሽ


ታላቅ የምስራች ለደሴ እና አከባቢዋ ሙስሊም ማህበረሰብ  በሙሉ እነሆ የፊታችን እሁድ በቀን 25/05/2017 ዓ·ል  በአላህ ፍቃድ የወሎ መናገሻ እና እንብርት በሆነችው  ደሴ  ከተማ ወሎ ባህል አምባ አዳራሽ  ከአድስ አበባ ፣ ከአፋር፣ ከኸሚሴ፣ እና  ከሌሎችም ሀገራት በሚመጡ ብርቅዬ መሻይኾችና ኡስታዞች   ከጧቱ 3:00 ጀምሮ  እጅግ በደመቀ እና ባማረ መልኩ  የደዕዋ ድግስ ተዘጋጅቶ ሲጠብቃችሁ በታላቅ ደስታ ነው
 
የዕለቱ ተጋባዥ መሻይኾችና ኡስታዞች


① ሸይኽ አወል አህመድ አል ኸሚሴ
ርዕስ:– ረመዷንን እንዴት እንቀበለው

② ኡስታዝ አብዱረህማን ሰዒድ(አቡ ሒዛም)
ርዕስ:–ሱናን አጥብቆ መያዝና ቢድዓን መራቅ(መጠንቀቅ)

③ ኡስታዝ አቡል አባስ (ናስር)
ርዕስ:– የተውሂድ አሳሳቢነትና የሽርክ አደገኝነት እንድሁም በምን ላይ ነው  አንድ የምንሆነው

④ ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር (ሙሀመድ አህመድ)
ርዕስ:–ኢልምን በመፈለግ ላይ መበርታት፣የሶሻል ሚዲያ አጠቃቀማችን ምን መምሰል አለበት እና መልካም ስነ ምግባር

ማሳሰቢያ:–ለሴቶችም በቂ ቦታ አለ‼

N·B :– የቻናልና የግሩፕ ባለቤቶች በሙሉ ሼር በማድረግ ተደራሽ አድርጉት 

አዘጋጅ፦ የጀዕፈር ኢብኑ አቢ ጧሊብ የደዕዋና የቂርዓት ማዕከል


URGENT: - የደሴ ከተማና በዙሪያዋ ያላችሁ ሙስሊም ማህበረሰብ በሙሉ ፕሮግራሙ ዘንድ ትታደሙ ዘንድ ጥሪ አድርገንላችኋል።

ጆይን ይበሉ ቻናል

t.me/yedesse_selfyochi_yedewa_channel
ግሩፕ

https://t.me/yedesse_selfyochi_group


አልሀምዱሊላህ

የእህቶቻችን ለጊዜው እፎይታ ማግኘት እረፍት ነው። ይህ ከማህበራዊ ሚዲያ እስከ ተቋማዊ (መጅሊስ) ንቅናቄ በተጽእኖ የተቀለበሰ ውሳኔ ነው።

ይሁን እንጂ ይህ ዘላቂ መፍትሄ አይደለም። እስከወዲያኛው የዚህን ችግር ማዳፈን የሚቻለው እስከጥግ ታግሎ የትምህርት ሚኒስቴር የአለባበስ ኮድ ኦፍ ኮንዳክትን (መመሪያ) ማሻሻል እና ኒቃብን ከግልጽ ክልከላ ወደ ግልጽ ፍቅድነት መቀየር ሲቻል ብቻና ብቻ ነው።

ይህንን ከህግ፣ ከሞራል፣ ከሀይማኖት፣ ከማህበራዊ aspects አንፃር መሞገት፡ ማሳመንም ይቻላል። እስከዛው ሁሉም በየፊናው ይታገል።

ኢንሻ አሏህ አንድ ቀን እህቶቻችን ከነሙሉ ክብራቸው ቀና ብለው እስከኒቃባቸው የሚማሩበት ጊዜ ይመጣል!

እኝህ የትግል ጊዜዎችም ታሪክ ይሆናሉ። ኢንሻ አሏህ!

ታዲያ ያንኔ ከታሪክ ሰሪዎች ሆኖ ለመገኘት እንደ አቅማችን፡ እንደ ሚናችን፡ የበኩላችንን እንወጣ።


የዲላ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ጀማዓህ ያወጣው መግለጫ!


#Ethiopia: Muslim students at #Dilla University allege niqab ban, forcing some to stay in Mosque for days

Forty-four female Muslim students at Dilla University allege they have been barred from entering the campus for wearing the niqab, with some staying in a mosque for over five days. According to the students, the niqab was previously allowed but was recently prohibited due to "security concerns." One student explained, “Initially, it wasn’t strictly enforced,” and later, they were told “we couldn’t wear a black mask while wearing a hijab.”

The Chairperson of the Muslim Students’ Association confirmed that “many Muslim students have been staying in the mosque for the past five days” and are unable to attend exams or complete assignments. The Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council has urged the Ministry of Education for a permanent solution, emphasizing, “Muslim female students at Dilla University should be allowed to resume their studies without obstruction.” The university has denied these allegations, stating, “Wearing the hijab has not been prohibited at our university.”

https://addisstandard.com/?p=48150


~ቁርኣን በረካ አለው፡፡ ቁርኣን የገባበት ነገር ሁሉ ረድኤት አለው፡፡ ቁርኣን ወደ አንድ ነገር የገባ እንደሆነ ጨለማው ብርሃን ይሆናል፣  ጥቂቱ ይበዛል፣ ትንሹ ይተልቃል ፣ ጠባቡ ይሰፋል፡፡

የቁርኣንን በረከት አብዝታችሁ ተቋደሱ፡፡ ማንበብ ባትችሉም ከፍታችሁ እዩት፡፡ ትረካላችሁ፣ ታድጋላችሁ፣ ትለወጣላችሁ፡፡ ቀደምት ደጋግ የአላህ ባሮች ሌሎች ትምህርቶችን በመተው ቁርኣን ላይ ብቻ ያተኩሩ ነበር፡፡ የቁርኣን ሰዎች አላህ ሰዎች ናቸው፡፡ አላህ ወዳጆች ናቸው፡፡ ቁርኣንን የሚወዱትን አላህ ይወዳል፡፡ አላህ የቁርኣን ቤተሰቦች ያድርገን!
=t.me/AbuSufiyan_Albenan


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
بِسْمِ اللَّــــهِ الَّرحْمَـــــــــنِ الرَّحِيمِ

💥 *وصايا مهمة لأهل السنة في بلاد الحبشة* 💥


💥 لفضيلة الشيخ أبي عبدالله محمد بن علي بن حزام الفضلي البعداني حفظه اللّــــه ورعاه ونفع به الإســلام والمسلمين. 💥


🕌  أُلقيت لأهل السنة والجماعة في بلاد الحبشة عبر البث المباشر.

ليلة الاثنين الموافق ٢٠ من شهر رجب، من عام ١٤٤٦ من الهجرة النبوية على صاحبها الصلاة والسلام

⌚المدة :- ٢١ : ٢٦ - دقيقة.

https://t.me/mohrdood

⬇⬇⬇⬇⬇⬇⬇


🎙የሼይኽ ረሻድ ሙሀደራ
---
- አንገብጋቢ ርዕሶች የተዳሰሱበት
- መደመጥ ያለበት ጣፋጭ ሙሀደራ

🕌 በአህሉ-ተውሒድ ኢስላሚክ ሴንተር ቻናል የተሰጠ
--
🔺 https://t.me/sefinetunuh


محاضرة الشيخ محمد بن علي بن حزام الفضلي البعداني حفظه الله ورحم شيخه محدث ديار اليمنية العلامة المحدث مقبل بن هادي الوادعي


#ተውሒድ!

ረሱል (ﷺ) ለኢብኑ አባስ እንዲህ ብለውታል፦

 ﴿يا غلامُ احفظ اللهَ يحفظك، احفظ اللهَ تجده تجاهك، إذا سألت فاسألِ اللهَ، وإذا استعنت فاستعن بالله، واعلم أن الأمةَ لو اجتمعت على أن ينفعوك بشيءٍ؛ لم ينفعوك إلا بشيءٍ قد كتبه اللهُ لك، ولو اجتمعوا على أن يضروك بشيءٍ؛ لم يضروك إلا بشيءٍ قد كتبه اللهُ عليك، رفعتِ الأقلامُ، وجفَّت الصحفُ.﴾

“አንተ ልጅ ሆይ! አላህን ጠብቅ ይጠብቅሀል። አላህን ጠብቅ ፊት ለፊትህ ታገኘዋለህ። ስትጠይቅ እላህን ጠይቅ። ስትታገዝ በአላህ ታገዝ። እወቅ! ህዝቦች
ባጠቃላይ በሆነ ነገር ሊጠቅሙህ ቢሰባሰቡ አላህ ላንተ በፃፈልህ በሆነ ነገር እንጂ አይጠቅሙህም። ስሆን ነገር ሊጎዱህ ቢሰባሰቡም አላህ ባንተ ላይ በፃፈው ነገር እንጂ አይጎዱህም። ብእሮቹ ተነስተዋል መዝገቦቹ ደርቀዋል።”

📚 አልሚሽካት: 5302

ጆይን፡‐ https://t.me/BuhariMuslimAmharic


🎊ታላቅ ሙሀደራና ቢሻራ ፕሮግራም🎊
➖➖➖➖➖

【በዕለተ እሁድ ረጀብ 19/1446ھ】

«ታላላቅ ኡስታዞች እና መሻይኾች የሚሳተፉበት»

⏰ከምሽቱ 2:40ጀምሮ የሚተላለፍ ይሆናል !

ተጋባዥ ኡስታዞች እና የክብር እንግዶቻችን
~
🎙ታላቁ ዓሊም ሸይኽ ሙሀመድ ቢን ሒዛም -ከየመን
🎙ኡስታዝ አቡ-ሒዛም - ከሰመራ
🎙ኡስታዝ ኸድር አህመድ _ከከሚሴ
🎙ኡስታዝ አቡ ሙዓዝ ሀሰን ኢድሪስ_ከሀርቡ
🎙ኡስታዝ አቡ አብዲረሂም አብዱረህማን ሹመት_ከጃሚዓቱል-ኢስላሚያህ - መዲና
---
☞እንድሁም የአህሉ ተዉሂድ መርከዝ አሚሮችና ወንድሞችም ይሳተፋሉ!

❝በአህሉ-ተውሂድ ኢስላሚክ ሴንተር - ሀርቡ❞ 💡የሚተላለፍበት አድራሻ↓↓↓↓↓↓
https://t.me/sefinetunuh
https://t.me/sefinetunuh


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
የዛ ህዝብ ሰቆቃ‼


“With tears and prostrations of gratitude”




This is how Palestinians of #Gaza welcomed the announcement of the ceasefire agreement between Israel and Hamas.


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
የጋዛዊያን ደስታ‼

Palestinians in #Gaza chant “Allahu Akbar”, celebrating the announcement of the ceasefire agreement between Israel and Hamas.



የተገደሉትን ህፃናት፣ ሴቶች፣ አዛውንቶችና ሁሉንም አላህ ከሸሂዶች ይመድባቸው።


ነገ ሐሙስ ነው
#አንተስ_አትወድም?
“ሰኞ እና ሐሙስ ስራዎች ወደ አሏህ ይቅቀረባሉ፡ እኔም ፆመኛ ሆኜ ስራዬ እንዲቀርብልኝ እፈልጋለሁ”
ረሱሉል አሚን صلى الله عليه وسلم


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
አምስቱ የወንጀል ሂደቶች

አነስ ባለ ሳይዝ


https://t.me/Muhammedsirage


የአክሱም ወረዳ ፍርድ ቤት ሒጃብ መልበስ የሚከለክለው መመሪያ ላይ ዕገዳ ጥሏል‼
====================

(በሒጃብ ምክንያት ተማሪዎችን ያገዱ ትምህርት ቤቶች ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ አዟል!)

||



✍ የትግራይ ክልል እስልምና ጉዳዮች ምክርቤት በአክሱም ሙስሊም ሴት ተማሪዎች ሒጃብ ለብሰው እንዳይማሩ አስተዳደራዊ እግድ ባደረጉ 5 ትምህርት ቤቶች ላይ ክስ መመስረቱ ይታወቃል።

ጉዳዩ በዛሬው ዕለት የአክሱም ከተማ ወረዳ ፍርድቤት ላይ ቀርቦ ውሳኔ ተስጥቶበታል። ፍርድ ቤቱ አስተዳደራዊ እግድ ባደረጉ ትምህርት ቤቶች ላይ እግድ ጥሏል።

ጉዳዩ በተማሪዎቹ ላይ የማይቀለበስ የሰብአዊ መብት ጉዳት ሊያደርስ ስለሚችል ተማሪዎቹ ሒጃባቸውን ለብሰው ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ የሚል ውሳኔ አስተላልፏል።

በሒጃብ ምክንያት ተማሪዎችን ያገዱ ትምህርትቤቶቹ ለጥር 16/2017 ፍርድ ቤት ቀርበው ቃላቸውን እንዲሰጡ ትእዛዝ ተሰጥቷል።

በተያያዘ ዜና የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት በሰጠው ማሳሰቢያ ፥ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ምዝገባ ዛሬ ጥር 6/2017 ዓ.ል ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ላይ ተጠናቋል።

የአክሱም ሁለተኛ ደረጃ ሙስሊም ሴት ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል አገር አገር አቀፍ ፈተና ለማሳተፍ የሚያስችላቸው ፎርም ሳይሞሉ የተሰጠው የምዝገበ ቀነ ገደብ ዛሬ አልቋል።

© ሀሩን ሚዲያ


አላህ ወንጀሌን ይቅር ይለኝ ይሁን!?

የ ማዒዝ ኢብኑ ማሊክ ደንቅ ታሪክ!

🎙ወንድም አቡ ሱፍያን
=t.me/Sle_qelbachn1

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.