༆ የፍቅር ክሊኒክ ༆™🥀🌹


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: Kitoblar


🔔🔔 ምን ማስተዋወቅ ይፈልጋሉ 🔔🔔❓
📌 የምንሰጣቸው የማስታወቂያ አገልግሎቶች 💸
📱➡️የ ቻናል ማስታወቂያ
📱➡️ የ ሙዚቃ ማስታወቂያ
📱➡️ የ ኮንሰርት ማስታወቂያ
📱➡️የ ድርጅት ማስታወቂያ
📱➡️ የ ሚዲያ ቻናል ማስታወቂያ
📱➡️ትሪትመንቶች እና ሌሎችም የሽያጭ ማስታወቂያዎች ✅📢 በተመጣጣኝ ዋጋ💯💯💯💯💯💯
@Yefiker_clinic98

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Statistika
Postlar filtri


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
'https://t.me/addlist/3KtXhUzd71IwOTQ0' rel='nofollow'>ከ30 ደቂቃ ቦኃላ ይጠፋል

የ 200 ብር ካርድ የሚያስሸልም ጥያቄ!

10+10×0+10=???


Y.W dan repost
⚠️⚠️◇አክሽን ◇የጦርነት ◇የጫካ ◇የወንጀል  እንዲሁም የፍቅር ፊልም ሚመችክ ከሆነ አሁኑኑ JOIN  በለው  ይሄ ቻናል ምርጥ ምርጥ  ፊልሞችን በጥራትና በፍጥነት ያሳያል። 𝐉𝐨𝐢𝐧👇👇


ልብ አንጠልጣዩ "የጠፋው ሬሳ"

             ተከታታይ ትረካ

#ክፍል_19


...ያ ሁካታ እና ጨዋታ በድጋሜ ፀጥ አለ በጣም ደነገጥኩኝ የምይዘው የምጨብጠው ጠፋኝ እንደምንም ተረጋግቼ አንድ ስርቻ ጋር ተሸጎጥኩ አሁንም ፀጥታው እንደቀጠለ ነው ይመስለኛል ጆሯቸውን ቀስረው በድጋሜ የኔን ድምፅ እየጠበቁ ነው ማንም ከተቀመጠበት የተነሳ የለም...በዚህ ሰዓት ከተደበኩበት ቦታ ቀስ ብዬ በጥንቃቄ ተነሳሁ ልወጣ በሩ አካባቢ ስደርስ ሰውዬውም ሊወጣ ነው መሰለኝ ከወንበሩ ተነሳ ወዲያውኑ ወደነበርኩበት ስርቻ ተመለስኩ እጅግ በጣም ደነገጥኩኝ ይባስ ብሎ ሰውዬው ሊወጣ ብሎ ወደሗላ መለስ አለ የጠረጠረው እንዳች ነገር እንዳለ ተሰማኝ "በቃ ከዚህ በሗላ ማምለጥና መትረፍ አይታሰብም" ብዬ ለራሴ ነግሬ ጭንቅላቴን ጉልበቴ መሀል አስገብቼ የሚሆነውን መጠባበቅ ጀመርኩ እዛው በቃረቀርኩበት ደቂቃዎች ተቆጠሩ ከዛም እንደምንም ድፍረቴን ሰብስቤ ፍራቻዬን ተቋቁሜ ከአንገቴ ቀና ብዬ ስመለከት ሰውዬው በሩ ጋር አልነበረም በጣም ግራ ገባኝ ሲራመድ እንኳን ኮቴ አልተሰማኝም ነበር አሁን የባሰ ጭንቅ ሆነብኝ ሰውዬው ከየት እንደሚመጣ ለመገመትም ከበደኝ ቀስ ብዬ ጥንቃቄ በተሞላበት መልኩ ከተደበኩበት ተነስቼ ቅድም ውስጥ ያለውን ነገር እመለከትበት ወደነበረው የመጋረጃው ሽንቁር ተጠጋሁ ሁለቱ ሴቶች እንደነበሩት ናቸው በአርምሞ ሆነው የሮቤልን አካል ይመገባሉ ቀና ብለው እንኳን አይተያዩም ነበር ግን ከዛ አረመኔ ሰውዬ የተሻለ የተስተካከለ የፊት አቀማመጥ እና ጤናማነት ይታይባቸዋል በድንገት አይኔ ተወርውሮ ግድግዳ ላይ ከተሰቀለው ሁለት የህፃናት ፎቶ ላይ አርፎ ቀረ "እነዚህ ብላቴናዎች ማን ሊሆን ይችላሉ" ብዬም አሰብኩ በድጋሜ በዛች ሽንቁር ዙሪያ ገባውን መቃኘት ጀመርኩ በድጋሜ አንድ ፎቶ ተመለከትኩ አንዲት መልከ መልካም እናት በጨርቅ የተጠቀለለ ልጅ አቅፋ ከሆስፒታሉ መግቢያ ላይ ቆማ ያሳያል በእርግጥም ሆስፒታሉን አውቀዋለሁ አሁን ያለንበት ቦታ ነው በጣም ግራ የሚያጋባ ነገር "ህፃን ታቅፋ ፎቶ ላይ ያለችው ሴት ማን ልትሆን ትችላለች" ብዬ ራሴን ጠየኩ ዳሩ መላሽ ባላገኝም በድጋሜ አይኔን ወርወር አድርጌ ሌላ ነገር ማየቴን ቀጠልኩ ፎቶዎቹ በአጠቃላይ ጥቁርና ነጭ ቀለመሸ ያላቸው ናቸው...አይኔን ግድግዳው ላይ ሳንከባልል አንድ መልከ ሸጋ ብላቴ ያለበትን ፎቶ ተመለከትኩ ማን ሊሆን እንደሚችል ለመገመት ቢከብድም ገዳዩ ሰውዬ ይሆን እንዴ ብዬም አሰብኩ ግን የማውቀውን የፊቱን ገፅታ እና አቀማመጡን ሳስበው ፈፅሞ ሊሆን እንደማይችል ደመደምኩ ግን እነዚ የፎቶ ስብስቦች ያለ ምክንያት እንዳልተሰደሩም ተገንዝቤያለሁ በድንገት በዕድሜ ጠና ያለችው ሴትዮ ተነስታ ስመለከት ወደነበረው መልከ መልካሙ ብላቴና ፎቶ ጋር ጠጋ ብላ በእጆቿ እየዳበሰች በስስት አይን እየተመለከተች ድምፅ ሳታሰማ የእንባዋን ጎርፍ በጉንጯ ላይ ታወርደዋለች ከዛው ሌላኛዋ ሴት ተነስታ ከሗላ በኩል እቅፍ አርጋ የፊቷን የግራ ክፍል ጀርባዋ ላይ አስደግፋ ዝም ብላ አብራት ቆመች ከደቂቃዎች በሗላም ሴትየዋ ማልቀሷን አቆመች ወደነበሩበትም ተመለሱ ግን አሁንም ፊቷ አልተፈታም ነበር ሁለት እጆቿን በእልህ ጨብጣ ከንፈሯን ነክሳ በፍጥነት መተንፈስ ጀመረች ምን ሆነች ሳይባል በድንገት ተነስታ የክፍሉን ዕቃ አመሰችው በዚ ጊዜ ሰውዬው ድምፅ ሰምቶ ሊመጣ ይችላል ብዬወደነበርኩበት ስርቻ ተመለስኩ አሁን ንግግር ጀምረዋል "እባክሽ እባክሽ ተይ ተረጋጊ" ትላለች በዕድሜ አነስ የምትለዋ "ልጄን ልጄን ልጄን በሉብኝ አንድዬን የአይኔን ማረፊያ የፈጣሪዬን ስጦታ በሉብኝ" እያለች ድምፇን ከፍ አርጋ አምርራ ታለቅሳለች "ራስሽን አትጉጂ እባክሽን ተረጋጊ መድሃኒትሽን መውሰድ አለብሽ እንዲ መሆን የለብሽም የባሰ ታስጨንቂዋለሽ" አለቻት "ማነው ሚጨነቀው" ብዬ ወዲያውኑ ራሴን ጠየኩ "ሴትየዋ ልጄን በሉብኝ ብላ ነው ምታለቅሰው በሉብኝ ማለት ደግሞ ገደሉት ይመስለኛል እና ስለየትኛው ሰው እና ስለየትኛው ልጅ ነው እንደዚ ካየሽ ይጨነቃል" የምትለው ብዬ ከራሴ ንግግር ጀመርኩ የዚህ ቤተሰብ ውስብስብ ታሪክ ይበልጥ ዘልቄ እንዳውቃቸው አጓጓኝ ግን መሞትም እንዳለ አልዘነጋሁትም በድጋሜ ከተደበኩበት ተነስቼ ወደመጋረጃው ሽንቁር አመራሁ አሁን ፀጥታው ተመልሶ ነግሷል ሴትዬዋ መሬት ላይ ተኝታለች በዕድሜ አነስ የምትለው ደግሞ በተኛችበት ፀጉሯን እየደባበሰች ታፅናናታለች የሴትየዋ ጉዳት ከባድ እንደነበር መገመት ቀላል ነው ልጇን ምንም ያርጉት ምንም በብዙ ተጎድታለች ሰው ነችና አሳዘነችኝ አነስ የምትለዋ ሴት መድሃኒቱን እንድትውጥ አድርጋ አረጋጋቻት እዛው ቆሜ በመጋረጃው ሽንቁር እየተመለከትኩኝ ሳለ በድንገት በሩ ተከፈተ ስዞር..........

Part 20....ይቀጥላል.........

ቶሎ ቶሎ እንዲለቀቅ 👍 አሳዩኝ

ከተመቻቹ ÷

                
#𝐑𝐞𝐚𝐜𝐭
                
#𝐂𝐨𝐦𝐦𝐞𝐧𝐭
                
#𝐬𝐡𝐚𝐫𝐞 🙏

 
   ¶ 𝚈𝙴𝙵𝙸𝙺𝙴𝚁 𝙲𝙻𝙸𝙽𝙸𝙲🥀 ¶™🌐

  📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት! 📱


'ካንቺ ጋራ ስሆን'😊 .....
ምሽቱ ይደምቃል ፣ ሀሳቤ ይሰምራል፣❤️
አስቀያሚው ያምራል 🤗፣
ጨለማው ያበራል ፡፡
ሰማሽኝ የኔ አለም ፡ ካንቺ ጋራ ስሆን ፣
ህይወቴ በሀሴት ፡ ፅዋ ትሞላለች🥰
ካንቺ ጋራ ስሆን አለም ለኔ እንዲህ ነች።




ልብ አንጠልጣዩ "የጠፋው ሬሳ"

            
  ተከታታይ ትረካ

                
#ክፍል_18


...በድጋሜ "እርዱኝ አድኑኝ" ብሎ ድምፅ አወጣ በዚ ሰውዬው ቡታጋዙ ላይ ተጥዶ የነበረው የሚፍለቀለቅ ዘይት ከመቅፅበት አንስቶ ከፊቱ ጀምሮ እስከ እግሩ ድረስ ደፋበት ሮቤል አምርሮ ክፉኛ ጮኸ ግን ድጋሜ አልጮኸም ነበር ለዘላለሙ በዛው አሸለበ...ይሄን መቆጣጠር አልቻልኩም በዘይት የተጠበሰው የስጋው ሽታ ወደኔ ሲመጣ አጥወለወለኝ ሊያስመልሰኝም ዳዳሁ በብዙ ተፈታተነኝ...እንዳጋጣሚ ሰውዬው ለምን እንደሁ እንጃ ከክፍሉ ወጣ እኔም የሱን አለመኖር ጠብቄ ሚተናነቀኝን አስወጣሁት ከአንድ ደቂቃ በሗላ ሶስት ነጫጭ ሳህን አምጥቶ ጠረጴዛው ላይ አስቀመጠ ምን ሊያደርግ እንዳሰበ ምንም አልገባኝም የሩቤል አስክሬን ድርቅ ብሏል አንደበቱ ሊጮህ እንደተከፈተ በዛው ስላሸለበ አልተዘጋም ይሄ ሁሉ ነገር ሲደረግ አይኔን ገልጬ ማየቴ ራሴን እንደ ጨካኝ እንዳይ አድርጎኛል በሌላ በኩል ደግሞ ይሄን ሁላ ትዕይንት መቋቋሜ መልሶ ለራሴ ይደንቀኛል ሰውዬው አሁንም ከዘፈኑ እኩል እየተንቀሳቀሰ ሚከውነውን ይከውናል አንድ ተለቅ ብሎ ስፋት ያለው የሚያብለጨልጭ ስለታም ቢላ እና አነስተኛ ቢላ ይዞ ወደ ሮቤል በድን ተጠጋ ሊሆን ያለውን ማሰብ ለኔ ከባድ ነበር ይህ ከገመትኩት በላይ ክፉና አረመኔ ነው ሰው መባል ሁሉ የለበትም ሰይጣን ስጋ ለብሶ እንጂ...ሰውዬው መለስ ብሎ አነስ ያለ ወንበር ይዞ ወደ በድኑ ተመልሶ ጠጋ ብሎ ተቀመጠ ከዛም በትንሿ ቢላ አስክሬኑን መክፈት ጀመረ ለሚመለከተው የሚያክም እንጂ የሚበልት አይመስልም ዘየት በደንብ ያገኘውን የሰውነት ክፍል እየመረጠ መቁረጥ ጀመረ የቆረጠውንም የሰው ስጋ ባመጣቸው ሳህኖች ላይ እያስተካከለ መደርደር ጀመረ...ሲለው ደግሞ መሀል መሀል ላይ ከሚቆርጠው ስጋ እየቀመሰ ጭንቅላቱን በመነቅነቅ ይደነቃል ይሄን መመልከት ምነኛ አለመታደል ነው ግን ከቤት ወደዚ የመጣሁበትን ቀን አምርሬ ጠላሁት ሲበዛም ረገምኩት...ሰውዬው አሁንም እየቆራረጠ ነው ከትንሽ ደቂቃ በሗላ ሁለቱን ሳህኖች አንስቶ ከክፍሉ ወጣ ብዙም ሳይቆይ በድጋሜ ተመልሶ አንደኛውን ሳህን ይዞ ወጣ እኔም የሚሄድበትን ለመመልከት ብዙ ሳይረቅ ወደ በሩ ተጠጋሁ ሆስፒታሉ ውስጥ ከሚገኝ አንዱን በር ከፍቶ ሲገባ ተመለከትኩት የከፈተውንም በር ሳይዘጋ ወደ ውስጥ አመራ እርምጃዬን አጥፍቼ ያለውን ነገር ለመመልከት ወደ ውስጥ ገባሁ ግን ክፍሉ ባዶ ነበር በጣም ደነገጥኩኝ ወጥመድም መሰለኝ እዛው በቆምኩበት በድንጋጤ እያለከለኩ ተዟዟርኩኝ ግን ማንም አልነበረም የት እንደተሰወረ ግራ ሆነብኝ ነገር ግን የቆምኩበት ወለል እስካሁ ከረገጥኩት የወለል ድምፅ ይለያል ግድግዳ እና ጣሪያ ላይ ሲያማትር የነበረው አይኔን ቁልቁል ወደ ወለሉ ወረወርኩት እውነትም የቆምኩበት ወለል የተለየ ነበር ከላዩ ላይ ወረድኩና በጉልበቴ በርከክ ብዬ ጆሮዬን ላዩ ላይ ደቀንኩና ማዳመጥ ጀመርኩ በጣቶቼም ቆረቆርኩት ከሰማሁት ድምፅ በመናሳት ከታች የሆነ ክፍል እንዳለ ድምዳሜ ላይ ደረስኩ ውስጥ ያለውን ነገር ገብቶ ለመመልከት ወሰንኩኝ ከዛም ወለል መሳይ በሩን ለመክፈት መታገል ጀመርኩኝ ግን ብዙም አድካሚ አልነበረምና ተከፈተልኝ ቁልቁል ስመለከት ውስጡ ብዙም ብርሃን አልነበረውም ቢሆንም ግን የመመልከት ሀሳቤን አላስቀየረኝም ቀስ ብዬ እግሬን ከደረጃው ላይ አሳረፍኩ በአንድ እጄ በሩን ይዤ በጥንቃቄ ቁልቁል መውረድ ጀመርኩ አልፎ አልፎ ከሚታይ ወጋገን በቀር ክፍሉ ጨለማ ነው እቃ ነገር ጥዬ እራሴ ላይ ወጥመድ እንዳልሆን በጥንቃቄ መራመድ ጀመርኩ ወደፊት በተጠጋሁ ቁጥር ብርሃን እየበዛ መጣ ትንሽ እንደተራመድኩ የሚሳሳቁ የሰዎች ድምፅ ተሰማኝ "ያ ክፉ ሰው ብቻውን አልነበረም ሌሎች የሚያግዙት ሰዎች" አሉ አልኩኝ ለራሴ እርምጃዬን ጠብቄ ወደፊት መሄዴን ቀጠልኩኝ ጨዋታቸው ደርቷል ምን እንደሚባባሉ ግልፅ ባይሆንም ሳቃቸው ግን ይሰማል በነሱ ሁኔታ ከራሴ ጋር እያወራሁ ሳለ በድንገት ሳላስበው በእግሬ መሬት የነበረ ጣሳ ረገጥኩኝ የፈጠረው ድምፅ ለተንኮል ከፍ ያለ ነበር የደራው ጨዋታቸው እና የሞቀው ሳቃቸው በአንድ ጊዜ ፀጥ አለ በር ሲከፈት ያለው ድምፅ ተሰማኝ የሆነ ሰው ነገሩን ለማጣራት እየመጣ ይመስለኛል እንደዚ ባሰብኩ ጊዜ ከአካባቢው መራቅ ነበረብኝና የሆነ ጥግ ላይ ተደበኩ ግን ማንም አልመጣም ነበር በድጋሜ ቀስ ብዬ ወደፊ ተጠጋሁ ቅድም ሲከፈት የሰማሁት በር ይመስለኛል ከፊት ለፊት ክፍት ሆኖ ይታየኛል ጨዋታው በድጋሜ ደርቷል እየቀረብኩኝ ስሄድ ድምፃቸው ግልፅ እየሆነ መጣ ከእርምጃዎች በሗላ ወደ ክፍቱ በር ደረስኩ አንገቴን አስግጌ ውስጡን ስመለከት የተቀዳደና በደም የመነቸከ ነጭ መጋረጃ ተመለከትኩ ሰዎቹም ከመጋረጃው ጀርባ እንዳሉ ተረዳሁ ቀስ ብዬ ተጠጋሁና በቀዳዳው መመልከት ጀመርኩ ሰውዬው ጀርባው ለኔ ሰጥቶ ነው የተቀመጠው በሱ በስተቀኝ በኩል ተለቅ ያለች አሮጊት ትታየኛለች ከሷ ሴትዮ በመቀጠል ደግሞ ከሁለቱም በዕድሜ ምትበልጥ ሴት ከሱ ፊት ለፊት ተቀምጣለች በድንገት አይኔ የሚመገቡት ነገር አረፈ እሱን ባየው ጊዜ ሳላስበው ድምፅ አወጣሁ..............


part #19  ___ ይቀጥላል

ቶሎ እንዲለቀቅ 👍 አሳዩኝ

ከተመቻቹ ÷

                
#𝐑𝐞𝐚𝐜𝐭
                
#𝐂𝐨𝐦𝐦𝐞𝐧𝐭
                
#𝐬𝐡𝐚𝐫𝐞 🙏

    
¶ 𝚈𝙴𝙵𝙸𝙺𝙴𝚁 𝙲𝙻𝙸𝙽𝙸𝙲🥀 ¶™🌐

  📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት! 📱


🥀🖤
እሷ:"ድብብቆሽ (አኩኩሉ) እንጫወት ልደበቅና ካገኘሀኝ ታገባኛለህ"አለችው "
.
.
እሱ:""ፈልጌ ካላገኘሁሽስ? አላት
.
.
እሷ:""ከበሩ ኋላ ነው ምደበቀው አለችው____🥰😍


#ቸር ቀን ተመኘው🙏

4k 0 9 17 62

፡  " ለምንድን ነው ግን ሁሌ እጄን እምትይዢኝ ?…" አይን አይንዋን እያየሁ ጠየኳት…ለእረጅም ደቂቃ አልመለሰችልኝም…


  " እጅህን ስይዘው ምንም ነገር አልፈራም…ስለቅህ ግን ይጨንቀኛል…ደግሜም እሚይዝህ አይመስለኝም…እጅህን ስይዘው ውስጤ ሰላም ይሰመኛል…መኖርን እመኛለው…ምነው አንተ ሲይዝህ ይደብርሀል እንዴ?…"

        አልመለስኩላትም…


 
       #𝐑𝐞𝐚𝐜𝐭
                
#𝐂𝐨𝐦𝐦𝐞𝐧𝐭
                
#𝐬𝐡𝐚𝐫𝐞 🙏

    
¶ 𝚈𝙴𝙵𝙸𝙺𝙴𝚁 𝙲𝙻𝙸𝙽𝙸𝙲🥀 ¶™🌐


ልብ አንጠልጣዩ "የጠፋው ሬሳ"

            
  ተከታታይ ትረካ

                
#ክፍል_17


...የሚሆነውን ሳስበው አንቀጠቀጠኝ ለማየትም ለመስማትም ሰቀጠጠኝ...በድን የመሰለኝ የሮቤል አካል መንቀሳቀስ ጀመረ እንደ ማሳልም ሲያረገው ከአፉ ደም ይረጫል ይሄን ባየ ጊዜ ያ ሰው ይበልጥ ደስ አለው ከሚሰማው ጫጫታ ይልቅ ይሄ ለሱ ደስታ ሰጥቶታል ጠጋ ብሎ አይን አይኑን እደተመለከተ ፈገግ ይላል በሌላ በኩል ሮቤል በለዘበ እና በቀሰስተኛ ድምፅ "እርዱኝ አድኑኝ ይላል" ይሄን መመልከት ለኔ እጅግ በጣም ከባድ ነው የማደውን ነገር ማመን አልቻልኩም እጄን አፌ ላይ አድርጌ ስቅስቅ ብዬ አለቀስኩኝ አቅም ቢኖረኝና ከዚ አረመኔ ሰው ባስጥለው ፍፁም ደስተኛ ነበርኩ ነገር ግን አልችልም...ሰውዬው አሁንም ዋይታ በሞላው የሰዎች ጫጫታ በደስታ እና እረፍት የተሰማው በሚመስል መልኩ ይንቀሳቀሳል የዘይቱን መፍላት እየተመላለሰ ይመለከታል ለምን እንደጣደው ባይገባኝም ብቻ አስፈርቶኛል...ሮቤል ሙሉ ለሙሉ ሰውነቱ በደም ተጨማልቋል ከቅንድቡ ትንሽ ከፍ ብሎ በስለት የተቆረጠ የሚመስል ቁስል አለ ይመስለኛል እኔ የተመለኩት ያ የተሰበረ መስታወት ሮቤል ለማምለጥ ሲል የሰበረው እንደሆነ ተረዳሁ ሳሩ ላይ የተመለከትኩት ደም ደሞ ከመስኮቱ ከወደቀ በሗላ ለማምለጥ በደረቱ የተሳበበት እንደሆነ ገባኝ ሁኔታዎቹን ከሮቤል መጥፋት ጋር ማመሳሰሌ ትክክል ነበርኩ ይሄን ሁኔታ ቅድስቴ አለመመልከቷ ለሌሎቻችን በህይወት መቆየት ምክንያት ነው...ብትመለከት ኖሮ ራሷን ማረጋጋት ስለማትችል ሁላችንም እንጠመድ ነበር...ሮቤል አሁንም ድምፁን እያሰማ ነው አረመኔው ሰውዬ ደግሞ እየደነሰ...እንቅስቃሴው ሁሉ ግራ ነው ጨፈረ ለማለት እንኳን አያስደፍርም...ከደቂቃዎች በሗላ የዘይቱን መፍላት አረጋገጠ ከዛም እየሳቀና እንደ ጭፈራ የሚያረገውን እንቅስቃሴ እያሳየ ወደ ሮቤል ተጠጋ ሁለት ተለቅ ያሉ ጥቋቁር ቀበቶ መሳይ ማሰሪያዎችን አንስቶ አንዱን ደረቱጋ አንዱን ደሙ ታፋው ጋር አድርጎ ከጠረጴዛው ጋር ሮቤልን የፊጥኝ አሰረው...የሮቤልን ስቃይ ለመረዳት ሮቤልን መሆን አልነበረብኝም ህመሙ አብዝቶ አመመኝ ስቃዩ አሰቃየኝ ወዲያውኑ ትሪ መሳይ በሆነው ነገር ካመጣቸው ስለቶች መሀል ሁለቱን አንስቶ ወደሰማይ እየተመለከተ ማፋጨት ጀመረ የዘይቱ መፍላት እኔ እስካለሁበት ቦታ ድረስ ሲፍለቀለቅ ይሰማል ብቻ እንደማስበው አይሁን ብዬ አምላኬን ተማፀንኩኝ..."እርዱኝ አድኑኝ እርዱኝ አድኑኝ" እያለ ሮቤል የማይደርስለትን አዳኝ ይጣራል አረመኔውም ሰውዬ አንድ ጣቱን አፉ ላይ አድርጎ ዝም እንዲል ለሮቤል በምልክት ያሳየዋል ነገር ግን ሮቤል የሚረዳውን ሰው ከማያገኝበት ስፍራ መጣራቱን ይቀጥላል በዚ ግዜ ሰውዬው አብዝቶ ይናደድና ሲያፋጭ የነበረውን ስለት ከፍ ሲያረገው አሁን ካሁን አንዳች ቦታ ላይ ወጋው ስል ከፍ ካደረገበት እጁን ሳይመልስ በንዴት የተለዋወጠው ፊቱ ወደ መጀመሪያ ገፅታው ተመልሶ በተረጋጋ ስሜት ሆኖ አሁንም አንድ ጣቱን ከንፈሩ ላይ አድርጎ ዝም እንዲል ይነግረዋል...ከዛ ከጋለ ስሜት ውስጥ መውጣቱ ለኔ በጣም ግራ ነው ሰውዬው በጣም አጠራጣሪና አወዛጋቢ በሆኑ ነገሮች ነው የተሞላው...ዶክተሮች የሚጠቀሙበትን የህክምና ጓንት ከአንዱ መሳቢያ አውጥቶ እጆቹ ላይ አጠለቀ በመሃል የከፈተው ዋይታ ፀጥ አለ እሱም እዛው የቆመበት ቦታ ለይ ሳይንቀሳቀስ ፀጥ ብሎ ቆመ ሰከንዳት አልፈው ደቂቃዎች ተቆጠሩ እንደዛው ካለበት ሳይንቀሳቀስ ፀጥ ብሉ እንደቆመ...በዚ ሰዓት ሮቤል አንዳች ድምፅ ቢያወጣ ምን ሊፈጠር እንደሚችል ማሰላሰል ጀመርኩ ይሄን እያሰብኩኝ ሳለ የቅድሟ ድመት እየጮኸች ወደክፍሉ ስትገባ ከቆመበት ተስፈንጥሮ መጥረቢያውን አንስቶ ወገቧን ብሎ ለሁለት ከፈላት ከቅድሙ ይልቅ አሁን አፌን አጥብቄ ያዝኩ ሰውዬው እዛው ድመቷ የሞተችበት ቦታ ላይ በድጋሜ ፀጥ ብሎ ቆሟል አይኑ እንኳን አይርገበገብም ከደቂቃዎች በሗላ የዋይታው ድምፅ ጀመረ መጥረቢያውን ትከሻው ላይ አድርጎ እያፏጨ መንቀሳቀስ ጀመረ ትንሽ ተንፈስ አልኩኝ ምን ሲያቀብጠኝ ወደዚ ክፍል እንደመጣሁ አላውቅም እዛው ከጓደኞቼ ጋር ሆኜ የሚሆነውን ብጠብቅ ይሻለኝ ነበር...መጥረቢያውን የነበረበት ቦታ ላይ አስቀምጦ ድመቷን ከወደቀችበት አንስቶ የቆሻሻ መጣያ ውስጥ ከተታት ያደረገውንም ጓንት አውልቆ ከድመቷ በድን ጋር አብሮ ጣለው ከዛም አዲስ ጓንት ለማድረግ ወደ መሳቢያው ተጠጋ አውጥቶም በዋይታው እየተንቀሳቀሰ ማድረግ ጀመረ ከዛም ከተሰጡት የዶክተሮች ጋውን አንዱን አንስቶ ለበሰ ከዛም ፈገግ እያለ እየቆለፈ ራሱን በራሱ መመልከት ጀመረ በጣም ደስ ያለው ይመስላል እጁን ኪሱ ከቶ ወደዛ  ወደዚ መንጎራደድ ጀመረ ጓንት ወዳወጣበት መሳቢያ በድጋሜ ሄዶ መነፅር አውጥቶ አደረገ አሁን የባሰ ፈገግ አለ የሚያረገው ነገር ትንሽም ቢሆን ከፍራቻዬ አውጥቶ በአግራሞት ዝም ብዬ እንድመለከተው አደረገኝ ደረቱን ነፍቶ አሁንም መንጎራደዱን ቀጠለ ነገር ግን ሙዚቃው በድጋሜ ፀጥ አለ እሱም ባለበት ቦታ እጁን ኪሱ እንደከተተ ቆመ እኔም እቺ ደቂቃ እስክታልፍ አፌን አፍኜ ያዝኩኝ ነገር ግን ሮቤል......


part #18  ___ ይቀጥላል

ቶሎ እንዲለቀቅ 👍 አሳዩኝ

ከተመቻቹ ÷

                
#𝐑𝐞𝐚𝐜𝐭
                
#𝐂𝐨𝐦𝐦𝐞𝐧𝐭
                
#𝐬𝐡𝐚𝐫𝐞 🙏

    
¶ 𝚈𝙴𝙵𝙸𝙺𝙴𝚁 𝙲𝙻𝙸𝙽𝙸𝙲🥀 ¶™🌐

  📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት! 📱


ልብ አንጠልጣዩ "የጠፋው ሬሳ"

            
  ተከታታይ ትረካ

                
#ክፍል_16

...ልቤ ስንጥቅ እስኪል ድረስ ድንጋጤዬ ከባድ ነበር ነገር ግን ድንጋጤዬን ዋጥ አድርጌ ምንም ድምፅ ሳላሰማ ፀጥ አልኩኝ...የነካሁት አካል በደም የተጨማለቀ መሰለኝ ይቀዘቅዛል ቀስ ብዬ ወደ ነበርኩበት ቦታ ለመመለስ እጄን በጥንቃቄ ከነካሁት አካል ላይ አነሳሁ ከዛ ወደሗላ ማፈግፈግ ጀመርኩ ትንሽ እንደተጠጋሁ መብራቱ ቦግ ብሎ በራ ያየሁትን ማመን አቃተኝ ድንጋጤዬ ከመጠን ስላለፈ ድምፄን ከፍ አድርጌ ጮውኩኝ በጭለማ ዳብሼ የነካሁት በደም የተጨማለቀው ገላ የሮቤል ነበር...ድምፄ ከተሰማ በሗላ ወዳለሁበት የሚራመድ ፈጠን ያለ እርምጃ ተሰማኝ ከገባሁበት ድንጋጤ ራሴን ለማረጋጋት እየሞከርኩ ምደበቅበትን አንዳች ስፍራ እንዳለ አይኔን እያማተርኩ ማሰስ ጀመርኩ ከፊት ለፊቴ የዶክተሮች ጋውን በብዛት የተሰቀለበትን ቦታ ተመለከትኩ እርምጃዬንም ፈጠን አድርጌ ከጋውኖቹ መሃል ተደበኩኝ ወደኔ ይመጣ የነበረው ያ እኔ የምፈራው ሰው ነበር በሩ ላይ ቆሞ ግራ ቀኙን ማማተር ጀመረ መጥረቢያውንም ከተቀመጠበት ስፍራ አንስቶ ያዘው ክፍሉ ውስ መዘዋወር ጀመረ ትንሽ ከተንቀሳቀሰ በሗላ ወደ ጋውኖቹ ትኩር ብሎ መመልከት ጀመረ እጅግ በጣም ጨነቀኝ አፌን በእጆቼ እፍን አድርጌ ደብዛዬን ለማጥፋት ፀጥ አልኩኝ ግን ከበስተሗላዬ ከሁለት የገመድ መስቀያ አለፍ ብሎ የነበረው መስቀያ ምን እንደነካው እንጃ ወደቀ ፀጥታውም በአንዴ ታወከ ከጋወኑ በታች የነበሩ ፕላስቲኮች እና ብረት ነክ ዕቃዎች ተንጫጩ ወደኔ በርቀት ሆኖ ሲመለከት የነበረው ሰው አሁን መጠጋት ጀመረ ምንም ማድረግ የማልችልበት ሁኔታ ውስጥ እንዳለሁ ተረዳሁ ለማምለጥ ምንም አይነት አጋጣሚ ሊፈጥር እንደማይችል ደመደምኩ ሰውዬው አብዝቶ ወደኔ ተቃርቧል በመሃላችን ያለው ልዩነት የሶስት ገመድ መስቀያ ብቻ ነበር መጥረቢያውን እያንፏቀቀ አንዱን መስቀያ አለፈ ከጋውኖቹ መሀል ላይም ቆሞ ዙሪያ ገባውን ቃኘ በድጋሜ አንደኛውን መስቀያ አልፎ ወደኔ እጅግ ተቃረበ በመሃላችን የአንድ መስቀያ ልዩነት ብቻ ቀረ መላ አካላቴ መርገፍገፍ ጀመረ ተውረገረገ አይኖቼን ከድኜ ሞቴን መጠባበቅ ጀመረኩኝ እያወቁ መሞት ምንኛ ከባድ ነው ግን አስተውያቸው የማላውቃቸው እነዛ የሰላም ቀናት አብዝተው ናፈቁኝ ሰውነቴ በላብ እና በደም ተጨማልቋል አይኔን ጨፍኜ ሞቴን ብጠብቅም ገዳዬ ግን ዘገየ ምን እንደተፈጠረ ለመመልከት አይኔን ገለጥኩኝ ሰውዬው የተመለከተኝ ይመስል ወደኔ አቅጣጫ እያየ መጥረቢያውን ከፍ አድርጎ በሁለት እጆቹ ያዛው እርምጃው ትንሽ ወደኔ አስጠጋና ለሰከንዳት ያህል ፀጥ ብሎ ቆመ በድንገት አዲት ድመት ድምፇን ከፍ አርጋ ጮኻ ከወዳደቁት ጋውኖች መሀል ተስፈንጥራ ወጣች ወዲያውኑ እኔን ትቶኝ ወደሗላው ተመለሰ ነፍሴም ተረጋጋች ነገር ግን ሰውዬው ከክፍሉ ውስጥ አልወጣም ይብሱኑ ክፍሉ  ውስጥ ያለውን ተለቅ ያለ ጠረጴዛ አየጎተተ ወደ መሃል አመጣው ከዛም ስለት ያላቸውን መቆራረጫዎች ተለቅ ባለ ብራማ መልክ ባለው አራት ማዕዘን ትሪ መሳይ ነገር ላይ አድርጎ አመጣ...የሚያደርገው ነገር እጅግ ግራ ያጋባል ከዛም ወደበሩ ጋር ጠጋ ብሎ የሮቤልን በድን አካል ጠረጴዛው ላይ አደረገው ሊያረግ ያሰበውን ሳስበው ሆዴ ተላወሰ ሊያስመልሰኝም ቃጣው ፈጥኜ እጆቼን አፌ ላይ አደረኩኝ መስኮቱ አጠገብ ካለው መሳቢያ ውስጥ ቆየት ያለ ሞዴል ያለው ቴፕ አውጥቶ ውስጡ ያለውን ካሴት በመዳፉ መታ መታ አድርጎ አድርጎ ከተተው ከዛም ግራ የሚያጋባ ግጥም የሌለው በጩኸት የተሞላ ድምፅ ጀመረ ዋይታ ይበዛዋል ለሰሚው በጣም ይጨንቃል ግን እሱ በደስታ ይንቀሳቀስበት ነበር ፊቱ የጤነኛ ሰው መልክ የለውም ከአፍንጫው ጀምሮ እስከ ጆሮው ድረስ ተቀዶ የተሰፋ ቁስል ይታየኛል አንደኛው አይኑ የአይን ኳሱ የለውም የግራ ጆሮው በከፊል ተቆርጧል ፊቱ በእሳት የተለበለበ ነው ሚመስለው የእጅ ጣቶቹ ላይ ጥፍር የሚባል የለባቸውም የጭንቅላቱ ፀጉር መሃል መሃሉ ባዶ ነው በአደጋ እንደዚ የሆነ ይመስላል ይሄን ሁሉ ነገር የምመለከተው ለጆሮ በማይመቸው የሰቀቀን ድምፅ በሆነው ዋይታ ሲደንስ ነው ትንሽ ከተንቀሳቀሰ በሗላ ከክፍሉ ከአንዱ ጥግ ተለቅ ያለ ድስት አንስቶ ውሃ በዛ ያለ ዘይት ጨምሮበት ቡታጋዝ ለኩሶ ጣደው የሚያረገውን ሁሉ እየደነሰ ነበር ሚከውነው ግን ያልጠበኩት እና ያስደነገጠኝ አንዳች ክስተት ተፈጠረ...............

part #17  ___ ይቀጥላል

ቶሎ እንዲለቀቅ 👍 አሳዩኝ

ከተመቻቹ ÷

                
#𝐑𝐞𝐚𝐜𝐭
                
#𝐂𝐨𝐦𝐦𝐞𝐧𝐭
                
#𝐬𝐡𝐚𝐫𝐞 🙏

    
¶ 𝚈𝙴𝙵𝙸𝙺𝙴𝚁 𝙲𝙻𝙸𝙽𝙸𝙲🥀 ¶™🌐

  📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት! 📱


 
ልብ አንጠልጣዩ "የጠፋው ሬሳ"

            
  ተከታታይ ትረካ

                
#ክፍል_15


...በሆስፒታሉ የመግቢያ በር ላይ የቆመ ሰው ተመለከትን እጅግ በጣም ከመደንገጣችን የተነሳ የነበርንበትን ክፍል በር ሳንዘጋ እየተጯጯህን ወደ ውስጥ ገባን አንድ ላይ ተጠባብቀን የሚሆነውን መጠበቅ ጀመርን ለደቂቃዎች ቢሆንም መብራቱ አልጠፋም ግን ብዙም አልቆየም ነበር ወዲያውኑ ጠፋ አሁን ፍራቻችን የባሰ አየለ...ከእስትንፋሳችን በቀር የሚሰማ አንዳችም ድምፅ የለም ግን ትንሽ እንደቆየ ከድቅድቁ ጨለማ ውስጥ ልዝብ ያለ የእርምጃ ድምፅ እና መሬት ላይ የሚጎተት የስለት ድምፅ ተሰማ አሁን ሆስፒታሉ ውስጥ ከኛ ሌላ ሰው እንዳለ እርግጠኛ ሆንኩኝ በመሃል መብራቱ መልሶ በራ ከመፍራታችን የተነሳ መብራቱ ሲበራ እንኳን ደንግጠናል...እርምጃው ቀጥ ብሎ ግን መብራቱ ብዙም ሳይቆይ ጠፋ የሆስፒታሉ በር መግቢያጋ ያለው ብቻ ነበር የሚበራው ለዛም ነው መሰለኝ ወለሉ ላይ የሰው ጥላ ይታየኛል...ጥላው መንቀሳቀስ ጀምሯል እነ ባርሳ ማልቀስ ጀምረዋል እኔ ግን ጥላው ምን እንደሆነ ለመመልከት ከክፍል መውጫ ወደሆነው በር ዝግ ባለ እና ጥንቃቄ በተሞላው መልኩ መጠጋት ጀመርኩ "ሜርሲ የት ነው ምትሄጂው" አለኝ ባባ በሹክሸካ ድምፀት ከሱ ቀጠል አርጋ "ነይ ተመለሺ" አለችኝ ባርሳ...ሽሽሽሽ ተረጋጉ ያለውን ሁኔታ ለመመልከት ነው አልሄድም አልኳቸው ግልፅ የሆነ እይታ ባይኖረንም ውጪ ከሚበራው መብራት የሚገባው ወጋገን በጥቂቱ ብርሃን ሆኖናል...ጥላው እየቀረበ መጣ እኔም ወደ በሩ መጠጋት ጀመርኩ ያለሁበት የድንጋጤ ስሜት  ነው መሰለኝ የእግሬ ህመም ብዙም አልተሰማኝም...አሁን በሩ ጋር ደርሻለሁ አንገቴን ወደ ውጪ አስግጌ ስመለከት አንዳች ነገር የለም የሆስፒታሉ መብራት በድጋሜ ፏ ብሎ በራ በዚ ጊዜ በፍጥነት ወደ ውስጥ ተመለስኩኝ እነ ባርሳ እዛው ቦታ ላይ ቁጭ እንዳሉ ነው "ምንድነው እዚ ውስጥ ያለው ነገር" አለችኝ ቅድስቴ በተረጋጋ ድምፅ "እስካሁን ምንም ያየሁት ነገር የለም ግን ከኛ ውጪ የሆነ ሰው እዚ ሆስፒታል ውስጥ እንዳለ ይሰማኛል ለማንኛው እናንተ ተረጋጉ እኔ ሁኔታው አጣራለሁ" አልኳቸው ሶስቱም በእሺታ አንገታቸውን ነቀነቁ እኔም መለስ ብዬ ያለውን ነገር ለመመልከት በድጋሜ ከክፍሉ ወጣሁ ሁሉም ክፍሎች ዝግ ናቸው ኮሪደሩም ቢሆን ባዶ ነው ግን ከክፍሎቹ ሁላ አንዱ ክፍል ገርበብ ብሏል ቀስ ብዬ እየተራመድኩኝ ገርበብ ወዳለው በር መጠጋት ጀመርኩኝ ጀርባዬን ግድግዳው ላይ አስደግፌ የጎን ነበር ስራመድ የነበረው ግራ ቀኜን ለመመልከት እንዲመቸኝ...ክፍሉ በር ላይ ደረስኩ እስከተከፈተበት ድረስ ስመለከት ምንም አልታየኝም ግራ ቀኜን አየሁና ወደ በሩ እጄን ሰደድኩ ግን ምንም አልነበረም አንገቴን ወደ ውስጥ አስገብቼም ተመለከትኩ አሁንም ባዶ ነው ግን አንዳች ነገር ቀልቤን ሳበው በደም የተጨማለቀ መጥረቢያ ተመለከትኩ እንደገመትኩትም ያ ሰው በዙሪያችን ነው ያለው ማንነቱን ለመለየት በድፍረት ወደ ውስጥ ገባሁ መጥረቢያው ወዳለበት ተጠግቼ ስመለከት በውስጥ በኩል ሌላ በር አለ መጥረቢያውን ትቼ ወደ ውስጠኛው በር አመራሁ ሆስፒታሉ አሰራሩ በጣም ውስብስብ ነው ወደ ውስጠኛው በር እንደተቃረብኩ ያልጠበኩትን ነገር ተመለከትኩ ወለሉ ላይ ወደ ውስጥ የሚያስገባ መንገድ ተመለከትኩ መስኮት የሚመስል መዝጊያ አለው ወለሉ ላይ በርከክ ብዬ ስመለከት ወደታችኛው ክፍል የሚወስድ በደም የተጨማለቀ ደረጃ ተመለከትኩ በጣም ደነገጥኩኝ ያ ሰው አዳኝ ሰውዬ መኖሪያው እዚ እንደሆነ ተሰማኝ በመሀል መብራቱ ድርግም ብሎ ጠፋ አሁን ካለሁበት ቦታ መሄድ ስላለብኝ ለደህንነቴም ስለሚያሰጋኝ የመጣሁበትን በምናቤ ስዬ ግድግዳውን እየተደገፈኩ ከክፍል ለመውጣት ሙከራ ጀመርኩ ግን ሳልጠብቀው እጄ የሰው አካል ላይ አረፈ.............


part #16  ___ ይቀጥላል

ቶሎ እንዲለቀቅ 👍 አሳዩኝ

ከተመቻቹ ÷

                
#𝐑𝐞𝐚𝐜𝐭
                
#𝐂𝐨𝐦𝐦𝐞𝐧𝐭
                
#𝐬𝐡𝐚𝐫𝐞 🙏

    
¶ 𝚈𝙴𝙵𝙸𝙺𝙴𝚁 𝙲𝙻𝙸𝙽𝙸𝙲🥀 ¶™🌐

  📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት! 📱

5.2k 0 22 16 74

 
ልብ አንጠልጣዩ "የጠፋው
ሬሳ"
            
  ተከታታይ ትረካ

                 #ክፍል_14


...
በጣም ደነገጥኩኝ አንዳች አደጋ ደርሶበት ወደዚ ሆስፒታል መጥቶ ነበር ግን ለምን ህክምናውን ሳይጨርስ ወጣ? ማንስ ሊያስወጣው ቻለ? ዶክተሮቹስ የት ሄደው ነው? የሚሉ መልስ አልባ ጥያቄዎች አይኔን ጫማው ላይ ተክዬ ሳለ ውስጤ ይመላለሱ ነበር ከጫማው ትንሽ ተስፈንጥሮ አንድ ግራ ሚያጋባ ነገር ተመለከትኩ ለማየትም እንዲያመቸኝ ወደፊት እየተጠጋሁ ሳለ ባርሳ "ሜርሲ" እያለች ስጠራኝ ተሰማኝ እኔ ያለሁበት ስፍራ ከመጡ የሚፈጠረውን ስሜት ስለማውቀው ቶሎ ወደ ሆስፒታሉ ተመለስኩ እግሬ ቢያስነክሰኝም እርምጃዬን ፈጠን አድርጌ ወደነሱ ሄድኩኝ ሳያቸው ሶስቱም ፊት ላይ አንዳች ልዩ ነገር ይታየኛል "የት ሔደሽ ነው?" አለች ሜርሲ በንዴት ስሜት ውስጥ ሆና የሷን ጥያቄ መመለስ ሳልጀምር ቅድስቴ ተከተለች "በቅጡ እንኳን የረባ ህክምና ሳታገኚ ምንድነው ሚያዞርሽ" አለችኝ በጣም ደነገጥኩት "ምን የተፈጠረ ነገር አለ" ብዬ ጥያቄዬን ቀጠል አደረኩኝ "የመኪናችንን ጎማ ማን እንደሆነ እንጃ በሆነ ነገር ወግቶታል" አለ ባባ ወዲያውኑ ያ ሰው ነበር ጭንቅላቴ ውስጥ ብልጭ ያለው "የመንደሩ ነዋሪ መሆን አለበት ማለትም ያ አንቺ ከምታስቢው ሰውዬ ሌላ" አለ ባባ እንዴት እንደዚ ማለት እንደቻለ ጥያቄ ፈጥሮብኛል ሆኖም ግን ምንም አላልኩትም ነበር...መልስ ሳልሰጣቸው ወደ መኪናው እያነከስኩኝ ሄድኩ እነሱም ከሗላዬ ተከተሉኝ የሗላው ጎማ ነበር የተወጋው...የቆምንበት ስፍራ ከአስፓልቱ ወረድ ብሎ ስለነበር አፈርማ ነው ግን መኪናው ዙሪያ ምንም አይነት የእግር ኮቴ የለም ከእኛ ውጪ...ከኛ መኪና ትንሽ ተስፈንጥሮ የሆነ ነገር ተመለከትኩ እያነከስኩኝ ተጠጋሁ "ምንድው ሜርሲ" አለችኝ ባርሳ የማየውን ነገር እስካረጋግጥ ድረስ ምንም አላልኳትም ነበር ግን ከእኛ ሌላ እዚ አካባቢ የቆመ መኪና እንዳለ ይሰማኛል እኛ ከቆምንበት በተቃራኒ አቋቋም የሆነ መኪና እንደነበር ያስታውቃል...ግን ሙሉ ለሙሉ ከአስፓልቱ ወርዶ አልቆመም ነበር በአንድ ጎን ያሉት ጎማዎች ናቸው አፈሩ ላይ ያረፉት አሁንም የጎማውን ቅርፅ ወዳየሁበት በጥንቃቄ መመልከት ጀመርኩኝ ይመስለኛል መኪናው ለኛ መኪና ጀርባውን ሰጥቶ ነው የቆመው አቅጣጫው ደሞ እና በቆምንበት ነበር...አተኩሬ ስመለከት የሰው የእግር ኮቴ አለ ኮቴውን እየተመለከትኩ ተጠጋሁ ብዙ ዱካ የለውም ከአምስት እርምጃ በላይ አልተራመዳም ታዲያ ወደመኪናችን እንዴት ሊደርስ ቻለ የሚለው ጥያቄ ውስጤ እያሰላሰልኩ ያለፍኳቸውን የእግር ዳና ድጋሜ እየተመለከትኩ ሳለ አስፓልቱ ላይ የእግር ዱካ ተመለከትኩ ይህ ሰው ካቆመው መኪና እስኪያልፍ ብቻ ነው የተራመደው ከዛ በአስፓልቱ ተራምዶ ወደ መኪናችን ይደርሳል አሁን ጥርጣሪዬ እውነት እየመሰለ ነው...እነ ሜርሲም የማየውን ነገር ሲያዩ የሆነ ነገር እንደተገለጠላቸው ያስታውቃሉ ወዲያው የመኪናው የፊት ጎማ ወዳረፈበት ተጠጋሁ ሲገባና ሲወጣ ይመስለኛል በዛ ያለ ዱካ ይታያል "ያ ሰው አሁንም እየተከታተለን ነው አልተወንም" አልኩኝ "ምነው እግራችንን በቆረጠው ባንመጣስ" አለች ባርሳ እጅግ ተበሳጭታ "አሁን ማማረሩን ትተን ከዚ አካባቢ የምንሄድበትን መንገድ እንፍጠር መዋከቡ ዋጋ ቢስ ነው" አለች ቅድስቴ የማልጠብቀውን የእርጋታ ስሜት እያሳየች "ልክ ብለሻል" በማለት ባባ በሀሳቧ ተስማማ "ትርፍ ጎማ አልያዝክም" ብዬ ባባን ጠየኩት በጭንቅላቱ ንቅናቄ አለመያዙን ነገሮኝ ቀጠል አርጎ "ጎሚስታ ቤት ነው ያለው ኔትወርክ እንኳን ቢኖር ብደውል ይልኩልኝ ነበር" አለ "እና ዛሬ እዚ ልናድር ነው" አለች ባርሳ በጭንቅላቴ ንቅናቄ አውንታዬን ገለፅኩላት ቢመራትም ትዋጠው ምንም ምርጫ የለንም እዚ ባናድር መልካም ነበር ግን አለማደር አንችልም...ሰዓቱ ተጉዞ ወደ አመሻሹ እየተቃረበ ነው ከመኪናው ውስጥ ምግብና አልባሳት ይዘን ወደ ሆስፒታሉ ውስጥ ተመለስን እኔ ከታከምኩበት ክፍል ፊት ለፊት ገባንና ማስተካከል ጀመርን እኔም ልብሴን ለመቀየር ወደ ሻንጣዬ ሄድኩኝ ለአይን ያዝ ያዝ ማረግ ጀምሯል ባባ መብራት ካለ ብሎ ሲሞክር ምንም የለም "መቆጣጠሪያው ጋ አይቼ ልምጣ" ብሎ ባባ ወጣ "ተጠንቀቅ አባቴ" አለች ባርሳ በስስት እያየችው ይሄን ጊዜ ቅድስቴ አይኗ እንባ አረገዘ የባሰ እንዳይከፋት ብዬ ምንም አላልኳትም እኔም ልብሴን ቀያይሬ ተቀመጥኩ ባባ ተሳካለት መሰለኝ መብራቱ በራ "የስ" አሉ ቅድስቴና ባርሳ እኔም ፈገግ አልኩኝ ወዲያውኑ ምግቡን አቀራረቡት ባባም መጣና ለመመገብ ተዘጋጀን በሩን ዘጋንና መመገባችንን ጀመርን አሁን ምሽቱ ጀምሯል ነፍሴ እየተጨነቀች ነው...እየተጨዋወትን መመገባችንን ቀጠልን ግን መብራቱ ጠፋ በጣም ደነገጥን ሁላችንም ፀጥ አልን የሆስፒታሉ አንዱ ክፍል በሃይል ጓ ተደርጎ ተዘጋ በጣም ደነገጥን ግን መብራቱ ወዲያውኑ መጣ ውጪ ያለውን ነገር ለመመልከት ሁላችንም ተነስተን በሩን ከፍተን ወጣን ግን አንዳች አልነበርም ወዲያውኑ ድጋሜ መብራቱ ጠፋ ግን ባሁኑ ብዙ አልቆየም ከመቅፅበት መጣ ደግሞም ጠፋ ድጋሜ ሲበራ ግን................


part #15  ___ ይቀጥላል

ቶሎ
እንዲለቀቅ 👍 አሳዩኝ

ከተመቻቹ ÷
                 #𝐑𝐞𝐚𝐜𝐭
                 #𝐂𝐨𝐦𝐦𝐞𝐧𝐭
                 #𝐬𝐡𝐚𝐫𝐞 🙏

    ¶ 𝚈𝙴𝙵𝙸𝙺𝙴𝚁 𝙲𝙻𝙸𝙽𝙸𝙲🥀 ¶™🌐

  📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት! 📱

7.7k 0 27 112 131

ልብ አንጠልጣዩ "የጠፋው ሬሳ"

            
  ተከታታይ ትረካ

                 #ክፍል_፲፫
 
..
.ሁኔታዋ ግራ ስላጋባኝ "ይመስለኛል ይሄ ታካሚ ድንገተኛ አደጋ ደርሶበት ነው የመጣው" አለች "በምን ልታውቂ ቻልሽ ብዬ" ጥያቄዬን ቀጠል አድርጌ እየጠየቋት "የህክምና ካርዱ ላይ የታካሚው ስም የለበትም የመድሃኒት መዘዢያውም ላይ እንዲሁ" ብላ መለሰችልኝ "ቀንስ አልተፃፈበትም" አልኳት በውስጤ የማስበው አንዳች ነገር ስለነበር ክፍሉ ወውስጥ ወዳለው ወደ አንዱ ጠረጴዛ እያመራች የመድሀኒት ማዘዣ ወረቀቱን እየተመለከተች "ቀኑ ትላንት ነው ወደዚ ስፍራ የመጣው ሰዓቱ ግን የለም" ብላ መለሰችልኝ የራጅ ወረቀት ከጠረጴዛው ላይ አንስታ ከፍ አርጋ እየተመለከተች "ግን ታማሚው አብዛኛው የሰውነት ክፍሉ ያን ያህል አልተጎዳም ግን የሗላ የጭንቅላት ክፍሉ ላይ የአጥንት መሰንጠቅ ይታያል ከሆነ ነገር ጋር እንደተጋጨ ወይም በሆነ ነገር እንደተመታ ገምታለው" ብላ ስለ ራጅ ምሰስሉ አብራራችልኝ የጭንቅላት የሗላ ክፍሉ ስትል ጫካ ውስጥ የተመለከትኩት የቅድስት ጓደኛ የአወዳደቅ ሁኔታ ውስጤ ብልጭ አለብኝ እሱ ሊሆን እንደሚችልም አሰብኩ "ግን እዚ ማን ሊያመጣው ይችላል"  ብዬም እራሴን ጠየኩ ሳላስበው ድምፄን ከፍ አድርጌ ነበርና "ምን አለሽኝ" አለችኝ ቅድስቴ "አይ ምንም እንዲሁ ከራሴጋ እያወራሁ ነው ብዬ መለስኩላት ከደቂቃዎች በሗላ እነ ባርሳ መጡ "ምነው ቆያቹ" አለች ቅድስቴ ባባም ቀበል አርጎ "ቶሎ ማግኘት አልቻልንም ለዛ ነው አሁን ሜርሲ እንዴት ነሽ" አለኝ "ደህና ነኝ አሁን ምንም አልልም" በማለት እንዳይጨነቁ ደህና ነኝ አልኩኝ እንጂ ክፉኛ እያመመኝ ነው ቅድስቴ መድሃኒቶችን መዘጋጀት ጀምራለች ግን በመጠራጠር ስሜት ሆና ደግማ ቁስሌን ተመለከተችው "ራጅ ብትታዪ መልካም ነው ሜርሲዬ" አለችኝ "እንዴ ለምን" ብዬ በጥያቄ መለስኩላት "የአናትሽ በስጋ የሸፈነው ክፍል ክፉኛ በወጋሽ ነገር ተቀዷል በዚህ ሁኔታ አጥንትሽም ሊነካ ይችላል" ብላ መለሰችልኝ ባለችው ነገርም ተስማማሁ የተኛሁበትንም አልጋ እየገፉ ወደ ክፍሉ ማምራት ጀመርን በሩ ላይ የተፃፉትን እያነበብን ነበር ፍለጋችን ከተወሰኑ ክፍሎች በሗላ አገኘነው ወደ ውስጥም ዘልቀን ገባን ግን ምንም አልነበረም ባዶ ክፍል ነበር ባየነው ነገር ሁላችንም ግራ ተጋባን "ይህ እንዴት ሊሆን ቻለ" አለ ባባ "አዲስ ሆስፒታል ነው እንዴ?" አለች ባርሳ ከባባ ቀበል አርጋ "በቅርብ ቀን የተሰራ የራጅ ውጤት እኮ አሁን ተመልክቻለሁ ግን እንዴት ላይኖር ቻለ" አለች ቅድስቴ ግራ በመጋባት ስሜት ሆና "ቁስሉ ንፋስ ስለሚገባበት በቃ መሰፋት አለበት" አለች ቀጠል አርጋ ከዛ ክፍል ወጥተን መጀመሪያ ወደነበርንበት ክፍል ማምራት ጀመርን ሆስፒታሉ ሲበዛ ነጭ ነው ፍሎረሰንት በሚባለው የአንፖል አይነት እጅግ ደምቋል እይታው ራሱ ትንሽ ህመምን ያቀላል ፈፅሞ ሰላም ይሰጣል ወደነበርንበት ክፍል ዘልቀን ገባን የህክምና ጓንቷን አድርጋ በደረቴ ከነ ባርሳ ጋ ሆነው አስተኙኝ ከዛም ህክምናውን ጥንቃቄ በተሞላው መልኩ ፈፀመችው ከዛም አገችው "አሁን ከኢንፌክሽን ነፃ ነሽ" አለችኝ "በቃ እሺ ከዚ አካባቢ በፍጥነት እንውጣ" አለ ባባ አዎ ብለው እነ ቅድስቴ በሀሳቡ ተስማምተው እኔን ደግፈው አነሱኝ እራሴን ችዬ መሄድ እንደምችል ነገርኳቸው እና የተኛሁበት አልጋ ላይ ቁጭ አልኩኝ እነሱ እዛው ባለሁበት ሆኜ ወደ መኪናው ሄዱ ከአልጋው ተነስቼ እየተራመድኩ ወደ መስኮቱ አመራሁ መጋረጃውን ገለጥኩት መስታወቱ ተሰብሮና በደም ተጨማልቆ ነበር ሲመስለኝ የሆነ ሰው ለማምለጥ በዚ በኩል ወድቋል በተሰበረው መስታወት ውስጥ አንገቴን ወደ ውጪ አውጥቼ ስመለከት ሳሩ በደም ተለውሷል የሆነ ሰው እየተንፏቀቀ እንደሄደበት አይነት ምልክት አለው አንገቴን ወደ ውስጥ መልሼ መስኮቱን በመክፈቻው ከፍቼ ቀስ ብዬ ወጣሁ የደሙንም ምልክት እየተመለከትኩ ወደፊት አመራሁ ማን እንደሆን እንጃ ብቻ ክፉኛ የተጎዳ ሰው ነው ከሆነ እርምጃ በሗላ ደሙ ላይ ተለቅ ያለ የጫማ ምልክት ተመለከትኩ እዛው ባለሁቡት ቆምኩኝና አይኔን አሻግሬ ወደፊት ሰደድኩት ከአንድ ስፍራ ላይ ሲንፏቀቅ ይፈስ ከነበረው ደም ይልቅ ብዙ ደም ፈሿል ሳሩም የተረጋገጠ ይመስላል ከዛ ከተጎዳው ሰው ሌላ ሌላም ሰው ነበር ... መሬት ራሱን እያንፏቀቀ ይሄድ የነበረው ሰው በድንገት ጠፋ እርምጃዬን ቀጠል አደረኩኝ አንዳች ምልክት አልነበረም ግን ከትንሽ እርምጃ በሗላ የተንጠባጠበ የደም ጠብታ ተመለከትኩ እሱን ተከትዬ መሄድ ጀመርኩ ዞር ብዬ ስመለከት ከሆስፒታሉ እየራኩኝ ነው ግን ለመመለስ አልፈለኩም እርምጃዬን ቀጠልኩ የደሙን ጠብታ ተከትዬ ስጓዝ ከአንድ ጫካ አጠገብ ደረስኩ አሁን እርምጃዬን ገታሁት ነገር ግን የደም ጠብታው እንደ ቀጠለ ነው ከጫካው መግቢያ ላይ አንድ ነጭ ነገር ተመለከትኩ ወደ ውስጥ ብዙም ያልገባ ስለነበር ለመመልከት ተጠጋሁ የቅድስቴ ጓደኛ ጫማ ነበር............

_part  #14  ___ ይቀጥላል


ሎ እንዲለቀቅ 👍 አሳዩኝ

ከተመቻቹ ÷
                 #𝐑𝐞𝐚𝐜𝐭
                 #𝐂𝐨𝐦𝐦𝐞𝐧𝐭
                 #𝐬𝐡𝐚𝐫𝐞 🙏

    ¶ 𝚈𝙴𝙵𝙸𝙺𝙴𝚁 𝙲𝙻𝙸𝙽𝙸𝙲🥀 ¶™🌐

  📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት! 📱

7.7k 0 34 114 94

ኧረ ግን እስቲ ምን ይሰማችኋል ልወቅ😌

𝙘𝙤𝙢𝙢𝙚𝙣𝙩
👇👇👇


ልብ አንጠልጣዩ "የጠፋው ሬሳ"

            
  ተከታታይ ትረካ

                 #ክፍል_፲፪

    
  
...በጣም ደነገጥኩኝ አንዳች ነገር ሆ
ነው እንደው ብዬም ተጨነኩኝ ባባ ይቁነጠነጣል ምን እንደሚያደርግ ፈፅሞ ግራ ገብቶታል ግን ከትንሽ ደቂቃ በሗላ ሁለቱም መጡ ባዩኝ ጊዜ በጣም ደነገጡ ባርሳም ወደኔ እየመጣች "ምንድነው ሜርሲ ምን ሆንሽብኝ" አለች ምንም መልስ አልሰጠሗትም ቅድስቴም እኔን አይታ "ከዚህ ቦታ አሁኑኑ ተነስተን መሄድ አለብን አንድ በአንድ ከማለቃችን በፊት" አለች ትዕዛዝ የሆነ ንግግር ቁጣም ቀላቅላበት "አሁን ተረጋጉ መጀመሪያ ሜርሲን ወደ ሀኪም ቤት እንውስዳት" አለ ባባ ድንኳኖቹን እየነቃቀለ እነ ባርሳም ሌሎች ዕቃ በማዘገጃጀት እያገዙት...ቅድሚያ እኔን ወደ መኪናው ወሰዱኝና እነሱ እየተመላለሱ ዕቃዎቹን ጫኑ ከደቂቃ በሗላ ጉዞ ጀመርን በተቀመጥኩበት የጋቢና መስኮት በኩል ፊቴን መስታወቱ ላይ ተደግፌ አይኔን ወደ ውጪ ልኬ ያንን ክፉ ጫካ እየተመለከትኩ ጉዞዬን ቀጠልኩ እጅግ በጣም ሰፊ ቦታ የያዘ ውስጡ ጨለማ የሆነ ጫካ ነው  ከዚ ስፍራ በሰላም መውጣታችን እጅግ ድንቅ ነው..."አይዞሽ የኔ ጓደኛ ምንም አትሆኚም" አለች ባርሳ በእጇ ትከሻዬን እየነካች እሺታዬን በአንገቴ ንቅናቄ ገለፅኩላት ጉዟችን ለረጅም ደቂቃዎች ፀጥታ የተሞላበት ነበር ሁላችንም የድንጋጤ ስሜት ላይ ስለሆንን ይመስለኛል ከግማሽ በላይ ለሆኑ ደቂቃዎች ጉዞ በሗላ አንድ የድሮ ሆስፒታል ተመለከትን  ታፔላው እንኳን የለም ነበር በሽተኛም ሆነ ዶክተር በዙሪያው አይታይም ባዶ ነበር መኪናችንን ከመግቢያው ትየይዩ አድርገን አቆምናት "እዚሁ ጠብቁኝ" አለ ባባ ከመኪናው እየወረደ ውስጡ ገብቶ ያለውን ነገር ቃኝቶ መግባት እንደምንችል ነገረን እነ ባርሳ ቀድመው ወርደው በጥንቃቄ ከመኪናው አወረዱኝና መሸከም የሚለው ቃል በሚገልፀው ድጋፍ ደግፈውኝ ወደ ውስጥ ገባን ፍፁም ፀጥ ያለ ስፍራ እርገግጠኛ ነኝ ከኛ ሌላ በዚ ሆስፒታል ውስጥ የለም ባባ ከኛ በፊት እየተራመደ ወዴት መሄድ እንዳለብን እየመራን ነው ከጥቂት እርምጃ በሗላ ከአንድ ክፍል በር ላይ ቆመ ወደ ውስጥም እንድንገባ ምልክት ሰጠን ገባንም ወዲያው ክፍሉ ውስጥ ካለው አልጋ ላይ አስተኝተውኝ መድሀኒት መፈለጉን ተያያዙት በነገራችን ላይ ቅድስቴ የህክምና ተማሪ ነች "አይዞሽ ሁሉም ሰላም ይሆናል አለ ባባ ከዛም ቅድስቴ በደረቴ መተኛት እንዳለብኝ ነግራኝ ለሶስት ገለበጡኝ የጭንቅላት ቁስሌን ለማከም እንዲመቻት...ከዛም ቁስሉን ለመመልከት ፀጉሬን ስትገለጥ ቁስሌ ላይ ተጣብቆ ኖሮ እጅግ አመመኝ ግን ህመሙን ጨክኜ ያዝኩት ከዛም ፀጉሬን መቁረጥ ጀመረች ባርሳ ከፊት ለፊቴ ካለው ወንበር ላይ ሆና አይዞሽ እያለች ታበረታኛለች አሁን ቅድስት ቁስሉን ለመመልከት ግልፅ ሆነላት መሰል መሰፋት አለበት አለች በሰለለ ድምፅ ሆኜ "እንደዚ አይሆንም እንዳታደርጊው" አልኳት "የጭንቅላትሽን ክፍተት ቶሎ ካልሸፈነው ወደ ሌላ ኢንፌክሽን ሊቀየር ይችላል እዛ ደረጃ ከመድረሱ በፊት አሁን ላይ እንፍጠን" አለች ባርሳ ጭንቅላቷን በመነቅነቅ በቅድስቴ ሀሳብ መስማማቷን ገለጸች "ግን እርግጠኛ ነሽ ይሄን ማረግ ትችያለሽ?" አለ ባባ እርግጠኛ ለመሆን እየጠየቀ "በኔ ተማመን ምንም አይፈጠርም" አለች ባባም ተስማማ እኔም ውስጤን አሳመንኩትና ተዘጋጀሁ የዶክተሮቹን ጓንት አድረገችና በሆነ ፈፃሽ ቁስሌን ማጠብ ጀመረች በትንሹ የማቃጠል ስሜት ይሰማኛል "አቃጠለሽ እንዴ" አለችኝ ቅድስቴ "በትንሹ" ብዬ መለስኩላት "ሰውነትሽ እየደነዘዘ ነው ማለት ነው" ብላ መለሰችልኝ "እንደዚም ቢሆን ግን ማደንዘዣ ያስፈልገናል" አለች ቅድስቴ በቁራጭ ወረቀት ላይ የሆነ ነገር ፅፋ "ይሄን መድሃኒት ፈልጉ" አለቻቸው እነ ባባን "ከየት" አለች ሜርሲ ግራ በመጋባት  "ከክፍሎቹ አንዱ የመድሃኒት ማከማቻ መሆኑ አይቀርም ፈልጉና አምጡ" ብላ ትዕዛዝ ሰጠች እነሱም ተቀብለው አብረው ወጡ ከዛ ጫማዬን ፈትታ የእግሬን ቁስል መመልከት ጀመረች "የወጋሽ ነገር ብረትነት አለው" ብላ ጠየቀችኝ "እሾህ ነው መሰለኝ አላስተዋልኩትም" ብዬ መለስኩላት "ለማንኛውም ለጥንቃቄ ቲታነስ መወጋት አለብሽ" አለችኛና መድሃኒቷን ማዋሃድ ጀመረች "ከዚ ክፍል የጠፋ ወይም ህክምናውን ሳይጨርስ የወጣ ሰው አለ " አለችኝ በጣም ግራ ተጋብቼ  "በምን አወቅሽ" ስላት የህክምና ካርዱ እና እዚ ያሉት መድሃኒቶች የሱ ናቸው" ብላ መለሰችልኝ "ስሟ ማን ይላል" ብዬ ጠየኳት እሷም እያነበበች ድንጋጤ በሚመስል መልኩ ግንባሯን አጨማደደች "ምነው" አልኳት...

_part  #13  ___ ይቀጥላል

ቶሎ እንዲለቀቅ 👍 አሳዩኝ

ተመቻቹ ÷
     
            #𝐑𝐞𝐚𝐜𝐭
                 #𝐂𝐨𝐦𝐦𝐞𝐧𝐭
                 #𝐬𝐡𝐚𝐫𝐞 🙏

    ¶ 𝚈𝙴𝙵𝙸𝙺𝙴𝚁 𝙲𝙻𝙸𝙽𝙸𝙲🥀 ¶™🌐

  📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት! 📱

8.8k 0 35 48 111

ልብ አንጠልጣዩ "የጠፋው ሬሳ"

            
  ተከታታይ ትረካ

                 #ክፍል_፲፩

..."
ምን ተፈጠረ ሜርሲ" እያለ ወደኔባባ ነበር ነፍሴ አሁን ተረጋጋች ምንም መልስ ሳልሰጠው መሬቱ ላይ ተንጋለልኩ "ሜርሲ" እያለ ወደኔ ተጠጋ ከተኛሁበት ደግፎ አንስቶ አቅፎ ወደ ድንኳናችን ይዞኝ መሄድ ጀመርን ላወራው እየፈለኩ ነው ግን አንደበቴ ሊታዘዘኝ አልቻለም ብቻ በአይኖቼ ሽቅብ እየተመለከትኩት ድንጋጤውን ከፊቱ ላይ እያነበብኩት ነበር ዞሪያ ገባውን እየቃኘ በፍጥነት ይራመዳል ከበድኩት መሰለኝ ማለክለክ ጀመረ ትንሽ እንደተጓዝን ቀጥ ብሎ ቆመ ምን እንደተመለከተ ባላውቅም ቀስ አድሮጎ አስቀመጠኝና ወደ ተመለከተው ነገር ጉዞ ጀመረ ከዚ ጫካ ቶሎ መውጣት እንዳለብን እና የደረሰብኝን ነገር ብነግረው ምነኛ ደስ ባለኝ ነበር ትንሽ ከተራመዳ በሗላ ጎንበስ ብሎ የሆነ ነገር አነሳ ምን እንደሆነ ባላስተውለውም ከዛን ወዲያውኑ እርምጃውን ጨምሮ ወደኔ መጣ በእጁ ላይ ጫማ ይዟል የቅድስቴ ጓደኛ ጫማ ነበር በዛ ክፉ ሰው ጥቃት እንደደረሰበት ተረዳሁ ከተቀመጥኩበት እንደምንም የዛፍ ግንድ ተደግፌ ተነሳሁ ጫማው ወደተገኘበት ቦታ ባባን ምርኩዝ አድርጌ ተጠጋሁ...ይመስለኛል ከድንኳኑ ጫማው እስከተገኘበት ስፍራ ድረስ ተሸክሞ ነው ያመጣው...ጫማውን ካገኘንበት በሗላ ደግሞ መሬት ላይ እንደተጎተተ የሚያሳይ የመሬት ቅርፅ አለ...ቀስ እያልኩ ወደፊት በመሄድ መመልከት ጀመርኩ በጫካው ውስጥ አነስ ብላ ጠንከር ያለች ተክል ተመለከትኩ ቅጠሎቿ እና አነስተኛ ቅርንጫፎቿ በደም ተለውሰዋል ይመስለኛል ሰውየሰው የቅድስትን ጓደኛ ሲጎትተው ተክሏን የሙጥኝ ይዟት ነበር ከዛም ሲመነጭቀው የውስጥ እጆ ተቦጫጭሮ ተክሏን ደም እንደለወሳት ተሰማኝ...አሁንም ባባን ተደግፌ ወደፊት እየተጓዝን ነው "ሜርሲ ከዚ ቦታ ቶሎ እንውጣ በጣም አስፈሪና ለኛም ጥሩ አይደለም የሆነው ሆኗል እኛ ከዚ መሄድ አለብን" አለኝ ባባ ወደሗላ እንድንመለስ እየጠቆመኝ እንደምንም ብዬ አንደበቴን ከፍቼ "ያ..ን ሰ..ሰ..ውዬ ሳ..ል..ገ..ለ..ው አልሄድም አልኩት "እየቀለድሽ መሆን አለብት እነዳለ እንድናልቅ ካልፈለግሽ በቀር ሌላ ምንም የሚያቆየን ነገር የለም" አለኝ ቁጣ ሀይል በተቀላቀለው ድምፅ "የበሰበሰ ዝናብ አይፈራም" ይላል ያገሬ ሰው አልኩኝ ለራሴ ምን እንደሆነ ባላውቅም ውስጤን እልህና በቀል ይሰማኛል "እንሄዳለን ግን ቢያንስ ወዴት እንደወሰደው ለማወቅ ትንሽ ወደፊት ሄደን እንይ" አልኩት በሚቆራረጥ ድምፅ "እሺ" ብሎ ደግፎ ወደፊት ወሰደኝ የተጎተተበትን ምልክት እየተከተልን ትንሽ እንደተጓዝን የልብስ ብጫቂ ተመለከትን ባባን ለቀኩትና ወደ ብጫቂው ጨርቅ ዝቅ አልኩኝ በእጄም ይዤ አነሳሁት ሹል ድጋይ ላይ ነበር የተጣበቀው እላዩ ላይ ትንሽ የስጋ ቁራጭ አለበት ይመስለኛል በመሬቱ ላይ ሲጎትተው ድንጋዩ ጀርባውን ፍቆታል ድንጋዩም ስጋውንና የልብሱን ብጫቂ እራሱ ላይ አስቀርቶታል ስቃዩን ሳስበው የሚያወጣውን የሲቃ ድምፅ በምናብ ሳደምጠው ልቤ ተሸበረ ግን ደሞ ክፉኛ እልህ ውስጥ ገባሁ "የሚበቃሽን ያህል ተመልክተሻል አሁን ተነሺና ከዚ ቦታ እንሂድ" አለኝ እጁን እየዘረጋልኝ  ባባ እጅግ ተጨንቋል ፊቱ ላይ ይነበብበታል እኔም እጄን ሰጠሁትና ከተቀመጥኩበት ተነሳሁኝ የባባንም ሀሳብ ተቀብዬ ወደፊት ማዝገም ጀመርን "አንቺ ግን እንዴት እንደዚ አይነት ጦስ ውስጥ ራስሽን ትከቻለሽ ለራስሽ አታስቢም እንዴ" ብሎ ጠየቀኝ "እንደዚ ከባድ መሆኑን አላወኩኝም እኔማ የቅድስቴን ጓደኛ ይዤ ምመለስ መስሎኝ ነው እንደዛ እየሆነች እያየሗት ምንም አለማድረግ ለኔ ከባድ ነው" ብዬ መለስኩለት "እንዳልሽውም ያ ሰው ክፉና መጥፎ ነው ከረፈደ ይሄን መረዳቴ ቢፀፅተኝም ዳሩ" አለ ባባ ልክ መሆኔን እየነገረኝ "ከሰውዬውጋ ተገናኝታችሁ ነው እንደዚ ያደረገሽ" ብሎ ጠየቀኝ እሱን በምሸሽበት ጊዜ የተፈጠረ አደጋ መሆኑን ቀለል አድርጌ አስረዳሁት እኔን ላለማስደንገጥ እንጂ ሁኔታዬ በጣም እንዳስጨነቀውና የደረሰብኝ ነገር አሳስቦታል ግን በንግግር አልገለፀውም ለደቂቃዎች ከተጓዝን በሗላ የፀሃይን ወገግታ ሙሉ ለሙሉ ተመለከትኳት ጫካው ውስጥ ያን ያህል ዘልቃ አትገባም ነበር እኛ ድንኳናችንን የጣልንበት ስፍራ ዙሪያው በጫካው ተከቧል መሀሉ ባዶ ነበር እና ፀሃይ በሃይል ታገኘዋለች ትንሽ እንደተጓዝን ድንኳናችንን ተመለከትኩት ከእርምጃዎች በሗላ ደረስን ሰውነቴ አቅም አንሶታል ድቅቅ ብያለሁ "ወደ ሀኪም ቤት እንሄዳለን" አልኩት ባባን "አዎ ግድ ነው በጣም ተጎድተሻል እኮ" አለኝ ሀሳቡን መደገፌን በጭንቅላቴ ንቅናቄ አውንታዬን አሳየሁት ከጥቂት እርምጃ በሗላ ድንኳኑጋ ደረስን ከኔ ድንኳን ፊት ለፊት ያለው ድንጋይ ላይ አስቀምጦኝ እሱ ወደ ድንኳኑ ተጠጋ እኔም ለማስተዋል እንደቻልኩት ሁለቱም ድንኳን ክፍት ነበር ባባ በድንጋጤ "ባርሳ ቅድስት" እያለ እየተጣራ ድንኳኖቹን ቢያይም ማንም አልነበረም ዞር ብሎም ድምፁን ከፍ አርጎ "ሜርሲ እነ ባርሳ የሉም" አለኝ................

_part  #12  ___ ይቀጥላል

ቶሎ እንዲለቀቅ 👍 አሳዩኝ

ከተመቻቹ ÷
                 #𝐑𝐞𝐚𝐜𝐭
                 #𝐂𝐨𝐦𝐦𝐞𝐧𝐭
                 #𝐬𝐡𝐚𝐫𝐞 🙏

    ¶ 𝚈𝙴𝙵𝙸𝙺𝙴𝚁 𝙲𝙻𝙸𝙽𝙸𝙲🥀 ¶™🌐

  📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት! 📱

9.8k 0 36 13 102

 
ልብ አንጠልጣዩ "የጠፋው
ሬሳ"
            
  ተከታታይ ትረካ

                 #ክፍል_፲

...ምን
እንደሆነ ያለየሁት ነገር ከአንዱ ዛፍ ወደ ሌላው ሲሸጋገር ተመለከትኩ ሰውዬው በአቅራቢያዬ እንዳለ ይሰማኛል ጀርባዬን ዛፉ ላይ የሙጥኝ አስደግፌ ወደላይ ማንጋጠጤን ተያያዝኩት...ሰውነቴ በፍራቻ ይርዳል ቁስሌ ልቤ ስንጥቅ እስክትል እያስጨነቀኝ ነው ...ወደ ጆሮዬ የሹኩሹክታ ድምፅ ወደኔ መጣ "መፍራትሽ እውነት ነው" የሚል ነበር ከዛ ጫካው በሚያስፈራ የሳቅ ድምፅ ተሞላ ከየት እንደሚመጡ ማላስተውላቸው ድምፆች ያስጨንቁኝ ጀመር "ሞተች ሞተች" ይላሉ ደጋግመው ድምፅ እየቀያየሩ አንዴ በህፃን አንዴ በአዋቂ ድምፅ እያረጉ ለደቂቃዎች ካስጨነቁኝ በሗላ ጫካው ፍፁም ፀጥታ ወረሰው ከኔ ትንፋሽ ውጪ ምንም አይሰማም...አሁን ባለሁበት ሁኔታ ምንም ነገር ቢፈጠር ራሴን ለማዳን የምችልበት ምንም አቅም የለኝም ሁሉንም በፀጋ ለመቀበል ዝግጁ ነኝ ድንገት ሳላስበው ጥቁር የሞተ ቁራ ከየት መጣ ሳልልለው እግሬ ስር ወደቀ ድምፄንም ከፍ አድርጌ ጮውኩኝ ግን ወዲያውኑ አፌን ይዤ ድምፄን አጠፋሁና ግራ ቀኜን ቃኘው ምንም አልነበረም ከዛም እይታዬን ሁሉ ቁራው ላይ አደረኩ በስህተት ነጭ የሚባል ቀለም የለበትም ሙሉ ጥቁር ነው በሚያስገርም ሁኔታ ደግሞ ሁለቱም አይኖቹ የሉም...የአይኖቹ ስፍራ ጎድጎዳነት እንኳን የላቸውም በጣም ደነቀኝ አይቼው የማላውቀው ልዩ ፍጡር ሆነብኝ አንገቴን አስግጌ በመገረም እና በፍራቻ ውስጥ ሆኜ እየተመለከትኩት ሳላ እግሩ መንቀሳቀስ ጀመረ ልብ ምቱም ትርታ ጀመረ መሰለኝ ትንፋሽ ያስገባና ያስወጣ ጀመረ ሁኔታው አስገርሞኝ የማየውም ነገር አጠራጥሮኝ ከአይኔ ይሆናል ብዬ ጨፍኜ ገለጥኩት ግን አይኔን ስገልጠው ሌላ ያልጠበኩት ነገር ተከሰተ ቁራው ተነስቶ መጮህ ጀመረ በድንጋጤ እየጮህኩኝ ወደ ሗላ ስመለስ ተደግፌበት የነበረው ዛፍ አናቴን ክፉኛ መታኝ ጉጥ የሚባለው ነገር ነበረበትና በጣም ጎድቶኛል ከመቅፅበት ደሜ በጀርባዬ ላይ መውረድ ጀመረ ግን እዛው ቦታ ላይ ሆኜ ሰዓት አላጠፋሁም የቱንም ያህል መጓዝ ባልችልም ግን የነበኩበት አልነበርኩም በደረቴ እየተንፏቀኩ መሸሽ ጀመርኩ ቁራው አሁንም መጮሁን አላቆመም ይብሱኑ የሱን ድምፅ ተከትሎ ሙሉ ጫካው ተናወጣ ተንጫጫ የቅድሞቹ ሽኩሽታዎች በዋይታና በሲቃ ድምፅ ታጅበው ነፍሴን አወኳት ባለሁበት በደረቴ ተኝቼ ጆሮዬን በእጆቼ ድፍን አደረኩት ትንሽም ቢሆን ድምፁን ቀንሶልኛል ግን ከዛ አካባቢ መራቅ ስለነበረብኝ ወዲያውኑ ጆሮዬን ለቅቄ ጉዞዬን ጀመርኩ ከጭንቅላቴ የሚፈሰው ደም ወደ አገጬ እና አንገቴ መውረድ ጀመረ ልብሴ በራሴው ደም ጨቀየ ያም ሆነ ይህ ግን ነፍሴን ለማትረፍ እየተውተረተርኩ ነው በደረቴ እየተንፏቀኩ...ትንሽ እንደተንፏቀኩ ቀኝ ታፋዬ ላይ አንዳች ነገር ስምጥጥ ብሎ ሲገባ ተሰማኝ ድምፄን ከፍ አድርጌ ጮውኩኝ በጀርባዬ ተንጋልዬ እንደ ህፃን ልጅ አነባው ከዛም ቀና ብዬ ተመለከትኩት የአጥር ሽቦ ነበር ሱሪዬን ከገላዬ እኩል ሰንጥቆታል ቀስ ብዬ ቀና አልኩና ተቀመጥኝ የተሰነቀረብኝንም ለመንቀል ተያያዝኩት ግን እጄ እየተብረከረከ ነበርና ምንም ሊመቸኝ አልቻለም እንባዬ ከአይኔ ዱብ ዱብ ይላል ደሜ ከጭንቅላቴ ላይ ይወርዳል አሁን ሸቦው የቀደደው እግሬ ነጩ እስኪታይ ዘልልቆ ሰንጥቆኛል በዛ ላይ ጠማማ ነው መሰለኝ እንደ ወስፌ የውስጥ ስጋዬን ይዞታል ስቃዬ እጅግ በዛ ቀስ ብዬ በጀርባዬ ተንጋለልኩ አይኖቼም መስለምለም ጀመሩ አቃተኝ...ትንሽ እንደተኛሁኝ እጅግ ፈጣን የእግር ኮቴ ተሰማኝ እዛው በተኛሁበት ስመለከተው ጥቁር ከስክስ ጫማ ማድረጉን ተመለከትኩ ከተኛሁበት በድንጋጤ ተነስቼ ስዞር...........

_part  #11  ___ ይቀጥላል

ቶሎ እንዲለቀቅ 👍 አሳዩኝ

ከተመቻቹ ÷
                 #𝐑𝐞𝐚𝐜𝐭
                 #𝐂𝐨𝐦𝐦𝐞𝐧𝐭
                 #𝐬𝐡𝐚𝐫𝐞 🙏

    ¶ 𝚈𝙴𝙵𝙸𝙺𝙴𝚁 𝙲𝙻𝙸𝙽𝙸𝙲🥀 ¶™🌐

  📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት! 📱


ልብ አንጠልጣዩ "የጠፋው ሬሳ"

            

           
  ተከታታይ ትረካ

                
#ክፍል_፱


....ሰውዬውም ባትሪውም የለም
በጣም ደነገጥኩኝ የሆነ ነገር እያሰበ እንዳለ በውስጤ ይታወቀኛል ከተደበኩበት ቦታ በእርጋታ ተነስቼ በፊት ወደነበርኩበት ስፍራ ተመለስኩ ተረከዜ አላስረግጥ ብሎ ያስነክሰኛል በዛ ላይ ደሜ መቆም አልቻለም... ወዲያውኑ በሰከንድ ልዩነት ተደብቄ የነበርኩበት የወደቀ ዛፍ ጋ ባትሪው በራ በዛው ቅፅበት መጥረቢያውም ተሰነዘረ በዛ ቦታ ብሆን ምን እንደምሆን አሰብኩት...በቦታው አለመኖሬን ሲመለከት እና ሲያጣኝ በጣም ተበሳጭቶ ባትሪውን መሬት ወርውሮ "ዛሬ ማንም አያመልጠኝም" እያለ እየተውተረተረ ማውራት ጀመረ እንዳጋጣሚ የወደቀው ባትሪ ሙሉ ከወገብ በላይ እሱ ላይ ያበራበት ጀመር ረዘም ያለ ኮፊያ ያለው ካፖርት ለብሷል ነገር ግን ፊቱን ለመለየት ያዳግታል ኮፊያው ግማሽ ፊቱ ድረስ ሸፍኖታል ወዲያው የተደበኩበት ስፍራ ጋር ዝቅ ብሎ እጁን ወደ መሬት ሰንዘሮ ወደ አፍንጫው መለሰው ይመስለኛል ደሜን እያሸተተ ነው ከዛም ከመቅፅበት ተነስቶ ቀጥ ብሎ ቆመ አፍንጫውንም እያንቀሳቀሰ ማነፍነፍ ጀመረ በዚ ሰዓት የሆነ መንገድ መጠቀም እንዳለብኝ ተረዳሁ ከውስጥ የለበስኩትን ቦዲ ቀስ ብዬ አውልቄ መልሼ ጃኬቱን ለበስኩት ተረከዜንም በቦዲው አሰርኩት ሽቶ ስለነበረው የደሜን ሽታ ይሸፍንልኛል ብዬ በማሰብ ሰውዬው አሁንም እያነፈነፈ ነው ከዛም እርምጃ ጀመረ እኔም ካለሁበት ተነስቼ ወደ ሌላ መደበቂያ መሄድ ጀመርኩ ባትሪው እዛው አሁን በሙሉ ጨለማው ውስጥ እኔና ሰውዬው እየተሳደድን ነው...ድንገት እርምጃው ቆመ እኔም እርምጃዬን አቆምኩ ይመስለኛል ከሱ ሌላ የእግር ኮቴ እንዳለ ተረድቷል እኔ ገብቶኛል ነገር ግን መቆም እየተሳነኝ ነው ምክንያቱ ደግሞ እሾህ በወጋው እግሬ ነው የቆምኩት በጤነኛው እንዳልቀይር ሰውዬው ኮሽታ እየጠበቀ ነው እርምጃውን ካቆመ በጣም ቆየ እግሬ መንቀጥቀጥ ጀመረ እንዳጋጣሚ አጠገቤ ዛፍ ነበርና እንዳልወድቅ በመዳፌ ተደገፍኩ እርምጃው ጀመረ ግን ቅድም ከነበረው ፍጥነት ጨምሯል ቦዲዬ በደም ተጨማልቋል የሽቶው ሽታ እንደጠፋ ይታወቀኛል ሰውዬውም ደሜ ሸቶት መሰለኝ በፍጥነት እየመጣ ነው እኔም እያነከስኩ ፍጥነቴን ጨምሬ መሸሽ ጀመርኩ በጣም እየቀረበኝ ከኔና ከሱ ሌላ ጫካ ውስጥ ኮቴ ተሰማ ይሄንን ኮቴ እንደሰማ ይመስለኛል እሱ ባለበት ቆሟል እኔ ግን ሽሽቴን ቀጥያለሁ ወዲያውኑ የሚጮህ የእንስሳ ድምፅ ሰማሁ ይመስለኛል ጥቃት ሲያደርስበት ነው የጮኸው በዚ ክፍተት መሀል እግሬ ላይ ያሰርኩትን ቦዲ ፈትቼ ከምጓዝበት በተቃራኒ መንገድ ወረወርኩት ከዛም ጉዞዬን ወደፊት አደረኩ ያለ ማቋረጥ ብዙ ተጓዝኩኝ ነገር ግን ኮቴው አልተከተለኝም ነበር የዛሬው ለሊት የሶስት ቀን ያህል ረዝሞብኛል የእግሬን ህመም መቋቋም አልቻልኩም ግን ቢሆንም ግን አልቆምኩኝም ነበር በዛው እሾህ በወጋኝ በኩል አንዳች ነገር እግሬ ውስጥ ተሰነቀረብኝ ድምፄንም አውጥቼ ጮውኩኝ ህመሙ ከቅድም እጅግ እጥፍ ነበር አልቻልኩም እግሬን ይዤ እየተንከባለልኩ ደጋግሜ ጮውኩኝ ጮውኩኝ አልቻልኩም ከእሾኩ የባሰ ስለት አለው ውስጥ ድረስ እየቆራረጠኝ ነው የገባው የቱም የህመም ስሜት አይገልፀውም ነፍሴ እግሬ ላይ ያለች ይመስል ትንፋሽ አጠረኝ መላ አካላቴ መብረክረክ ጀመረ የእግሬ እንቅጥቃጤ ቃል አይገልፀውም እየተንፏቀኩኝ ለመሄድ ግን አልቻልኩም ካንዱ ዛፍ ስር ተደገፍኩኝ ነፍሴ ዛለች የተወጋው እግሬን ወደራሴ ይዤ አንዱ እግሬ ጉልበት ላይ አኖርኩት የተሰነቀረብኝን ነገር ስነካው እጅግ በጣም ያማል ቀስ አድርጌ ወደነበረበት መለስኩ ጎህ እየቀደደ ነው እዚ ጫካ ውስጥ ፀሀይ ካልወጣች ወገግታ ብቻ ብርሃን አይሰጠውም ግን ፀሀይ ወጣች መሰለኝ ውስጡ መታየት ጀምሯል ሌላ አለም ያለው እስኪመስለኝ ድረስ ጨነቀኝ ዙሪያ ገባዬን ከግራ ከቀኝ ቃኘው ምንም አልነበረም ፀሀይ አብዝታ ባታፈካው እስከ ሆነ ርቀት ድረስ ያለውን ነገር የምለይበት ብርሃን አለ...ማንም እንደሌለ ባስተዋልኩ ጊዜ ራሴን ለማረጋጋት ወሰንኩ ከደቂቃዎች በሗላ ከተደገፍኩት ዛፍ ላይ ቅጠሎች መርገፍ ጀመሩ ቀና ስል ...........

_part #10 _ ይቀጥላል

ቶሎ እንዲለ
ቅ 👍 አሳዩኝ

ከተመቻቹ ÷
                 #𝐑𝐞𝐚𝐜𝐭
                 #𝐂𝐨𝐦𝐦𝐞𝐧𝐭
                 #𝐬𝐡𝐚𝐫𝐞 🙏

    ¶ 𝚈𝙴𝙵𝙸𝙺𝙴𝚁 𝙲𝙻𝙸𝙽𝙸𝙲🥀 ¶™🌐

  📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት! 📱

10.9k 0 40 30 106

ልብ አንጠልጣዩ "የጠፋው ሬሳ"

            
  ተከታታይ ትረካ

                 #ክፍል_፰

...ከጓ
ደኞቼ መሀል ማንም እንዳላየኝና እንዳልተከተለኝ አረጋግጬ እርምጃዬን ቀጠልኩ...እንደዚ አይነት ድፍረት ከየት እንዳመጣው ባላውቅም ደፋር ሆኛለሁ...ባትሪዬ የሚያሳየኝ አቅጣጫ እንጂ ሌላው በከባድ ፅልመት ተውጧል ፀጥ ያለ የሚለው ቃል እስከማይገልፀው ድረስ ፀጥ ብለሏል የደረቀውን ቅጠል ስረገጠውና ስተነፍስ ከሚሰማው ድምፅ በቀር አንዳች የለም...አሁን እየሄድኩበት ያለውን አቅጣጫ ፈፅሞ አላውቀውም ከገባንበት ፈፅሞ ተቃራኒ ነው እናም ስመለስ እንደምቸገር ለራሴ ታውቆኛል...በቀዝቃዛው ለሊት ብቻዬን ከድቅድቁ ጨለማ ጋር ግብግብ ገብቻለሁ...ከእርምጃዎች በሗላ ከኔ ሌላ በጫካው ውስጥ የእግር ኮቴ ተሰማኝ ባትሪውን አጥፍቼ ባለሁበት ቁጭ አልኩኝ ትኩረቴን ሰብስቤ የኮቴውን አቅጣጫ ለማወቅ ትኩረት ማድረግ ጀመርኩ...አረማመዱ ከሰው ይለያል የሚሰነዝረው እርምጃ ሰፋ ያለ ነው የሚረግጣቸው የረጋገፉ ቅጠሎች ይጨነቁ ይመስል ይጮሃሉ...አሁንም ከየት በኩል እየመጣ እደሆነ አለየሁትም...ቀስ ብዬ ባትሪውን መሬት ላይ እንዳስቀመጥኩ አቅጣጫውን ያለሁት እርምጃ ቀጥ አለ በጣም ደነገጥኩኝ እቺን ትንሽ ኮሽታ ሰምቶ እንዳይሆን ብዬ ራሴን ጠየኩት...ለደቂቃዎች ፀጥ አለ ጫካው እርምጃውም ቆሟል የሱን እንቅስቃሴ እንደምጠብቅ እሱም የኔን እንቄስቃሴ እየጠበቀ ይመስለኛል...አንድ ውሳኔ ለመወሰን ከራሴ ጋር ተስማማሁ እዚ ቁጭ ብሎ ጊዜ መፈጀቱ ዋጋ ቢስ እንደሆነና እርምጃዬን መቀጠል እንዳለብኝ...ከዛም ከተቀመጥኩበት ተነስቼ ባትሪው አብርቼ ዙሪያዬን ቃኘው አንዳች ነገር የለም ከዛም እርምጃዬን ፈጠን አድርጌ ወደፊት ቀጠልኩ ነገር ግን የሆነ ነገር አሁንም እርምጃዬን አስቆመኝ ከኔ ሌላ አሁንም የኮቴ ድምፅ ይሰማኛል ከቅድሙ የፈጠነ አረማመድ እየቀረበኝ መጣ አሁን አቅጣጫውን ለይቼዋለሁ ከፊት ለፊቴ ነው ወደኔ ሚገሰግሰው ባትሪው ከኔጋ ቢቆይ አቅጣጫ ጠቋሚ እንደሆነ እና የሚከታተለኝም ነገር ብርሃኑን አይቶ እንደሆነ ግልፅ ሆኖልኛል ከዛም ባትሪው ወደ ግራ አቅጣጫ ወርውሬ እኔ በሱ ተቃራኒ ከአንድ ዛፍ ስር ተደበኩኝ በሰከንዶች ልዩነት ሲከታተለኝ የነበረው ባትሪው ጋ ደረሰ ከፊት ለፊቱም ብርሃኑ ላይ ቆመ ረዘም ያለ ጥቁር ካፖርት ለብሷል ቁመቱ ለግላጋ ይመስላል ባትሪው ግማሽ አካሉ ላይ ስላረፈ ፊቱን ማየት አልቻልኩሜ ነበር...ይመስለኛል ከባትሪው ጀርባ የሆነ ሰው እንዳለ አስቧል ለዛም ነው መሰለኝ ከፊት ለፊት ለማስፈራራት በሚመስል አረማመድ ከግራ ወደ ቀኝ ይንጎራደዳል ከዛም ካፖርቱን ገለጥ አደረገና ረዘም ያለ የሚያንፀባርቅ ሰይፍ መሳይ ስለት አወጣ ይሄን ባየው ጊዜ በድንጋጤ ውስጥ ሆኜ "እ" አልኩኝ ወዲያውኑ አፌን በእጆቼ ያዝኩኝ እሱም አቅጣጫውን እኔ ወዳለሁበት አደረገ ቀስ እያለም እየተራመዳ መቅረብ ጀመረ ከዛፉ በስተሗላ እኔም ቀስ ብዬ ተነሳሁ እርምጃዬን ከሱ እርምጃ እኩል አድርጌ ወደ ሗላ መሸሽ ጀመርኩ በድንገት እግሬ ውስጥ እሾክ መሰለኝ ተሰነቀረብኝ ህመሙን ዋጥ አድርጌው ዝም አልኩኝና ማፈግፈጌን ቀጠልኩ የምራመደው ወደሗላ ነበርና የወጋኝም ተረከዜን ነው በለዘበ እርምጃ እየተጠጋኝ ነው እኔም እርምጃውን ጠብቄ እያፈገፈኩኝ ነው...ነገር እሾሁ ረጅም ነበርና በተራመድኩ ቁጥር ወደ ውስጥ ይገባብኝ ጀመር ትንሽ እንደተራመድኩ ተለቅ ያለ እንጨት ጋ እንደደረስኩ በእግሬ ንክኬ ለየሁ ፊቴን ወደ እንጨቱ አዙሬ ነካካሁት የወደቀ ዛፍ ነበር ቀስ ብዬ በላዩ ላይ አለፍኩና ከስሩ ተኛሁ እርምጃዬንም ድምፄንም አጠፋሁ ነገር ግን ህመሙን አልቻልኩትም ይከተለኝ የነበረው ነገር ድንገት ወደሗላ ተመለሰ ግን ለምን እንደሆነ አልገባኝም ከተኛሁበት ጥንቃቄ በተሞላው አነሳስ ቀና ብዬ መመልከት ጀመርኩ የሰውዬውን ማንነት ባለይም እንኳን...ትንሽ ከተጓዘ በሗላ ልክ እንደቅድሙ ባትሪው ፊት ለፊት መንጎራደድ ጀመረ...ህመሜ ግን ከብርዱ ጋር ተደምሮ ስቃዬን አበዛው በጫማዬ ውስጥ የገባውን እሾህ ለመንቀል ወሰንኩ አሁንም ቢሆን ግን አይኔን ከሰውዬው ላይ አልነቀልኩም...እዛ ቦታ ላይ ሚንጎራደደው ጠቋሚ ድምፅ እስኪሰማ ይመስለኛል የለበስኩትን ሹራብ አወለኩና እጁን ጠቅልዬ አፌ ውስጥ ከተትኩት ከዛም እሾሁን ለመንቀል ተዘጋጀሁ...በጣም ማለክለክ ጀመርኩ ትንፋሼ ቁርጥ ቁርጥ ማለት ጀመረ ጨከን አልኩና ትንሽ ጎተት አደረኩት እጅግ በጣም ያማል ቢሆንም ግን መውጣት ነበረበትና መጎተቴን ቀጠልኩ እስከ ግማሽ ድረስ አወጣሁትና ሹራቤን ከአፌ አውጥቼ ትንሽ ተነፍስኩ ልቤ ጥፍት ብላለች ወደ ሰውየው ተመለከትኩ አሁንም እዛው ይንጎራደዳል ሹራቤን መልሼ አፌ ውስጥ ከተትኩና መጎተቴን ተያያዝኩት ሙሉ ለሙሉም ነቀልኩት እንደነቀልኩትም ከተጋደመው ዛፍ ስር ራሴን ጥዬ ተኛሁ ሲውጣ የነበረው ህመም እጅግ ያማል ትንሽ ደቂቃ ተኛሁና ራሴን አረጋጋሁ ከዛ ቀና ብዬ ሳይ ....................

_Part #9 __ይቀጥላል

ቶሎ እን
ዲለቀቅ 👍 አሳዩኝ

ከተመቻቹ ÷
                 #𝐑𝐞𝐚𝐜𝐭
                 #𝐂𝐨𝐦𝐦𝐞𝐧𝐭
                 #𝐬𝐡𝐚𝐫𝐞 🙏

    ¶ 𝚈𝙴𝙵𝙸𝙺𝙴𝚁 𝙲𝙻𝙸𝙽𝙸𝙲🥀 ¶™🌐

  📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት! 📱


       

ልብ አንጠልጣዩ "የጠፋው
ሬሳ"
            
 
           
    ተከታታይ ትረካ

                
#ክፍል_፯

...ሜርሲ ድምፇን ከፍ አርጋ ጮ
ኸች ሁላንም ተደናገጥን ማን ሊወስደው ይችላል ከዛ ሰውዬ ውጪ አንድም ሰው እንደዚ አይነት ስራ አይሰራም...ቅድስቴ ድንኳኑ ጫፍ ላይ ቁጭ ብላ ትንሰቀሰቃለች ባርሰናይትም በፊናዋ ፊቷን ባባ ደረት ላይ አድርጋ ታለቅሳለች እኔ በድንጋጤ የማወራውም የማስተውለውም ነገር የለም ፍዝዝ ድንዝዝ ብያለው ነይ "ቅድስቴ ተነሺ" ብሎ ባባ ሊያነሳት ሲሞክር "ልቀቀኝ ብቻዬን መሆን እፈልጋለው" አለች ከፍ ባለና ቁጣ በተሞላው ድምፅ በዚ ጊዜ ባባ ወደሗላ ተመለሰ ቅድስቴ ደሞ ወደ ድንኳኑ ገብታ ደሙን በእጆቿ መንካት ጀመረች በዚህ ገዚ ከተያዝኩበት የድንጋጤ እና የድንዛዜ ስሜት ነቃሁኝ ወደ ቅድስቴም ድንኳን ገብቼ እጇን ያዝኳት ባባ ላይ እንደሆነችው ጮኸች "ልቀቂኝ ልቀቂኝ" አለች እየደጋገመች እኔ ግን እንደ ባባ አልተውኳትም መመነጫጨቋንና ቁጣዋን ችዬ እቅፍ አድርጌ ወደራሴ አስጠጋሗት "ተረጋጊ ተረጋጊ የኔ ውድ አይዞሽ" እያልኩኝ ለማረጋጋት ሙከራ ጀመርኩ ግን አሁንም መወራጨቷንና እየጮኸች ማውራቷን አላቆመችም ለሩብ ደቂቃዎች ያህል ያለ ማቋረጥ ቀጠለች እኔም ድምፇ የቱንም ያህል ቢከብደኝም እንዳቀፍኳት አለሁ...ድካም ተሰማት መሰለኝ ድምፇ እየተስለመለመ መጣ ረጋ ባለ ድምፅ "እኔን ለማ ጥለኸኝ ነው ምትሄደው ምነው ብትነግረኝ ልሄድ ነው ብትለኝ እኔ አልሰማም ብዬሃለሁ ጨካኝ ነህ" እያለች ከራሷጋ ሰጣ ገባ ውስጥ ገባች...በዚ ሁኔታ ውስጥ ብዙም ሳትቆይ እንቅልፍ አሸለባት ወደ ድንኳኑ መውጫ ስመለከት ባባ እና ባርሳ በሚያቆረፍደው፡የለሊት ብርድ ውስጥ ቆመዋል...ባባ ወደኔ እንዲመጣ ምልክት ሰጠሁት ከዛም ጥንቃቄ በተሞላበት አያያዝ ለሁለት ተሸክመን ከድንኳኑ አወጣናትና እኔ ድንኳን ውስጥ አስተኛናት..."እሷ ትተኛ እኛ ደሞ ሮቤልን እንፈልገው" ሲል ባባ ባርሳ ሰምታ ኖሮ "ምንድነው ምታወራው ከእንግዲህ ተጣጥለን መንቀሳቀስ የለብንም የማይሆን ሀሳብ ነው" አለችው "ባርሳዬ እሱን ለመፈለግ ምንም አለማረጋችንን ስታውቅ ታዝንብናለች ብዬ እኮ ነው ስለሱ ምንም ግድ እንደሌለን ነው ምታስበው ከደረሰባት ነገር ጋ ተያይዞ የባሰ ትጎዳለች ከጓኗ እንዳለን እንድታውቅ ይህን ማድረግ አለብን" አለ ባባ ሊያሳምን የሚችል ምክንያት በማቅረብ "ምንም ሊሆን ይችላል እኔ አንተ በምትለው ነገር ፈፅሞ አልስማማም ራሳችንን አደጋ ውስጥ በመክተት ነው እንዴ ከሷጋ እንደሆንን ምናሳየው በዚ ሁኔታ ውስጥ ድጋሜ አንዳችን ብንጠፋስ?" በማለት ባርሰናይት የባባን ሀሳብ ተቃረነች "እንዴ ምንድነው ምትጨቃጨቁት ተረጋጉ እንጂ ለጊዜው ራሳችንን እናረጋጋ ግን ሮቤልን መፈለጋችን አይቀርም ለቤተሰቡስ ምን ብለን ነው ምንናገረው" እያልኩ እየተናገርኩ ሳለ ባርሳ ጣልቃ ገብታ "አንቺም ሜርሴ እንደዚ ትያለሽ ያለንበት ስፍራ እጅግ አስፈሪ ስፍራ ነው እኛም ማደራችንን እንጃ ጭራሽ ደግሞ ፍለጋ እንሂድ ትያለሽ" ብላ ጥያቄዋን አስከተለች "እንደሱ ማለቴ አይደለም ግን ቢያንስ ስለሱ የሆነ ነገር ማወቅ አለብን ተማለት ነው" ብዬ ሃሳቤን በእርጋታ አስረዳሗት ግን ባርሳ አሻፈረኝ "የማይደረገውን አጠይቁኝ" ብላ በእንቢተኝነቷ ቀጠለች "እሺ አሁን እንተኛ ማልዶ ሲነጋ ሁሉንም እናወራለን  " አለ ባባ በሀሳቡ ተስማምታ ባርሳ ወዲያውኑ ወደ ድንኳናቸው ገባች "ደና እደሪ" ብሎ ባባም ተከተላት እኔ ደግሞ ቁጭ ብዬ የቅድስቴን አይን አይኗን ማየት ጀመርኩ...ከጥቂት ደቂቃዎች በሗላ መወረጫጨት ጀመረች በጣቶቿ አንሶላውን ወዲያ ወዲህ እየጎተተች...ሊሞት እንደሚያጣጥር ሰው አደረጋት በጣም ተደናግጬ ተጠጋሗትና መወራጨቷን እንድታቆም አጥብቄ ያዝኳት ወዲያውኑ ከፍ ባለና ቁጣ በተሞላበት ድምፅ "ልቀቀኝ" ብላ ተነስታ ወደ ድንኳኑ ግድግዳ ተጠግታ ቁጭ አለች አይኖቿ መገለጣቸውን ሳይ ላረጋጋት ስጠጋት "እንዳትጠጋኝ ልገለኝ ነው" አለች በጣም ደነገጥኩኝ ቅድስቴ ችግር ውስጥ እየገባች ነው የሷን ጩኸት ሰምተው ይመስለኛል ባባ እና ባርሰናይት ከውጪ ቆመው "ምንድነው" አሉ ድንጋጤ በተሞላበት ድምፅ ከዛም ቀጠል አርጎ "ክፈቺው ሜርሲ" አለኝ ባባ ውስጥ ያለውን ነገር ለመመልከት እኔም ከፈትኩላቸው አንገታቸውን ወደ ውስጥ እያሰገጉ ምን እንደተፈጠረ እንድነግራቸው ጠየቁኝ "ቅዠት ነው መሰለኝ አላውቅም ድንገት ነው የጮኸችው" ብዬ መለስኩላቸው...ቅድስቴ በጣም እያለቀለከች ነበር በዚ ቢሚጋራፍ ውርጭ ሰዓት እሷ ግን ላበላብ ሆናለች "ቅድስቴ" አላት ባባ በተንጨበረረው ፀጉሯ መሀል አይኗን ወደሱ አንስታ ተመለከተችው ግን ምንም አይነት ምላሽ አልሰጠችውም ጉልበቷን ወደ ደረቷ ስባ እጆቿን ጉልበቷ ላይ አስደግፋ አገጯን እጇ ላይ አድርጋ ወደፊት ወደሗላ እያለች ትወዛወዛለች ግን አንዲትም ቃል አተነፍስም ውስጧ በጣም መረበሹን እና ድንጋጤው እንዳልተዋት ተረዳሁ "ቅድስት አይዞሽ ተረጋጊ እኛ አለንልሽ" አለቻት ባርሰናይት እሷንም በአይኗ ከመመልከት ውጪ አንዳች መልስ አልሰጠቻትም ነበር...በጥቂቱም ቢሆን አሁን አተነፋፈሷ እየተስተካከለ ነው ከገባችበት ድንጋጤ እየተላቀቀች ነው "ድንጋጤው ነው እንደዚ ሚያረጋት በቃ ግቡና ተኙ እኔ አለሁ" አልኳቸው ለነ ባባ ሁሉም ነገር ሰላም እንደሆነ እየነገርኳቸው "እሺ ችግር ካለ አሳውቂን" አለ ባባ "ጓደኛዬ አለንልሽ" አለች ባርሳ ወደ ቅድስቴ እየተመለከተች...የተፈጠረባት ነገር የሰላም እንቅልፍ እንደማይሰጣት የታወቀ ነው እናም ተረጋግታ እንድትተኛ የእንቅልፍ መድሃኒት ሰጠሗት ደረቴ ላይም አስጠግቼ "አይዞሽ አይዞሽ" እያልኩ ፀጉሯን እያሻሸው አስተኛሗት ከላዬ ላይ አውርጄ ወደ ፍራሹ ካደረኳት በሗላ ብርድ ልብስ አለበስኳት ከዛም ሻንጣዬን ከፍቼ ወፍራም ጃኬት አውጥቼ ለበስኩ ከድንኳኑ ወጣሁና ቅድስቴ ላይ ዘጋሁባት በያዝኩት ባትሪ ድንኳናችን አካባቢ ያለውን ነገር ቃኘሁት እነ ባርሳ ድንኳን አጠገብ አጠር ያለ ትንሽ ውፍረት ያለው እንጨት ተመለከትኩ ሄጄም አነሳሁት ከዛ ማንም ሳይሰማ ሮቤልን ፍለጋ ወደ ጨለማው ጫካ ውስጥ ገባሁ............

_Part #8 ___ይቀጥላል

ቶሎ እንዲለ
ቀቅ 👍 አሳዩኝ

ከተመቻቹ ÷
                 #𝐑𝐞𝐚𝐜𝐭
                 #𝐂𝐨𝐦𝐦𝐞𝐧𝐭
                 #𝐬𝐡𝐚𝐫𝐞 🙏

    ¶ 𝚈𝙴𝙵𝙸𝙺𝙴𝚁 𝙲𝙻𝙸𝙽𝙸𝙲🥀 ¶™🌐

  📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት! 📱


  ልብ አንጠልጣዩ "የጠፋው ሬሳ"

               ተከታታይ ትረካ

                 
#ክፍል_፮

.......ሙሉ በሙሉ ከእግር እስከ ራሱ ጥቁር በጥቁር ለብ
ሶ ጀርቦውን ለኔ ሰጥቶ አንድ ሰው ቆሞ አየው የምሆነው የማረገው ጠፋኝ ተርበተበትኩ መጮህ እየፈለኩ አልቻልኩም መሮጥ እየፈለኩ እግሬ ከዳኝ ብቻ ባትሪውን እሱ ላይ አነጣጥሬ ዝም ብዬ ቆምኩኝ ላቤ እንደ ጉድር ይወርዳል ሰውነቴ ግሏል አተነፋፈሴ ተቀይሯል እንደውም መተንፈስ እየተሳነኝ ነው ከፊት ለፊቴ የቆመው ሰው አንገቱን ወደኔ ማዞር ጀመረ በዚህ ጊዜ እግሮቼ ወደሗላ ማፈግፈግ ጀመሩ ድንገት ከበስተሗላዬ የሳቅ ድምፅ ሰማው በድንጋጤ ከመቅፅበት ዞርኩኝ ግን ማንም አልነበረም ፊቴን ወዲያውኑ ወደ ቅድሙ ሰው መለስኩ ግን እሱም አልነበረም...አሁን ይሄንን ነው መፍራት ያየሗቸው እና የሰማሗቸው ከአይኔ ይሸሻሉ...ጥንቃቄ በተሞላው አረማመድ ሀሳቤን ቀይሬ ወደ ድንኳኑ ማዝገም ጀመርኩ ዞሪያዬን እየቃኘው መጓዜን ቀጠልኩ እኔ ከማበረው ባትሪ ውጪ ጫካው በድቅድቅ ጨለማ ተውጧል እርምጃዬ ከመቆም አይተናነስም በጣም ዝግ ያለ ነው...ውስጤ በጣም እየፈራ ነው እዚ ድቅድቅ ጨለማ ውስጥ ብቻዬን መጓዜ ለራሴም እየደነቀኝ ነው የሚያግዘኝ አንዳች ልዩ ሀይል እንዳለ ይሰማኛል...ከራሴ ጋር እያወራሁ ጉዞዬን እየቀጠልኩኝ ሳለ ከበስተሗላዬ መሬት ላይ የሚንፏቀቅ የብረት ድምፅ ተሰማኝ ወዲያውኑ ዞርኩኝ ግን ምንም አልነበረም...የሚከተለኝ ነገር እንዳለ ጀርባዬ ይነግረኛል ጥላውም አካሌ ላይ ይከብደኛል ግን ከአይኔ ከመቅፅበት ይሰወራል ይህ ነገር ከመንፈስ ጋር ጥብቅ ትስስር እንዳለው ይሰማኛል ከጨለማው ጋ ተዋዶ ነፍስን የሚያስጨንቅ ክፉ መንፈስ ነው...ይሄን ሀሳብ በውስጤ እያመላለስኩ ሳለ በድንገት ከጨገገው ሰማይ ላይ ፍክት ያለች ጨረቃ ወጣች ሰዓቱ ወደ እኩለ ለሊት እየተጓዘ ነው የተከሰተው ነገር እጅግ አስደነቀኝ ወዲያው የሰይጣን መልዕክተኛ የሚባለው የወፍ ዘር(ቁራ) ከየት መጣ ሳይባል አጠገቤ ካለ ዛፍ ላይ ቆሞ በእኩለ ለሊት መጮህ ጀመረ ድምፁ እስከዛሬ ከሰማዋቸው ድምፆች ከበደኝ መሬት ላይ ወደኩ ጆሮዬንም በእጆቼ ያዤ እዛው መሬት ላይ ቀረሁ ግን የቱንም ያህል ጆሮዬን ብይዘውም ድምፁን ማቆም አልቻልኩም ከመጠን አልፎ አወከኝ ልቤን አደከመው አንዳች ሀይል ከሱ ጋር እንዳለ ያስታውቃል ከድምፁ መሀል ብዙ የጣር ድምፆች ይሰማሉ "ወይኔ...ኡኡኡ" የሚሉ አይነት ድምፆች አልፎ አልፎም ሳቅ ይቀላቀልበታል እዛው በተኛሁበት ለደቂቃዎች ቆየሁኝ የቁራው ድምፅ የለም ቁራውም ከዛፉ ላይ አይታይም ጨረቃዋል ጠልቃለች ጫካው ወደ ቀድሙ ድቅድቅ ጨለማነቱ ተመልሷል የማየውን ነገር ማመን አቅቶኛል ከተኛሁበት በእርጋታ ተነሳሁኝ...ቁራው ሲጮህ ደንግጬ ስወድቅ ባትሪውን ጥዬው ነበር እሱንም ለመፈለግ በእጆቼ መዳበስ ጀመርኩ ላገኘው አልቻልኩም በጉልበቴ እየዳሁ መፈለጌን ቀጠልኩ ከትንሽ ፍለጋ በሗላ በሁለቱም እጄ የሚያዝ ነገር አገኘሁ በግራ እጄ ባትሪውን እንዳገኘሁት ተረድቻለሁ ግን ቀኝ እጄ ላይ ያለውን ማስተዋል አልቻልኩም...ባትሪውን አብርቼ ስመለከተው ሰዓት ያለበት የሰው እጅ ነበር በድንጋጤ እሪታዬን አቀለጥኩት ወዲያውኑ እነ ባርሰናይት ስሜን እየተጣሩ በመደናገጥ ስሜት ውስጥ ሆነው ወደኔ መጡ "ሜርሲ ሜርሲ" እያሉ ደጋግመው ይጣራሉ አንደበቴ ተሳስሯል ምላሽ መስጣት አልቻልኩም ብቻ ያለሁበትን እንዲያውቁ ባትሪውን ከፍ አድርጌ አበራሁት ሁሉም ወደኔ መጡ "ምን ሆንሽ ሜርሲዬ" ብላ ቅድስቴ ተንበርክካ እቅፍ አረገችኝ ምንም ምላሽ አልሰጠሗትም ብቻ የማልቆጣጠረው እንባ ከአይኔ ይወርዳል ባባም ግራ ቀኙን ከቃኘ በሗላ "የሆንሽውን ተረጋግተሽ ንገሪን ሜርሲ" አለኝ ለሱም ምላሽ አልሰጠሁትም ዝም ነበር ያልኩት እንደሚመስለኝ የቅድሙ የቁራ ጩኸት እና የጨረቃዋ ወገግታ ለኔ ብቻ ነው የታየኝ ግን የ፡እጁ ለሁሉም ይታያል ብዬ አሰብኩ ወዳስጮኸኝ ነገር ባትሪዬ አበራሁላቸው ሁሉም ተደናገጡ "ተነሺ ከዚ አካባቢ እንራቅ" አለ ባባ በእጆቹ እኔን ለማንሳት እየሞከረ...እንደምንም ብዬ ተነሳሁና ወደ ድንኳናችን አመራን እነ ባርሳ በጣም ፈርተዋል ባባ በያዘው ባትሪ ዙሪያውን እየቃኘ ደህንነታችንን እየጠበቀ ነው ዱንኳናችን ጋ እንደደረስን መተኛት እንደምፈልግ ነግሬያቸው ወደ ድንኳኔ አስገቡኝ ጭንቀቴንና የተፈጠሩትን ነገሮች ለመርሳት እንቅልፍ የተሻለ ነውና ጋደም አልኩኝ ከደቂቃዎች በሗላ ቅድስቴ ጮኸች ከተኛሁበት ተስፈንጥሬ ተነሳሁና ወደሷ አመራሁ ባባ እና ባርሰናይትም አብረዋት ነበሩ "ምንድነው ቅድስቴ" ብዬ ወደሷ ተጠጋሁ "አንቺጋ ስንመጣ ሮቤል ተኝቶ ነበር አሁን ፍራሹ ላይ ያለው ደሙ ብቻ ነው".........

........P.7....ይቀጥላል.........

ቶሎ ቶሎ እንድለቅ 👍አሳዩኝ

  
ከተመቻቹ ÷
                 #𝐑𝐞𝐚𝐜𝐭
   
              #𝐂𝐨𝐦𝐦𝐞𝐧𝐭
                 #𝐬𝐡𝐚𝐫𝐞 🙏

    ¶ 𝚈𝙴𝙵𝙸𝙺𝙴𝚁 𝙲𝙻𝙸𝙽𝙸𝙲🥀 ¶™🌐

  📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት! 📱

12.5k 0 57 90 123
20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.