የፍቅር ቴሌግራም ❤️‍🔥™


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha


𝐖𝐞𝐥𝐜𝐨𝐦𝐞 t̑̈ȏ̈ የፍቅር ቴሌግራም™ ❤
💙በዚ 𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥 ላይ
💜ድርሰቶች
💚የፍቅር ግጥሞች
💛ጣፋጭ ታሪኮች
❤️ምክሮች ...
አልፎ አልፎ ቀልዶች ይለቀቁበታል 😂

Since 2016 e.c
❤️ከናተ ሚጠበቀው 𝐉𝐨𝐢𝐧 to request በማረግ ብቻ መከታተል ነው ❤️
👇👇👇

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Statistika
Postlar filtri


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
ከ15 ደቂቃ ቦኃላ ይጠፋል


የ 200 ብር ካርድ የሚያስሸልም ጥያቄ!

ማየት ,መዳበስ እና መንካት የምንችለው የኮምፒውተር ክፍል የቱ ነው






Wallpaper ወይስ Profile ይፈልጋሉ? 😍


      🔸🔸🔺🔺🔹🔸

      
❤️ የፍቅር ጥግ ❤️

ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ  ታሪክ
❤️

ፀሀፊ
✍️ ማኔ


                        ክፍል  
2️⃣8️⃣


ኤጭ ደሞ ጀመረሽ ልታለቃቅሺ ነው ቻው በቃ እኔ ልመለስ ነው ብያት ዞር ስል እዮብ ከኋላችን የለም ደንግጠን ደጋግመን ደወልን አንስቶ ድንገተኛ ስልክ ተደውሎለት እንደተመለሰና ቤት አድርሻት እንድመለስ ነገረኝ ፡፡አማራጭ ስለሌለኝ ሸኘኋት ልክ ወደሰፈር ለመድረስ የተወሰነ ሲቀረን እኔ ልመለስ እንደሆነ ነግሪያት ፊቴን አዙሬ ልሄድ ስል አንድ ነገር ላስችግርህ እዚህ ድረስ መተህ እቴቴን ሳታያት ልትሄድ ነው አለችኝ፡፡
ኪሴ ያለችውን ፎቶ አውጥቼ አሳየኋትና መቼ ሳላያት ውዬ ነው ሳታያት ምትይኝ ብዬ ተናደድኩባት።

አረ አደለም ይሄኔኮ ፎቶዎቿ እራሱ አንተን ለማየት ናፍቀው ይሆናል የእናትህ ቀልብኮ አሁንም ቤት ውስጥ አለ ለምን ቤት ገብተህ አቴድም ይሄ ቤትኮ ስንት ነገራችሁን ያሳለፋችሁበት ቤት ነው በዛ ላይ እቴቴ ይሄን ላለማጣት ነው ህይወቷን ያጣችው ቢያንስ ዛሬ እንኳን እዚህ እደር እያለችኝ እዮብ ስልክ ደውሎ ዛሬ ቤት እንደማይመጣና ሌላ ቦታ እንደሚያድር ነገረኝ እያወራን የነበረው በሷ ስልክ ነው ነገሩ ባይዋጥልኝም እሺ አልኳት ቦርሳዋ ውስጥ የያዘችውን የቤት ቁልፍ አውጥታ እንካ ይሄ የቤቱ ቁልፍ ነው ቤት ገብተህ ጠብቀኝ እኔ ቤት እንዳይቆጡኝ ገብቼ ተደብቄ እመጣለሁ ብላኝ ሄደች፡፡በሩ ላይ ቆሜ ልግባ አልግባ ብዬ የተወሰነ አመነታሁና ዝም ብዬ ወደውስጥ ገባሁ፡፡

ገና ግቢ ውስጥ ስገባ ደረጃው ላይ ቆማ መጣህልኝ የኔ ልጅ በቃ ወተህ እስክትገባ ንፍቅ ትለኛለህኮ ና እስቲ ሳመኝ ምትለኝ ነገር ትዝ አለኝ ጭንቅላቴ ጭጭጭጭጭ የሚል ድምፅ እያወጣ አጨናነቀኝ ወዲያው ኪሴ ውስጥ ያለውን ሲጋራ አውጥቼ ምንም ትንፋሽ ሳልወስድ ሳብ አደረኩት ለውጥ የለውም ደግሜ ለኮስኩ እሱንም ጣልኩት ዝም ብዬ ግቢ ውስጥ መንጎራደድ ጀመርኩ ቤቱን ከፍቼ ወደውስጥ ስገባ ሚያንቀኝ ነገር ያለ ይመስል ጭፍግግ አለኝ።

ሶስተኛውን ሲጋራ ለኩሼ እየሳብኩ ልእልት በሩን ያለማቋረጥ አንኳኳች ከፈትኩላት ወይኔ የሆነ ሰው አየኝ ብዬ ልቤ ባፌ ልትወጣ ነበር እስካሁን ቤት አልገባህም እንዴ አለችኝ ዝም አልኳት።ቁልፉን ተቀብላኝ ወደውስጥ ገባችና መብራቱን አበራችው ወዲያው መልሳ አጠፋችው ምን ሆነሻል አልኳት ጎረቤት አይቶ አንተን ለማናገር እንዳይመጡና እንዳያጨናንቁህ ብዬኮ ነው አለችኝ፡፡

እሺ ብዬ ወደመኝታ ቤት ገባሁና መብራቱን አበራሁት የእናቴን ፎቶ ከፊት ለፊቴ ስመለከት ምናለ አምላኬ ሆይ ላንተ ምን ይሳንሀል አሁን ፎቶዋን ድንገት ወደ እውነተኛዋ እናቴ ቀይረህ ላንዴ ባቅፋት ምናለ ብዬ ፀልይኩ፡፡ የእናቴ ፎቶ ትኩር ብሎ እያየኝ በጣም ነው ያፈርኩብህ እንዴት እንደዚህ እራስህን ትጥላለህ እንዴት እንደዚህ አይነት ህይወት ትመርጣለህ ብሎ እየወቀሰኝ እንዳለ ተሰማኝ ለመሸሽ በሚመስል መልኩ ከክፍሉ ለቅቄ ወጣሁ የእናቴ መኝታ ክፍል ስገባ ልእልት ድምጿን አፍና እያለቀሰች ነበር መብራቱን አበራሁትና አየኋት አይኗ ቀልቷል ከተቀመጠችበት ሆና እጇን ወደኋላ ደበቀችው ምን ሆነሻል አልኳት።

ምንም እቴቴ ትዝ ብላኝ ነው አለችኝ፡
አትዋሽ ምን ሆነሻል እጅሽን አሞሻል እንዴ አልኳት ዝም አለችኝ።እራሴ ሄጄ ከተቀመጠችበት አንስቼ እጇን አየሁት ፡፡ እጇ በሀይለኛው እየደማ ነው ።
ምን ሆነሽ ነው ምን ሆነሽ ነው ደጋግሜ ጠየኳት። መኝታ ክፍሌ ገብቼ የተኛሁ እንዲመስላቸው በመስኮት ነው ዘልዬ የወጣሁት መብራት አጥፍቼ ስለነበር ሰላስበው እጄን ባጭሮኝ ነው አለችኝ።

ይሄኮ ባጨረኝ ሳይሆን ቀደደኝ ነው ሚባለው እያየሸ ነው እንዴት እንደሚደማ እእ እጅሽኮ ተቀዷል አልኳት፡፡ተወው ችግር የለም ትንሽኮ ነው ያመመኝ አለች፡፡አናደደችኝ ወዲያው ተቀየርኩባት ዝም ብዬ መጮህጀመርኩ።

ቆይ አንቺ አይገባሽም ቆይ ለምንድነው ይሄን ሁሉ መስዋትነት ለኔ ምትከፍይው እስኪ ተመልከቺኝ የሰውነቴ ጠረን ያስጠላልኮ እስኪ ተጠጊኝ ለስንት ደቂቃ ነው ካጠገቤ መቆም ምትችይው ምን ያህል ሰአት ነዎ መጥፎ ጠረንን መቋቋም ምትችይው እስኪ ተመልከቺኝ ፀጉሬ ላይ ያለውን ቆሻሻ የጊንጮቼ አጥንት ፈጠውኮ የ77 ድርቅ የመታው ሰውዬ መስያለሁ ለምንድነው አሁንም ምትከተይኝ አልኳት፡፡

እኔኮ ያፈቀርኩህ ስላንተ ፀባይ ምንም ሳላቅ መልክህን እንኳን በቅጡ ሳለየው እንዲሁ ባጠገቤ ስላለፍክ ብቻኮ ነው ስላንተ ማሰብ የጀመርኩት እእ አንተን መልክህን ፀባይህን ወይ ደሞ ጥሩ መአዛህን አይቼ አደለም የወደድኩህ በቃ ምንም ሁን ምንም ለኔ አንድ ባህራን ነህ አለችኝ።

ንግግሯን ከምንም ሳልቆጥር አቦ አታስመስይ ፊልም አደለም ይሄ ህይወት ነው አልኳት፡፡
ገፍትራኝ ከቤት ወጣች እኔ አልተከተልኳትም እዛው የእናቴ አልጋ ላይ ተንጋልዬ ጣራ ጣራውን እያየሁ ንግግሯ ጆሮዬ ላይ ያቃጭልብኝ ጀመር....


ይቀጥላል...



🔻ክፍል2️⃣9️⃣1️⃣5️⃣0️⃣ like በዃላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!
😀

💔 https://t.me/yefikirtelegramet 💔


ቤተሰብ እንዴት ሰነበታችሁ ሰሞኑን ስላልተመቸን የፍቅር ጥግን ባለመልቀቃችን ይቅርታ እየጠየቅን ክፍል 28 ዛሬ ይለቀቃል

ሰዓቱ እስኪደርስ start እሚለውን ሁላችሁም start አድርጉት


START
START


በአለም ረጅሙ የማዕረግ ስም

"His Excellency President for Life, Field Marshal Al Hadji Doctor Idi Amin Dada, VC, DSO, MC, Lord of All the Beasts of the Earth and Fishes of the Sea, Conqueror of the British Empire in Africa in General and Uganda in Particular."

" የተከበሩ የእድሜ ልክ ፕሬዝዳንት  ፊልድ ማርሻል  አል ሐጂ  ፕሮፌሰር  ዶክተር  ኢዲ አሚን ዳዳ ቪሲ ዴኤስኦ ኤምሲ  የምድር አራዊቶች እና የባህር አሳዎች ሁሉ ጌታ በአጠቃላይ የእንግሊዝ ና የስኮትላንድ ኢምፔሪያሊዝም በአፍሪካና በኡጋንዳ ድል አድራጊ ።"

እንግዲህ ይህ ሁሉ አጭር መጣጥፍ ወይም ድርሰት ሳይሆን  ኡጋንዳን ለ8 አመታት ሰጥለጥ አድርጎ ያስተዳደረው  አምባገነን መሪ መጠሪያ የማዕረግ ስም  ነው ።

ኤዲያሚን ዳዳ አፈሩን ገለባ ያድርግለትና በእነዚህ ሁሉ የማረግ ስሞች ያለማጓደል እንዲጠራ በመመርያ ሳይቀር ደንግጎ ነበር ።

ኤድያሚን ዳዳ ትምህርቱን ከ4ተኛ ክፍል ያቋረጠ  ታሪክ በአምባገነንታቸውና በጨካኝነታቸው በግንባር ቀደምትነት ከፈረጃቸው " ምርጥ አምባገነኖች" አንዱ ነበር።



ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! 😀

💔 
https://t.me/yefikirtelegramet 💔


      🔸🔸🔺🔺🔹🔸

      
❤️ የፍቅር ጥግ ❤️

ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ  ታሪክ
❤️

ፀሀፊ
✍️ ማኔ


                        ክፍል  
2️⃣7️⃣



እኛ ባናት ባናቱ መጠጣት ጀመርን።
እሷ ተሳቃ ቀስ ብላችሁ እንጂ የናንተ አደል የት ይሄዳል ትለናለች። ልክ ሁለት ሰአት ሲሆን ከቤት አስሬ ስልክ እየተደወለላት ልታወራ እየወጣች መግባት ጀመረች።
እዮብ አይኑ ቤቱን በሙሉ እያማተረ ነው እኔ
ስለመውጣቷም ስለመግባቷም ግድ አይሰጠኝም ሁለት ወይ ሶስቴ እየወጣች ከገባች ቡሀላ በቃ እንሂድ ወይ እናንተ ቆዩ እኔ ልሂድ ከቤት እየደወሉልኝ ነው ከዚህ ቀላይ ከቆየሁ ጥሩ አይመጣም አለችን።

እዮብ በሀሳቧ ተስማምቶ ሂሳብ ከፍሎ ተነስተን ወጣን በእግራችን እየተራመድን እዮብ ከት ብሎ ሳቀና እኔ ምልሽ ልእልት ያ አስሬ ስትወጪ ስትገቢ ቁጥ ቂጥሽ ሲል የነበረው ልጅ ምን እያለሽ ነው አላት።
አንተ እንዴት አየኸው ብላ መለሰችለት።
አይን አይከለከል አለ ዘፋኙ አይኑ ካንቺጋ ተንከራተተኮ እንዴት በስስት እያየሽ እንደነበር ሳይ ሳቄ መጥቶ ነበር ውጭ ግን ምን አለሽ እእ??
ምንም ዝም ብሎ ነው የለፈለፈብኝ እኔ ምን እንዳለ እራሱ አልሰማሁትም አለችው።
በመሀል እዮብ ስልክ ተደወለልኝ ላውራ እናንተ ተራመዱ ብሎ ወደኋላ ቀረ።እኔና ልእልት ዝም ብለን መራመድ ጀመርን ልእልት እጇን በደረት አድርጋ ታቃለህ ግን ባህራን በዚህ በምሽት በዚህ መንገድ ላይ አንተ ከጎኔ ሆነህ አብረን እየተራመድን መሆኑን ሳስብ ህልም ነው ሚመስለኝ ትቆጣኛለህ ብዬ ፈርቼ ነው እንጂ ዝም ብዬ እቅፍ አድርጌህ ለደቂቃዎች ብቆም ደስ ይለኝ ነበር አለችኝ።


ምንም ሳላቅማማ አዎ እቆጣሻለሁ እኔ ማንም
እንዲያቅፈኝ አልፈልግም አልኳት።
ትንሽ ዝም ካልን ቡሀላ ግን ለምን ምን ችግር አለው ባቅፍህ ምንህ ይጎዳል አለችኝ።
ልቀፍህ አትበይኝ መታቀፍ ፈራለሁ
ልሳምህ አትበይኝ መሳም እፈራለሁ
ለምን? ታቅፎ የተሳመው ሲሰቀል ስላየሁ ..
የሚል ጥቅስ አንብቤ ትርጉሙ ምን እንደሆነ አልገባኝም ነበር ለረጅም ጊዜ ጥያቄ ፈጥሮብኝ ከቆየ ቡሀላ ለእናቴ ነገርኳት፡፡ ይሄ ትርጉሙ ከሀይማኖት ጋ የተያያዘ ነው ጌታችንን አቅፎ ስሞ ነው እንዲሰቀል አሳልፎ የሰጠው ያንን ለማስታወስ ነው ይሄ አባባል የተነገረው አለችኝ፡

አሁን ግን ያቺ አባባል ከሀይማኖት ትርጉም ባለፈ አሁን ባለንበት እያቀፉ እየሳሙ አሳልፈው ሚሰጡ ብዙ ይሁዳዎች አሉ አይገርምሽም ግን ይሁዳ ቢያንስ ተፀፅቶ ነበር ዘንድሮ ግን እነሱ እያስለቀሱን በኛ እንባ ውስጥ የነሱ ሳቅ ነው ሚታየው አልኳት።
ቆይ ሁሉም ሰው ከሀዲ ነው ሚመስልህ አደል አለችኝ። እኔ መስሎኝ ሳይሆን ስለሆነ ነው ከእናቴ ጀምሮ ተመልከቺ ሁሉም ከሀዲ ነው እዚህ ምድር ላይ መጥቼ አይኔን ስገልጥ ያየኋት ሴት እናቴ ናት እሷም ከሀዲ ናት ስለፍቅር አውቄ ለፍቅር ልቤንም አይኔንም ስከፍትም የተመለከትኳት ሴት ፋኖስ ናት እሷም ደሞ የምድራችን ጨካኝና ከሀዲ አስመሳይ ሴት ናት አልኳት።
ግን ባህራን ከፋኖስ ቀድሜ የጠየኩህ እኔ ብሆን እኔን ታፈቅረኝ ነበር??!አይ አላፈቅርሽም ምክንያቱም አንቺ አሰልቺና ማትፈቀሪ አይነት ሴት ነሽ አልኳት ተናዳ ከጎኔ ጥላኝ እንድትሄድ ፈልጌ ነበር።


እሷ በተቃራኒው ፈገግ ብላ ላንተ ማልፈቀር አይነት ሴት ልመስልህ እችላለሁ ግን እኔ እያጋነንኩ ሳይሆን በዙሪያዬ ያሉ አብዛኞቹ እና እኔን ለመቅረብ እድሉን ያገኙ ወንዶች አብዛኞቹ አፍቃሪዎቼ ናቸው።
እኔ ግን የነሱን እንዳለ ጨምቆ አንተ ብቻ አፍቅረኸኝ አብረን በኖርን ብዬ ነው ምመኘው ብላ እንባዋ ዱብ ዱብ አለ...



ይቀጥላል...



🔻ክፍል2️⃣8️⃣1️⃣5️⃣0️⃣ like በዃላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!
😀

💔 https://t.me/yefikirtelegramet 💔1️⃣


ሰላም ሰላም ቤተሰብ የፍቅር ጥግ ክፍል 27 ሊለቀቅ ነው አላችሁ ወይ?


      🔸🔸🔺🔺🔹🔸

      
❤️ የፍቅር ጥግ ❤️

ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ  ታሪክ
❤️

ፀሀፊ
✍️ ማኔ

                        ክፍል  
2️⃣6️⃣

ፓፓ በቃ ይቺን ማስመሰል ተክናችሁባታል አደል አልኳት።
ተነስታ በተቀመጥኩበት ጥላኝ ሄደች።
እኔም ወደሰፈር ተመለስኩ።
ቀናቶች ተቆጠሩ እዮብ ቀን በቀን ስራ እንድጀምር ይገፋፋኝ ጀመር፡፡
እኔ ግን አቀዋለሁ ያለሁበት ሁኔታ እንኳን አስቦ ስራ ሰርቶገንዘብ ማግኘት ይቅርና መንገድ ላይ ስሄድ የማደርገውን የምሰራውን አላቅም አንዳንዴ እየተራመድኩ ከፊት ለፊቴ
እየሄዱ ያሉ ሰዎችን መመልከት ያቅተኛል አንዳንዴ ደሞ መንገዱ በራሱ ወደቀኝ ይሁን ወደግራ ድንግርግር ይለኝና ለትንሽ ሰአት ቆም እላለሁ ።

እየቆየ ሲሄድ ከልቤ ደስተኛ መሆን ናፈቀኝ ላንዴ እንኳን መሳቅ ለኔ ህልም ሆነ
መንገድ ላይ ስሄድ ከልባቸው ሚስቁ ሰዎችን ስመለከት ውይ ታድለው እንደዚህም ስቄ አቃለሁኮ ማለቱን ተያያዝኩት።

ሲጋራ አጨሳለሁ ጫት እቅማለሁ አረቄ እጠጣለሁ ግን ሁሉንም ለምን እንደማደርገው አላቅም ብቻ እንጠጣ እሺ እንቃም እሺ እንስረቅ እሺ እናጭስ እሺ አለቀ በቃ
ሚያደርጉትን መቃወምም አልፈልግም።
ቨያንን ከተናርኳት ወዲያ ልእልት ጠፍታ ነበር የቆየችው እዮብ ምክንያት እየፈለገ ሊያስመጣት ቢፈልግሜ እንቢ
አለች። ሰፈሯ ድረስ ሄደን ካላየናት ብሎ አስጨነቀኝ እኔ እዛ ሰፈር ፊቴን እንኳን ማዞር አልፈለኩም።

የተፈጠረ ወይ ያስቀየምኳት ነገር ካለ አጥብቆ ጠየቀኝ ነገርኩት ሁሉንም በኔ ምክንያት ትምህርት እንዳቆመች ምናምን በቃ ምንም አልቀረኝም። እረጅም ሰአት ቁጭ አድርጎ አወራኝ ያንተም ህይወት ተበላሽቷል የሷም አይበላሽ ቢያንስ አንዳችሁ እንኳን ሰው
ሆናችሁ መቆም አለባችሁ። አስታውስ እንጂ እናትህ ስትሞት እንኳንኮ ለሷ ነው አደራ
ያለችህ ስለዚህ አንድ ያየችባት ጥሩ ነገር አለ ማለት ነው ቢያንስ ቢያንስ እንኳን ትምህርቷን እንድትማር አግዛት እንጂ አለኝ።

እሱን ደስ እንዲለው እዛው ደውዬ አወራኋት በአካል መጥታ በደንብ እንድናወራ ነገርኳት እሺ አለች መጣች፡፡
እኔን ማግኘት ማውራት ከፈለገች ትምህርቷን መማርና ከቤተሰብጋ መታረቅ እንዳለባት ካልሆነ ግን ጭራሽ እንደማታየኝ ተኮሳትሬ ነገርኳት።እሺ አለችኝ።

እዮብ አብሮን ቁጭ ብሎ ስለነበር
ከፈለግሽ ሁሌ እኛ ትምህርት ቤት እያደረስን
እንመልስሻለን ስትሄጂም አብረንሽ ስትመጭም አብረንሽ መሆን እንችላለን ስራ የለን እኛ ምን ይሰራልናል አላት።
ፊቷ ሁላ ብርት እያለ ባንዴ ተስማማች።


እኔ ግን በሁኔታው አልተስማማሁም ፊቴን አጥቁሬ ዝም አልኩ።እነሱ የኔን ሀሳብ አልሰሙም የደስ ደስ ዝም ብለው
መሳሳቅ ጀመሩ እዮብ ባይኑ ምንም እንዳልናገር ምልክት እያሳየኝ ስለነበር ዝም አልኩኝ።
ከዛን ቀን ጀምሮ ከሩቅ እየጠበቅን እኛ ትምህርት ቤት እያደረስናት መመለስ ጀመርን አንዳንዴ አውቃ ክላስ ሳይኖራት ትምህርት ቤት ድረስ ትወስደንና እረስቼው ነው በቃ ተመልሰን ወክ እናድርግ ትለናለች፡፡

እኔ ብሽቅ እላለሁ እሷ ግን ፊቷ ላይ ሚታየው ብርሀን ይለያል። ሁልጊዜ ከእዮብጋ ቁጭ ብለው ሲያወሩ የኔን አይን እያየች ነው ምትሰማው እኔ ደሞ ያ ነገር በጣም ምቾት
ይነሳኛል፡፡ ቅዳሜ ቀን እዮብ ለምን ወተን ዘና አንልም እኔ ሰሞኑን አሪፍ ነው የሸቀልኩት አለ።
ልእልት በምንም አሳባ መውጣት እንደማትችል
ተናገረች።

እዮብ ስንት ምክንያት ደርድሮ ለቤተሰቦቿ
እንድትነግራቸው ነገራትና አሳመናት።
ተስማምተን ወጣን ልእልት ለወትሮው ጠቅልላ ነፃነቱን የነፈገችውን ፀጉሯን ጀርባዋ ላይ ነስንሳ ቅርጿን ጉልት አድርጎ የሚያሳይ ግን ደሞ ጨዋነትን የተላበሰ አለባበስ
ለብሳ መጣች።

ሳያት ውስጤን ምን እንደነዘረኝ አላቅም ግን የሆነ ነገር ጠቅ አድርጎኝ አለፈ።
ግን ላለመረታት ምነው ተቁላልተሽ መጣሽ ምትሄጂውኮ ከኛጋ ነው እኛ እንደምታይን ሱሪያችን እላያችን ላይ ነትቧል የለበስነው ሹራብም ቢሆን ከመሬተጋ ተመሳስሏል አልኳት
ቅልስልስ ብላ እያየችኝ አይገርምም አንተም ከመቼው ከነሱጋ እንደተመሳሰልክ እኛ ብለህ ማውራት ጀመርክ አደል፡፡
አንተም እራስህን እንደጎዳና ሰው መመልከት እራስህን በዛ ሚዛን ማስቀመጥ ጀመርክ ጎበዝ እንዲህ ነው እቴቴ እንድትሆንላት ምትፈልገው አለችኝ።

እንደማያገባት ነግሪያት ዝም ብዬ ሄድኩኝ እዮብና እሷ ተከተሉኝ አብረን ወደ አንድ ቤት ሄድን ከበር ስንገባ ጀምረን ቤት ውስጥ የነበሩትን ሰዎች ቀልብ እንደሳብን
ግልፅ ነው አንደኛ የልእልት ውበት ብቻውን ማንንም ማፍዘዝ ይችላል።
ሁለተኛ እሷ በዛ ልክ ለብሳና ተውባ ከግራና ከቀኟ ሁለት ቦርኮ ወንዶችና ይዛ መጠጥ ቤት ለመዝናናት ስትገባ ሁሉም ሰው ግራ መጋባቱ ግልፅ ነው፡፡ ልእልት ምንም አይነት መጠጥ ጠጥታ ስለማታቅ አልጠጣም ብላ ለስላሳ አዘዘች እዮብ አልተጫናትም
በሀሳቧ ተስማምቶ እሺ አላት.....

ይቀጥላል...



🔻ክፍል2️⃣7️⃣1️⃣5️⃣0️⃣ like በዃላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!
😀

💔 https://t.me/yefikirtelegramet 💔


እንዴት አመሻችሁ ቤተሰብ የፍቅር ጥግ ክፍል 26 ሊለቀቅ ነው አላችሁ ወይ?


      🔸🔸🔺🔺🔹🔸

      
❤️ የፍቅር ጥግ ❤️

ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ  ታሪክ
❤️

ፀሀፊ
✍️ ማኔ

                        ክፍል  
2️⃣5️⃣


አንች ከሌሎች በምን ትለያለሽ አሁን አንቺ ከፋኖስ ተሽለሽ ነው አልኳት።
ለምን ሁሉም ሰውኮ እሷን አደለም ልብህን ክፍት አድርገህ ሰዎችን ለመውደድ ካላመንክኮ ይከብድሀልአለችኝ፡፡
እኔ ግን በተቃራኒው ከቻልሽ እንደውም ባትከታተይኝ ባይ ነኝ ሰላሜን አታሳጭኝ አልኳት፡፡ተነስታ ወጣች ምንም አላሳዘነችኝም። ማታ ላይ እዮብ መጣና ከአጠገቤ ጋደም አለ።

እኔ ተነስቼ ላጨስ ወጣሁ፡፡ተከትሎኝ መጣና ከፊት ለፊቴ ቁጭ አለ።
እኔ ምልህ ግን ልእልት ዝም ብዬ ሳስባት ታሳዝነኛለች ለምንድነው አለኝ፡፡እኔጃ እኔ ግን ምኗም አያሳዝነኝም አልኩት፡፡
ስላንተኮ አደለም ስለኔ ነው ያወራነው ታቃለህ ቀን እንደዛ ስጮህብህ የተናገረችኝ አነጋገር ውስጤን በላው ባህራን ለምን እንደሆነ አላቅም ግን ዝም ብዬ ሳስባት ሳያት ልቤ ልውስ ልውስ ይላል አለኝ።
በቃ አፍቅረሀት ነው እንኳን ደስ አለህ አልኩት።

አይ ባህራን ፈጣሪ እንዳያረግብኝ እኔ አሁንኮ አርጅቻለሁ እድሜዬን ጎዳና ላይ ጨርሼዋለሁ ስታስበው እንደልእልት አይነት ሰው በምን ተአምር ነው እኔን ሚፈልገኝ አለ።ንግግሩን ሳይጨርስ ደም ባፉም ባፍንጫውምመምጣት ጀመረ።

አልደነገጠም እኔም አልደነገጥኩም ዝም ብዬ አጠገቤ ያገኘሁትን ጨርቅ እየሰጠሁት ጀመረህ ደሞ ይሄ ደምህ አንዴ መፍሰስ ከጀመረ አያቆምም አደል አልኩት፡፡ግባና ተኛ እኔ ደሜ እስኪቆም ትንሽ እቆያለሁ በዛውም ጨረቃዋን እያየሁ ልእልቴን ላስባት አለኝ።

ገብቼ ተኛሁ።በነጋታው በተለመደው ሰአት የእናቴ መቃብርጋ ስሄድ ልእልት ቀድማኝ ደርሳ ቁጭ ብላለች።
ስታየኝ እየጠበቀችኝ እንደነበር በሚያስታውቅ መልኩ ፈገግ አለች፡፡ሳያት አናደደችኝ ለእናቴ ብዙ መንገር ምፈልገው ነገር አለኮ እዚህ እንኳን ነፃነቴን ስጪኝ እንጂ አልኳት።ተነስታ እራቅ ብላ ተቀመጠች እኔም የእናቴን መቃብር በቀኝ እጄ ተደግፌ ቁጭ አልኩና ዝም ብዬ ለፈለፍኩባት እያበድኩ ሆኖ ይሆን ወይ ምን አስቤ እንደሆነ እንጃ ግን ልክ ሌላ ጊዜ ስራ ውዬ ስመጣ እንደማወራት አድርጌ ነበር ያወራኋት።ስጨርስ ወደ ልእልት ሄድኩና ቻው ልሄድ ነው አልኳት፡፡ትንሽ አታወራኝም ማለቴ ካልደበረህ አለችኝ።
እሺ ብዬ ካጠገቧ ቁጭ አልኩ ወሬ ለመፍጠር
በሚመስል መልኩ እኔ ምልሽ ልእልት እዮብ ግን ካንቺ ፍቅር ቢይዘው ምን ትያለሽ አልኳት።
መቼም እንዲይዘው አልፈልግም ምክንያቱም ትርፉ ጉዳት ነው እኔ መቼም ልቤ ካንተ ውጭ አያስብም አለችኝ።

ቀልዱን ተይው ቁም ነገር ነው ማወራሽ አልኳት፡፡እኔ መች ቀለድኩ ቆይ ባህራን እኔኮ አሁን ላይ ብዙ ነገሬን እያጣሁ በብዙ እየተወቀስኩ ነው ያለሁት። አይታይህም እንዴ ባንተ ምክንያትኮ ዘንድሮ ትምህርቴን አቁሚያለሁ ባንተ ምክንያት ሁሉም ቤተሰቦቼ ፊት ነስተውኛል እንደልጃቸው አያዩኝም አውጥተዎ አይጥሉኝ
ነገር ሆኖባቸው ነው ሚያኖሩኝ ስራም እየሰራሁ
አደለም ብቻ ልነግርህ የማልችለው ብዙ መስዋትነትን እየከፈልኩልህኮ ነው አለች

ይቀጥላል...



🔻ክፍል2️⃣6️⃣1️⃣5️⃣0️⃣ like በዃላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!
😀

💔 https://t.me/yefikirtelegramet 💔


እንዴት አመሻችሁ ቤተሰብ የፍቅር ጥግ ክፍል 25 ሊለቀቅ ነው አላችሁ ወይ?


      🔸🔸🔺🔺🔹🔸

      
❤️ የፍቅር ጥግ ❤️

ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ  ታሪክ
❤️

ፀሀፊ
✍️ ማኔ

                        ክፍል  
2️⃣4️⃣


ፊቷን ፀጉሯ ስለሸፈነው ላያት አልቻልኩም ዝም ብዬ የሚሰማኝን ህመም እየተቋቋምኩ ሰውዬው የተናገረውንም ግጥም ቅኔውን እየፈታሁ ነበር። ትንሽ እንደሄድን ቤትህ ወዴት ነው የት እናውርድህ አለኝ። የተመቻችሁ ቦታ ጣል አድርጉኝ አመሰግናለሁ አልኩት። ሴቷ ወደኔ ዞራ በድንጋጤ አይን አየችኝ ፋኖስ ነበረች እርጉዝ ናት ደሞ በጣም አምሮባታል ፊቷ ከበፊቱ የበለጠ ያንፀባርቃል ወደኔ ዞራ አፈጠጠችብኝ ወደመኪናው ስትገባ ፊትህ አዲስ አልሆነብኝም ነበር አሁን ግን በድምፅህ ነው ያወኩህ ባህራን እንዳትሆን ብቻ አለችኝ።

ተሸማቀኩ የመኪናው መስኮት እንድዘል የሚመቸኝ ቢሆን ካለማቅማማት አደርገው ነበር።ሰውዬው ግራ ተጋብቶ እየተመለከተኝ ፋኖሴ ታቂዋለሽ እንዴ አላት።ወይኔ የኔ ባል ፊቱ ጠፍቶብህ ነው ይሄኮ ነው የህቴ ገዳይ አለችው።
ምን ባህራን ማለት እሱ ነው እንዴ ቆይ ያ መልከ መልካሙ ልጅ ነው አላት ።ወይኔ በጌታ እኔ እራሱ መጀመሪያ አላወኩትምኮ እንደዛ አፈር አይንካኝ የሚለው ባህራን ነው ዛሬ እንደዚህ ሆኖ ያየሁት አይገርምም እኔም የእህቴ ሀዘን እንዲህ ነበር ከሰውነት ተራ ያስወጣኝ ፈጣሪ ለሁሉም እንደየስራው ይሰጣል አሁን ውረድ ከመኪናው አለች
ባልየው ካለምንም ማቅማማት መኪናውን አቆመው ፋኖስ ቦርሳዋን ከፍታ ያገኘችውን መቶ ብር አውጥታ ወርውራልኝ የፌዝ ሳቅ ስቃብኝ ሄደች።

የሰው ልጅ ሆኖ ከዚህ በላይ ሞት ከዚህ በላይ ቅጣት ያለ አይመስለኝም። መጀመሪያ ላይ ስላገኘኋት ደስ ብሎኝ ብቻዬን ለመሳቅ እየሞከርኩ ነበር ከዛ ግን ጠቅልዬ የያዝኩትን ብር ተመለከትኩና ሰውነቴን ጠላሁት አሁን አሁን ጭንቅላቴ ማገናዘብ አቁሟል የቱን ቀድሜ ማሰብ እንዳለብኝና በየቱ መናደድ እንዳለብኝ በራሱ ግራ እየተጋባሁ ነውዝም ብዬ ወደሰፈር ሄድኩ ልእልትና እዮብ ግቢ ውስጥ እየተንጎራደዱ ጠበቁኝ። እዮብ ገና እንዳየኝ ንዴቱን ፊቱ ላይ አስተዋልኩት አንተ ሞኝ ነህ እንዴ እኔን ተከትለህ ምትሮጠው አባረህ ልትይዘኝ ነው ወይስ አነተ እሮጠህ እስክትደርስ ቆሜ እንድጠብቅህ ነው ምን ያርበተብትሀል አለኝ።

ልእልት የእዮብን አይን እየተመለከተች እዮብእየጮክበትኮ ነው ተረጋጋ እንጂ አለችው።
ያልመታሁትም እሱ ሆኖብኝ ነው አታይም እንዴ እንዴት አድርገው እንደላኩት ቆይ ቢያስሩትስ አላትና ትቶን ወጣ፡፡ ልእልት እንደለመደችው እያለቀሰች ቁስሌን ትጠራርግልኝ ጀመር። የሷ ማልቀስ ይባስ አናዶኝ ምንድነው በሆነው ባልሆነው እንደህፃን ልጅ ዝም ብሎ መነፋረቅ ያምሻል እንዴ አልኳት። እንባዋን እየጠረገች እኔኮ ባፌ ጮክ ብዬ መናገር ስለማልችል ብሶቴን በእንባ ነው ምገልፀው ከቃላቶቼ በፊት እንባ ነው ሚቀድመኝ ደሞ እንደዚህ ሆነህ እያየሁ አለማልቀስ አልችልም አለችኝ።

ፋኖስ የሰጠችኝን ጨብጬ የያዝኳትን መቶ ብር እያሳየኋት አይገርምሽም ግን ፋኖስንኮ ዛሬ ከባላጋ አየኋት እንዲህ ሆኜ ነበር ያየችኝ እንደኔ ቢጤ መቶብር ወርውራልኝ ሄደች ደሞ አርግዛለች እንዴት እንዳማረባት አልኳት። ከምርህን ነው ፋኖስ መቶ ብር ወርውራልህ ሄደች አለችኝ፡፡
አው አልኳት፡፡ቆይ ባህራን የሰው ልጅ በዚህ ልክ በዚህ ፍጥነት መቀየር ይችላል እንዴ ቆይ ከመቼው ነው በዚህ ልክ እራስህን ያጣኸው ሌላ ጊዜ ቢሆንኮ ለምን ቀና ብላችሁ አያችሁኝ ብለህ ምትጣላ ሰው ነበርክ አለችኝ።
እሱ እናቴ እያለች የምኖርበት ምክንያት እያለኝ ፋኖስ ፍቅረኛዬ በነበረችበት ጊዜ ነው አሁን ግን ልቤን ፍቅሬን ሰውነቴን ባንዴ ነው ያጣሁት አሁን የትኛው ክብሬን ልጠብቅ ለማን ብዬ ልኑር የውስጤ ንዴትስ እእ እናቴ ስትናፍቀኝ ልቤ ላይ ምን እንደሚሰማኝ አታቂም የማላቀው ህመም ይተናነቀኛል ልቤን እፍን ያደርገኛል ወደሰማይም በርሬ ቢሆን ላንዴ እንኳን ማቀፍ መሳም ፈገግ ስትል ማየት እፈልጋለሁ ግን አልችልም።
እናቴ አፈር ውስጥ ተቀብራ ሰውነቷን ምስጦች እየበሉት እንደሆነ ማሰብ በራሱ ይገላልኮ አልኳት።
በስስት እያየችኝ ቆይ ባህራን እኔ ያን ያህል ምንም ማልፈቀር ማስጠላ ሰው ነኝ እንዴ እእ የቱጋ ላንተ አንሼ የታየሁህ ለምን ለኔ ብለህ አትኖርም ለምን ህይወትህን አታስተካክልም አለችኝ....

ይቀጥላል...



🔻ክፍል2️⃣5️⃣1️⃣5️⃣0️⃣ like በዃላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!
😀

💔 https://t.me/yefikirtelegramet 💔


እንዴት አመሻችሁ ቤተሰብ የፍቅር ጥግ ክፍል 24 ሊለቀቅ ነው አላችሁ ወይ?


      🔸🔸🔺🔺🔹🔸

      
❤️ የፍቅር ጥግ ❤️

ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ  ታሪክ
❤️

ፀሀፊ
✍️ ማኔ

                        ክፍል  
2️⃣3️⃣

እዛ ቤት ከመጣች እኔ ለማጨስ ሲጋራ ሳወጣ የሷ እንባ ቀድሞ ዱብ ዱብ ይላል ያላትን ብር እንዳለ ሰታንትሄዳለች።
ወደዛ ቤት እንድመለስ ብትለምነኝም እኔ ጭራሽ ድጋሜ እንደዛ አይነት እርእስ ካነሳች ደግሜ እንደማላወራት እነግራትና ዝም አስብላታለሁ። እኔ እናቴ መቃብርጋ ሄጄ አልቅሼ ወደቤት ተመልሼ ቁጭ እንዳልኩ እዮብ ከውጭ ገባ ባህራን ግን ታውቆሀል አደል ምንም ብር የለንምኮ ወተን ተፍ ተፍ እንበል እንጂ አለኝ።ተስማማሁ ተከተልኩት ለመጀመሪያ ጊዜ ለመስረቅ ወሰንኩ የት እንደምሄድ ምን እንደምንሰርቅ አላቅም ግን ዝም ብለን አይናችን እየቀላወጠ መራመዱን ተያያዝነው እዮብ አይን አይኔን እያየ እስከዛሬ እንዴት እየሰረኩ እንዳኖርኩህ ዛሬ ይገባሀል አለኝ። ወደ አንድ ሆቴል አመራንና ከርቀት ቆምን ዝም ብለህ አይንህን ከበሩ ላይ እንዳትነቅል አንዳንዱ ሚስጥራዊ
ነኝ ባይ ከሆቴሉ ወጥቶ ያወራሉ አንዳንዱም መናፈስ ሚፈልግ ይኖራል ብቻ ከእጃቸው ላይ መንትፈህ መሮጥ ነው ዞረህ እንኳን እንዳታይ አለኝ። እሱ እንዳለኝ ማድረግ ጀመርኩ አንዲት ልጅ ወጣችና አየር እየወሰደች ስልኳን መነካካት በሩ ላይ ቆማ ሰልፊ መነሳሳት ጀመረች::

ከሷ እንቀበላት እንዴ ልለው ዞር ስል እዮብ ካጠገቤ ተሰውሯል ::በምን ቅፅበት ከልጅቷ እንደመነተፋት ሳላውቅ ከእጇ ላይ ላጥ አድርጓት እሮጠ ድንጋጤ ውስጥ
ስለነበርኩ እሱ ወደሚሮጥበት ተከትዬው መሮጥ ጀመርኩ እዮብ ካይኔ ተሰወረ ዞር ስል ሁሉም እኔን እየተከተሉኝ ነው የልቤ ድንጋጤ ሰውነቴን መሮጥ እንዳይችል አደረገኝና ዝም ብዬ ቆምኩኝ የመጣው ሰው ሁሉ ቡጢና እርግ ጫ ያሳርፍብኛል እኔ አደለሁም እኔ አደለሁም እያልኩ ከመጮህ ውጭ ቃላት አልነበረኝም ብቻ ሰውነቴ ላይ የሚሰማኝ ህመም ወደር አልነበረውም መሬት ላይ አስተኝተው እንደኳስ አንከባለሉኝ ።

በመጨረሻም አንድ ሰውዬ አቁሙ አቁሙ ብሎ ሲጮህ ሰማሁት አይኔን ወደላይ ቀና አደረኩና ተመለከትኩት ፊቱ አዲስ አልሆነብኝም ዝም ብላችሁ የወደቀና የቆሸሸ ሰው ስታገኙ መራገጥ ይቀናችኋል የተሰረቀባችሁ እቃ ካለ ፈትሹና እቃችሁን መልሳችሁ ወስዳችሁ ልጁን ለፖሊስ ማስረከብ ነው እንጂ ዝም ብሎ የሰውን ልጅ መደብደብ ምን ይሉታል አላቸው:: "እኔ ያቺን አጋጣሚ ተጠቅሜ ከመሬት ተነሳሁ ፊት ለፊታቸው ሙሉ ልብሴን እያወላለቀ ፈተሸኝ ምንም ነገር የለም ከሰዎቹ መሀል ይዞኝ ወጣና ወደመኪናው አስገባኝ ውስጥ ገብቼ ልብሴን እያረጋገፍኩ ከላይ በለበስኩት ሹራብ ደሜን መጠራረግ ጀመርኩ፡፡

አይገርምሽም በቃ በየመንገዱ የሰውን ልጅ መደብደብ ጀብድ አደረጉት አደል ይሄን ልጅ ሳየው አንድ ግጥም ትዝ አለኝ

7.1k 0 12 3 265

እንዴት አመሻችሁ ቤተሰብ የፍቅር ጥግ ክፍል 23 ሊለቀቅ ነው አላችሁ ወይ?


      🔸🔸🔺🔺🔹🔸

      
❤️ የፍቅር ጥግ ❤️

ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ  ታሪክ
❤️

ፀሀፊ
✍️ ማኔ

                        ክፍል  
2️⃣2️⃣



ሁኔታው ግራ አጋባኝ እዮባ ግን ጤነኛ ነህ ማለቴ አንተ መንገድ ላይ እንኳን ሴት ስታይ እንዴት ፊትህን አዙረህ እንደምቴድ አቃለሁ ታዲያ አሁን ምን ተገኘ አልኩት።

ብዙ ጊዜ እኔ ውስጤ ይነግረኛል ይቺ ውስጧ ነጭ ወረቀት ነው አንዳንድ ሰዎች የልባቸው ንፁህነት ፊታቸው ላይ ነው የሚታየው አታይም የውስጧ ጉዳት አይኗ ላይ ይታያልኮ ስታይህ አይኗን ስብር አድርጋ ነው አለኝ።

ዝም ብዬው ምግባችንን መመገብ ጀመርን ።
ማታ ላይ ሁሉም ተሰብስቦ ቦታ ቦታውን ይዞ ተኛ እኔና እዮብ ዝም ብለን ቁጭ አልን መተኛት አልፈለግንም ነበር ወደውጭ ወጣንና ቁጭ ብለን ማጨስ ጀመረን።

እዮብ በእጁ የያዛትን ሲጋራ ወደመሬት ጣለና እረገጥ እያደረገ አይገርምህም ግን የሰው ተፈጥሮ አሁን እኩለ ሌሊት ነው ግማሹ የሞቀውን የሚስቱን ገላ አቅፎ ሚገርም ፍቅር እየሰራ ነው ግማሹ ደሞ ከሚወደው ቤተሰቡጋ  ጤነኛ እንቅልፍ ወስዶት እያንኮራፋ ነው የተወሰነው ታሞ እየማቀቀ ነው እንደኛ አይነቱ ቁጭ ብሎ ሲጋራ እያጨሰ ነው ሌሎቹ ደሞ ክለብ ላይ እየቀወጡት ነው ዝብርቅርቅ ያለ መላ ቅጡን ያጣ ህይወት ባይኖርስ እንዴ አለኝ።

ዝም አልኩት።
ስልኩን አውጥቶ ልእልትጋ ደወለ ሳይጠራ ማለት በሚቻል መልኩ አነሳችው ስፒከር ላይ አድርጎት ማውራት ጀመሩ።

እንዴት አመሸሽ ቀሰቀስኩሽ እንዴ???

አይ አልተኛሁም ነበር ብደውልኮ ማስጨነቅ ይሆንብኛል ብዬ ነው ባህራን ገብቷል አደል አብራችሁ ናችሁ እንዴ አለችው።
እኔ በእጄ ተኝቷል እንዲላት ምልክት ሰጠሁት።

እሱም ሳያስባንን ተኝቷል ቤት ነው እኔ እንቅልፍ እንቢ ብሎኝ ነው የደወልኩት ያ ውበትሽኮ ካይኔ አልጠፋ አለ እንዳንቺ አይነት እንቡጥ አበባ አይቼ አላቅም አላት።

ልእልት እየሳቀች ምናለ አሁን ያልከኝን ቃል በሙሉ ከባህራን አፍ ብሰማው አለች።

እዮብ የማዘን ፊት እያሳየኝ እንደውም ተነሳ አውሪው በቃ ብሎ ስልኩን ወደኔ ሰጠኝ እኔ ጆሮዋ ላይ ዘጋሁትና እዮብ ላይ ተበሰጫጭቼ ወደውስጥ ገብቼ ተኛሁ።

እዮብ ምክንያት ፈልጎ ልእልትጋ ይደውላል እሷም ምክንያት ፈልጋ እሱ ነይ ሲላት ትመጣለች ።
እኔ ከነሱ ለመሸሽ ስሞክር ሁሉቱም ንቅንቅ አያስደርጉኝም ።

ልእልት ሁሉ ነገሯ ደስ የሚል ብትሆንም ለኔ ምኗም አይዋጥልኝም ምክንያት ፈልገህ ምታት ምታት ይለኛል።



ይቀጥላል...



🔻ክፍል2️⃣3️⃣1️⃣5️⃣0️⃣ like በዃላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!
😀

💔 https://t.me/yefikirtelegramet 💔


እንዴት አመሻችሁ ቤተሰብ የፍቅር ጥግ ክፍል 22 ሊለቀቅ ነው አላችሁ ወይ?


      🔸🔸🔺🔺🔹🔸

      
❤️ የፍቅር ጥግ ❤️

ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ  ታሪክ
❤️

ፀሀፊ
✍️ ማኔ

                        ክፍል  
2️⃣1️⃣


ምንም አትወዳትም ነበር ማለት ነው አለችኝ ዝም አልኳት ጉልበቴን አቅፌ የእማዬን ፎቶ እያየሁ ትክዝ አልኩኝ።
ልእልት ሙሉ ነገሬን ተመልክታኝ ግን ሰው በዚህ ፍጥነት መቀየሩ ይገርማል እራስህን ተመለከት እንደዛ ሰው ሁላ አይቶ ሚወድህ ውበትህን ሚያደንቅልህ አንዴ በሳቀ ብለው ሚጠብቁት ወንዳወንዶነትህ በሙሉ ጠፍቶ ባንዴ የጎዳና ሰው መሰለክ እቴቴ በህይወት ኖራ ይሄን ሁሉ ጉድ ብታይ እራሷን አጥፍታ መሞቷ አይቀርም ነበር አለችኝ። 

ፊቴን ወደ ልእልት አዙሬ እየተመለከትኳት ለምንድነው አሁንም ድረስ ጥቂር ሻርፕ ምታደርጊው አልኳት።
እቴቴኮ ለኔም ሁለተኛ እናቴ ናት በጣም ነበር ምወዳት ምሳሳላት እንደልጇ ነበር ምታየኝ ልእልት ብላ የጠራችኝም እሷ ናት እንጂ እኔ ስሜ ልእልት አደለም  እሷን ማጣት ከባድ ነው አለችኝ።

እሺ ለምንድነው እኔን በዚህ ልክ ምትከታተይኝ???

እኔ እናንተ ሰፈር ከገባሁ ጀምሮ አይኔ ያየው የመጀመሪያው ወንድ አንተ ነህ ከልጅነቴ ጀምሮ እንዲሁ ሳይህ ደስ ይለኛል ግን እኔ በጣም ጭምት ልጅ ስለሆንኩ ለማውራትም እፈራለሁ ገና ከሩቅ ሳይህ ነው ምደበቀው እቴቴ ሁሉንም ታቃለች የልጄ ሚስት አንቺ ነሽ ወገቤን አስሬ ነው ምድርሽ እያለች ነው ያሳደገችኝ አለችኝ።

እኔን ትወጂኛለሽ ማለት ነው አልኳት።
አዎ አለችኝ።

እስከመቼ ብዬ ጠየኳት።
ከልጅነቴ ጀምሮ እስካሁን ወድጄሀለሁ ካሁን ጀምሮ ደሞ እስትንፋሴ እስከቆመችበት ሰአት ድረስ እወድሀለሁ አለችኝ አንገቷን እንደደፋች ሳቄ ተናነቀኝ አይገርምሽም ፋኖስም እንደዛ ብላኝ ነበር ልክ እንዳንቺ ነበር ስታወራ ምትቅለሰለሰው አንቺን ጎበዝ አስመሳይ ነሽ አልኳት።

ዝም አለች ።
ተነስቼ ልሄድ ስል ተከተለችኝና እቤት ለምን አትሄድም የእቴቴ ጠረን አልናፈቀኽም አለችኝ።
አሌድም ያ ቤት የእናቴ ገዳይ ነው ሚመስለኝ ያልሸጥኩትም እኔ ሆኜ ነው አልኳት።

እሺ አንተ ያለህበት እንሂድ እየመጣሁ አረብሽም አንተ ስትፈቅድልኝ ብቻ ነው መጥቼ ማይህ አለችኝ።
እንደማላምናት ነገርኳት።
በእቴቴ ምያለሁ አንተ ሳትፈቅድ ላልመጣ የት እንዳለህ ለማንም ሰው እንደማልናገር ቃሌ ነው አለችኝ።

እሺ ብዬ ይዣት ሄድኩ አሳየኋት እዮብ ጋደም ብሏል እኛ ወደውስጥ ስንገባ ከአፍንጫው እየፈሰሰ ያለውን ደም እንኳን አላስተዋለውም ነበር።
ልእልት እንዳየችው ደንግጣ ምን ሆነህ ነው ምን ሆነህ እያለች አንገቱን ቀና አድርጋው ያደረገችውን ሻርፕ አውልቃ ደሙን ጠራረገችለት እዮብ ፈገግ ብሎ ተመለከታትና ቆንጅዬ አትጨነቂ ደምኮ ብርቅ አደለም እኛ የእለት ተእለት ህይወታችን ነው ሸበላው ይዞሽ መጥቶ ነው በሉ ፈታ በሉ እኔ ልሂድ አለ።

እኔ እየሳኩ አረ እዮባ ምንም የለንም የሰፈር ልጅ ናት ቤታችንን ላሳያት ነው ይዣት የመጣሁት አልኩት።

በቃ ምግብ ይዤ ልምጣ ብሎን ወጣ ልእልት በደንብ ቤቱን ቃኝችና ግን እዚህ መሆን ይሻላል ብለህ ነው ማለቴ ቤትህ አይሻልህም ስራ እየሰራህ መኖሩኮ ነው ላንተም ሚጠቅምህ አለችኝ።
ፊት ለፊቷ ሲጋራ አውጥቼ ለኮስኩና ጨስ ጨስ አድርጌ ጣልኩት።

ልእልት ፈገግ ብላ ይች አለም ግን ትገርመኛለች ጥሩ ነገር ሲሆን ነው እንጂኮ መጥፎ ነገር ለመልመድ በጣም ቀላል አደል አሁን አንተም ሁለት ምርጫ ተቀመጠልህ ወይ ስራህን እየሰራህ የሞቀ ቤትህ ውስጥ መኖር ወይ ደሞ ተራ ሰው ሆነህ ተራ ቤት ውስጥ እየኖርክ ችግረኛና ሱሰኛ መሆን አንተ ደሞ መጥፎውን መረጥክ አለችኝ።

አጉል አትመፃደቂ ሂጂ በቃ እዚህ መቆየትሽ ጥሩ አደለም አልኳትና ከቤት አስወጣኋት።

ብዙም ሳይቆይ እዮብ መጣ ።
እየሳቀ ነበር ወደውስጥ የገባው

አንተ እንዴት አባቷ ነው ምታምረው አይተኸዋል ስትስቅ እንዴት ጉንጮቿ ጉድጉድ እንደሚሉ ደሞ ቸኮሌት የሆነ ከለርኮ ነው ያላት ጡቶቿ ጉች ጉች ብለው ጨብጡኝ ጨብጡኝ ይላሉ ደም እርጋታዋ አሁን ወንድ ልጅ ሆኖ እሷን አለመፈለግ ጤነኝነት ነው ብለህ ታስባለህ አንተ ፋራ አለኝ።

እየሳኩ እና አንተስ ወንድ አደለህ ለምን አንተ አታገባትም አልኩት።
ይብላኝ ላንተ  እኔማ ተፍ ተፍ እላለሁ አሁን እራሱ ስላንተ መረጃ ለመስጠት በሚል ሰበብ ቁጥሯን ተቀብያት ነው የመጣሁት ብሎ እየደነሰ መሳቅ ጀመረ



ይቀጥላል...



🔻ክፍል2️⃣2️⃣1️⃣5️⃣0️⃣ like በዃላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!
😀

💔 https://t.me/yefikirtelegramet 💔

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.