♥️ ተማሪዋ ♥️ ...
.
.
🌹...ክፍል 28...🌹
.
.
አዘጋጅ እና አቅራቢ=- ከደራሲያን አለም የቴሌግራም ቻናል ✍
.
.
"ቁልፍህን ይዘሀል አደል ኤፊ?"
"የምን ቁልፍ?"
"የባጃጇን ነዋ ረስተህ እንዳትወጣ ብዬ ነው"
"እንዴ ገና አልነቃህም ልበል ? እየቃዥህ ነው እንዴ አንተ ልጅ ረስቼ ብወጣስ በምን አስነስቼ እነዳለሁ?"
"አቦ ታድያ ተመልሰህ ቁልፉን ለመውሰድ እንዳትደክም ብዬ ነዋ"
"እዚሁ ግቢ በር ላይ ነች እኮ ባጃጇ የት ያደረች መስሎህ ነው? እዚሁ ገኒ ሱቅ በር ላይ እኮ ነው ያሳደርኳት"
"ሀይ እዚሁ ነች እንዴ?" አለና ትንሽ ቆይቶ ደግሞ
"መንጃ ፍቃድ ዋሌት ገለመሌህንስ ይዘሀል አደል ኤፊ?" አለኝ። "አዎ ይዣለሁ "አልኩት ሳቅ እያፈነኝ።
ዝም አለና ልክ ልወጣ ስል ጠብቆ
" ምንም አረሳህም አይደል ኤፍዬ መታወቂያ እና ሌሎች የሚያስፈልጉህን ነገር በሙሉ ይዘሀል ?" ሲለኝ በጤናው አልመስልህ አለኝ።ዛሬ ለሊቱን ሙሉ በህልሙ እኔ እቃ ረስቼ ስወጣ ያየም መሰለኝ።
"ቆይ አንተ ከመች ወዲህ ነው እኔ መታወቂያ መንጃ ፍቃድ ረስቼ እንዳልወጣ ማሰብና ማስታወስ የጀመርከው"
"ዛሬ ብጀምርስ ምን ችግር አለው"
"ምንም ችግር የለውም ኪያ ፣ አንተስ ጭንቅላትህን ይዘኸዋል አይደል?"
"ማለት?"
"አይ ያው በትንሹም ቢሆን ለማሰብ ይጠቅምሀል ብዬ ነው ፣ረስተኸው እንዳትወጣ እሺ" ብዬው እየሳቅኩ ወጣሁ።
ቁርስ በልቼ ፣ ፀጉሬን ተስተካክዬ ስመለስ አራት ሰአት ሆኗል።
ቃልዬ ጋር ተገናኝተን ወደ ሀረር ለመሄድ የቀረችኝ አንድ ሰአት ነች። ቃልዩ ጋር ደውዬ ልትወጣ እየተዘገጃጀች እንደሆነ አረጋገጥኩ።
ገላዬን ተጣጥቤ ልብስና ጫማዬን ቀያይሬ ለመውጣት ወደቤት እየሄድኩ በር ላይ እንደደረስኩ እኔና ኪያ ተከራይተን ከምኖርባት ግቢ ፊት ለፊት ካለችው ሱቅ
"ኤፊ ፣ ኤፍሬም " ብለው ተጣሩ ባለስቋ ገኒና ሱቁ በር ላይ የቆመ አንድ ተስፋዬ የሚባል የኪያ ጓደኛ ።
"አቤት ምነው ?" አልኳቸው በሩቁ።ባለሱቋ ገኒ የታላቅ እህቴ እኩያ ነች ። ከታላቅ እህቴ ጋር አብረው ነው የተማሩት። ና አንዴ አለችኝ በምልክት።
እኔ ልቤ ተሰቅሏል ምን ፈልገው ነው የሚጠሩኝ ? እያልኩ ጠጋ ብዬ
"ምነው ፈለግሽኝ ገኒ ?" አልኳት። ከተስፋዬ ጋር ተያዩ እና ዝም አሉ። ግራ ገባኝ
"ምንድን ነው? ለምን ጠራችሁኝ " አልኳቸው ሁለቱንም በየተራ እየተመለከትኩ።
"ኤፊ ምነው ዛሬ ስራ የለም እንዴ?" አለኝ ተስፋዬ።
"እንዴ ይህንን ልትጠይቁኝ ነው የጠራችሁኝ ?"
"አይ አደለም ፣ ኣረ አይደለም " አሉኝ በየተራ አሁንም እየተያዩ።
"እህ እና ምንድን ነው ?"
"አይ ወደቤት ልትገባ ከሆነ ቤቱ ዝግ ነው"
"ምንድን ነው እየቀለድክ ነው ተስፋዬ ዝግ ቢሆንስ የቤቱ ቁልፍኮ እኔም ጋር አለ"
"አይ ኤፍዬ ከውስጥ ነው የተዘጋው ኪያ ውስጥ ከሰው ጋር ነው ያለው እንግዳ አለበት ኪኪኪኪ" አለች ባለስቋ ገኒ።
"ገ. ባ. ኝ " አልኳት ፈገግ ብዬ ።
ተያይተው እሷ ስትስቅ ተስፋዬ ፊት ላይ ግን ፈገግታ ሳይሆን ጭንቀት ነበር የሚነበበው።
"ኪያ ጥዋት ስወጣ ያለወትሮው እቃ ረስቼ እንዳልወጣ አስታዋሽ የሆነበት ሚስጥር ተገለጠልኝ"
ስል ገነት "ኪኪኪኪኪ እቃ ረስተህ እንዳትመለስ እያሳሰበህ ነበር አይ ኪያ ይገርማል"ስትል
"አቦ ገኒ ደሞ ተያ ነገር አታጋግይ " አላት ተስፋዬ።
"ስለምን ነገር ማጋጋል ነው የምታወራው ፣ ለማንኛውም እኔ ልብስ ቀይሬ ልወጣ ነው ብዙ አልቆይም"
ብያቸው ልሄድ ስል
"አይ አትሂድ ይቅርብህ ኤፊ ብትደውልም አያነሳም ብታንኳኳም አይከፍትልህም ልብስ ለመቀየር ከሆነ የምትገባው ይቅርብህ ፣ ትርፉ መቃቃር ነው" እያለ እንዳልገባ ሲሞግተኝ ጤነኛ መስሎ አልታይህ አለኝ።
"ማነው ውስጥ ያለው ኪያ አይደል እንዴ? ማለቴ ከማንም ጋር ይሁን ግን ኪያ ነው ውስጥ ያለው አይደል?"
"አዎ እሱማ ኪያ ነው ሌላ ማን ይሆናል"
"እና ታድያ ምን እያልከኝ ነው ለምንድን ነው የማይከፍትልኝ ልብስና ጫማዬን በር ላይ ሆኜ እንዲያቀብለኝ መንገር እንጂ መግባት አልፈልግ"
" በሩን ከፍቶ እንደማያቀብልህ እርግጠኛ ስለሆንኩ ነው" ብሎኝ እርፍ ። ብልጭ አለብኝ።
"ቆይ ውስጥ ከማን ጋር ነው ያለው?"
"ከሴ ጋር"
"እና ከሴት ጋር ቢሆንስ ታድያ ቆይ ማነች ሴቷ እኔ አውቃታለሁ?" ስለው ለኔ መልስ ሳይሰጠኝ ልንገረው አልንገረው በሚል ዳይለማ ውስጥ በገባ ስሜት እንዴ እኔን አንዴ ከሳቋ ጋር የምትታገለውን ገነትን ሲመለከት ኪያ ከማን ጋር እንደሆነ ገባኝ።
"ተወው አትንገረኝ ከማን ጋር እንዳለ ገብቶኛል ፣ ከመክሊት ጋር ነው አይደል?"
"አዎ ኤፊ " አለኝ ፈራ ተባ እያለ።
"እንኳን መክሊትን ዘር ማንዘሮቿን ይዞ ቢጋደም ለደንታው ነው እኔ ገብቼ ልብሴን ወስዳለሁ ሳንኳኳ አይክፈትና እንትያያለን እንግዲህ!" ብዬ ልሄድ ስት ክንዴን ያዝ አድርጎ
"ኤፍሬምና ኪያ በሴት ተጣሉ ሲባል አይደብርም ኤፊ ፣ ልብስ መቀየሩ ይቅርብህ አትግባ"
" ሀ••••ይ አቦ ልቀቀኛ እንግዲህ አታበሳጨኝ ከመክሊት ጋር ስለሆነ ነው ከሱ ጋር የምጣላው ዝም ብለህ በማታውቀው ነገር ውስጥ ገብተህ አትንቦጫረቅ ልቀቀኝ አቦ"
ስለው ጭራሽ ወገቤ ላይ ተጠምጥሞ " ኤፊ ኤፊ የለበስከው እኮ አፖስቶ ነው በቃ ዛሬ ቅዴ ቢሆንም በዚሁ ልብስ ብትውል ብዙ አያሳጣም ልጅቷም ኪያም ከሚደብራቸው"
ሲለኝ ከኪያ በላይ በማያገባው ገብቶ የሚንዛዛብኝ ጓደኛው ደሜን አፈላው።
"ተስፋዬ የምሬን ነው ከኪያ ጋር ሳይሆን ካንተ ጋር ልጣላ ነው ፣ ሰአቴን አትግደልብኝ ፣ አሁን ትለቀኛለህ አትለቀኝም?"
"አለቅህም ኤፊ" ሲለኝ ..ትዕግስቴ በዚህ መሀል ባለስቋ ገነት ከሱቅ ወጥታ መሀላችን ገባች።
"ኤፊዬ በሱም አትፍረድ እንዳትጣሉ ብሎ እኮ ነው ፣ አንተ ደሞ እላዩ ላይ እንደባብ ተጠምጥመህ ነው እንዴ እንዳይገባ የምታደርገው ኧረ ትገርማለህ" እያለች አላቀቀችኝ።
"ኤፍዬ እንደድሮው በረባ ባረባው በየመዳው መጣላት እንደተውክ አውቃለሁ ፣ ብትሄድም እንደማትጣላው እርግጠኛ ነኝ ግን ኤፍዬ የግድ አሁን ገብተህ ልብስህን መቀየር አለብህ?"
"አዎ ገኒ ዛሬ ስራ አልሰራልም ሌላ ፕሮግራም አለኝ አሁኑኑ ልብሴን ቀይሬ መሄድ አለብኝ " አልኳት ሰአት እያየሁ አራት ሰአት ከሀያአምስት ሆኗል።
"ከልጅቷ ጋር ስለሆነ አልተናደድክም አይደል ኤፍዬ?
"ኧረ ገኒ ምናገባኝ እና እና ነው የምናደደው? ዛሬ ነው እንዴ ኪያ ከመክሊት ጋር የጀመረው ቆየኮ፣ የዚህ ድርቅ ማለት ነው እንጂ የገረመኝ እኔ ስወጣ ትገባለህ ኤፍሬም እንዳይመጣብን ጠብቅልን ብሎሃል እንዴ? ወዳ ከተደፋች እንኳን አንተና ኪያ ስትፈልጉ የገራዥን ወንዶችን በመሉ አስለፋችሁ አስገቡላት አይመለከተኝም ፣ ያንተ ግግም ማለት ግን ያስጠላል እሺ"
ስለው ዝም አለ።
"በቃ ኤፍዬ እራሱ ተስፋዬ ሄዶ ልብስና ጫማህን ያምጣልህ አንተም እርግጠኛ ነኝ ባታየቸው ነው የምትመርጠው ፣ ሂድ እራስህ ይዘኽለት ና ፣ ንገረው ኤፍዬ እንዲያመጣልህ የምትፈልገውን ልብስና ጫማ!" አለችኝ።
"አሪፍ መላ ነው ገንዬ እንዴት እንደዚህ አይነት ሀሳብ እስካሁን እንዳልመጣልኝ ይገርማል " አለ ተስፋዬ።
"ይገርማል አደል የምትገርመው እማ አንተ ነህ። አንተ እንድታመጣልኝ አልፈልግም እራሴ ሄጄ ነው የምወስደው...።
ክፍል 29 እሁድ ጠዋት 4:00 ይለቀቃል🌹
https://vm.tiktok.com/ZMhUh1Ynb/