ልብ አንጠልጣዩ "የጠፋው ሬሳ"
ተከታታይ ትረካ
#ክፍል_፲፫
...ሁኔታዋ ግራ ስላጋባኝ "ይመስለኛል ይሄ ታካሚ ድንገተኛ አደጋ ደርሶበት ነው የመጣው" አለች "በምን ልታውቂ ቻልሽ ብዬ" ጥያቄዬን ቀጠል አድርጌ እየጠየቋት "የህክምና ካርዱ ላይ የታካሚው ስም የለበትም የመድሃኒት መዘዢያውም ላይ እንዲሁ" ብላ መለሰችልኝ "ቀንስ አልተፃፈበትም" አልኳት በውስጤ የማስበው አንዳች ነገር ስለነበር ክፍሉ ወውስጥ ወዳለው ወደ አንዱ ጠረጴዛ እያመራች የመድሀኒት ማዘዣ ወረቀቱን እየተመለከተች "ቀኑ ትላንት ነው ወደዚ ስፍራ የመጣው ሰዓቱ ግን የለም" ብላ መለሰችልኝ የራጅ ወረቀት ከጠረጴዛው ላይ አንስታ ከፍ አርጋ እየተመለከተች "ግን ታማሚው አብዛኛው የሰውነት ክፍሉ ያን ያህል አልተጎዳም ግን የሗላ የጭንቅላት ክፍሉ ላይ የአጥንት መሰንጠቅ ይታያል ከሆነ ነገር ጋር እንደተጋጨ ወይም በሆነ ነገር እንደተመታ ገምታለው" ብላ ስለ ራጅ ምሰስሉ አብራራችልኝ የጭንቅላት የሗላ ክፍሉ ስትል ጫካ ውስጥ የተመለከትኩት የቅድስት ጓደኛ የአወዳደቅ ሁኔታ ውስጤ ብልጭ አለብኝ እሱ ሊሆን እንደሚችልም አሰብኩ "ግን እዚ ማን ሊያመጣው ይችላል" ብዬም እራሴን ጠየኩ ሳላስበው ድምፄን ከፍ አድርጌ ነበርና "ምን አለሽኝ" አለችኝ ቅድስቴ "አይ ምንም እንዲሁ ከራሴጋ እያወራሁ ነው ብዬ መለስኩላት ከደቂቃዎች በሗላ እነ ባርሳ መጡ "ምነው ቆያቹ" አለች ቅድስቴ ባባም ቀበል አርጎ "ቶሎ ማግኘት አልቻልንም ለዛ ነው አሁን ሜርሲ እንዴት ነሽ" አለኝ "ደህና ነኝ አሁን ምንም አልልም" በማለት እንዳይጨነቁ ደህና ነኝ አልኩኝ እንጂ ክፉኛ እያመመኝ ነው ቅድስቴ መድሃኒቶችን መዘጋጀት ጀምራለች ግን በመጠራጠር ስሜት ሆና ደግማ ቁስሌን ተመለከተችው "ራጅ ብትታዪ መልካም ነው ሜርሲዬ" አለችኝ "እንዴ ለምን" ብዬ በጥያቄ መለስኩላት "የአናትሽ በስጋ የሸፈነው ክፍል ክፉኛ በወጋሽ ነገር ተቀዷል በዚህ ሁኔታ አጥንትሽም ሊነካ ይችላል" ብላ መለሰችልኝ ባለችው ነገርም ተስማማሁ የተኛሁበትንም አልጋ እየገፉ ወደ ክፍሉ ማምራት ጀመርን በሩ ላይ የተፃፉትን እያነበብን ነበር ፍለጋችን ከተወሰኑ ክፍሎች በሗላ አገኘነው ወደ ውስጥም ዘልቀን ገባን ግን ምንም አልነበረም ባዶ ክፍል ነበር ባየነው ነገር ሁላችንም ግራ ተጋባን "ይህ እንዴት ሊሆን ቻለ" አለ ባባ "አዲስ ሆስፒታል ነው እንዴ?" አለች ባርሳ ከባባ ቀበል አርጋ "በቅርብ ቀን የተሰራ የራጅ ውጤት እኮ አሁን ተመልክቻለሁ ግን እንዴት ላይኖር ቻለ" አለች ቅድስቴ ግራ በመጋባት ስሜት ሆና "ቁስሉ ንፋስ ስለሚገባበት በቃ መሰፋት አለበት" አለች ቀጠል አርጋ ከዛ ክፍል ወጥተን መጀመሪያ ወደነበርንበት ክፍል ማምራት ጀመርን ሆስፒታሉ ሲበዛ ነጭ ነው ፍሎረሰንት በሚባለው የአንፖል አይነት እጅግ ደምቋል እይታው ራሱ ትንሽ ህመምን ያቀላል ፈፅሞ ሰላም ይሰጣል ወደነበርንበት ክፍል ዘልቀን ገባን የህክምና ጓንቷን አድርጋ በደረቴ ከነ ባርሳ ጋ ሆነው አስተኙኝ ከዛም ህክምናውን ጥንቃቄ በተሞላው መልኩ ፈፀመችው ከዛም አገችው "አሁን ከኢንፌክሽን ነፃ ነሽ" አለችኝ "በቃ እሺ ከዚ አካባቢ በፍጥነት እንውጣ" አለ ባባ አዎ ብለው እነ ቅድስቴ በሀሳቡ ተስማምተው እኔን ደግፈው አነሱኝ እራሴን ችዬ መሄድ እንደምችል ነገርኳቸው እና የተኛሁበት አልጋ ላይ ቁጭ አልኩኝ እነሱ እዛው ባለሁበት ሆኜ ወደ መኪናው ሄዱ ከአልጋው ተነስቼ እየተራመድኩ ወደ መስኮቱ አመራሁ መጋረጃውን ገለጥኩት መስታወቱ ተሰብሮና በደም ተጨማልቆ ነበር ሲመስለኝ የሆነ ሰው ለማምለጥ በዚ በኩል ወድቋል በተሰበረው መስታወት ውስጥ አንገቴን ወደ ውጪ አውጥቼ ስመለከት ሳሩ በደም ተለውሷል የሆነ ሰው እየተንፏቀቀ እንደሄደበት አይነት ምልክት አለው አንገቴን ወደ ውስጥ መልሼ መስኮቱን በመክፈቻው ከፍቼ ቀስ ብዬ ወጣሁ የደሙንም ምልክት እየተመለከትኩ ወደፊት አመራሁ ማን እንደሆን እንጃ ብቻ ክፉኛ የተጎዳ ሰው ነው ከሆነ እርምጃ በሗላ ደሙ ላይ ተለቅ ያለ የጫማ ምልክት ተመለከትኩ እዛው ባለሁቡት ቆምኩኝና አይኔን አሻግሬ ወደፊት ሰደድኩት ከአንድ ስፍራ ላይ ሲንፏቀቅ ይፈስ ከነበረው ደም ይልቅ ብዙ ደም ፈሿል ሳሩም የተረጋገጠ ይመስላል ከዛ ከተጎዳው ሰው ሌላ ሌላም ሰው ነበር ... መሬት ራሱን እያንፏቀቀ ይሄድ የነበረው ሰው በድንገት ጠፋ እርምጃዬን ቀጠል አደረኩኝ አንዳች ምልክት አልነበረም ግን ከትንሽ እርምጃ በሗላ የተንጠባጠበ የደም ጠብታ ተመለከትኩ እሱን ተከትዬ መሄድ ጀመርኩ ዞር ብዬ ስመለከት ከሆስፒታሉ እየራኩኝ ነው ግን ለመመለስ አልፈለኩም እርምጃዬን ቀጠልኩ የደሙን ጠብታ ተከትዬ ስጓዝ ከአንድ ጫካ አጠገብ ደረስኩ አሁን እርምጃዬን ገታሁት ነገር ግን የደም ጠብታው እንደ ቀጠለ ነው ከጫካው መግቢያ ላይ አንድ ነጭ ነገር ተመለከትኩ ወደ ውስጥ ብዙም ያልገባ ስለነበር ለመመልከት ተጠጋሁ የቅድስቴ ጓደኛ ጫማ ነበር............
_part #14 ___ ይቀጥላል
ቶሎ እንዲለቀቅ 👍 አሳዩኝ
ከተመቻቹ ÷
#𝐑𝐞𝐚𝐜𝐭
#𝐂𝐨𝐦𝐦𝐞𝐧𝐭
#𝐬𝐡𝐚𝐫𝐞 🙏
¶ 𝚈𝙴𝙵𝙸𝙺𝙴𝚁 𝙲𝙻𝙸𝙽𝙸𝙲🥀 ¶™🌐
📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት! 📱