The Home of all የሁሉም ቤት


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha


Well come to the home of all in this channel all things about human being life post every day
* Motivate for free
* learn for free
* earn more for free
Buy ads: https://telega.io/c/+LiBy-b_3bjIyMjk0
══════❁✿❁═════════

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Statistika
Postlar filtri


♥️ ተማሪዋ ♥️ ...
           .
           .
🌹...ክፍል 11...🌹
.
.
Notice :- እውነተኛ ታሪክ ነው!

ነፍሷን ይማረው እና እማዬ•••••" ኪኪኪኪ ኤፊዬ ቅናተኛ ነው። ልጅ እያለም መሽቶ በተኛን ቁጥር  አባቱን ተነስ ከማዬ አጠገብ! •••• እማ ከኔ ጋር ብቻ ነው የምትተኛው! ••• ውረድ ካልጋው ላይ እያለ ይጎትተው ነበር!" እያለች ብዙ ግዜ ታወራ ነበር ።
"አቦ ተያ እማዬ ደሞ!" አላለሁ እቤት ውስጥ ያለውን እንግዳ፣ ታላቅ እህቴን እና  አባዬን በፈረቃ እየተመለከትኩ።

ኤፍዬ ሙት እውነቴን እኮ ነው ኪኪኪኪኪ ለብዙ ግዜ አባትህ አንተ ካልተኛህ በቀር አጥገቤ ድርሽ አይልም ነበር ኪኪኪኪ ይህ የሁሉም ልጅ ባህሪ እኮ ነው ኤፍዬ ያንተ ግን ጫን ያለ ነበር ትልቅ ሆነህም ላንተ ሳይገዛ ለህትህ ልብስም ጫማም ከተገዛ መች ታስደርጋታለህ  አይ ኤፍሬሜ !" ትላለች።
አንድ እህት ነው ያለኝ።  በሰባት አመት ትበልጠኛለች። እማ ልክ ነች እቀናለሁ  ቃልዬ ለምን ታስቀናኛለች ••••? ለምንድን ነው ሁሉንም የሚደወሉላትን ስልኮች አጠገቤ እያናገረች  ከሁሉም በተለየ ሁኔታ እኔ አጠገብ ሆና የማታወራው አንድ  ስልክ የኖራት•••። የደዋዩን ስም አይቼዋለሁ። ዛኪ ብላ ነው የመዘገበችው።
ዛኪ በሚል ስም የሚደወልላትን ስልክ አንድም ቀን አጠገቤ ሆና አናግራ አታውቅም። አጠገቤ ሆና አለማናገሯ ብቻ አይደለም ያንን ስልክ ካወራች በኋላ እንደምትቀየረም አስተውያለሁ። እየሳቀች የነበረችው ልጅ ያንን ስልክ
አናግራ ስትመለስ ሳቋ ብቻ ሳይሆን  መረጋጋቷም ጠፍቶ ድውክውክ ትላለች። ምነው ስላት መልሷ ምንም••• ምን ሆንኩ?  ነው። ምን ሆንሽ እንደምላት ግራ ይገባኝና ዝም እላለሁ። መጀመሪያ የመሄድ ሀሰብ ያልነበራት ልጅ አብረን ልናመሽ ከተነጋገርን በኋላ ያ ዛኪ የተባለ ሰው ከደወለ በቅፅበት ውስጥ  ልሂድ በቃ ኤፍዬ ብላ ለመሄድ የምትነሳው ነገር ደግሞ ይበልጥ ያናድደኛል።ቢሆንም ቃልዬን አፈቅራታለሁ።

ቀኑ እሁድ ነው። የተኛሁበት ክፍል ገና በጥዋት ሲንኳኳ ነበር እህቴ እንደሆነች ያወቅኩት። በባጃጅ ስራው በየሳምንቱ የሚጣል እቁብ አለ። ከቃልዬ ጋር ከመተዋወቃችን በፊት አንድ ቀንም አጉድዬ አላውቅም እንደውም ከሚፈለገው በላይ አጠራቅሜ በየሳምንቱ ቅዳሜ ማታ ወስጄ ለህቴ እሰጣታለሁ ። ወላጆቻችን በሂወት ስለለሉ ከህቴ ጋር ነበር የምኖረው ይህን ስራ ስጀምር ነው አንድ ክፍል እዛው ሰፈር ውስጥ ተከራይተን ከጋደኛዬ ጋር አብረን መኖር የጀመርነው። አስራ ሁለተኛ ክፍል ተፈትኜ ውጤቴ ዩንቨርስቲ ለመግባት ባያስችለኝም በማታው መርሀ ግብር እዛው ድሬ ዩንቨርስቲ ከፍዬ ላስተምርህ ስትለኝ አልፈልግም ባጃጅ ግዢልኝ ብዬ ነው ያስገዛኋት።
ቅዳሜ ማታ ከኔ ብሩን ትቀበል እና እሁድ ጥዋት ወስዳ ትጥላለች። ትናንትና ፣ ቅዳሜ ማታ ግን አልሄድኩም ብሩንም አልሰጠኋትም። ትናንት ብቻ አይደለም ለተከታታይ አራት ሳምንታት የቁቡን ብር እየናድኩት ስለሚጎድል እህቴ ጋር ሳልሄድ ድምፄን አጥፍቼ ገባና ተኛለሁ። እሁድ ጥዋት ትመጣለች ።
"ስላልሞላልኝ እኮ ነው ዝም ያልኩሽ እቴትዬ!" ስላት•••
"ምነው ኤፍዬ •••? ሰሞኑን ስራ የለም•••? ነው ባጃጇ ረብሻህ ለገራዥ ወጪ አወጣህ•••?" ትለኛለች ።
"አዎ እቴትዬ " እላታለሁ። ያለውን ትቀበለኝ እና ከራሷ ሞልታ እቁቡን ትጥላለች። እውነቱ ግን ባጃጇ ምንም አለመሆኗ ገራዥም አለመግባቷ ነው። የታመምኩት እኔ ነኝ። ከህመሜ የምትፈውሰኝ መካኒኳ ደግሞ ቃልዬ ናት።
እሷን ሳገኛት አይደለም የእቁቡን ብር ባጃጇንስ  ባጠፋት መች ልክ ያልሆንኩ መች ያጠፋሁ ይመስለኛል •••? ብዬ ለ እቴትዬ አልነግራት  ነገር የማይባል የማይነገር ሆነብኝ።
ዛሬም በጥዋት የመጣችው ያንኑ መከረኛ የቁብ ብር ልጠይቀኝ ነው። ኪሴ ውስጥ ያለው ከሚያስፈልገው ግማሹ ነው።  በሩን ደጋግማ ስታንኳኳ እንዳልሰማሁ ሆኜ ተኛሁ። ከተኛ የማይሰማው ጓደኛ እንዴት ዛሬ እንደሰማ እንጃለት ብቻ ተነስቶ ከፈተላት።
"ተኝቷል እንዴ•••? ቀስቅሰው እና የቁቡን ብር ይዞልኝ ይምጣ እሺ ኪያዬ ድስት ጥጃለሁ አሁኑኑ ቀስቅሰው!" ብላው ሄደች።
" እሺ!" ብሏት ዘወር ሲል ተነስቼ ፍራሼ ላይ ቁጭ ማለቴን ተመለከተ።
"እንዴ •••••? እየሰማህ ነው እንዴ ዝም ያልካት ኤፊ••••?"
"እንኳን እኔ አንተም ሰምተሀል እንቅልፎ!  " አልኩትና  ቀጠል አድርጌ " ባክህ የቁቡን ብር ረሚም አድርጌዋለሁ ለዛ ነው " አልኩት።
"አንተ ልጅ ግን ምን ጀመርክ ስራ ለጉድ እየሰራህ ነው ባጇጇ ለስከንድ ገራጅ ገብታ የማታውቀውን ገራጅ ገባች ምናምን እያልካት ነው ኧረ ይደብራል ኤፊ !"
"ዝም በል ወደዛ ! ወሬህን ተውና ይልቅ ብር ካለህ አበድረኝ ሞልቼ ልስጣት!" አልኩት ። ሰጠኝ ። ሰጠኋት።
ከቃልዬ ጋር ሰኞም ማክሰኛም ተገናኝተናል ። ዛሬም ምርጥ ቦታ ወስጄ ምሳ ልጋብዛት ተቀጣጥረናል። እየመጣች ነው ። እኔም ወደዛው እየሄድኩ ነው።
ተገናኝተን ምሳ እየበላን እኔ የባጥ የቆጡን ሳወራ እሷ እንደሁልግዜው ስትስቅ ቆየንና በመሀል ••••
"ቃልዬ !" አልኳት።
"ወዬ ኤፊ!"
"አንድ ነገር ልጠይቅሽ•••?"
"ለምን አንድ ብቻ  ••••? ሁሌ አንድ አንድ እያልክ ከምጠይቀኝ ሰብሰብ አርገህ በጅምላ ብጠይቀኝ አይሻልም ኤፊዬ••••?"
"እባክሽ አትቀልጂ ቃል•••?"
"እሺ ምንድን ነው•••?"
"ምኑ•••?"
"ጥያቄህ ነዋ!"
"እ•••••ማለት •••? ቃዬ ምን መሰለሽ ••••እኔን የሚሰሙኝን ስሜቶች ማለት እኔ ስላንቺ የሚሰሙኝን ስሜቶች አንቺ ጋር በከፊል እንኳን ያሉ ይመስልሻል•••?"
"ሰው እንዴት አንድ አይነት ስሜት ይሰማዋል አንተም የራስህ እኔም የራሴ!"
"እኔማ የኔ አይደለሁም!"
"እና የማን ነህ?"
"ያንቺ!" 
"ኪኪኪኪ እኮ አንተ ለኔ የሚሰማህ ስሜት እኔ ላንተ ከሚሰማኝ ስሜት ጋር አንድ መሆን አለበት•••?"
"እንዴት ምን ለማለት ፈልገሽ ነው?"
"እኔ እንጃ!"
"እሺ እሱን ተይው ቆይ ትወጂኛለሽ •••? ማለት ታፈቅሪኛለሽ•••?"
"ኪኪኪኪኪ•••••"እየፈጩ ጥሬ!"  አለች አያቴ!"
"አያትሽ ደሞ ምን ነካቸው"
"ምንም!"
"እቦ ታድያ እየፈጩ እንዴት ጥሬ ይሆናል•••••?  ከተፈጨ ዱቄት አይደል እንዴ የሚሆነው!"
"ኪኪኪ •••ጥሬው ያንተ ቢጤ ሆኖ ይሆናላ!"
"ቢጤ••••! ምንድን ነው ደሞ ቢጤ••••?"
"ካካካካካካካካ ኧረ በጌታ አታዝገኝ ኤፊዬ!"
"አንዴ ጥሬ አንዴ ቢጤ እያልሽ እየተሳደብሽ ያለሽው እኮ አንቺ ነሽ ቃልዬ!"
"ለምን ሰድብሃለሁ ኤፍዬ በጭራሽ አልሰደብኩህም ግን ኤፊ እኔ ካንተ ጋር ሁሌ የምገናኘው እና አብሬክ የማሳልፈው ምንህ ስለሆንኩ ነው•••?  ከአንደበት በላይ እኮ ተግባር ነው ለእውነቱ የሚቀርበው አይደለም እንዴ ኤፍዬ•••? ካልነገርኩህ አታምንም•••?"
"ብትነግሪኝስ ምን አለበት አያስከፍል ቃልዬ! "
"እሺ ወድሃለሁ!"
"እሺ ወድሀለሁ አልሽ እህህ በጣም ደስ ይላል!"
"እንዴ እጠላሃለሁ አላልኩህ ለምን ደስ አይልም•••?"
"አይ አባባልሽ ከውስጥ ተቀድቶ በወጣ ስሜት ሳይሆን ለጥያቄዬ መልስ ለመስጠት ያህል የተባለ መስሎ ስለተሰማኝ ነው!" ስላት ፊቷን ቅጭም አርጋው ትክ ብላ ስትመለከተኝ ቆየችና •••
"ኤፊዬ!"
"ወዬ ቃል!"
"ምንድን ነው ማወቅ የፈለከው•••?"
"እኔን የሚሰማኝ ሁሉ አንቺን እንደሚሰማሽ?
" ለምሳሌ ምን•••?"
ከ 20 ላይክ ቡኋላ ክፍል 12 ይለቀቃል


♥️ ተማሪዋ ♥️ ...

🌹...ክፍል 10...🌹

Notice :- እውነተኛ ታሪክ ነው!

እያልኩ ከግቢያቸው በር ላይ በሀሳብ መወዝወዝ የጀመርኩ ሳይታወቀኝ ሰፈር ደረስኩ።
ውስጤ ሌላ ኤፍሬም ያለ እስኪመስለኝ ከትናንት ማታ ጀምሮ ቃልኪዳን አምናህ ነውና የተኛችው ጫፏን እንዳትነካት እያለ ሲሞግተኝ የነበረ አንድ ሌላ ስሜት እኔ ያሻኝን አስቤ ፍቅርን ከስሼ እስካበቃ በጥሞና ሲያደምጠኝ ቆየና  እንደጭረስኩ  ድንግገት ተከስቶ •••
የፈለገ ቢሆን ማታ አግኝተኻት ጥዋት አፈቀርኩሽ ! የኔ ሁኚ ስትላት ማመን ቢከብዳት ጭራሽ ሹፈት እና ስላቅ ቢመስላት በሷ አይፈረድም። አንተም አሁን ውስጥህ የተቀጣጠለው ስሜት በውሃ የሚጠፋ ግዚያዊ እሳት ይሁን ምንም የማያጠፋው እውነተኛ ፍቅር ለመለየት ግዜ ያስፈልግሀል።
ምን አጣደፈህ•••? እውነቷን ነው እኮ ቃል •••በጣም ተጣደፍክ እኮ! ቆይ ያንተ ካላት የት ትሄዳለች•••? ተረጋጋ ኤፊ ተረጋጋ •••እያለ ሲሞግተኝ ጆሮዬን አልይዘው አልደፍነው ነገር ንግግሩ  ከውስጤ እንጂ ከደጅ አይደለምና ተቸገርኩ።
አይ ቃል እሷ ጨቀጨከኝ ትላለች ። እኔ ኤፍሬም አንድ ሆኜ ሳለ እኩል ሁለት ቦታ ሰንጥቃ ከራሴ ጋር እያጨቃጨቀችኝ እንደሆነ አንድ ቀን ይገባት ይሆናል እያልኩ ባጃጄን በር ላይ አቁሜ ገባሁና ፍራሼ ላይ ተጠቅልዬ ተኛሁ።

እኔና ቃል ከሷ ካልመጣና ግድ ካልሆነብኝ በስተቀር በስተቀር በየቀኑ አገኛታለሁ። አብረን የተወሰነ ሰአት አሳልፈን እንለያያለን።
ከዛች ቀን በኋላ በየቀኑ ሁሌም ባገኘኋት ቁጥር •••እንደማፈቅራት፣ ቀሪ ህይወቴን በሙሉ ከሷ መለየት እሷን ማጣት እንደማልፈልግ ስልነግራት የመሸም የነጋም ቀን የለም።የሷ መልሶች ግን  እጥር፣ ቁጥብ ያሉ ናቸው። ቃልዬ የውስጧን ስሜት ዘክዝካ በግልፅ የማትናገር ልጅ ነች ። ባለፉት ሁለት ወራት ውስጥ ከአንደበቷ ይልቅ ሁኔታዋ  አስተያየት እና ስሜቷ ነበር የኔ እንደሆነች የሚነግረኝ።
የኔ ፍቅር ስላት ያንተ አይደለሁም የእናት እና የአባቴ ነኝ ማለቷን ትታ ወዬ ኤፍዬ ማለት የጀመረችባትን ቀን መቼም አረሳትም ። እንደዛ ማለት ከጀመረች ሁለት ሳምንት ሆናት። ቢሆንም የፍቅር ጥያቄህን ተቀብያለሁ ፣ ያንተ ሆኛለሁ፣ ብላ በአንደበቷ እንድትነግረኝ እፈልጋለሁ። በቃ ያንን መስማት እና ማረጋገጥ ሁሌም እፈልጋለሁ።
ቃልዬ አውቃለሁ የኔ ነሽ ግን ከአንደበትሽ መስማት እፈልጋለሁ እባክሽ ንገሪኝና ልቤን አሳርፊያት ስላት •••
"እንዴ ኤፍዬ እቺ ልብህ ዛሬም እየዘለለች ነው  እንዴ ኪኪኪኪኪ" በቃ ትስቃለች ። እኔን እያስጨነቀች መሳቋ ያናድደኝ እና እንደማኩረፍ እላለሁ። ያኔ መለስ ትልና•••
"እሺ ኤፍሬሜ እንድነግርህ ከፈለክ ደግመህ ጠይቀኝ?"
"ምንድን ነው እምጠይቅሽ?"
"በቃ የባለፈው ጥያቄህ ግዜ ስላለፈበት አሁን ያለህን ስሜት ትክክለኛውን በደንብ ንገረኝና ድጋሚ ጠይቀኝ !" ትለኛለች።
የልቤን ያንጀቴን ፍቅርና መውደዴን ፣ ስስይና ናፍቆቴን ሁሉ አንድ ባንድ ስነግራት ምስጥ ብላ ስታደምጠኝ ትቆይና •••
"እ ንገሪኛ •••?" ስላት።
" አይ  ኤፍዬ•••••" ትልና ያን ፍልቅልቅ ሳቋን በረጅሙ ትለቀዋለች !።
ወንዝ እያሳሳቀ ይወስዳል እንዲሉ እሷ እየሳቀች እኔ አበቃልኝ።
አይደለም ገንዘብ እና ጉልበቴን ፣ አይደለም ሀሳብ እና ማንነቴን ነፍሴን እስከመስጠት የምሳሳላት የልቤ ንግስት ሆና አረፈችው።
እሷ አጠገቤ ስትኖር እና ሳትኖር ያለኝ ማንነት ተራራቀ። ሲላት ብዝት ትልልኝና በፈለኳት ሰአት ሁሉ አገኛታለሁ። ሲላት ጥፍት ፣ ድርግም ፣ ስልካንም ጥርቅም ታደርገውና ነፍሴን በናፍቆት ሲቃ ታዋትታታለች ።ከሁሉም በተለየ ሁኔታ እኔ አጠገብ ሆና የማታናግረው አንድ ስልክ ናላዬን ያዞረው ጀምሯል። ማነው•••?  ምንድን ነው? ለምን እንደሌሎቹ ስልኮች አጠገቤ ቁጭ ብለሽ አታናግሪም ብያት አላውቅም ። ልላትም አልፈልግም። ምክንያቱም ቃልዬ ጨቅጫቃ ወንድ አትወድም።
እሷ ምንም ታድርግ እኔ ውስጥ ያለው ፍቅር  ሀይሉን እየጨመረ ፣ አጠገቤ ስትኖር በፍቅር እያሰከረ፣ ሳትኖር በናፍቆት ልብና አንጀቴን እየቦረቦረ ••••ፍቅር በዘፈን ይብስ እንደሁ እንጂ ላይቀንስ ላይወጣ ነገር•••
ብክን ••• ብክንክን ፣ ብትን••• ብትንትን
ያደርጋል ወይ መውደድ••••?  ያደርጋል ወይ ፍቅር የሚል ዘፈን ••• በየመንገዱ ያዘፍነኝ ጀመር ...

በቃ ከሷ ውጪ ማሰብ፣ ከሷ ውጪ ማውራት፣ እሷ ጋር ካልሆነ ማንም ጋር መሄድ ከማንም ጋር መዋል አስጠላኝ።እሷን ለማግኘት ስል የማታ ስራዬን ወደ ቀን ቀየርኩት።
ለስራ ስወጣ የትራንስፖርት አገልግሎት ለማግኘት በኔ ባጃጅ ላይ በኮንትራትም በመደበኛው ሂሳብም ወደፈለገበት አቅጣጫ ለመሄድ የኔን ባጃጅ  የሚጠቀም ማንኛውንም ግለሰብ በእኩል አይን ማየት ቢኖርብኝም ወደነቃል ዩንቨርስቲ አቅጣጫ የሚሄድ ተሳፋሪ ግን ለኔ ንጉስ ነው። በኮንትራት ሂሳብ ከሆነ ከየትኛውም የድሬ ዳዋ ሰፈር ወደ ግቢ አቅጣጫ ለሚሄድ ሰው ግን ሂሰቤ ቅናሽ ነው።
እዛ ሄጄ ቃልን ባላገኛት እንኳን እዛ አከባቢ ደርሼ ያለችበትን ግቢ አይቼ መመለስ ልዩ ደስታ ይሰጠኛል።
የሚያስተውለኝ ተሳፋሪ የለም እንጂ ቢኖር  ወደ ግቢ ስሄድ የማሳየው ፈገግታ፣ ተሳፋሪውን የማጫውተው ጫወታ፣ባጄጅ ውስጥ የምከፍተው ሙዚቃም ፣ የማስከፍለው ሂሳብም ከሌላው ይለያል። እስካሁን አላጋጠመኝም እንጂ አንድ ቀን ወደ ግቢ ወይም ወደዩንቨርስቲው አከባቢ ያደረስኩት ያው ሰው በሌላ ግዜ  ሌላ ቦታ እንዳደርሰው ቢሳፈር••••" ሹፌር ምነው ባለፈው ስትስቅ ስትጫወት አልነበር እንዴ ዛሬ አኩርፈሀል በሰላም ነው•••? ችግር አለ እንዴ•••? "  ብሎ መጠየቁ የማይቀር ነው።
የምን ችግር እንዲህ ያደረገኝ ፍቅር ነው እለው ይሆን ? የጠየቀኝ የለም እንጂ እለዋለሁዋ! ቃልዬን እንዴት እደማፈቅራት ቀኑን ሙሉ ባወራ መች ይሰለቸኛል። ምናልባት የሚሰማኝ ካልሰለቸው በስተቀር እኔ አይሰለቸኝ።
ነገር ግን አብሮኝ ለሚኖረውና በጣም ለምወደው ጓደኛዬ እስካሁን ስለቃልና ስለኔ ትንፍሽ  አላልኩም።
ብዙ ግዜ በተለይ "  ኤፊ ምነው እንቅልፍ እንቢ አለህ እንዴ?" ብሎ ሲጠይቀኝ  ልነግረው ይዳዳኝና•••
ገና ••••••" አንድ ቀን ሸኝቻት ስንሰነባበት  ፍቅር ሲያደናብረው አቅጣጫ በሳተው ከንፈሬ ከሳምኩት  ከግማሽ ከንፈሯ ውጪ እስካሁን  ምኗንም አልነካሁም" ብዬ እንደተናገርኩ  •••
" እና እስከዛሬ ከቃል ጋር ምንም አላደረጋችሁም ኤፊ ? ፈዘዝክ፣ ቀዘዝክ ፣ቀዘቀዝክ እያለ
ወቀሳ አይሉት ሙገሳ፣ ምክር አይሉት መፈክር ••••  ብቻ •••••" ለተቀማጭ ሰማይ ቅርቡ ነው እንዲሉ የፍቅሬን ክብደት ሳይሆን የኔን ፈዛዛነት እያነሳ የሚያዥጎደጉድብኝን ያን ምላሱን  አስበውና እፈራለሁ። ይቅርብኝ  ቃልዬ እንዴት በፍቅር እንደነደፈችኝ •••? በዚች አጭር ግዜ ውስጥ ከምን ውስጥ አውጥታ ምን ውስጥ እንደከተተች እንኳን ለሱ ላብራራለት እና ላስረዳው ለራሴስ መች በቅጡ ገባኝ ! ይቅርብኝ !" እልና መናገሬን እተወዋለሁ።የውስጤን ትኩሳት ከራሴ ጋር ብቻ  እያወራሁ መታመሜን ቀጥያለሁ።
አይ ቃልዬ እንዴት እንዴት ነው ያፈቀርከሽ ግን•••?  ሰው ለካ እንደዚህ በፍቅር ጨርቁን ጥሎ  ብን••• ብትን •••ብትንትን  ይላል። ግን ህመሙ ደስ ይላል።  እየታመ እየተደሰቱ መታመም የሚቻለው በፍቅር ብቻ ነው። ሀያ አምስት አመት ሙሉ ስኖር ይሄ ፍቅር አላውቀውም።

ቶሎ ቶሎ እዲለቀቅ ላይክ ሼር በደንብ አርጉ ቤተሰብ ♥️👍


♥️ ተማሪዋ ♥️

🌹...ክፍል 9...🌹


Notice :- እውነተኛ ታሪክ ነው!

.
.
"ምንሽን ማለት•••? ኪኪኪኪ ••••ምኔን ማወቅ ፈለክ •••? እርስ በርስ ፣ ባህሪ ለባህሪ እንተዋወቅ ነው የምልህ!"
"አቦ ታድያ እኔ አውቄሻለሁ በቃኝ  አልኩሽ አይደል እንዴ•••ከዚህ በላይ አልፈልግም ••••ነው አንቺ እኔን አላወቅሽኝም!"
"አዎ!"
"አዎ ማለት•••?"
"እንዴ በአንድ ምሽት ውስጥ ስድስት አይነት ሰው ሆነህብኝ እንዴት ብዬ ነው የማውቅህ•••?"
"ምናልሽ ቃል••••? ስድስት አይነት እኔ ስድስት አይነት ሰው ሆንኩብሽ የምርሽን ነው•••?
" እንደውም ቀንሼልህ ነው?"
"ሀዬ ይሁንልሽ እሺ •••• እና ከስድስቱ አይነት የትኛው ተመቸሽ?"
"ኪኪኪኪ•••• ጨወነትህ ብቻ !"
"በቃ በጨዋነቴ ቀጥላለሁዋ ምን ችግር አለው!"
"ሌሎቹንስ እንደምትተዋቸው በምን አውቃለሁ ለምሳሌ ጨቅጫቃነትህን •••••?ኪኪኪኪኪ•••!"
"ቃልዬ ሙች ጨቅጫቃ አይደለሁም!"
"አሁን ምን እያደረክ ነው•••?"
"አሁንማ ከቃል ኪዳን ጋር ቁርስ እየበላሁና እያወራኋት ነዋ ሀይ !"
"ሌላስ•••?"
"ሌላ ምን•••?"
"
እየተጨቃጨክ መሆኑ አልታወቀህም አደል•••? ውጋት ነገር ነህ !፣ ውጋት ሆንክብኝኮ!"
"የምን ውጋት•••?"
"የጎን ውጋት!"
"ቃልዬ ሙች እኔ አልነካሁሽም ! ምናልባት ለሊት ስትከፋፈቺ ብርድ መቶሽ ይሆናል እንጂ እኔ መች ደረስኩብሽ•••? ስላት ያንን ሳቋን ደገመችው። ከቃልኪደን ጀርባ የጠረጴዛ መወልወያ ጨርቅ ይዛ ግርግዳውን ተደግፋ የቆመችው አስተናጋጅ የቃል ኪዳን ሳቅ ተጋባባት መሰለኝ ቃልንም እኔንም እያየች ትስቃለች።
ቃልም እያረፈች ስትስቅ ቆየች። እኔም በልቤ  " በጭቅጭቅ ከልቧ የምትስቅ ሴት አንቺን አየሁ ቃልዬ !" እያልኩ ሳቋን እስከምትጨርስ ጠበኳት••••
" እህም አይ ኤፍሬሜ ••••ቆይ  ተከፋፍተሽ ማለት ምን ማለት ነው ግን •••? እሚከፍት ይክፈትህና!"
"አቦ ካንቺ በላይ የሚከፍተኝ ኬት ይመጣል •••? ልቤንም አፌንም ከፋፍተሽው ይሄው ጨቅጫቃ እስከምባል እያወራሁ አይደል እንዴ!"
"እሺ ያንተ አፍህ ነው የተከፈተው የኔስ•••?"
"ያልተከፈተውን ብጠይቂኝ አይቀልም!"
"እስቲ ቃል ኪዳን ሙች በለኝ•••!"
"አልልም!"
"እና ኤፊ•••?"
"እና ምን•••?
" አየኸኝ••••?"
"መች•••? አሁን•••? ምንሽን•••?
" ተገላልጠሽ ነበር አላልክም ያኔ ነዋ!"
"አዎን በደንብ ነዋ ያየሁሽ!"
"እኮ ምኔን•••?"
"አቦ ምንሽን ልበልሽ•••? ያው ወንድ ልጅ የሚያየውን ነዋ!"
"ወንድ ልጅ የሚያየው የተለየ ቦታ አለ እንዴ •••?"
"ያንን የማታውቅ ሴትስ አለች እንዴ ቃልዬ •••? ያንን ባታ ስለምታውቁማ ነው •••፣ ብቻ ይቅር •••ለምንድን ነው ሌላ ነገር እያስወራሽኝ ዋናውን ጥያቄ የምታረሻሽኝ ቃልዬ•••?
"ብዙ ነገር ስላየኽ ስንቱን እነግራታለሁ ብለህ ነው አደል እሺ ምኔን ነው ያላየኸው•••?
ስትለኝ እኔንም ሳቅ አፈነኝ።
" ካካካ •••ያላየሁትማ ውስጥ ያሉትን ብቻ ነው!"
"ውስጥ ያሉትን ማለት•••?

" ጨጓራ፣ ሳንባ ፣ ልብ ገለመሌሽን ነዋ?" ስላት ትን እስኪላት ሳቀች። እኔ ልቤ ተሰቅሏል። እሷ እያስለፈለፈችኝ ትስቃለች ። በሀይል ስትስቅ አፏ ውስጥ አየዃት እና ••••
"እሄው የቀሩኝንም አሁን አየዃቸው !" አልኳት!
"ሂሂሂሂ ምኖቹን ?"
"ሳንባና ጨጓራሽን እንዲህ እየሳቅሽ ላይታዩ ነው እንዴ አልታይ ያለኝ ልብሽ ብቻ ነው! እሱን ለምን ደበቅሽው ቃልዬ?"
"እሱ ቁልፍ ነው፣ ለመክፈት ብዙ ይቀርሀል ሞክር!"
"ምን ልሞክር ቃልዬ?"
"ሰው የሚልህን ለመስማት ሞክር!"
"እሺ ሰማለሁ እና ምን አልሽኝ•••?"
"አሁን ግዜው አይደለም ትንሽ እንተያይ •••?"
"ምንም የቀረኝ የለም  ሁሉ ነገርሽን አይቼዋለሁ አልኩሽ እኮ ማሬ!"
" ኪኪኪ•••• ሳይፈቀድልህ  ማየትህ ብልግና ነው እሺ ባለጌ!"
እያለችኝ እጇን ለመታጠብ ስትሄድ ተነስቼ እየተከተልኳት •••"ብልግና ከተባለም ያሳየችውም ያየውም ነው ባለጌ በተለይ ያሳየችው!" አልኳት።
"አሁን ትሸኘኛለህ ወይስ ሌላ ባጃጅ ይዤ ልሂድ•••?"
"በቃ ልትሄጂ ነው ቃልዬ ምናለበት የሰቀልሻትን ልቤን አውርደሻት ብትሄጂ!"
"ተሰቅላ ትቆይ እኔ እስካወርዳት ማንም እንዳያወርዳት እሺ!"
"እሺ ቃልዬ ካልሽ ይሁን!" ብያት ወደ ግቢ መጓዝ ጀመርን። መለያየቱ ቅር እያለች ስልክ ቁጥሯን እንድትነግረኝ ጠየካት። ነገረችኝ። ስደውል ዝግ ነው ይላል።
"ዝግ ነው እንዴ ቃልዬ!"
"አዎ ማታ ነው እኮ የዘጋሁት ገና አንተን ሳላገኝህ !"
"ለምን•••?"
"ሌላ ግዜ ነግርሀለሁ አሁን ግቢ እየደረስን እኮ ነው!"
"ሌላ ግዜ ማለት •••? ዛሬ ማታ አንገናኝም እንዴ•••?"
"የጎን ውጋት ማለት ይሄ አደል ታድያ ••••? ውጋት ነገር ነህ በል ቻው አመሰግናለሁ እሺ ኤፊዬ እንደዋወላለን ቻው!" ብላ ጉንጯን ከጉንጬ ጋር አላትማ ስትለየኝ ከመቅፅፈት ነበር  የብቸኝነት ናዳ ሲናድብኝ የታወቀኝ። ግቢ ገብታ ከአይኔ እስክትሰወር ባጉንጯ ዳብሳው የሄደችውን ጉንጬን በመዳፌ ደግፌ ስመለከታት እሷም በተወሰነ ርቀት ልዩነት ዘወር እያለች ታየኝ ነበር።
የማታዋ ቅፅበት ከቃል ጋር ያሳለፍኳት ለሊት ደግማ ደጋግማ  እንድትከሰት እየተመኘሁ ባጄጄን አዙሬ መመለስ ጀመርኩ። አንድ ነገር ትዝታ ለመሆን ከተከሰተ እስኪታወስበት ያለው እድሜ ምን ያህል መሆን እንዳለበት አላውቅም። የኔ እና የቃል ቆይታ  ግን በትዝታ ይሁን በትውስታ እኔን ለመናጥ እድሜና ቆይታ አላሻውም ነበር። ወድያው ፣ ከቃል ጋን ያሳለፍኳትን ፣ ያቺን ቅፅበት እያስታወስኩ ፣  ያለችኝን ነገር በሙሉ ደግሜ ደግሜ እያደመጥኩ ፣ መጓዝ ጀመርኩ..

ቸኮልክ !" አለች ቃልዬ! ...ቆይ እኔ ምን ላድርግ•••? የቸኮልኩት እኔ ነኝ እንዴ•••? እኔ አይደለሁም እኮ •••የቸኮለው ፍቅር ነው። ፍቅር ነው በሰአታት ውስጥ ሁሉ ነገሬን ለመቆጣጠር የተጣደፈው! ፣ ፍቅር ነው እኔን ባንቺ ፍቅር ለማንበርከክ፣ ከነሙሉ ትጥቁ ከነሙሉ ወታደሩ የወረረኝ። ተው እንጂ ፍቅት ምነው ተጣደፍክ•••?
.ገና መተዋወቃችን አይደለም እንዴ•••?
ምነው አድፍጦ ሲጠባበው እንደነበረ ጠላት አጋጣሚውን ስታገኝ ዘለህ አናቴ ላይ ፊጥ ለማለት ተንገበገብክ•••?

ስንቶቹ  አመት ሁለት አመት ፣ አምስት አመት እየተዋወቁ ፣ እየተቀራረቡ ፍቅር በደረሱበት የማይደርስባቸው አሉ አይደል እንዴ•••? ምነው እኔን የመተያያ እና የመቀራረቢያ ግዜ እንኳን ሳትሰጠኝ ባንድ ቅፅበት እጅ ወደላይ ልታስብለኝ ተራሯጥክ •••?
ብዬ እንድነግረው እና እንዲረጋጋ  እንኳን የምናገርበት የማስብበት  እድል ሰጥቶኛል እንዴ ቃልዬ•••? ገና እንዳየሁሽ እኮ ነው መጥቶ የተከመረብኝ።

እኔ ፍቅር ላንተ አዲስ ነኝና እስክንተዋወቅ ትንሽ ግዜ ልስጥህ ብሎኛል እንዴ••?
ጭራሽ ውጋት ሆንክብኝ አለችኝ  አይደል ቃሌ•••? እኔ እሷ ላይ የጎን ውጋት የሆንኩት ፍቅር የተባለ ነገር የልብ ውጋት ሆኖብኝ እንደሆነ እንዴት ላስረዳት•••?

....ቶሎ ቶሎ እዲለቀቅ ላይክ ሼር በደንብ አርጉ ቤተሰብ ♥️👍


#ሶስት_ቦዘኔ_ወንድ_ልጆች_ያሉት_አዛውንት_አባት ለልጆቹ እንዲህ አላቸው…

« ልጆቼ እኔ ከሞትኩ በኋላ ይህን ቤት አፍርሱት ፤ ከቤቱ ስር ለናንተ ብዬ በብረት ሳጥን ያጠራቀምኩት አንጡራ ሀብት አለና ለቀሪ ህይወታችሁ ይሆናችኋል »

ልጆችም ወዲያው ፀሎት ይጀምራሉ...« ፈጣሪያችን ሆይ! አባታችን እንደምታየው አርጅቷልና እባክህ ወዳንተ ጥራው» ። አባትም ከ2 አመት በኋላ ሞተ ። በሞተ በማግስቱ ቤቱን ድምጥማጡን አጠፉትና የተቀበረውን ሳጥን አወጡት። ሲከፍቱት አንዲት ቁራጭ ወረቀት ብቻ አገኙ ፤ እሷ ላይ የተፃፈውን ሲያነቡት…



« ወንድ ከሆናችሁ ያፈረሳችኋትን ገንቧት»   ይላል🙈


ፍቅረኛ የለኝም ብለህ አትዘን 🥺🥺


በፍቅረኛው ምክንያት ጨጓራ የሌለው አለና😜😂


♥️ ተማሪዋ ♥️
🌹...ክፍል 8...🌹

Notice :- እውነተኛ ታሪክ ነው!
.
"ለዚህ ነው ስነርቺኝ ያደርሽው !"
"ኪኪኪኪ እሱን አልክድም አርፌ እንደማልተኛ ታላቅ እህቴ ብዙ ግዜ ትነግረኝ ነበር"
"ሌላስ ማንም ነግሮሽ አያውቅም•••?"
"ሌላ ማለት•••?"
"ሌላ ማለት ••••?ሌላ ማለት••••? እንደኔ ባለ ፍሬ የሆነ ነዋ!"
"ካካካካካካ••••ታናሽ ወንድም ነው ያለኝ ግን አብሮኝ ተኝቶ አያውቅም!"
ስትለኝ •••" በለው በለው እቺ ልጅ ድንግል ነች ማለት ነው•••? እሄ ማለት  ወንድ አላውቅም ማለት አይደል•••?  ነው እንጂ !  ምን ጥያቄ ያስፈልገዋል ፣ ገና ብዙ ስራ አለብህ ኤፍዬ!" አልኩ በልሆሳስ አጎንብሼ ጫማዬን እያጠለኩ።
"እ••? •ምን አልክ ኤፊ•••?"
"ወንድምሽ ካንቺ ጋር ያልተኛው ፈጣሪ ሲጠብቀው ነው፣ በእውነት  እኔ ያልቻልኩትን እርግጫሽን አንድ ፍሬ ልጅ በምን አቅሙ ይቋቋመዋል!"
"ኪኪኪኪ ወሬ አለብህ ለማንኛውም  ወንበሩ ላይ ቁጭ ብዬ ፀጉሬን ሳስተካክል ቁልፍና ቦርሳህን ትራስህ ስር አድርጌልሀለሁ ፣ አገኘኸው••••? " አለችኝ ሁለት እጆቿን ሽቅብ ሰቅላ እየተንጠራራች ። የጇን ወደላይ መወጠር ተከትለው እኔ ላይ የተቀሰሩትን ጡቶቿን ስመለከት ተኩሰው የሚመቱኝ ይመስል ልቤ ፍርስ ስትል ታወቀኝ።
"ጉድህ ፈለ ኤፍዬ ፍቅር መረቡን ጥሎ እያጠመደህ ነው! "አልኩ በልቤ አይኖቼን ጡትና ከጡቷ ስር ባለው ቀጭን ወገቧ ላይ እያንከራተትኩ ሳያት የተሰማኝ ስሜት ከዚህ ቀደም ተሰምቶኝ አያውቅም።  የመረታት ፍርሀት ወረረኝ።
" አንስተኸዋል አደል•••? አለችኝ ደግማ ቁልፍ እና ቦርሳውን ወዳስቀመጠችበት እየተመለከተች።
"አዎ አንስቼዋለሁቆንጆ አመሰግናለሁ!"
"ኧረ ባክህ ••••! ያንተ ቆንጆማ አይደለሁም!"
"እና የማን ነሽ•••?"
"ኪኪኪኪ ለግዜው የማንም አይደለሁም የእናት ያአባቴ ብቻ!"
"እስከመቼ•••?"
"እስከመቼ እንደሆነ አላውቅም!"
"እኔ ግን አውቃለሁ!"
"ምንድን ነው የምታውቀው•••? እስከመቼ እንደሆነ•••?"
"አዎ የኔ እስክትሆኚ ነው!"
"እ. ን. ዴ. ኪኪኪኪ ••• ያንተ እንደምሆን በምን አወቅክ•••?
" ውስጤ ነገረኝ!"
"ታድያ የኔስ ውስጥ ለምን አልነገረኝም•••?"
"ነግሮሻል ባክሽ ለመደበቅ እየሞከርሽ ነው!"
"ተው ባክህ እኔ እስካሁን ምንም የሰማሁት የውስጥም የውጪም ድምፅ የለም!"
"እሄው እኔ እየነገርኩሽ አይደል እንዴ•••?"
"ምን ብለህ•••?"
"የኔ ነሽ ብዬ ነዋ!"
"ኪኪኪኪ ጭራሽ ••••ከየኔ ነሽ የኔ ሁኚ አይቀድምም•••?"
"እሺ የኔ ሁኚ!"
"ለምን•••?"
"እንዴ እንዴት ለምን ስለወደድኩሽ ነዋ!"
"ኪኪኪ ባንድ ለሊት ትናንት ማታ እኮ ደስ አልሽኝ ብቻ ነበር ያልከው!"
"ደስ ያላለ ነገር ይወደዳል እንዴ ቃልዬ ደስ ስላልሽኝ እማ ነው የወደድኩሽ!"
"ትንሽ አልቸኮልክም•••?
"አዎ ቸኩያለሁ ምን ላድርግ ቃልዬ አሁን ተለይተሽኝ ወደ ግቢ ስትሄጂ አንዱ ላፍ የሚያደርግብኝ መስሎ ተሰማኝና ፈራሁ ለዛ ነው!" ።
"ተው ባክህ••••ኪኪኪ•••እስከዛሬ አንዱ ላፍ ያላደረገኝ አንተ እየጠበከኝ ነበር እንዴ?"
"አዎ እየጠበኩሽ ነበር ሁሉም እኮ የግራ ጎኑ ማን እንደሆነች ባያውቅም እየጠበቃት ነው የሚኖረው!"
"ላፍ ያልተደረኩት ነው ያልኩህ ባክህ!"
"ላፍ ያልተደረግሽው እማ ያው ፈጣሪ እኔ እስከማገኝሽ ድብቅ ክልል አድርጎልኝ ነዋ!"
"እንደዛ ካመንክ ታድያ ታድያ አሁን ለምን ፈራህ!?"
"ያው ሰውኛ አስተሳሰቤ ካየሁሽ በኋላ ሀያ አመት ሙሉ ያስቀመጠልኝን በሀያ ደቂቃ የማጣሽ እየመሰለኝ ነዋ!"
"ለዚህ ነዋ ሁሉ ነገርህ ሱሪ ባንገት የሆነው!"
"አቦ ይሄን ያዲስ አበቤዎች ተረትሽን ተይልና ወደዛ የምን ሱሪ ባንገት ነው ሱሪ እማ በእግር እንጂ በአንገት ላይ እንዴት ሆኖ ይሆናል•••? የማይሆነውን!"
"ኪኪኪ አታላግጥ እሺ ! ምን እንዳልኩ በደንብ ታውቀዋለህ ሁሉ ነገርህ ጥድፍድፍ አለኮ!"
"ለምሳሌ ምን••?"
"ምነው ከተገናኘን በኋላ የሆነው ሁሉ በዚች አጭር ግዜ እንዲህ የሚሆን ይመስላል!"
"ምን ሆነና ነው•••?  አብረን እራት ስለ በላን•••?  አብረን አንድ ክፍል  ውስጥ ስላደርን•••?"
"ምነው ከዛ በላይም ፈልገህ ነበር•••?"
"አቦ ብፈልግማ ማን ከልክሎኝ •••? አንቺ•••?"
"በነገራችን ላይ ኤፍዬ ጭዋነትህን ወድጄዋለሁ፣ አመሰግናለሁ እሺ ኤፍዬ!" እያለች ጠጋ ብላ ጉንጬን ሳም ስታደርገኝ ከንፈሬን  አጣብቃ ምላሴን የወሰደችው ይመስል መልስ መስጠት ተስኖኝ ፍዝዝ ድንግዝ ብዬ ሳያት •••
"ተነስ እንውጣ ባክህ ታለምጣለህ አይደል •••? ለምንድን ነው እንደዚህ የምታየኝ•••? ተነስ እንውጣ!" አለችኝ።ሁኔታዬ ግን ማልመጥ ሳይሆን እውነት ነበር።  ለሷ እያለመጥኩ መስሎ ስለታያት  ደስ ቢለኝም ስትስመኝ የተሰማኝ ስሜት ግን የተለየ ነበር እራሴን ታዘብኩት።

እሷ ከፊት እኔ ከጀርባዋ ተከታትለን ከክፍሉ ወጣን። ማታ ያየሁት የቃል ውበት እንደጥዋቷ ፀሀይ ቀስ እያለ የሚፈልቅ፣ ቀስ እያለ የሚሞቅ፣ ቀስ እያለ የሚፈካ ይመስል አብሪያት በቆየሁ ቁጥር ይበልጥ ውብ እየሆነችብኝ ግራ ተጋባሁ ፣ ምናልባት መውደዴ እየጨመረ፣ እሷን የማይበት መነፅርም እየተቀየረ ይሆን•••?

ዛሬውኑ አሁኑኑ የኔ ትሁን አትሁን ቁርጤን ማወቅ ፈለኩ።
ቁርስ አብረን እየበላን ነው።
"ቃልዬ!"
"ወዬ ኤፊ!"
"ቆይ አንድ ወንድ የፍቅር ጥያቄ ለማንሳት ፣ ማለት•••የወደዳትን የኔ ሁኚ ብሎ ለመጠየቅ ቸኮልክ የማይባለው ከተዋወቃት ከስንት ቀን በኋላ ሲጠይቅ ነው•••?"
"ኪኪኪኪ እኔ እንጃ!"
"ካላወቅሽ ታድያ ለምን ቸኮልክ አልሽኝ•••?"
"ስለቸኮልክ!"
"እባክሽ አትቀልጂ ቃሌ!"
"ኤፊ ሙት እየቀለድኩ አይደለም!"
"ለማንኛውም እኔ የልቤን ተናዝዣለሁ አንቺ የማሰቢያ ግዜ ከፈለግሽ እሺ!"
"እእእእእ በችኮላ የተሰነዘረ ጥያቄ ስለሆነ እንዳልሰማሁህ አስበው፣ ለኔ ብቻ ሳይሆን ላንተም የማሰቢያ ግዜ ያስፈልግሀል!"
"ምንድን ነው የማስበው •••? የምን ግዜ•••?"
"እኔን የማወቂያ!"
"ከዚህ በላይ ላውቅሽ አልፈልግም!"
"እኔ ግን እፈልጋለሁ!"
"እሺ የናትሽ ስም ማነው•••?  ስላት ሳቋን ለቀቀችው•

"ምን ላድርግ ቃልዬ ስምሽን ከነአባትሽ ከመታወቂያሽ ላይ አውቂያለሁ፣ የቀረኝ የናት ስም ነው ብዬ እኮ ነው!"
"እህህ አየ አንተ እና የቤተሰብ ስም ማወቅ ታድያ እኔን ማወቅ ማለት ነው ••••? እ ኤፊ የምር እንደዛ ነው የምታስበው•••?"
"ሀይ••••! ታድያ ምንሽን እንዳውቀው ነው የምትፈልጊው?
ከ 50 ላይክ ቡኋላ ክፍል 9 ይለቀቃል🌹


ሚስቶች ተሰበሰቡና እግዜርን ሊያናግሩ ሄዱ አሉ....

እግዜር - ምን ሆናችሁ ልጆቸ

ሚስቶች -መረረን !

እግዜር - ምነው ምን የሚያማርርነገር ተፈጠረ

ሚስቶች - እኛ ሴቶች ጫናው በዛብን አንገፈገፈን እኛ አርግዘን፣ እኛ አምጠን ፣እኛው አጥብተን... አልቻልንም ! ይሄ ጉዳይ ስራ እንዳንሰራ ሆነ ተብሎ ወንዶችን ለመተባበር የተደረገ ሴራ ነው ይስተካከልልን አሉ እያለቀሱ፡፡

እግዜር -ጥሩ! ምን እንዲደረግላችሁ ትወዳላችሁ ታደያ

ሚስቶች -ቢያንስ ከማርገዝ ፣ከማማጥ ወይም ከማጥባት ወንዶች አንዱን የተፈጥሮ ግዴታ ያግዙን

(እግዜር ቅዱስ ገብኤልን ጠራና‹‹ እስቲ ወንዶችን ጥራልኝ ››አለው
ወንዶች ገቡ)

እግዜር - ሴቶቻችሁ ተማረዋል ተመካከሩና ከማርገዝ ፣ ከማማጥ ወይም ከማጥባት አንዱን አግዟቸው ወንዶች ተመካከሩ 9 ወር መሸከም ይደብራል .... ማጥባትማ የባሰ ነው .... ያው ቢያምም ምጥ ይሻለናል አጠር ያለ ሰአት አምጠን ወደድራፍት ቤት በቃ!! ወሰኑ!

እግዜር- ‹‹እንግዲህ ይህ ውሳኔ ከተወሰነበት ቀን ጀምሮ ሴቶች ያረግዛሉ ልክ ምጥ ሲጀምር ያስረገዘው ወንድ ያምጣል !በሰላም ሂዱ›› ብሎ ሸኛቸው !!

ከውሳኔው በኋላ የመጀመሪያዋ እርጉዝ በመንደሩ ስሟ የተጠራ ቆንጆ እና ሃብታም ወ/ሮ ሄለን ነበረች ባለቤቷ አቶ ዘሩ ጋር ያላቸው ፍቅር ሁሉን የሚያስቀና እግዜር ሁሉን ያሟላላቸው የተራበ የሚያበሉ የታረዘ የሚያለብሱ ወዘተ ነበሩ ..... ይህን ደግነታቸውና ፍቅራቸው ነው የአዲሱ ህግ አስጀማሪ ያደረጋቸው ተብሎ በመንደሩ ተወራ ...6..7..8...9 ወር ሞላት ወ/ሮ ሄለን !

ባለቤቷ አቶ ዘሩ ተዘጋጀ የህዝብ ጆሮ አይን አቶ ዘሩ ላይ ሆነ ወንድ ሲያምጥ ለማየት ..... ቀኑ ገፋ ምጥ የለም !ልክ 9 ወር ከ9 ቀን ሆነ ምንም የለም! .... በቀጣዩ ቀን ማታ ይህን ተአምር ሊያይ ግቢውን የሞላው ሰው ሁሉ ግቢው በር ላይ ተንጫጫ ... ምንድነው ብለው ቤት ውስጥ ያሉት ሲወጡ የነወይዘሮ ሄለንን ‹‹ ዘበኛ ምጥ እያጣደፈው ነበር !›› ያስረገዘው ወንድ ያምጥ አልነበር ውሳኔው !

አቶ ዘሩ ማሪያም ማሪያም በሚለው ህዝብ መሃል ‹‹ በማሪያም ውርደት›› ብለው እራሳቸውን ሳቱ!! ሴቶችም ያኔውኑ ማታ ይሄ ውሳኔ ይነሳልን ሲሉ ወደግዜር ቀርበው ጮሁ የሚበዙት ቀናቸው የደረሰ ነፍሰ ጡር ሴቶች ነበሩ!

Via ማራኪ ወግ


♥️ ተማሪዋ ♥️ ...

🌹...ክፍል 7...🌹


ሴቶች በተለይ በመጀመሪያው ቀን በአንደበታቸው እሺ ከማለት ይልቅ በአካላዊ እንቅስቃሴ ፍቃዳቸውን መግለፅ ይቀናቸዋል። ካካሆነም ወንዱ ገፋ አድርጎ እንዲመጣ ይፈልጋሉ።
አየህ ክብር የሚባል ነገር አለ።ዛሬውኑ አግኝተሀት  ካንተ ጋር አንሶላ ለመጋፈፍ ፍቃደኝነቷን በአንደበቷ ትገልፅልኛለች ብለህ ከጠበቅክ ሞኝ ነህ። ሴትን ልጅ አታውቃትም ማለት ነው። ምክንያቱም ተገናኝተን ሀያ አራት ሰአት ባልሞላ ግዜ ውስጥ ጭኔን ብከፍትለት •••ክብሬን የማልጠብቅ ርካሽ ሴት አድርጎ ያስበኛል፣ ይንቀኛል፣ በየአጋጣሚው ካገኘሁት ወንድ ጋር በቀላሉ የምጋደም  ሴት አስርጎ ይቆጥረኛል ብላ ትፈራለች።
ስለዚህ ካንተ ጋር ወሲብ መፈፀም ብትፈልግ እንኳን ይህ ፍርሀቷ ሳትወድ በግዷ እንድትግደረደር ያደርጋታል።
በርግጠኝነት በቀላሉ እሺ ብትልህ አንተም እንደዛ ማሰብህ የማይቀር ነው። ወደድክም ጠላህም የፈራችው ወይ ያልፈለገችው ማድረጉን ሳይሆን እንዲዚህ ማሰብህን ነው። ስለዚህ በአንደበቷ አይሆንም አይደረግም ትልሀለች። ያላት አማራጭ  አንተ ሀላፊነቱን ወስደህ ያሻህን እንድታደርግ ላንተ መተው ነው። እንደዚህ እየተፈታተነችህ ዝም ካልካት ደግሞ ••••ምኑ ቀዝቃዛ ነው ባካችሁ. ፣ በረዶ !  ፣ አፍ ብቻ ነው እንዴ ለካ ያለው፣ ይሄማ አይደለም በውስጥ እግር እና በጣት በክሬንም የሚነሳ አይመስልም ትልሀለች። ነግቶ ከተለያያችሁ በኋላ አይደለም ድጋሚ ልታገኝህ ኤፍሬም ተብሎ የሚጠራ ወንድ በሙሉ የወንድ አልጫ መስሎ ነው የሚታያት። ያንተስ ይሁን ለምን ባንተ ስም የሚጠሩትን ወንዶች ታስንቃለህ•••? ደሞ ወድጃታለሁ የኔ እንድትሆን እፈልጋለሁ ትላለህ ዛሬ እንዲህ የተኛች መስላ እየተገላለጠችና እየነካካችህ ወንድነትህን ካላሰየዃት ዘወር ብላ እንደማታይህ አታውቅም•••?
በርግጠኝነት አንዴ ደፈር ብለህ ብትጀምራት እንዴት እንደዚህ ታደርጋለህም ተውም አትልህም።
ብትልህም ለይስሙላ ስለሆነ•••ምን ላድርግ ቃልዬ መብራቱ አይጥፋ ያልሽው አንቺ ነሽ ፣ መብራት ካልጠፋ እንቅልፍ አይወስደኝም እኔ ሳልተኛ አንቺ ተኝተሽ መገላበጥ ሳይሆን መከረባበት ጀመርሽ ፣ ወደ ግራ. ስዞር ወደ ግራ ወደ ቀኝ ስዞር ወደቀኝ እየተከረባበሽ ስትገላለጪ ሳልተኛ አይኔን ጨፍኜ መቆየት ደከመኝና አየሁሽ ፣ አማትቤ ጣራው ላይ አፈጠጥኩና አንቺን ላለማየት ሞከርኩ ፣ ወድያው እግሮችሽን እያፈራረቅሽ የማይሆን ቦታ ትነካኪኝ ጀመር ፣ አልቻልኩም ከዛ በኋላ እንዴት ዞሬ አንቺ ጋር እንደመጣሁ እንዴት እንዳደረግን ትዝ አይለኝም አንቺም እስክጨርስ ጠብቀሽ ምን እያደረክ ነው ማለትሽ ልክ ነው ቃልዬ•••? እኔኮ ዝም ስትይ የተመቸሽ መስሎኝ ነው ትላታለህ ።
በቃ አለቀ ጉደኛ ነህ ኤፊ ከማለት በስተቀር ምንም ክፉ ነገር አትናገርም። ተነስ ! ልብስህን ወለቅ ወለቅ አድርግና ብድግ አድርገህ አለሟን አሳያት። " አለኝ ። ሁለቱንም ሀሳብ እያፈራረቀ የሚነግረኝ ውስጤ ነው ። እውነት አሁን ደፈር ብዬ ብጀምር ዝም ትል ይሆን •••? ብዬ ሳስብ ያው መከረኛ ገረዥ የሚሰራ ጓደኛዬ እዛው የሚሰራበት ገራዥ መኪናውን ሊያስጠግን ከመጣ የአይሱዙ ሹፌር ሰማሁ ብሎ  የነገረኝ ነገር ትዝ አለኝ•••
ሹፌሩ ሚስቱን ጋቢና ረዳቱን ከላይ ብርድ ላይ ጭኖ በለሊት እየተጓዘ ሽፍታ ያጋጥመዋል። ሽፍቶቹ የሚፈልጉትን ወስደው ብቻ አልሄዱም የሹፌሩን ሚስት አስገድደው ባሏ እያየ ከረዳቱ ጋር ወሲብ እንድትፈፅም ያደርጋሉ።
ታድያ ሹፌሩ በሌላ ግዜ ይህን አጋጣሚ ለአንድ የቅርብ  ወዳጁ ሲያወራለት •••የገረመኝ ወሲብ ማድረጋቸው ሳይሆን የሚስቴ በርታ እያለች መነቃነቋ ነው!" አለው አለኝ።
እና ቃል ኪዳንም አንዴ ከጀመርኩ በኋላ በርታ እያለችመነቃነቋ ነው!" አለው አለኝ።
እና ቃል ኪዳንም አንዴ ከጀመርኩ በኋላ በርታ እያለች ትነቃነቅ ይሆን•••? እያልኩ ገና ከተጋደምኩበት ቀና ብዬ ጠጋ ስላት  ብንን አለችና ••••" ምነው ኤፊዬ እስካሁን አልተኛህም እንዴ •••?" አለች። አልጋ ልብሱን ጎትታ ከወገቧ በታች እየሸፈነች። ብስጭት ብዬ "ታድያ እንድተኛ ከፈለግሽ ምን ያበላቅጥሻል አርፈሽ አተኝም !" ልላት ምንም አልቀረኝም።
"ኧረ በለው ቆይ አንቺ ግን ዩንቨርስቲ የምትማሪው ካራቴ ነው እንዴ?"አልኳት።
"የምን ካራቴ•••?"
"እህህህ በንቅልፍ ልብሽ ቻይንኛ የመሰለ ቋንቋ እየለፈለፍሽ ስትፈራገጪ ነበርኮ፣ ፊኛዬን ብለሽ ልትገላግይኝ ነው እንዴ•••? ዘለሽ ፊኛዬን ፣ ዘለሽ ፊኛዬን ፣ ሌላ ቦታ አይታይሽም እንዴ•••? ማነች አኮላሽልኝ ብላ የላከችሽ•••?" ስላት••••ፈገግ አለችና •••"ይሄ ሳቅ ይደርልኝ ጥዋት እስቃለሁ፣ ና በቃ እሺ በዚህ ጋር ተኛ፣ ቆይ እንደውም እኔ በዛ ጋር ልሁንልህ !" አለችና  ትራሷን ይዛ ወደኔ በመምጣት አልጋ ልብሱን ተጠቅላላ ሁለት ጉልበቶቿን እንደሚሳኤል በእንብርቴ ትዩዩ ቀስራ በግርግዳው በኩል  ተኛችና •••" ተኛ በቃ ከፈለክ መብራቱንም አጥፋው!" አለችኝ ፈገግቷዋን አሳይታኝ ይኗን እየጨፈነች።
"ቀላል ተኛለሁ እንዴ አንቺም እዛው ከግርግዳው ጋር ተደባደቢ !"እልኳትና መብራቱን ደረገምኩት። ጥዋት ከረፋዱ ሶስት ሰአት አከባቢ ያለንበት ክፍል በሀይል ተንኳኳ!።"ማነው?"  አልኩ ከጥልቅ እንቅልፍ ውስጥ በርግጌ በመነሳት።
" እኔ ነኝ !" አለ የወንድ ድምፅ። ወደ ግራ ስዞር ቃል ኪዳን አልጋው ላይ የለችም። ወደቀኝ ስዞር ማታ ከኪሴ አውጥቼ ወንበሩ ላይ ያደረኩት ዋሌት ቦርሳዬ እና የባጃጄ ቁልፍ ወንበሩ ላይ የለም..
የጉድ ቀን አይመሽም ይባል ነበር ድሮ የጉድ ቀን አይነጋም ሊሆን ነው ዘንድሮ!" እያልኩ ተፈናጥሬ ከአልጋው ላይ በመውረድ በሩን ከፈትኩና •••
•" ምን ነበር•••?"አልኩት።"ሰላም አደርክ•••? አንሶላ አጣቢዋ እኮ ባንኳኳ ባንኳኳ አባ ከና የሚለኝ አጣሁ ስትለኝ ነው እኔ የመጣሁት ። ሶስት ሰአት ሊሞላኮ ነው! ያው እኩለ ለሊት ካለፈ እንደገባችሁ ነግረውኛል፣ ቢሆንም አንሶላው መታጠብ አለበት፣ ለዛ ነው የቀሰቀስናችሁ ይቅርታ!" አለኝ።
"እሺ ችግር የለውም!" ብዬው  ለራሴ" እድሜ ለቃል ኪዳን  መች ውስጥ ገብተን ተኛን እና ነው የምታጥቡት?"  እያልኩ ወደ አልጋው ተመለስኩና ከአልጋው ላይ አንሶላውን ገፍፌ ሳነሳው ዋሌት ቦርሳዬና ቁልፉ ከኔው ትራስ ስር ወደ  መሬት ወደቁ።
አመዱ ቡን ያለው ፊቴ በፈገግታ እንደተሞላ አንሶላውን ሰጥቼው ስመለስ የመታጠቢያ ቤቱን የበር እጀታ ቁልቀል ዘወር አድርጌ ገፋ ሳደርገው ከውስጥ ተከርችሟል።
"አቦ በዚች ሰከንድ ውስጥ ስንት ቦታ ሄድኩ፣ ስንቱን አሰብኩት በፈጣሪ!" እያልኩ አልጋው ጫፍ ላይ ቁጭ እንዳልኩ ብዙም ሳትቆይ ቃልኪዳን እርጥብ ፊቷን በፎጣ እያደራረቀች ወጣች።
"ደና አደርክ ኤፊ ተነሳህ እንዴ?"
"እህህህህ አዎ ተነስቻለሁ ግን ደና አላደርኩም!"
"ኪኪኪ•••ምነው ጥሩ ህልም አላየህም •••? ነው ቅዥቱ አላስተኛ አለህ•••?
" ተይ ባክሽ ••••! ህልምም ቅዠትም የሚኖረው ሲ'ተኛ እኮ ነው ስደበድቢኝ አድረሽ ቤት በኩል ልቃዥ? አሁን እንደወጣሁ ሃኪም ቤት መሄድ አለብኝ!"
"እንዴ ለምን•••?"
"ሁለቱም ፍሬዎቼ ጤነኛ እንደሆኑ ማረጋገጥ አለብኝ!"
"እንዴ ሁለት ፍሬ ነው እንዴ ያለህ? አንድ አይበቃም ሁለት ምን ያደርጋል?"..

ከ 50 ላይክ ቡኋላ ክፍል 8 ይልቃል


የዘንድሮ ሚስት ባሏን ከልቧ የምታዳምጠው
.
.
.
.
ባሏ ከሌላ ሴት ጋር በስልክ ሲያወራ ብቻ ነው😂


ሚስት :- ናዝሬት ልሄድ ነው ምን ላምጣልህ?
ባል:- ቆንጅዬ የናዝሬት ልጅ

ከናዝሬት መልስ👇👇

ባል :- የታለች የናዝሬቷ ልጅ
ሚስት :- 9 ወር ታገስ😁


♥️ ተማሪዋ ♥️
🌹...ክፍል 6...🌹

ባጭሩ እኔ ኤፍሬም ሴት ልጅ ፈልጋና ፈቅዳ ካልሆነ በስተቀር እንኳንስ ገላዋን የቀሚሷን ጫፍም መንካት አልፈልግም ! •••ይህንን ፈርተሽ ከሆነ ከወንበሩ ላይ ንቅንቅ አልልም ያልሽው ስጋት አይግባሽ ። ይልቅ አሁን ተነሽና ገብተሽ ተኚ!" አልኳት። "ኪኪኪኪ ምን ውስጥ ነው የምገባው•••?"
"አልጋ ስር!" "ሂድ ወደዛ ብሽቅ ! ለማንኛውም አንተ እንደዛ አስበኻል ማለቴ ሳይሆን ያው አለ አይደል•••"እያለች  ከወንበሩ ላይ ስትነሳ •••
" በቃ ልተኛበት ወሬ አልፈልግም!" አልኳት ኮስተር ብዬ። "ኧረባክህ  ማን ሲያስተኛህ ፣ገና እናወራለን፣  ደሞ አንጣው አንዱን ትራስ እኔ በዚህ በኩል ነው የምተኛው ፣ ከነ ልብሴ፣  ከላይ ነው የምተኛው ••••" አለችና ። በፈገግታ እያየችኝ አንዱን ትራስ በግርጌ በኩል አድርጋ ወደ መታጠቢያ ቤት ገባች። እኔ በራስጌ እሷ በግርጌ ከነልብሳችን ከላይ ተኛን። መብራቱን ላጠፋው ስል •••"ተወው ይሁን !" አለችኝ።
"እንዳልሽ!"  አልኩና በጀርባዬ ተንጋለልኩ።
"ኤፍ ተኛህ እንዴ?"
"አልተኛሁም!"
"ምነው ዝም አልክ ታድያ•••?
" ተኝቼ!"
"ኪኪኪኪኪ አድርቅ ! አድርቅ ነገር ነህ!"
"እስካሁን ያደረቅኩትን ላርጥበው ስልሽ  እንቢ ያልሽው አንቺ አይደለሽ እንዴ•••? "  ልላት ብዬ ካፌ መለስኩት። ዝም አለች ፣ አተነፋፈሷም ተቀየረ፣  እንቅልፍ ወሰዳት። መተኛት የለም አዋራኝ እያለች ቀድማኝ ተኛች።ምስኪን ለዚቹ ነው ያ ሁሉ ጫጫታ አያልኩ ቀና ብዬ ሳያት  እጥፍጥፍ ብላ ተኝታለች።
ትንሽ ቆይታ መዘረጋጋት ጀመረች። መጀመሪያ አንድ እግሯን እዛው አስቀርታ አንዱን ዘረጋችው። ተጀመረ አልኩ በልቤ። ትንሽ ቆይታ ሁለተኛውን ደገመችው•••ትንሽ ቆይታ እግሯን ከፈተችው። ትንሽ ቆይታ መገለባበጥ ጀመረች። እኔ እስካሁን ከቦታዬ ንቅንቅ አላልኩን እሷ ሶስት መቶ ስልሳ ድግሪ መሽከርከር ጀምራለች። በዚህ ሁኔታ እንቅልፌ እንኳንስ በዛ ሰአት በማግስቱ እራሱ የሚመጣ አይመስለኝም። ወደ ግራ ገልበጥ አልኩና አይኔን ገለጥ አድርጌ  ቁልቁል ስመለከት••••ከአንገቷ በገመድ ወርዳ ፣ ጡቶቿን በቪ ቅርፅ አስጎብኝታ፣ ከጉልበቷ በላይ የምትቀረው ፣ ፣ ከእንብርቷ ተስቦ ወገቧ ላይ የሚቃጠር ሁለት ተንጠልጣይ ገመድ ያላት፣  ቀይ ሮዝ አበባ ጣል ጣል ያለባት ደብዛዛ ነጭ ቀሚሷ፣  እሷ በተገላበጠች ቁጥር ተስባ ተስባ እምብርቷ ላይ ደርሳለች ፣ እግራ ተከፍቷል።  በጠይሙ ንፁህ እና ውብ ገላዋ ላይ በጭኖቿ መሀል ላይ ያረፈውን ደማቅ ቀይ ሽፏኗን ስመለከት እንደስጋቤት አንፖል አይኔ ላይ ተንቦገቦገብኝ።
•••አይኔን ጨፈንኩ ፣ መልሼ ገለጥኩ፣ ከአጠቃላይ የአካል ክፍሌ አብዛኛውን ቦታ የሸፈነ ከባድ ንዝረት ነዘረኝ..!! ይቺ ልጅ ከራሴ ጋር ልታጣላኝ ነው ። እንደዛው ተኝቼ እሷን አለማየትም እሷን እያየሁ መቆየትም የማልወጣው አቀበት ሆነብኝ። ያለው አማራጭ መጀመሪያ እንደነበርኩት በጀርባዬ መንጋለል እና እንቅልፌ እስኪመጣ ጣራ ጣራውን ማየት ብቻ ነው።  እንደዛው አደረኩ። እንቅልፌን ለማምጣት እየታገልኩ  ውስን ደቂቃዎች አለፉ። ልክ እንቅልፌ እንደመምጣት ሲል ብቻ  ገልበጥ ገልበጥ አለችና እግሯን ቀጥታ በእግሮቼ መሀል ለመሀል ልካ  ፈንጂ ወረዳው ላይ ጫነችው። እቺ ናት ጫወታ••••! እቺ ልጅ አርፋ አተኛም ማለት ነው። እዚህ ቤት ውስጥ  ፈንጂ አምካኝ  ከሷ ውጪ አለመኖሩን እያወቀች ፈንጂ ረግጣለች እንግዲህ ሀላፊነቱን እራሷ ትወስዳለች። አይቻት ከምሳሳት ባላያትስ ብዬ ከራሴ ጋር ስታገል ከማየትም በላይ ፈታኝ የሆነ ወረዳ ውስጥ ሰተት ብላ ገብታለች ፣ ከዚህ በኋላ እዚህ ቤት ውስጥ ለሚከሰተው ነገር በሙሉ እኔ ተጠያቂ አልሆንም።
አትንካኝ ያለችው እራሷ ነች።  አትንካኝ ካልሽ አልደፍርሽ እንግዲህ ካልፈለግሽ ይቅራ አልኩ። አሁን በንግግር ተስማምተን የዘጋነውን ጉዳይ በእግር እየነካኩ መቀስቀስ ምን ይሉታል እስቲ።
ይህ  ሰውን  ለስሜትም፣ ለስተትም ፣ ለፀፀትም የሚያነሳሳ ተግባር  አካላዊ ትንኮሳ ካልተባለ ምን ሊባል ነው••? በየሰከንዱ እየተገላበጥሽ እርቃኑን ባስቀረሽው ገላሽ ምክንያት የተጋረጠብኝን ከባድ ፈተና በጀርባዬ ተኝቼ ጣራ ላይ በማፍጠጥ ልቋቋመው ስጣጣር፣ ጭራሽ  በውስጥ እግርሽ ፍሬዬን በግሮችሽ ጣቶች ፍሬኔን እየነካከሽ ሞተሬን እያሞቅሽው እንደሆነ እወቂው  ። "ሆዴ ጭሶ ጭሶ የነደደ እንደሆን •••አለ ሰውየው ። ከዚህ በላይ እንዴት ሆኜ ልተኛላት። ስልጠናው ቅዥት ሆኖበት በእንቅልፍ ልቡ አሳርፍ!!!  ተጠንቀቅ !  እንደተባለ ወታደር እግሬን ገጥሜ አልተኛ እንግዲህ •••እያልኩ  ከጭኖቼ መሀል  የእግሯን አውራ ጣት ይዤ አነሳሁትና  ወደ ጎን አደረኩት። ትንሽ ቆይታ ሌላኛውን እግሯን አነሳችና ባልጠፋ ቦታ እዛው ከምብርቴ በታች ጫነችው። አለቀ ነካክታ ነካክታ አንዱን ኤፍሬም ሀለት ቦታ ከፍላኝ አረፈችው። ሁለት ኤፍሬም ሄንኩ•••ውስጤ በሁለት ተቃራኒ ሀሳቦች ጭቅጭቅ ገጠመ።
አንደኛው ስሜቴ  ዝም ብለህ ለመሳሳት ሰበብ አትፈልግ ባክህ !! ፣ አደብ ግዛ!  ገና ለገና በእንቅልፍ ልባ ስትገላበጥ ነካችኝ ብለህ ከሰው ወደ እንሰሳነት ልትቀየር ይቃጣሀል እንዴ•••? አታፍርም•••? እንቅልፍ የወሰዳት እኮ ስላመነችህ ነው። እግሯን ስትዘረጋ ነካችኝ ብለህ ምን ልትሆን አማረህ•••? አሁን በጉልበትም በምንም ያሻህን አደረክ  ነገ እንዴት ብለህ አይኗን ልታይ ነው•••?  ይልቅ ከወደድካትና አብራህ እንድትቀጥል ፍላጎት ካለህ ስሜትህን ግዛ!። እንደማትነካት ቃል ገብተኽላታል፣አምናሀለች። ለቃልህ ስትታመን ላንተ ያላት አመለካከት ጥሩ ይሆናል። ያለ በለዚያ ስሜቱን መቆጣጠር የማይችል ፣ ሴትን ልጅ ጉልበቱን ተጠቅሞ አስገድድዶ የሚደፍር አውሬ አድርጋ ነው የምታይህ እንኳን ያንተ ልትሆን በሂወት ዘመና ካንተ በላይ የምትጠየፈው ወንድ አይኖርም። ብትታመንላት ግን ይቺ ለሊት የሷን ልብ ለመክፈት እና  ለማሸነፍ  አንዷ ቁልፍ ትሆናሀለች ። ወደሃታል፣ ስለዚህ ማሸነፍ የምትፈልገው ልቧን ነው። ልቧን የምታሸንፈው ደግሞ ስታከብራት ነው። ያለፍቃዷ ገላዋን መንካት ግን ንቀት ነው። አለኝ።
የጋለው ስሜቴ የተቆጣጠረው ሌላኛው ኤፍሬም ደግሞ  በተቃራኒው እንዲህ ይለኛል•••
" አይ ኤፍሬም እውነትም ያ አብሮህ የሚኖረው ጋደኛህ እንደሚልህ አንተ አራሯጭ ነህ እንጂ ሯጭ አይደለህም ። እስከዛሬም ብዙ ሴት ትቀርባለህ ታጫውታቸዋለህ ፣ ታስቃቸዋለህ ፣ አብረኻቸው የተወሰነ ግዜ ትቆያለህ  ፣ ሁሌም እነሱ መግደርድራቸው አይቀርም ፣ ሲግደረደሩ እውነት እየመሰለህ  ምን አስቸኮለኝ እያልክ
ዝም ትላለህ ፣ ሳትነካቸው ለሌላ ወንድ አስረክበህ ትቀመጣለህ ። ከዚህ በላይ ምን አሯሯጭነት አለ።
አሁን ባንተ ቤት ቃል ኪዳን የእውነት የተኛች  መስሎሀል አይደል•••? በፍፁም አልተኛችም ። በዚች ደቂቃ ውስጥ ይሄን ያህል እራሷን እስክትጥል ጥልቅ እንቅልፍ ውስጥ የገባች ይመስልሀል•••? አትሞኝ ባክህ ኤፊ •••እንደዚህ የምትገላለጠውም አንዴ ቀኝ እግሯን አንዴ ግራ እግሯን እየላከች የማይሆን ቦታ የምትነካካህም ሆን ብላ ነው !። አይገባህን እንዴ •••? ቆይ ከዚህ በላይ ፍቃደኝነቷን በምን ታሳይህ•••
ክፍል 7 ከ 100 ላይክ ቡሀላ ይለቀቃል ♥️♥️


♥️ ተማሪዋ ♥️
🌹...ክፍል 5...🌹
እንደገባን ከእቅፌ ውስጥ አፈትልካ ወጣችና ከአልጋው እራስጌ በስተግራ ባለ ወንበር ላይ ቁጭ አለች።
"እንዴ እዚህም ገብተሽ ቁጭ አይንሽ እኮ በእንቅልፍ ማጣት ደክሟል አተኝም እንዴ ተማሪዋ•••?
" ተማሪዋ አትበለኝ አትሰማም•••?" "ትትክክለኛ ስምሽን እስክትነግሪኝ አማራጭ የለኝም!" "ሰላም አልኩህ እኮ!"
"የስንቱን ሰላም በውበቷ የምትረብሽ ልጅ ሰላም ልትሆን አትችልም ! ውስጤ ነግሮኛል ፣ስምሽ ሰላም እንዳልሆነ እርግጠኛ ነኝ!" "ትገርማለህ ግን ! ••ይሄው ስሜ!•••  የዋሸሁክ መስሎህ ነው አደል•••?  አለችና ከሞባይሏ ላይ ከቨሩን አንስታ በሞባይሏ ጀርባ ላይ ያስቀመጠቻትን የድሬ ዳዋ ዩንቨርስቲ  ተማሪ መሆኗን የምትገልፅ መታወቂያዋን አንስታ ሰጠችኝ። " ካካካካካ እሄው እንደዋሸሽኝ መች አጣሁት •••ቃል ! ነው ስምሽ!  ቃልኪዳን ሰመረ !  ካሁን በኋላ ተማሪዋ መባልሽ ይቆማል!•••••እና አሁን ከወንበሩ ላይ  ተነስተሽ አተኝም ቃል!" አልኳት። ትከሻዋን ወደ ላይ ሰብቃ አልተኛም አለችኝ።
ነፃ ሆና ማውለቅ ያለባትን አውልቃ እንድትተኛ ብዬ  ወደ መታጠቢያ ክፍሉ ገባሁላት። ከደቂቃዎች ቆይታ በኋላ ስመለስ ጭራሽ ጫማዋን አውልቃ እግሯን ወንበሩ ላይ ሰቅላ ተቀምጣለች።
ጉድ ፈላ  እዚሁ ወንበሩ ላይ ነው የማድረው ልትለኝ ነው እንዴ•••? እያልኩ በሆዴ  ጠጋ አልኩና•••"  ቃልዬ አተኝም እንዴ•••?" አልኳት።"ቁጭ በል!" አለችኝ••• አልጋውን በአገጯ እያመላከተችኝ። ቁጭ አልኩ። ተፋጠጥን። የሆነ የሆነ ሰአት የምታየኝ አስተያየት ልቤን ስልብ ሲያደርገው ይታወቀኛል። ያ አስተያየት አልፎ አልፎ የሚመጣ መሆኑ በጀኝ እንጂ ዘለግ ላለ ደቂቃ እንደዛ ብታየኝ የልቤን ትርታ ታቆመው ነበር። "እእእ ••••እእእእ•••" እያለች ልትናገር ያሰበችውን አፏ ላይ አድርሳ  መልሳ ትውጠው ይመስል ለመናገር ስታምጥ ቆየችና•••
"እእእእ እኔ በጣም የምታዘበው ባስ ሲልም  የምጠላው ምን አይነት ባህሪ ያለው ወንድ እንደሆነ ታውቃለህ ኤፊ•••?" ስትለኝ ••••" አዎ አውቃለሁ ! በደንብ ነዋ የማውቀው!" አልኳት።
"ምን •••? እንዴት ልታውቅ ትችላለህ•••?  አታውቅም!" አለችኝ ።
"አውቃለሁ ባክሽ •••አንቺ የምትጠይው ወንድ እንደኔ  ገና ለገና መቶ ሀምሳ ብር ሂሳብ አልከፈልሽም ብሎ መቶ ሀምሳ ዘፈን ካልዘፈንኩብሽ ፣ የሀረርጌን ሸጎግን አትጥይኝ ባህርይ በፍፁም እንደዛ አይደለም። እውነቱን ለምናዘዝ እኔ ገና መጀመሪያ ላይ ቆመሽ እንዳየሁሽ ነው ደስ ያልሽኝ ••••" ብዬ ልቀጥል ስል በሳቅ አቃረጠችኝ ••••"ኪኪኪኪኪ ደስ ያልኩህ አደል በቃ ከዛ አያልፍም  ኪኪኪ"
"አስጨርሽኛ ቆይ እና ባንዴ እንዳየሁሽ ነው ያፈቀርኩሽ ብልሽ ያንን ማለት ይቻል ይሆናል እኔ ግን በቃ እንድታምኝኝ ስለምፈልግ እውነቱን ነው የምነግርሽ ደስ አልሽኝ ወይም ወደድኩሽ በቃ በቃ ምንድነው ለማንኛውም መሄድ ጀምረን ግማሽ መንገድ ላይ ሂሳብ የለኝም ስትይኝ አንቺ እንደምታስቢው ወይም እኔ እዛ ጋር እንዳስመሰልኩት አልተናደድኩብሽም እንደውም አንቺን የምግባባበት አጋጣሚ ስለተፈጠረልኝ በጣም ነበር ደስ ያለኝ።
ባጭሩ እንደዛ ያካበድኩት እንደዚህ አሁን እንደተግባባነው እንድንግባባእንድንቀራረብ ነው። ብር የለኝም ስትይኝ ችግር የለውም ሲኖርሽ ትከፍያለሽ ብዬ ባደርስሽ እኔ እንኳን ባልረሳሽ አንቺ ሲነጋ ትረሽኛለሽ!"
"ገብቶኛል ኤፊ!••• አቋረጥከኝ እንጂ እኔም ጨቅጫቃ ወንድ ምናምን ልልህ አልነበረም። ይህን ሁሉ ከምትናገር እኔን ብታስጨርሰኝ ምን ነበረበት•••?"
"የቱጋ •••? እዛው ወንበሩ ላይ•••? "ስላት ••••"የምን ወንበር •••?" አለች ግር እያላት።
"የማስጨርስሽ ነዋ! ወንበር ላይ ነው እንዴ የሚመችሽ እኔ መች ገባኝ ••! አልገባኝም ነበር እኮ እያልኩ ከላይ የለበስኩትን ቲሸርት ሳወልቅ" "ካካካካካካካካ ••••ሂድ ወደዛ ! ሞዛዛ !! ሞዛዛ ነገር ነህ እሺ እንዴ ኪኪኪኪኪ ደሞ  ፍጥነትህ ትገርማለህ እሺ! ፣ እኔ ወሬዬን እስክጨርስ ብትጠብቀኝ ምናለበት ነው ያልኩት ፣  ዝም ብልህ ነገር አታጣምም!"
"ግንኮ ከለሊቱ አስር ሰአት ሆኗል፣ በዚህ ሰአት ወሬ አይከብድም •••? ነገ ብናወራስ•••? አሁን እንተኛ ባክሽ ነገ እናወራለን !" "አአአ•••አሁን ከመተኛታችን በፊት ነዋ ማውራት ያለብን ኤፊ!"
"እህህ••••ገባኝ! አሁን እናውራ ፣ በቃ እናወራለና ምን ችግር አለው •••• እሺ ምንድን ነው•••?""እእእ••••እኔ የሚጫነኝ ወንድ አልወድም ኤፍ ••ማ•••ማ  ማለት•••" "አቦ ተይው አታስረጂኝ  በቃ ይበቃል! ፣ ይህን ምን ማብራራት ያስፈልገዋል! እንደገባኝ ያው  የሚጫንሽን  ወንድ ሳይሆን መጫኑን ነው የምትጠይው መፍትሄው ከላይ መሆን ነው አንቺ ከላይ ከሆንሽ ወዴት ይጫንሻል•••?"
"ኧረ በፈጠረህ••••! ላለማውራት  ሆን ብልህ ነው አደል ነገር የምታምታታው አውርቼ እስክገላገለው ብጠብቀኝ ምናለበት•••?" ስትለኝ እስክገላገለው የሚለው ቃል ሰቀጠጠኝ። ምን ልታወራኝ ነው ይቺ ልጅ ••• አውርቼ እስክገላገለው ስትል ምን ማለት ነው•••? እያልኩ •••
"እሺ ምንድን ነው ንገሪኝ!" አልኳት።
"ኤፊ በቃ እኔ በጣም የሚያናድደኝ ወንድ የኔን መጥፎ አጋጣሚ ከፍላጎቴ ውጪ በሆነ መልኩ ለመጠቀም የሚፈልግ ወንድ ነው ! " ስትለኝ ምን አስባ እንደሆነ ገባኝ። ለምን እንደሆነ አላውም ውስጤ የንዴት እሳት ሲጫር ተሰማኝ።  ብልጭ አለብኝ።
ወድያው ስሜታዊ ሆኜ ክፉ ነገር ልናገራት አልፈለኩም። ምክንያቱም ወድጃታለሁ። ግኑኝነታችን እንዲቀጥል እፈልጋለሁ ። ወደፊት የሚሰማኝን እና የሚሆነውን ባላውቅም አሁን ላይ ዛሬን ብቻ  ሳይሆን ነገ ከነገወድያም ላገኛት እንደምፈልግ ነው የሚሰማኝ።ባዶው ወለል ላይ አፍጥጬ ዝም አልኩ።  "ልልህ የፈለኩት ገብቶሀል አደል ኤፊዬ•••?"ገብቶኛ ቃል! •••በደምብ ገብቶኛል •••በመጀመሪያ ደረጃ ሁሉም ግንኙነቶች በአጋጣሚ በተፈጠረ  ቅፅበት የሚጀምሩ ናቸው !። ያ አጋጣሚ ደግሞ ጥሩም መጥፎም አጋጣሚ ሊሆን ይችላል። ስለዚህ አጋጣሚውን ተጠቅሞ መተዋወቅ ፣ መቀራረብና መግባባት አንዱ የህይወት ገፅታ ነው። ያ በራሱ ምንም ክፋት የለውም። የተቸገርሽበትን ወይም ጥሩ አጋጣሚ ላይ ያልሆንሽበትን ግዜ ተጠቅመው ችግርሽን ለመፍታት አልያም ከዛ መጥፎ አጋጣሚ ለመውጣት ያለሽ ብቸኛ አማራጭ እነሱ መሆናቸውን ሲያውቁ ያንን ክስተት አንቺን ያለፍላጎትሽ ያሻቸውን ለማድረግ የሚጠቀሙበት ወንዶች የሉም ብዬ አልልም። በሌላ መልኩ  ሰው ስለሆንሽ ብቻ ካንቺ ምንም ሳይፈልጉ አንቺን በመርዳታቸው ብቻ ደስ የሚላቸው ወንዶችም ብዙ ናቸው። ሁሌም ረጂ ወንዶች ተረጂ ሴቶች ናቸው ብሎ ማሰብም ትልቅ ስህተት ነው ። ያው እንደየሁኔታው ይቀያየራል። እኔ ግን ቃል ኪዳንን ወይም አንቺን በመጥፎ አጋጣሚ የተዋወኩሽ መስሎ አልተሰማኝም ነበር። እኔና አንቺ የተዋወቅነው በመጥፎ አጋጣሚ ነው ብዬ በጭራሽ አላሰብኩም ነበር።
በርግጥ እኔ ሳላገኝሽ በፊት እዛ ብርድ ላይ በምን ምክንያት እንደቆምሽ በዝርዝር አላወራንም ። ንገሪኝ ብዬያልወተወትኩሽም አንቺን ማጨናነቅ ስላልፈለኩ ነው። ግቢ ያላደረስኩሽም በግድ ተጭኜሽ ነው ብዬ አላስብም። በቃ ደስ ስላልሽኝ ፍቃድሽ ከሆነ አብረሽኝ እንድትዝናኚ ስለፈለኩ ነው ያስቀረሁሽ


♥️ ተማሪዋ ♥️
🌹...ክፍል 4...🌹

ምንጭ =- ከደራሲያን አለም   ✍

ምንም ሳንቀምስ ቅልጥ ያለ ጭፈራ ቤት ይዣት ከምገባ ሰከን ረጋ ያለ ቤት ትንሽ ብንሟሟቅ እንደሚሻል አሰብኩና ጫጫታ የለለበት ፣ሰፋ ባለው ግቢው ውስጥ ጥንዶች በነፃነት ዘና የሚሉበት የጥንዶች ማቆያ (couple house) ያለው ረጋ ካለው ሙዚቃው ጋር ረጋ ብልን መጨዋወት ወደምንችልበት ሀያ አራት ሰአት ወደማይዘጋ ሆቴል ይዣት ገባሁ።
ቢራ አልጠጣም ብላ ትንሽ ብትሟገተኝም እንደምንም አስጀመርካት።
ወድያው ጫወታ ለመጀመር ያህል •••"እና ስምሽን አትነግሪኝም ማለት ነው•••?" አልኳት በድጋሚ።

ኪኪኩኩ እሺ ትንሽ ለምነኝና እነግርሀለሁ!"
"አቦ እኔ መለመን አልችልበትማ!"
"ቀረብሃ ካለመንክ ማን ይሰጥሀል!"
"ካካካካ እሺ ከለመንኩስ ምን ይሰጠኛል?"
"ኪኪኪ •••እኔ ካልለመንክ ማን ይነግርሃል ለማለት ፈልጌ ነው ባክህ"
"እሺ እንድትሰጪኝ  ምን ብዬ ልለምንሽ  !"
"ጭራሽ እኔ ልንገርህ ምነው ፍቅረኛህ ትንሽ እንኳን ሳታስለምንህ ነው እንዴ ሁሉን ነገር የምታቀርብልህ?"
"ካካካካካ ምንድን ነው የምታቀርብልኝ•••? ለምሳሌ ምን •••?"
"ኪኪኪኪ እኔ እንጃልህ እስከዛሬ የሰጠችህን አንተው ነህ የምታውቀው?"
"ቆይ አንቺ እኔ ፍቅረኛ  አለኝ የሚል ነገር አልወጣኝ ፍቅረኛ  ይኑረኝ አይኑረኝ  በምን አወቅሽ•••?
" በግምት ነዋ!  ••• ባታገባም ፍቅረኛ አታጣ!"
"የለኝም ! ያው እንደነገርኩሽ እኔ መለመን አልችል ካለመንኩ ፍቅረኛ ኬት ይመጣል•••?"
"ነገሩ አንተ እንደሽማግሌ መጨቃጨቅ እና ማስጨነቅ እንጂ መለመን እንደማትችል ታስታውቃለህ አምኜሀለሁ ኪኪኪኪ•••"እንዴ አንቺ ልጅ እየሰደብሽኝ እኮ ነው ታውቆሻል!"
"ሲያንስህ ነው ••••ኪኪኪኪ•••• እንዴ • ሲያዩህ እድሜህ ሀያ አምስት እንኳን የሚሞላ አይመስልም ስትጨቃጨቅ ግን የሰባ አመት ሽማግሌ ነው የምትመስለው ኪኪኪኪኪኪ•••" አለችና ረጅም ሳቅ ሳቀች። በቃ በአንድ ምሽት ለወራት እና ለአመታት የምንተዋውቅ ያህል ተቀራረብን።
ፍርሀት እና ንዴቷ  ፣ ድንጋጤ እና ጭንቀቷ ፣ ድፍረትና ነፃነቷ ፣ ሳቅና መልኳ ••••በቃ  ሁሉ ነገሯ ወደድኩላት ሴት ልጅ እንደዚህ በፍጥነት ቀርቤም ወድጄም አላውቅም።
"ሁሉ ነገርሽ ደስ ይላል!" ስላት " እንኳን !" አለችኝ።
"ስምሽን ንገሪኛ •••?"
"አልነግርም!"
"የኔንም አልነግርሽም !"
"ያንተንማ ሰማሀት እኮ ያቺ ክፍት አፍ የሆነች አስተናጋጅ ኤፍዬ ስትልህ ያልሰማሁ መሰለህ !" አለችኝ። አነጋገሯም አኳኋናም በጣም ነበር ያሳቀኝ።
በዚህ ሁኔታ እየተጨዋወትን እኔ በላይ በላይ ብጠጣም እሷ ግን ጥንቃቄዋ ይገርም ነበር። ሁለት ቢራ ላይ እንደቆመች እኔ ብዙ ጠጣሁ። ግን ሞቅ አለኝ እንጂ አልሰከርኩም።
"እሺ ስሜ ሰላም ይባላል !" አለችኝ በጫወታ መሀል ሳልጠይቃት።
"ሰላም እንዳልሆነ ስምሽ እርግጠኛ ነኝ ደሞ ማን ንገሪኝ ብሎ ለመነሽ !" አልኳት።ኮርኪ ከጠረጴዛው ላይ አንስታ በመወርወር መታችኝ። ተሳሳቅን።
"ኧረ በቃ እንሂድ ሸኘኝ ኤፊ ሊነጋ እኮ ነው!"  አለች።
"ካካካካካ " ከነዱ አይጠጡ፣  ከጠጡ አይንዱ" የሚለውን ማስታወቂያ ሰምተሽ አታውቂም ማለት ነው?" ስላት
"ም••••••ን ?" አለች።
"ከማስታወቂያው ስር በጥቃቅን ፅሁፍ ሌላ የተጨመረችውን መልክትስ አንብበሻት አታውቂም•••ምን ትላለች መሰለሽ
" ከነዱ አይጠጡ፣ ከጠጡ አይንዱ " ከሚለው ትልልቅ ፅሁፍ ስር በደቃቁ•••" ከጠጡ በኃላ መንዳት የሚችሉት አልጋ ላይ እንጂ መኪና አይደለም!" የምትል መልክት አለች።
ትቀልጃለሽ እንዴ መሄድ ከፈለግሽ እንጠጣ ስልሽ ለምን ተስማማሽ ካካካካካ  አይ የምሬን ነው  ጠጥቼ ስነዳ አኔንም አንቺም ይዤ ገደል ከምገባ
ከሌላ ተሽከርካሪ ወይ ከግንብ እና ከግንድ ጋር  ከምጋጭ ••• እዚሁ እንደጀመርነው  የቢራ ጠርሙሳችንን እያጋጨን ብንጠጣ አይሻልም •••?
ትንሽ ቆይተን ደግሞ ወደያዝኩት ክፍል ገብተን  ወይ እኔ አንቺን ወይ አንቺ እኔ ብገጭኝ አይሻልም  የኔ ቆንጆ  ካካካካ? አልጋ ይዣለሁ እኮ እሄው ቁልፉ!"  ብዬ ሳሳያት•••
"ምናልክ ኤፊ •••?" አለች በድጋሚ እንቅልፍ ባስለመለማቸው  አይኖቿ ተስለምልማ እየተመለከተችኝ ።
" እንቅልፍሽ መጥቷል አደል••••?  ነይ በቃ  ወደክፍላችን እንግባ!"  ብዬ  እጇን ይዤ ከተቀመጠችበት  አነሳኋትና ሳብ አድርጌ አቀፍኳት። ድምፅ የለም።
ይዣት ስሄድ •••• "ኤፊ እኔ ••••" ብላ ልትናገር ያስበችውን ሳጨርሰው ከንፈሯ ላይ የግራ እጄን  ሁለት ጣቶች በስሱ ደገፍ አደረኳቸው። ዝም አለች ።ጠበቅ አድርጌ እንዳቀፍኳ ተያይዘን ወደያዝኩት ክፍል ገባን....

ክፍል 5 ከ 50 ላይክ ቡሀላ ይለቀቃል ♥️♥️


*መጣሁ ባክሽ መላቀቅ የለም ዛሬ!"
አስፓልቱ ዳር ቆማ ጠበቀችኝ አጠገባ እንደደረስኩ ባጃጅ ውስጥ ገብታ እየተቀመጠች ወደ ሌላ ቦታ ሳይሆን ወደ  ዩንቨርስቲ መሄድ እንደምትፈልግ ብትነግረኝም ትንሽ ጠጥተን እና ተዝናንተን እንደምሸኛት ቃል ገብቼ ወደ ግቢ ሳይሆን ወደ ከዚራ ይዣት ከነፍኩ።
እንደዉም በጣም ለምናችኋል አሁን part 4 ይለቀቃል🌹


♥️ ተማሪዋ ♥️
...ክፍል 3...
Notice :- እውነተኛ ታሪክ ነው
አዘጋጅ እና አቅራቢ=- ከደራሲያን አለም የቴሌግራም ቻናል ✍

መጣሁ ሽንቴን ልሽና ያው በዚህ ሰአት ጥብስ ነው የሚኖራቸው ሁለት ጥብስ እዘዥ" ብያት እሷ ወንበር ይዛ ቁጭ ስትል እኔ  ወደወስጥ ገባሁ።
በልተን ልንጨርስ አከባቢ •••
" ስሚ እንጂ ተማሪዋ!"
"እንዴ ኪኪኪኪ ተማሪዋ ብለህ ከምጠራኝ ስሜን መጠየቅ አይቀልም!"
"እኔ አንቺ ጋር ያለኝን ብር እንጂ ስምሽ ምን ያደርግልኛል•••?"
"ኪኪኪኪ እንዴ አሁንም እዛው ላይ ነህ•••?  የተውከው መስሎኝ ነበርኮ!"
"የተውኩት መሰለሽ አደል ደፋር ነሽ አቦ እውነቱን ልንገርሽ የተውኩት እየመሰልኩ ነው እንጂ በጭራሽ አልተውኩትም !"
"ምን ማለት ነው••• ?"
"ምን ማለት እንደሆነ ቀስ ብሎ ቢገባሽ ይሻላል ብዬኮነው ንገረኝ ካልሽ ልንገርሻ በቃ•••እኔ ሰው በምክር ሳይሆን በተግባር ማስተማር ነው የሚመቸኝ። እዚህ ያመጣሁሽም ምግቡን አንቺ እንድታዢ ያደረኩትም ሆን ብዬ ነው። አንቺ አዘዝሽ ማለት ከፋይ አንቺ ነሽ ማለት ነው።ለሰጠሁሽ የትራንስፖርት አገልግሎት በጥሬው ባትከፍይኝም በተዘዋዋሪ መንገድ በጥብስ  ሂሳቤን አግኝቸዋለሁ።
በቃ እኔ እንዲህ ነኝ፣ ሰው ሲሸውደኝ ደስ አይለኝም። ሂሳቤን እንድትከፍይኝ ካንቺ ጋር ብጣላ ምን አተርፋለሁ ፣ከዛ ይልቅ ጭንቅላቴን ተጠቅሜ መላ ማፍለቅና እንደትከፍይኝ ማድረግ ነበረብኝ። እስቲ እኔ ጋር የለኝም አልከፍልም ያልሽውን ሂሳብ እዚህም እንደምትደግሚው አያለሁ። ያው ባይኖርሽም አንድ  ሁለት ቀን እቃ ቢያሳጥቡሽ ነው ቻይው!"
"ካካካካካካ ኧረ በጌታ ሰዎቹ ወደኛ እያዩ ነው አታስቀኝ!"
"ይዩሽ ችግር የለውም በኋላ ስታለቅሺ ያዋጡልሻል፣ ባጭሩ ይህን የበላነውን ሁለት ጥብስ ከፋይዋ አንቺ ነሽ እኔ የምከፍለው አምስት ሳንቲም የለኝም!

"እህት ሂሳብ!" አለቻት። ዘወር ብዬ ሳያት ግራ ገብቷት አንዴ እኔን አንዴ አስተናጋጇን ትመለከታለች። ባጃጄ ውስጥ ገብቼ በማስነሳት ቁልቁል ስፈተለክ ባስተናጋጇ ክንዷን ተይዛ እንደቆመች  ማመን አቅቷት አራት ጣቶቿን አፏ ላይ ጭና ትመለከተኝ ነበር••••
****
ብዙ መራቅ አልቻልኩም። ምን ያህል እንደምትጨነቅ ሳስበው አላስችልህ አለኝ። ከአይኗ እስክሰወር  ትንሽ ሄደት ብዬ ዞሬ መመለስ ጀመርኩ፣ ተማሪዋ ሳታየኝ አስተናጋጇ ገና ከሩቁ እየተመለስኩ እንደሆነ  አየት አደረገችና አፍና ያቆየችውን ሳቋን ለቀቀችው።
ተማሪዋ አስተናጓጇ ምን እንደሚያስቃት ግራ ገብቷት አይን አይኗን ከማየት ውጪ አጠገባቸው እስከምደርስ መመለሴን አላስተዋለችም። አምስት እርምጃ ያህል እስኪቀረኝ ድረስ ተጠግቼ ከጀርባዋ እንደቆምኩ ዘወር ብላ አየችኝና ••••
"በጣም ትገርማለህ እሺ ! ስታናድድ ደሞ ትስቃለህ እንዴ አናዳጅ !" አለችኝ ። ከተጨነቀው ፊቷ የከፋው ፈገግታ ፈገግ ብላ።
አስተናጋጇ ••••• "አስደነገጥኩሽ አደል የኔ ቆንጆ ! ኡፍፍፍ ኤፊ ግን ነብስህ አይማርም ! ስትርበተበት ቀላል አሳዘነችኝንዴ! ይቅርታ እሺ ማሬ የኔ ሳይሆን የሱ ተንኮል ነው ኪኪኪኪኪ በሉ እንኩ መልሳችሁን ገና ሳትበሉ እኮ ነው የከፈለው ኪኪኪኪ•••"  እያለች ብሩን ፊቷ ሳይፈታ በንዴትም በጭንቀትም ቅጭም እንዳደረገችው  በክፉ አይን  ለምታያት ለተማሪዋ ሰጠቻትና እየሳቀች ወደ ውስጥ ገባች።
ተማሪዋ ካስተናጋጇ የተቀበለችውን መልስ ይዛ ወደኔ ተጠጋችና ታፋዬ ላይ ወርውራልኝ••••" ማሚ ትሙት እንደዛሬ ደንግጬ አላውቅም•••• አንተ ግን ምን አይነት ልጅ ነህ  በጌታ••••? ክፉ ነህ እሺ!" አለችኝ።። ከመሳቅ ውጪ  መልስ ልሰጣት አልቻልኩም።
"አናታም !" ብላኝ ቀስ እያለሽ ወደላይ መሄድ ጀመረች። ነፃነት እና ድፍረቷ ደስ ይላል።  ክላክስ እያደረኩ ተከተልኳት። ዘወር ብላ አላየችኝም። የእግረኛ መንገድ ላይ ስለሆነች  ባጃጇን  ጥግ አስይዤ አቆምኩና በግሬ ተከተልኳት አጠገባ እንደደረስኩ•••
"ካሁን በኋላ አታውቀኝም አላውቅህም እሺ እንዳታናግረኝ!" አለችኝ።  ክንዷን ያዝ ሳደርጋት ••••"ልቀቀኝ!" አለች ቆም ብላ።
"አለቅሽም !"አልኩ።  ዝም አለች። ዝም ብዬ አየኋት እሷም አየችኝ ። ቃላት የማይገልፁት ልዩ ውበት ፣ ፈጣሪ የባረከሽ የቆንጆዋች መፍለቂያ የሆንሽው አገሬ ዘርሽ ብዝት ይበል አልኩ በልቤ። ዝም ብዬ ሳያት ዝም ብላ ታየኛለች።
"ስምሽ ማነው••••?" አልኳት።
"ሂድ ወደዛ! ጣጣህን ጨርሰህ ፣ የልብህን አድርሰህ ስታበቃ ነው እንዴ ስሜ ትዝ የሚልህ አልነግርህም!" በማለት እጇን አስለቅቃኝ ለመሄድ ስትሞክር ጠበቅ አድርጌ ያዝኳት።ቀና ብላ አየችኝ አይኗ ውስጥ በጥልቀት ተመለከትኳት ። አቀረቀረች። ከፍቷታል።
"ሀይ አቦ በቃ ትንሽ ላስጨንቅሽ ብዬ እንጂ ይሄን ያህል ይከፋሻል ብዬ መች ገመትኩ እና በዚህ ምክንያት ልታኮርፊኝ ነው?" ስላት እንደዛው እንደከፋት ቀና ብላ•••
"ደሞ የልጅቷ ይባስ ! ሁኔታዋ በጣም ነበር የሚያስጨንቀው ስትገርም ግን ! ቀልድ መሆኑን እያወቀች እንደዛ ምንጭቅጭቅ ስታደርገኝ ትንሽ እንኳን አይከብዳትም እንዴ? ደሞ ቀልድ ነው ምናምን እያለች ትገለፍጣለች ግልፍጥ ነገር ነች ! ድዳም !"አለች።በጣም እንደደበራት ይበልጥ ተገለጠልኝ።
"ኦኦኦኦ ይህን ያህል ተናደሻል እንዴ ተማሪዋ ! በእውነት በጣም ይቅርታ የማይሆን ቀልድ ነው ማለት ነው የቀለድኩት፣ ቶሎ የተመለስሉት እኮ ግን  ብዙ እንዳትጨናነቂ በማስብ ነበር "
"ትንሽ ብትቆይ እማ ልጅቷ በቁሜ ልብሴን ከላዬ ላይ ከመግፈፍ የምትመለስም አይመስለኝ ፣ እንደዚህ አይነት ቀልድ አለ እንዴ •••? ሲጀመረ አንተ ብትቀልድ እንኳን እንዴት ከማላቃት ልጅ ጋር ታላትመኛልህ ?"
"አቦ አታካብጅዋ ይህን ያህል ቆይ ምን ብላሽ ነው•••?*
"ያለችው ምን ያደርግሀል•••?  ልጅቷ ግን በጣም ችግር አለባት ! አላውቃት አታውቀኝ ፣ ቀልድ መሆኑን እያወቀች እንደዛ መንጣጣቷ ይገርማል! ነገሩ ተወው እኔ ሴት አይሆንልኝም ፣ እንኳን እሷ የኔ የቅርቤ ጋደኛዬ እህቴ የምላቸው ሴቶች እንኳን አንደበታቸውን እንጂ ልባቸውን ከፍተውልኝ አያውቁም !ለምን እንደሆነ እንጃ ብቻ ሴት አይወጣልኝም!"
አለች እንባ እምባ እያላት። በቀለድኩት አጉል ቀልድ የጥፋተኝነት ስሜት ተሰማኝ።  ተፀፀትኩ።
"በናትሽ በቃ እርሽው እኔ ነኝ ጥፋተኛው ማንም አይደለም!" አልኳት ዝም አለችኝ። ትግስቴ አለቀ።
"አቦ ተይና አንቺ ደሞ እኔም እኮ ቅድም እዛ ድረስ ወስጄሽ የምከፍለው የለኝም ስትይኝ ከዚህ በላይ ደንግጬ የለ እንዴ? በቃ ይቅርታ !" በማለት ትንሿን  ጣቴን ወደሷ ቀሰርኩና" እንታረቅ!"  አልኳት። ያንን ፍልቅልቅ ሳቋን አፍለቀለቀችው።  እሳን ለማሳቅ ያደረኩት ሙከራ ተሳካ። ከዛ አስቀያሚ ስሜት በመውጣቷ  ደስ አለኝ።
"አቦ እንደዚህ ስስቂ ብቻ ነው የሚያምርብሽ ሁለተኛ እንዳታኮርፊ እሺ! እዚሁ ጠብቂኝ  ባጇጇን ይዜ ያበደ ጭፈራ ቤት ወስጄ ደስ ያለሽን እጋብዝሻለሁ፣ ስንቀውጠው ነው የምናድረው!"
"እንዴ አብደሀል እንዴ እራት በልተን እሸኝሻለሁ አላልክም?"
ይቀጥላል....

ከ 200 ላይክ በኋላ ክፍል 3 ይለቀቃል🌹


♥️ ተማሪዋ ♥️
🌹...ክፍል 2...🌹
Notice :- እውነተኛ ታሪክ ነው
"እሺ የቱጋ ይዤ ልዘቅዝቅሽ••••?  ነይ ውረጃ ባጃጇ ውስጥ ዘቅዝቆ ለማራገፍ አይመች!የቱጋ ቆሜ አንቺን ተሸክሜ አራግፋለሁ! ስለዚህ ነይ ውረጅ " ብያት የባጇጇን የሁዋላም የፊትም መብራት አጠፋፍቼ ስወርድ•••
"እንዴ ኧረ በፈጠረህ?" አለች  ጭራሽ ከተቀመጠችበት ወደጥግ ተጠግታ እየተቁለጨለጨች
"የፈጠረኝማ ሰርተህ ብላ ነው ያለኝ ፣ለስራ አደል እንዴ የወጣሁት!•••? ቀልድ የለም!  ቀጥታ ፖሊስ ጣብያ፣  ዘቅዝቀህ ብታራግፈኝ ትላለች እንዴ ቀላል አራግፍሻለሁ፣  ገንዘብማ ይዘሻል፣ ባይኖርሽማ እዚህ ደርሰሽ የለኝም  እንደምትይኝ ስለምታውቂ አትከራከሪም ነበር። ቆይ ስታይኝ ሞኝ እመስልሻለሁ•••? ምንም ገንዘብ የለለው ሰው ቀንስልኝ ብሎ ይከራከራል•••?  በለው በለው ቆይ እናንተ ሴቶች በሌላ በስንተ መንገድ የምታራቁቱን አነሰና ጭራሽ ተሳፍራችሁ አልከፍልም ማለትን ሙድ አደረጋችሁት እንዴ•••? ቆይ ማነው አደራጅቶ የለቀቃችሁ•••? ነው ወይስ ወንድ ልጅ ሴት ልጅ ላይ አይጨክንም ብላችሁ ስለምታስቡ ነው እንዲህ እየተፈራረቃችሁ ጢባጥቤ የምትጫወቱብን•••?" አልኳት ፊቴን ከስክሼ  የባጇጁን የኋላ በር ከፍቼ እየገባሁ።
"እእእ•••• እነማን•••? "  አለች።  ግራ ገብቷታል። ድምጿም ሳስቷል።
"አንቺ !•••እነሱ•••ሁላችሁም ። ያው አንድ ናቹሁ።
በተለይ ቆንጆ ነሽ፣ ታምሪያለሽ፣ የሚል ወንድ በዙርያችሁ ሲበዛ •••የፈለጋችሁትን ብታደርጉን ፣ ስጋችንን ግጣችሁ ባጥንታችን ብታስኬዱን ፣ የሚናገር አፍ የሚሰነዝር እጅ ቢያንስ ሮጦ እሚያመልጥ እግር የለለን ነው አደል የሚመስላችሁ•••ንገሪኝ አንቺም እንደዛ ነው አደል የምታስቢው•••?"
"እባክህ ይሄ እኮ ጓደኞቼን አምኜ ምንም ሳልይዝ ስለወጣሁና እኔ ያላሰብኩት ሙድ ውስጥ ሲገቡና ከማላውቀው ሰው ጋር ምንም ማድረግም ፣  ምንም ነገር ውስጥ መግባትም ስለማልፈልግ ከነሱ ስለይ የተፈጠረ አጋጣሚ እንጂ እኔ ሆን ብዬ ያደረኩት ነገር አደለም፣ ግቢ ስደርስ ቆይ ከክፍሌ ይዤልህ ልምጣ ብዬ ልሸውድህም አልፈልግም፣ በቃ የለኝም !።  ለምንድን ነው ከሌሎቹ ጋር አንድ ላይ የምትወቅሰኝ•••? በቃ ይቅርታ!"
"የምን ይቅርታ!  ይቅርታ እራት ይሆናል እንዴ•••? ቆይ ይቅርታ ነዳጅ ይሞላል•••? አሁን ይቅርታውን ተይውና እንዴት አድርጌ ዘቅዝቄ እንደማራግፍሽ ብቻ ንገሪኝ ግን ባትነግሪኝም ችግር የለውም ፣ፍላጎትሽን ለማወቅ እንጂ  ምን እንደማደርግ አልጠፋኝም!"

" ምኑን •••? የምን ፍላጎት•••? እኔኮ  ተጫወቺ ምናምን ስትል እና ወሬ ስንጀምር በቃ ብዙ ሳናወራና ሳንቀራረብ ልንገርህ ብዬ ነው።  ዘቅዝቀህ ብታራግፈኝ ያልኩትም ያው እንድታምነኝ ያህል ነው እንጂ •••"

"ካካካካ ነው እንዴ••••? አቦ መች ገባኝ እኔ ካወራን ሂሰብ አልከፍልም ማለትሽ ነው ለካ ••••? አሁን  ገባኝ ፣እኔ ለወሬ እንደምታስከፍይ መች አወቅኩኝና ፣ በቃ ዩንቨርስቲ  ደርሰሽ እስክትወርጂ ምንም አታውሪኝ፣ እንደዛው መጀመሪያ ላይ ዝም ብለሽ እንደነበረው ዝም በይ፣ እኔም ተጫወቺ ምናምን እያልኩ አላስቸግርሽም፣ጭራሽ ትንፍሽ አልልም ፣ይቅርብኝ ፣ ብቻ ሂሰቤን ስጪኝ፣ ሁለት መቶ ብር ነበር አደል ያልኩት•••? ሀምሳውን ትቼልሻለሁ መቶ ሀምሳ ብሩን ክፈይና እንሂድ" ብዬ እጄን ስዘረጋላት•••
"በማዬ ሞት ! አለመንከኝም እንዴ ቆይ አንተ ግን የድሬ ልጅ ነህ አደል•••?"
"እና ብሆንስ•••!  የድሬ ልጅ ፍቅር እንጂ፣ አሽከር ነው ያለሽ ማነው•••?  ገና ለገና የድሬ ልጅ ነው ጣጣ የለውም ብለሽ ነው እንዴ ? በውድቅት ለሊት ጣጣ ውስጥ የከተትሽኝ?"
"የምን ጣጣ?"
"አቦ  አለመክፈልሽ ሳያንስ የጥያቄሽ ብዛት፣  አላመንከኝም እንዴ? ትላለች እንዴ አዋ አላማንኩሽም ! ዘቅዝቄ ሳላራግፍሽማ መቼም አላምንሽም ! ዛሬ አንላቀቅም!"  እያልኳት ወደ ጋቢና ገብቼ፣  ባጃጇን አስነስቼ ፣ በፍጥነት  እሷ መሄድ ወደምትፈልግበት ሳይሆን ወደመጣንበት አቅጣጫ  አዙሬ መብረር ስጀምር  ክፉኛ ደነገጠች።
ከጀርባዬ  በሁለቱም እጆቿ ትከሻዬ አከባቢ ያዝ አድርጋ ወደ ጆሬዬ በመጠጋት ፊት ለፊት እየተመለከተች•••

" ኧረ በጌታ ወዴት ነው የምትወስደኝ•••?"
"አንቺን ዘቅዝቄ ወደ ማራግፍበት ምቹ ቦታ!"
"ኧረ በናትህ ቆይ አንተ  ግን እህት የለህም••••?"
"እህትማ አለኝ! ሊያውም በጣም የምወዳት! አንዲት ብቸኛ  እህት አለችኝ፣  ይህንን ባጃጅ የገዛችልኝም እሷ ነች።  ነገር ግን ሰርተህ ዋጋውን መልስ ከዛ ባጃጁን ትወስደዋለህ ነው እንጂ ሴት በነፃ አመላልስበት አላለችኝም ገባሽ!"
"እሺ የማታደርሰኝ ከሆነ በቃ አውርደኝ ያለበለዝያ ልጮህ ነው !!!!••••!"አለች እንባ እንባ በሚል ድምፅ። ታደርገዋለች ። በእርግጠኝነት ከዛ በላይ ባስጨንቃት ትጮኽ ነበር ። ሳቄን መቆጣጠር አልቻልኩም።
"ካካካካካካካ••••"  ባጃጇን ጥግ አስይዤ ትንሽ ሳቅኩባት። ከባጃጁ ውስጥ ወረደች። ግን አልሄደችኝ ግራ በተጋባ ስሜት ቆማ ስታየኝ አሳዘነችኝ።
"ተማሪዋ ! ለምን ወረድሽ •••? ካካካካ  በግርሽ ልትሄጂ  ወሰንሽ በቃ••• ?" አልኳት። መልስ አልሰጠችኝም።
"ሰአትሽን አይተሽዋል ሰባት ሰአት ሊሆን ነው ? ነይ ግቢ እነዛ እዛ ጋር የቆሙት ሰዎች ታክሲ ፈልገው ነው ፣እንጠይቃቸውና ባንቺ መስመር ከሆኑ ይዘናቸው እንሄዳለን፣ ነይ አንቺ እዚህ እኔ ጋር ጋቢና ሆኚ!" አልኳት። አላመነችኝም። ፈራች።
" ነይ ግቢ አቦ ደሞ ባንቺም ብሶ እንድለማማጥሽ ትፈልጊያለሽ እንዴ?" ስላት ገባች። ሰዎቹ ጋር ደርሰን ስንጠይቃቸው እሷ ወደምትሄድበት ሳይሆን ሌላ መስመር ናቸው።
" ክፍያው ዘጭ ነው! እንሸቅላ በቃ !  አንዴ ጣል አድርገናቸው እንመለስ•••?" ስላት••• "
"ወይኔ ጉዴ መሽቷል እኮ!"
"ካካካካካ•••• ኧረ ባክሽ መሽቷል ትላለች እንዴ!  የመሸውማ ገና እኔን ሳታገኝኝ ነው።  አሁን ሊነጋኮ ነው፣  ደሞ ቢመሽስ ግቢያችሁ እንደሆነ አጥር የለው ፣ አደርስሽለሁ !" አልኳትና "  ግቡ  እንሂድ"  አልኳቸው እነሱንም ።  ገቡ፣ ጉዞ እንደጀመርን የባጇጇን ፍጥነት ስጨምር እኔ ላይ ልጥፍ አለች።  ከጀርባ ወገቤ ላይ ልብሴን ጨምድዳ ይዛኛለች።
" ልቀቂኝ ባክሽ ! ሂሳብ ሳትከፍይ ደሞ የድሃ  ልብሴን ልቀጂ ነው እንዴ•••?"
"ካካካካካ! ኧረ ምን ይሻለኛል!"
"ምንም አይሻልሽም መክፈል ብቻ ቆይ የየት አገር ልጅ ነሽ?"
"የ አዲስ አበባ"
"እህህህም አጅሪት ከቀለጠው መንደር መጥተሽ ነዋ ይህንን የድሬዳዋ ሙቀጥ ልቡን ያሳሳውን ልጅ በውበቴ አቅልጬው ሳልከፍል እብስ እላለሁ ብለሽ ምንም ብር ሳትይዢ ዋጋ ተከራክረሽ የገባሽው! እኔ ግርም ያለኝ አለመክፈልሽን እያወቅሽው ዋጋ መከራከርሽ"
"ኪኪኪ ኧረ ተወኝ በፈጠረህ! በብዙ ብር ከተስማማሁ  ያው አልከፍልም ስልህ ብዙ ትናደዳለህ ብዬ ነዋ "
"ካካካካካካካ አቦ ይመችሽ ! አይ የገባሽ ነሽ ግን ባጃጁን ሳዞረው  የምሬን መስሏት እርርይ  ብላ ጉድ እንዳታደርገኝ ብዬ ፈርቼ ነበር የምር!" አልኳት።

እኔ ሳወራ መልስ ከመስጠት ይልቅ መሳቅ ይቀናታል።ሳቋ ደሞ ዜማ አለው የዘመኑን ዘፈን ከመስማት የሷ ሳቅ በስንት ጣእሙ።
ሰዎቹን አድርሰን ስንመለስ •••" በጣም ርቦኛል ነይ እራት እንብላና ሸኝሻለሁ !" አልኳት ትንሽ አቅማማች። ጫን ስላት ተስማማች ።አንድ ብዙ ግዜ ምግብ የምበላበት ሆቴል ይዣት ገባሁ...
ከ 200 ላይክ በኋላ ክፍል 3 ይለቀቃል🌹


♥️ ተማሪዋ ♥️ ...
           .
           .
🌹...ክፍል 1...🌹
.
.
Notice :- እውነተኛ ታሪክ ነው!
.
.
ኤፍሬም እባላለሁ ፣ በድሬ ዳዋ ከተማ ነው ተወልጄ ያደኩት፣ ባጃጅ ሹፌር ነኝ፣ ብዙ ግዜ ማታ ማታ ነው ስራዬ ፣ በርግጥ ስራውን ከጀመርኩ ገና ሁለት ወሬ ነው ማታ ማታ በመስራት የጀመርኩትም በደንብ እጄን እስክፈታ መንገዱ ነፃ በሆነበት ሰአት ብሰራ የተሻለ ነው ብዬ በማስብ ነበር። ቢሆንም የማታው ስራ ከእንቅልፍ ማጣቱ ውጪ ገቢው ከቀኑ የተሻለ ነው፣ እንደተለመደው እራቴን በልቼ ቡናዬን ጠጥቼ ከምሽቱ 3:15 ላይ ወደ ስራ ወጣሁ፣ እስከ ምሽቱ አምስት  ሰአት ድረስ ሲዝናኑ ካመሹት መሀል ከፊሉን ከመጠጥ ቤት ወደ ቤታቸው ከፊሉን ከመጠጥ ቤት አልጋ ወደያዙበት ሌላ ሆቴል ፣ ከፊሉን ከመጠጥ ቤት ወደ ሌላ መጠጥ ቤት ሳገላብጥ ቆየሁ።

ከምሽቱ አምስት ሰአት ካስር አከባቢ ፣ አንድ ቀን ቀን ሆቴል ሆኖ ማታ ማታ ቅልጥ ወዳለ ጭፈራ ቤት ወደ ሚቀየር  እንደሆቴልም እንደጭፈራ ቤትም ለመሆን ወደሚቃጣው ሀረር መንገድ ሆት-ጭፈራ ቤት አከባቢ  ከውስጥ የሚወጣ እና ትራንስፖርት መጠቀም የሚፈልግ ሰው  እስኪወጣ ለመጠባበቅ ጠጋ ብዬ እንደቁምኩ •••አንዲት ከራስ ፀጉሯ እስከ እግር ጥፍሯ የሚጣል ነገር የለላት፣ መግቢያ በሩ በስተቀኝ በኩል የግንብ አጥሩን ተደግፋ ፣ ብርዱን ለመቋቋም ከጡቶቿ በታች እጆቿን አጠላልፋ በማጣመር የቆመች ቀሽቲ ላይ አይኔ አረፈ።
ሁኔታዋ ሲታይ ግራ ግብት ያላት ትመስላለች ፣እዛው ቆማ አንዴ ወደ ግራ አንዴ ወደቀኝ ትገላመጣለች፣ የምትጠብቀው ቀርቶባት ይሆን•••? እድሜዋ በግምት በ 19 እና በ21 መካከል ቢሆን ነው፣ ይቺን የመሰለች ልጅ በዚህ ሳአት ሊያውም ብቻዋን እንዴት?  ለምንስ ቆመች••• በዚህ ሰአት ግንብ አስደግፎ  የቆየባት ወይ የቀረባት  ደፋር ማን ይሆን•••? እንዴትስ ብርድ ላይ ቆማ ልትጠብቀው ትግስቱን አገኘች•••?  ለአከባቢው እዲስ ሳትሆን አትቀርም፣  ከዚህ በፊት አይቻት አላውቅም፣መልስ በለለቸው በራሴ መላምቶችና ጥያቄዎች እየተናጥኩና•••  ከባጃጄ ወርጄ  ምነው ብቸሽን ልበላት•••? አልበላት•••? እያልኩ ከፍርሀቴ ጋር እየተነታረኩ •••አንዱ ስልክ ሊያናግር ከጭፈራ ቤቱ  ወደ ውጪ ወጣናስልኩን አናግሮ እንደጨረሰ  ወድያው ••• ወደ ልጅቷ ጠጋ ብሎ ሊያወራት ሞከረ፣ ኮስተር አለች፣ ያኔ እድሉን ሊሞክር አጋጣሚዉን ሊጠቀም እንጂ ከዚህ ቀደም እንደማያውቃት ተረዳሁ።
"አቦ ኤፊ ፈሪው!  አንተ ከራስህ ጋር ስትጨቃጨቅ፣  ይሄው ገና እንዳያት ዘሎ ሊከመርባት ነው! ፣ በለው ፍጥነት! ቦልት ሆነባትኮ!  በቃ ይዛት ወደውስጥ ይገባል ! ፣ ትንሽ ታንገራግርና ተከትላው ትገባለች ፣የቀጠራት ከቀጣት ምን አማራጭ አላት?  በብርድ ከምትንሰፈሰፍ ገብታ ልጁን በወጪ ብታንሰፈስፈው አይሻልም፣ ኤፍዬ አንተ ግን ፈዘኻል ! ፈሪ ነህ ! " አልኩት እራሴን ! እኔ ለደቂቃዎች ቆሜ እያየኋት ሳመነታ የልጅ ፍጥንት ገርሞኝ።

የዋዛም አይደለች፣ እሱ በእጁም ፣በአፉም፣ በእግሩም የሚያወራ ነው የሚመስለው ፣ እሷ ግን እስካሁን ፊቷም አንደበቷም አልተፈታም፣ ጠጋ ሲላት ጠጋ  ትላለች፣ ጭራሽ እሱ እያወራ እሷ የምታየው ሌላ ቦታ ነው፣
"አቤት የወንድ ልጅ ትግስት !" አልኩ። የኔ ትግስት እህቴ ሁሌ እንደምትለኝ እውነትም አፍንጫዬ  ላይ ነች መሰለኝ  ታጋሽ ወንዶች ሳያስቀኑኝ አይቀሩም። አልፋታ ብሎ ድርቅ ሲልባት ብስጭት ብላ••••• ውዝውዝ ቅንጥስ ብጥስ እያለች በቆመበት እንደንጨት አድርቃው ፣ ቀጥታ ወደኔ ባጃጅ መጣች  ከመድረሷ በፉት ባላየ ፍቴን ወደ ፊት ለፊት አዞርኩ።

"ነይ የኔ ቆንጆ!! ••• ምኑ ቀዥቃዣ ነው ባካችሁ !  በተንቀዥቀዠ መሰለው እንዴ•••? ቅድም እኮ ዝም ብዬ ነው እራሴንየሰደብኩት፣  እንደውም የኢትዮጲያ ሴቶችኮ ••• ኮራ፣  ዘብነን፣ ጀነን፣ ቁንን፣ ጥብርር ፣ ረጋ፣ የሚል እንጂ ወንድ እንጂ እንደደላላ ጥድፍድፍ የሚያደርጋቸው፣ ቅልብልብ ፍጥንጥን የሚልባቸው፣ እራሱ አውርቶ እራሱ የሚስቅባቸ ቀዥቃዣ  ወንድ መች ይመቻቸውል ? መች ቀልባቸውን ይገዛውና ? እሄው እሱ ቢፈጥንም  ኩም አድርጋው ወደኔ ባጄጅ መጣች !"እያልኩ  ለምን እንደልጁ ፈጣን አልሆንኩም ብዬ በራሴ መናደዴ ትክክል እንዳልነበር ሳስብ••• ልጅቷ ባጃጄ አጠገብ ደርሳ••••
" ይቅርታ ወንድም ግቢ ትወስደኛለህ•••? ኮንትራት " አለችኝ።
ድንገት ድምፅ ሰምቶ ብንን እንዳለ ሰው  በፍጥነት ወደሷ ዞርኩና••••
"እ ምን አልሽኝ•••?" እልኳት። ደገመችው።
ግቢ ማለት ? ዩንቨርስቲ ማለቷ ነው፣  ልጅቷ የዩንቨርስቲ ተማሪ እንደሆነች ለማወቅ ግዜ አላጠፋሁም ዩንቨርስቲው ደግሞ  አሁን ካለንበት እሩቅ ነው፣ ሼል በመባል ከሚታውቀው  የድሬ መግቢያ ከሰኢዶ ተሻግሮ  መልካ መውጫ ጫፍ ነው ያለው። ቢሆንም ይቺን ልጅ ባጃጇ አቅሟ ይፍቀድ እንጂ እንኳን ድሬዳዋ ውስጥ ከድሬ ውጪም ክፍለሀገር ውሰደኝ ብትል አልሄድም የሚል የባጃጅ ሹፌር አለ እንዴ•••? ኧረ የለም።
"200  ብር ትከፍያለሽ!"  አልኳት።ግማሽ ፉቷ ላይ ዘንፈል ብሎ ጋደም ያለውን ፀጉሯን በቀኝ እጃ ሁለት ጣቶች ወደ ጀርባዋ ብትን አደረገችና •••
"200 ብር ለተማሪ አይበዛም  ወንድሜ ቤተሰብ በወር የሚልክልኝ እኮ 300 ብር ነው !" አለችኝ።
መጀመሪያ አሳዘነችኝ !

"ቆይቼ ደግሞ ታድያ አርፈሽ ትምህርትሽን አታጠኝም በዚህ ሰአት እዚህ ምን ትሰሪያለሽ •••?" አልኩና በልቤ •••
"አይበዛም!" አልኳት በለሆሳስ
"እ ምናልክ " አለችኝ ።
በደንብ ተመለከትኳት። ውስጤ ተላወሰ ።

"እሺ ግቢ  እንሂድ!"  አልኳት ።

"በስንት?" አለችኝ
"ደስ ያለሽን ትከፍያለሽ" ዘላ ገባች ። ትንሽ በዝምታ እንደተጓዝን  ድንገት ዘወር አልኩና•••
"አቦ ተያ አንቺ ደሞ ተጫወች እንጂ መንገዱ ረጅም ነው ሂሳብም አስቀንሰሽ ዝምም ብለሽማ አያዋጣኝም !"

"ኦኬ  እእእእእ ግን  ይቅርታ በናትህ ከሚከብዱኝ ነገሮች አንዱ ጫወታ ቀድሞ  መጀመር ነው" አለች እየተቁነጠነጠች

*ምን አይነት ጫወታ  ነው ቀድሞ መጀመር የሚከብድሽ••••? ያው ብዙ አይነት ጫወታ አለ ብዬ ነው።"

"ኪኪኪኩኩ እህ ያው ወሬ ነዋ ሌላ ምን አለ?"

*ኧረ ብዙ አይነት ጫወታ አለ ተጫውተሽ አታውቂም እንዴ•••"

"እንዴ ! ክክክክክ እሱማ ብዙ አይነት ጫወታ አለ እኔ ለማለት የፈለኩት ግን ወሬውን ነው"

ሳቋ ልክ እንደ ህፃን ልጅ ሳቅ  ደስ የሚል ለዛ አለው ።

*ምን አይነት ጫወታ  ይቀልሻል? ወይም ትወጃለሽ?"

"እቃቃና እኩኩሉ ልበልህ " ተሳሳቅን ሳቋን ወደድኩት ፣ወደ ዩንቨርስቲው እየተቃረብን ነው።

"እሺ እኔ ጫወታ በመጀመር ላግዝሻ•••?"

"ከዚህ በላይ••••?  እሄው ጀመርከው እኮ! "አለችኝ
"የዩንቨርስቲ ተማሪ ሆነሽ በዚህ ሰአት ብቻሽን እዛ ጭፈራ ቤት በር ላይ ለምን ቆምሽ••••? ወይ ገብተሽ አልተዝናናሽ ምን አጋጥሞሽ ነው•••?"

በረጁሙ ተነፈሰች  ቀጠል አርጋም •••

"እሱን ተወው ታሪኩ ረጅም ነው ግን አንድ ነገር ልንገርህ  እንኳን ለኮንትራት ለምንም የሚሆን አምስት ሳንቲም ኪሴ ውስጥ የለም  የፈለከውን አድርገኝ፣ ዘቅዝቀህ ብታራግፈኝ እራሱ ጡብ የሚል ነገር ዱዲ የለኝም ! እውነቴን ነው !" አለች።
ሲጢጢጢጢጥ ባጃጇን  ከመቅፅፈት ቀጥ አድርጌ ስዞር ሽምቅቅ ብላለች•••

"እና ዘቅዝቄ ላራግፍሻ!" አልኳት።

"እ••••?!" አለች•••••

ከ 200 ላይክ ቡኋላ ክፍል 2 ይለቀቃል🌹


አሪፍ ተከታታይ ታሪክ ላቀርብላችሁ ነው እንደምትወዱት እርግጠኛ ነኝ react አድርጉ ቤተሰብ


❤❤ውዴ❤❤
ለመጀመርያ ግዜ እንዳየሁሽ ለማናገር ፈራሁ
ለመጀመርያ ግዜ እንዳናገርኩሽ እንዳልወድሽ ፈራሁ
ለመጀመርያ ግዜ እንደወደድኩሽ እንዳላፈቅርሽ ፈራሁ
አሁን ግን አፍቅሬሻለሁ። እንዳላጣሽ ደግሞ እፈራለሁ።

ከ "ምትሀተኛው በር" መፅሓፍ የተወሰደ


ለነበረን ቆይታ እጅግ በጣም አመሰግናለሁ ቀጣይ ሳምንት በሌላ ጥያቄ እንገናኛለን🙏🙏

ሀሳብ አስተያየት ካላችሁ Comment ላይ አሳውቁን🫡

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.