🔵ናታኒም ፕሮሞሽን🔵


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: ko‘rsatilmagan


#ኤልሮይ_ፕሮሞሽን
ቀጥተኛ የሆነች የተዋህዶ ሃይማኖቻችንን አገልግሎቶች የሚያቀርቡበት ቻናል አሎት እግዲያውስ አውኑ ይቀላቀሉ ይመዝገቡ !!!
👤ኤልሮይ ፕሮሞሽን
@alroy_promotion
@alroy_promotion
👤ቻናል ለማስመዝገብ
@Mane_tekel
@Mane_tekel
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri




🎤🌼ድምፀ ተዋህዶ🌼🎤 dan repost
ጾም በእግዚአብሔር ታዟል፤ተፈቅዷልም ።
++++++++++++++++++++++++++
ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጾምን እንድንጾም ባርኮ የሰጠን እሱ ነው ።ለዚህም ማረጋገጫ ፦
"ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ሚዜዎች ሙሽራው ከእነርሱ ጋር ሳለ ሊያዝኑ ይችላሉን? ነገር ግን ሙሽራው ከእነርሱ የሚወሰድበት ወራት ይመጣል፥ በዚያ ጊዜም ይጦማሉ።"
ማቴ 9:15
በዚህ መሰረት ፦
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የራሷ የሆነ የጾም ህግና ስርዓት አላት ።
"ነገር ግን ሁሉ በአግባብና በሥርዓት ይሁን ።"እንዲል
1ኛ ቆሮ 14፥40
በቤተክርስቲያናችን ህግና ሥርዓት ተሰርቶላቸው
ከሚጾሙ 7 የአዋጅ አጽዋማት መካከል አንዱ ጾመ ነብያት ይባላል ።የጾሙ ጊዜ ከህዳር 15-እስከ ጌታ ልደት ታህሳስ 28 ድረስ ያለው ነው ።ይህን ጾም የምንጾመው ነቢያት በየዘመናቸው ስለክርስቶስ መምጣት ንጽህት ከምትሆን ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም መወለዱን በናፍቆት ይጾሙና ይጸልዩ ስለነበር የእነርሱን አርአያ ተከትለን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ልደት ከማክበራችን ቀደም ብለን ይህን ጾም እንድንጾም በሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን ሥርዓት ተሰርቷል። (ፍት.መ.ን.አንቀጽ 15)
ስለሆነም እኛም ክርስቲያኖች ይህን ተከትለን ብልቶቻችንን ሁሉ(አይን ይጹም ፤እጅ ይጹም፤ እግር ይጹም ፤አንደበት ይጹመ...እንዳለ ቅዱስ ያሬድ) ከኃጢአት ጠብቀን፤እግዚአብሔርን ከማያስደስቱ ማናቸውም ነገሮች ራሳችንን አርቀንና ፤በወንድሞቻችን በማናቸውም ላይ ቂም በቀልን በማስወገድ ይቅርም በመባባል ፤ጸሎትን ስግደትን ምጽዋትንም በመጨመር በንጹህ ልቦና መጾም ይገባናል።ይህን ካደረግን ዘወትር የሚዋጉንና የሚፈታተኑን የአጋንንት ሰራዊት በሙሉ ይደመሰሳሉ፤ኃይላቸውም ይደክማል ።ከእግዚአብሔር ከአምላካችን ፍቅርን ሰላምና በረከትንም እንቀበላለን ።
"የጌታ ቃል የታመነ ነውና።"ቲቶ 3:8
".....ይህ ዓይነት ግን ከጸሎትና ከጦም በቀር አይወጣም አላቸው።"
ማቴ 17:21

#ድምፀ_ተዋህዶ

        📹📹📹📹
   ✨ፊላታዎስ ሚዲያ✨
               👇👇
https://youtu.be/PYhgHxupzLI?si=pQaqogjyj_DUcNXW


🎤🌼ድምፀ ተዋህዶ🌼🎤 dan repost
ለመገናኛ ብዙኃን ሥርጭት ድርጅት የተገነባው  ዘመናዊ ስቱዲዮ   በቅዱስ ፓትርያርኩ ተመረቀ።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በማኅበራት ምዝገባና ቁጥጥር መምሪያ እውቅና የተሰጠው "ፍኖተ ጽድቅ ጠቅላላ ማኅበር "ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መገናኛ ብዙኃን ሥርጭት ድርጅት ያስገነባው ዘመናዊ ስቱዲዮ  በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት'  ቡራኬ ተመረቀ።
በመዝግጅቱ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ' የባሕርዳና የሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት እና የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የሥራ ኃላፊዎች ከመላው ዓለም ለ43ኛው ዓለም አቀፍ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ስብሰባ የተሰባሰቡ ልዑካን ተገኝተዋል ።
ስቱዲዮው አንድ ዘመናዊ ስቱዲዮ ማሟላት የሚገባው ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ያሟላ ሲሆን ግዙፍ 8k ስክሪን የተገጠመለት ሲሆን በተጨማሪም በስቱዲዮው የተለያዩ ቀረጻዎችን ማከናወን የሚያስችሉ ገጽታዎች እና የግንኙነት ካሜራ ተሟልቶለታል። የስቱዲዮ መቆጣጠሪያ ክፍል ያለው ሲሆን ግንባታው ባለፉት ከ2 ዓመታት በላይ የወሰደ ሲሆን ዘመናዊ መሣሪያዎች ከውጪ ሀገራት ተገዝተው ተገጥመውለታል።
በፍኖተ ጽድቅ ማኅበር መስራች መጋቤ አእላፍ ጸጋዬ ደበበ ሙሉ ወጪ የተገነባው ይኸው ስቱዲዮ ድርጅቱ በሚያሠራጫቸው ይዘቶች የፕሮዳክሽን ጥራት ለመጨመር ከፍተኛ አስተውጽኦ እንደሚያመጣ ተገልጿል።

#ድምፀ_ተዋህዶ


🎤🌼ድምፀ ተዋህዶ🌼🎤 dan repost
እንኳን ለጻድቁ አባታችን ለአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ አመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደርሳቹ❗️

ጥቅምት 5-ኑሮአቸው እንደሰው ያይደለ በምድረ በዳ እንደመላእክት የኖሩትና በዝቋላ ተራራ ባለው ባሕር ውስጥ 100 ዓመት ተዘቅዝቀው ለኢትዮጵያ ሰዎች ምሕረትን የለመኑት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ታላቅ ቃልኪዳን የተቀበሉበት ዕለት ነው፡፡ 

አባታችን አራት ሺህ እልፍ እየሰገዱ፣ 300 ጊዜ የቀኝ 300 ጊዜ ደግሞ የግራ ፊታቸውን በድንጋይ እየመቱ፣ መዝሙረ ዳዊትን እየደገሙ፣ 15ቱን መኅልየ ነቢያት፣ መኅልየ ሰለምንንና ውዳሴ ማርያም እየጸለዩ ለኃጥአን ምሕረትን ሲለምኑ ዕንባቸው እንደ ውኃ ይፈስ ነበር፡፡ ጌታችንም ‹‹በተወለድሁባት፣ በተጠመቅሁባትና ከሞት በተነሣሁባት ዕለት እልፍ እልፍ ነፍሳትን እምርልሃለሁ›› የሚል ቃል ኪዳን ሰጣቸዉ

አምላካችን በቃል ኪዳናቸው ይማረን


✝️#ድምፀ_ተዋህዶ ✝️


🎤🌼ድምፀ ተዋህዶ🌼🎤 dan repost
“አሁን ባለን የአስተዳደር ክፍተቶችና በውስጣችን ያሉ ግልጽነት የጎደላቸው አሠራሮች ለአገልግሎታችን እንቅፋት እየሆኑብን ነው”ሲሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ገለጹ፡፡

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት 43ኛው ዓለም አቀፍ መደበኛ ጉባኤ መክፈቻ ላይ ለተገኙ ተሳታፊዎች መልእክት አስተላልፈዋል።

ቅዱስነታቸው በመልእክታቸው አሁን ባለን የአስተዳደር ክፍተቶችና በውስጣችን ያሉ ግልጽነት የጎደላቸው አሠራሮች ለአገልግሎታችን እንቅፋት እየሆኑብን ነው። በዚህ ጉባኤ በቤተ ክርስቲያናችን የሚታየውን  ችግር ለመፍታት በጥናት ላይ የተመሠረተ መፍትሔ ማምጣት ይገባል ሲሉ አፅዕኖት ሰጥተዋል፡፡

ቅዱስነታቸው ጨምረው እንደገለጹት ቅዱስ ሲኖዶስ ተግባራዊ እንዲሆን የወሰነውን የቤተ ክርስቲያን የ10 ዓመት መሪ ዕቅድ ውጤታማ ለማድረግ ሁላችንም በትብብር መሥራት ይገባናል ብለዋል።

በዛሬው ዕለት የተጀመረው 43ኛው አጠቃላይ መንፈሳዊ ጉባኤ ከሀገር ውስጥ እና ውጪ ከሚገኙ አህጉረ ስብከቶች፣ ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አድባራት እና ገዳማት እንዲሁም ከተለያዩ መንፈሳዊ ማኅበራት የተወከሉ ተሳታፊዎች በተገኙበት እየተከናወነ ይገኛል።

#ድምፀ_ተዋህዶ


🎤🌼ድምፀ ተዋህዶ🌼🎤 dan repost
"በሰማይ የምትኖር ሆይ፥ ዓይኖቼን ወደ አንተ አነሣሁ፤ እነሆ፥ የባሪያዎች ዓይኖች ወደ ጌታቸው እጅ እንደ ሆኑ፥ የባሪያይቱም ዓይን ወደ እመቤትዋ እጅ እንደ ሆነ፥ እንዲሁ እስኪምረን ድረስ፡ ዓይናችን ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር ነው'' መዝ. 122:1-3

#ድምፀ_ተዋህዶ

▫️https://t.me/dmtse_tewaedo




🎤🌼ድምፀ ተዋህዶ🌼🎤 dan repost
#እንኳን #ለፆመ_ጽጌ በሳላም አደረሳቹህ

✤ወርኃ ጽጌ 40 ቀናት ነው፤ መስከረም 26 ተጀምሮ ኅዳር 5 ያልቃል፤ ጾመ ጽጌ የፈቃድ ጾም ነው (ከሰዓትም ቅዳሴ የሚቀደሰስባቸው አካባቢዎች አሉ (ጎንደር )፡፡
በግዕዝ ጸገየ ማለት   አበበ ፤ አፈራ ፣ በውበት ተንቆጠቆጠ ማለት ነው፡፡ 
በማኀሌቱም ወቅትን እመቤታቸንን 3 ዓመት ከ6 ወር እስከ ግብፅ ከዚያም የአሥራት ሀገሯ  በሆነችው በኢትዮጵያ የተሰደደችበትን ወቅት በማሰብ  በጽጌና በአበባ እመቤታቸንን እና ጌታቸንን በመመሰል ሲያመሰግኗት ፣  ከልጇ ጋር ያየችውን መከራ  እያሰቡ  እና  ምልጃዋን ሲለምኑ ያድራሉ ፡፡

✤እምግብጽ ጸዋዕክዎ ለወልድየ ለክብረ ቅዱሳን፤ ለቅዱሳን ክብር ልጄን ከግብጽ ጠራሁት››
በማለት ነቢዩ ሆሴዕ በምዕራፍ ፲፩ ቍጥር ፩ እና ፪ ላይ አስቀድሞ እንደ ተናገረው ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በልጅነቱ ወደ ምድረ #ግብጽ (ምስር) የተሰደደው የነቢያት ትንቢት ይፈጽም ዘንድ ነው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ሕፃናትን በመፍጀት ከሚታወቀው ከአረመኔው ንጉሥ ከሄሮድስ ለማምለጥ ነው፡፡ አምላካችን ክርስቶስ ያለጊዜው (ዕለተ ዓርብ) #ደሙ #አይፈስምና፡፡ ስለዚህም ‹‹ሕፃኑንና እናቱን ይዘህ ወደ ምድረ ግብጽ ሽሽ፤ ሄሮድስ ሕፃኑን ለመግደል ይፈልጋልና›› ብሎ መልአኩ ቅዱስ #ገብርኤል ለዮሴፍ በነገረው ቃል መሠረት ሕፃኑንና እናቱን ይዞ በሌሊት ወደ ግብጽ ምድር ተሰደደ፡፡ ይህንን ስደት አስመልክቶ #ሰቆቃወ ድንግል የሚባለውን ቃለ እግዚአብሔር ካህናቱ በሚያሳዝን ዜማ ያደርሳሉ፤ ያቀርባሉ፡፡

#በመቶ ሺሕ የሚቆጠሩ ሕፃናትን ሄሮድስ አስፈጅቷል፡፡ ‹‹ድምፅ በራማ ተሰማ፤ ለቅሶና ብዙ ዋይታ፡፡ ራሔል ስለ ልጆቿ አለቀሰች፡፡ መጽናናትም አልወደደችም፤ የሉምና›› የሚለው ትንቢትም ተፈጸሟል፡፡

#ከሦስት ዓመት ከመንፈቅ የግብጽ ስደት በኋላ ሊቃውንቱ፡- ‹‹ተመየጢ ማርያም ሀገረኪ ናዝሬተ፣ በላዕሌኪ አልቦ ዘያበጽሕ ሁከተ፣ ወኢትጎንድዪ በግብጽ ከመ ዘአልብኪ ቤተ፣ ዘየኀሥሦ ለወልድኪ ይእዜሰ ሞተ፣ በከመ ነገሮ መልአክ ለዮሴፍ ብሥራተ›› እያሉ ከስደት መመለሷን ያበሥራሉ፡፡ ትርጉሙም፡- ‹‹ማርያም ሆይ! ወደ ሀገርሽ ወደ ናዝሬት ተመለሺ፡፡ በአንቺ ላይ ሁከት የሚያመጣ ማንም የለም፡፡ ቤት እንደሌለሽ ሁሉ በግብጽ አትቆይ፡፡ ለዮሴፍ በሕልሙ መልአክ እንደ ነገረው የሕፃኑን ነፍስ የፈለገው (ጠላት ሄሮድስ) ሞቷልና›› ማለት ነው፡፡ የኢትዮጵያ #ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምእመናን በዐርባው ቀን (በዘመነ ጽጌ) ወቅት የማርያምን የሽሽትና የመመለስ (የሚጠት) ታሪክ እያነሡ ውዳሴ የሚያቀርቡትና ማኅሌት የሚቆሙት በዚሁ ምክንያት ነው፡፡ በዚህ ወቅት ለእመቤታችን ክብር ሲባል የፈቃድ ጾም የሚጾሙ ምዕመናንና ምዕመናትም ብዙዎች ናቸው በመሃል ኢትዮጵያ  በፈቃድ ጾምነት ሲጾም ; በሰሜኑ አካባቢ ተጹሞ ከሰዓት ይቀደሳል ሌሎች ጋር ግን ጠዋት ያበቃል፡፡

የእመቤታችን ምልጃ ና ጸሎት አይለየን

#ማኅሌተ_ጽጌ
✤የማኅሌተ ጽጌ  የሰቈቃወ ድንግል ደራሲ አባ ጽጌ ድንግል ነው ፡፡
  ገዳሙም ትልቅና ሰፊ የኾነ የፍልፍል ዋሻ ሲኾን ወሎ ወግዲ ወለቃ ወንዝ አጠገብ በረሃ ላይ (ከጋሥጫ ገዳም የ4 ሰዓት የእግር መንገድ) ይገኛል፡፡
✤✤ በየዓመቱ ሳይመረገዱ ያመይታለፉ የማይቀሩ፤ ዚቃቸው የማይለወጥ፤
      እጅጉን በምንወደው የማኅሌተ ጽጌ ቁመት ላይ በየዓመቱ ሳይመረገዱ የማይታለፉ የማይቀሩ፤ ዚቃቸው የማይለወጥ
( ከማኅሌተ ጽጌ፤ ጽጌ አስተርአየ(የመጀመሪያው ሳምንት)፣ በከመ ይቤ መጽሐፍ፣ ትመስል እምኪ ማርያም፣ ዘኒ ስብሐተ ወዘኒ ማኅሌተ፣ ኢየሐፍር ቀዊመ ቅድመ ሥዕልኪ እና ኅብር ሐመልሚል (የመጨረሻው ሳምንት)ናቸው፡፡
✤ ከሰቈቃወ ድንግል፤ በስመ እግዚአብሔር ሥሉስ፣ ብክዩ ኅዙናን፣ እስከ ማዕዜኑ እግዝእትየ እና አብርሂ አብርሂ ናቸው፡፡
✤ከማኅሌተ ጽጌ ውስጥ እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕፃንኪ እና ክበበ ጌራ ወርቅ በየሳምንቱ (በኹሉም ዓመታት) ይመረገዳሉ፤ ዚቁ ግን በዓሉን በተመለከተ ይኾናል፡፡
✤ ከላይ ካየናቸው ውጪ የሚገኙት #የማኅሌተ ጽጌና የሰቈቃወ ድንግል ክፍሎች ግን #በየሰባት ዓመት አንዴ ነው የሚመረገዱት፡፡
( የማኅሌቱ ሥርዐት የላይ ቤት (የጎንደር መካነ ነገሥት ግምጃ ቤት ማርያም አብነት) እና የታች ቤት (የጎንደር ደብረ ኀይል በዓታ ለማርያምን አብነት) የሚያደርግ ሲኾን፤

የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለም ወደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤ.ክ የማኅሌት ቁመትም የላይ ቤትን አብነት የተከተለ ሲኾን የዚቁ ወረብ ግን የደብሩን የራሱን (የሸዋን) የተከተለ ነው፤
( የላይ ቤት ቁመት የሚቆሙ አድባራት #ዘግምጃ ቤት የሚለውን እንዲከተሉ፤ የታች ቤትን #ቁመት የሚቆሙ አድባራት ዘበዓታ የሚለውን እንዲከተሉ፡፡ የዚቁ ወረብን ግን የቀጨኔ ደብረ ሰላም
የቤቱን ቀለም አስቀድመን ቀጥሎ ደግሞ ዓዲ (ወይም) በማለት የጎንደርን ስላስቀመጥነው እንደ ደብራችሁ ይትበሃል መርጣችሁ  ተጠቀሙ፡፡

/በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት የተዘጋጀ ::/

    #ድምፀ_ተዋህዶ

https://t.me/dmtse_tewaedo




🎤🌼ድምፀ ተዋህዶ🌼🎤 dan repost
ይህችን ቅደስት ቤተ ክርስቲያን ካሰባችሁላት ተዋት!

ለልጆቻችሁም ካሰባችሁ ተውን!

ይህ ሕዝብ በጦርነት ዜና፣ በኑሮ ውድነት በሌላም ብዙ ጭንቀት አለበት። እንደአባትነታችሁ ሰላምን ባትሰጡት እንኳ ሌላ ወከባ አትጨምሩበት።

እንደፖለቲከኛ የያዛችሁት ሽኩቻ ሰልችቶናል።

ተናግራችሁና ሠርታችሁ አርአያ መሆን ካልቻላችሁ ዝም በማለት አርአያ ሁኑን!

ይህ ምእመን ቤተ ክርስቲያን ላይ ለደረሰው ሁሉ ዝም ያላችሁ ከላይ እስከታች ስላላጠፋችሁ አልነበረም።

አሳልፈው የሰጡት አባቶች ከመካከል እንደነበሩ ጠፍቶትም አይደለም። ግን ስለማእተቡና ስለቀደሙት አባቶቹ የደም ሰማእትነት ሲል ብዙ እየተደረገ በብዙ ዝም አለ።

እናንተ የተቋም መሪዎቻችን እንጂ ሃይማኖታችን አይደላችሁምና መሠረቱን ክርስቶስን አስቦ ታገሰ!

እናንተ ግን ተጸፅታችሁ ወደ አንድ መጥታችሁ ከውጫዊ ጥቃት ልትጠብቁት ይቅርና እያደረ አዲስ የውስጥ ፈተና ትጠራላችሁ።

ሙስናው፣ መልካም አስተዳደር ችግርና ውጫዊ ፈተናችን ብዙ ነው አይካድም።

የእናንተ የአደባባይ ንተርክ ግን እውነት ለቤተ ክርስቲያን ለውጥ አስባችሁ ነው? ወይስ ለክብራችሁ? ወይስ ስልጣናችሁን ለማጽናት?

ራሳችሁን በጾም በጸሎት የወሰናችሁ ብፁዓን አባቶችስ እስከመቼ ጥግ ይዛችሁ ታያላችሁ? ጸሎት ከሁሉም የበለጠ ኃይል እንደሆነ ብናምንም ተስፋ እንዳንቆርጥ ተግሳጻችሁን እንመኛለን!

እናም ጽሑፉ የሚመለከታችሁ ብፁዓን አባቶች የአደባባይ መዘላለፉን ትታችሁ በውስጥ ተሟገቱ። የውጭ ፈተናችን ይበቃናል። እንደተከታታይ ድራማ እናንተን መከታተል ደክሞናል።

እንዳው በልጅነት የምጠይቃችሁ ድፍረት አይሁንብኝና ከቻላችሁ ወደ ገዳም ገብታችሁ አረፍ በሉ። የጥሞና ጊዜ ጥሩ ነው ብላችሁ አስተምራችሁን የለ?

እስኪ እኛም ካለእናንተ አይነት መሪዎች ቤቱ ምን እንደሚሆን እንየው!

(ከድፍረት ያልሆነ በመድከም የተጻፈ)

✍️ መስከረም

#ድምፀ_ተዋህዶ


|°°ለጀማሪ የግእዝ ቋንቋ ወዳጆች ሁሉ
  🙌 ሰላም ጤና ይስጥልን ክቡራት እና ክቡራን የልሳነ ግእዝ ስልጠና በ @lesangeez128 እየሰጠን እንደሆነ ይታወቃል ሆኖም የጀማሪዎች ስልጠና  በቅርቡ በonline ስለሚጀመር በዚህ #ዙር ላይ 20 ተማሪዎች ብቻ ስለሚካተቱ ከወዲሁዠለጀማሪችሁን እንድታዘጋጁና በፍጥነት እንድትመዘገቡ መልእክታችንን እናስተላልፋለን።
#ለሁለት ወር የመማሪያ ክፍያ #250ብር ብቻ ለበለጠ መረጃ በ @asrategabriel ያነጋግሩን አልያም በ +251970908094 ይደውሉልን።

   🤲ሰብሕዎ የልሳነ ግእዝ ማሰልጠኛ ተቋም🧑‍🎓


🎤🌼ድምፀ ተዋህዶ🌼🎤 dan repost
መስቀል ሃይላችን ነው ፣መስቀል መፅናኛችን ነው ፣ መስቀል የነፍሳችን መድሃኒት ነው፣ መስቀል ቤዛችን ነው ።
አይሁድ ይክዱታል እኛ ግን እናምነዋለን ያመነውም እኛ በመስቀሉ እንድናለን ድነንማል።
የተወደዳቹ የቻናላችን ቤተሰቦች
እንኳን ለታላቁ የመስቀል ደመራ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን!

#ድምፀ_ተዋህዶ

https://t.me/dmtse_tewaedo


🎤🌼ድምፀ ተዋህዶ🌼🎤 dan repost
መስከረም  ፲፮


በዚች ቀን በኢየሩሳሌም አገር ንግሥት ዕሌኒ የገለጠቻቸው የከበሩ ቦታዎች ሁሉ የተሠሩበትና የከበሩበት ሆነ ።

ቆስጠንጢኖስ ከነገሰ በኋላ እናቱ ቅድስት ዕሌኒ ልጄ ሆይ እኔ ወደ ቅድስት አገር ኢየሩሳሌም በመሔድ የክርስቶስን ዕፀ መስቀል ፈልጌ አወጣ ዘንድ ለእግዚአብሔር ስዕለትን ተስያለሁ አለችው ።

ቆስጠንጢኖስም ሰምቶ ደስ አለው ብዙ ሠራዊትና ገንዘብ ሰጥቶ ላካት። ኢየሩሳሌምም በደረሰች ጊዜ ከከበሩ ቦታዎች ተባረከች ። ከዚህም በኋላ የከበረና አዳኝ  የሆነ የክርስቶስን ዕፀ መስቀል ከብዙ ፍለጋ በኋላ አገኘች እግዚአብሔርንም አመሰገነች።

ከዚህም በኋላ በጎልጎታ፣ በቤተልሔም፣ በጽርሐ ጽዮን፣ በጌቴሴማኔ፣ በደብረ ዘይት እና በከበሩ ቦታዎች ሁሉ በዕንቁ በወርቅና በብር የቤተ መቅደስ መሠዊያዎች እንዲሠሩ አዘዘች።

ጻድቅ ንጉሥ ቆስጠንጢኖስም በነገሠ በ፴ ዓመቱ የከበሩ ቦታዎች ሕንፃቸው በተፈጸመ ጊዜ ለቁስጥንጥንያ፣ ለአንጾኪያ፣ለእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት ኤጲስቆጶሶቻቸውን በመያዝ ሁሉም በኢየሩሳሌም የታነፁትን አብያተ ክርስቲያናት እንዲያከብሩ አዘዘ። ንጉሡም እንዳዘዘ ሁሉም ተሰበሰቡ የቁርባን ቅዳሴንም ቀድሰው ለምእመናን ሥጋውንና ደሙን አቀበሉ በዚችም ቀን ከቶ እንደርሱ ሆኖ የማያውቅ ታላቅ ደስታ ሆነ።

የቅዱሳን በረከታቸው ይደርብን! አሜን!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር

#ድምፀ_ተዋህዶ
https://t.me/dmtse_tewaedo


🎤🌼ድምፀ ተዋህዶ🌼🎤 dan repost
👉 ያለፈው ዘመን ይበቃናል 👉
    ፩ ጴጥ ም ፬ ቁ ፫
                   4     3

✝ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ✝

🙏 እንኳን ለሊቀ መላዕክት ለቅዱስ ሩፋኤል በዓለ ሢመት አው ለካህኑ መልከጼዴቅ በዓል አደረሳችሁ አደረስን 🙏

👉 ጳጉሜን ፫ (3) በዓለ ሥሉስ ቅዱስ በዓሉ ለቅዱስ ሩፋኤል ሊቀ መላዕክት ወመልከጼድቅ ወሰራጵዮን ወዘርያዕቆብ ንጉሥ ኢትዮጵያ 👉

👉 ዘነግህ ምስባክ 👉

መሐለ እግዚአብሔር ወኢይኔስሕ
አንተ ካህኑ ለዓለም በከመ ሢመቱ ለመልከጼድቅ
እግዚአብሔር በየማንከ

✥ ትርጉም ✥

እንደ መልከጼዴቅ ሥርዓት አንተ ዘላለም ካህን ነህ ብሎ
እግዚአብሔር ማለ አይጸጸትም
እግዚአብሔር በቀኝህ
   
   መዝ ፻፱-፬
        109  4

✤ ወንጌል ✤

ሉቃ ም ፲፯ ቁ ፳-፴፩
           17   20  31

✝ የቅዳሴ ምንባባት ✝

ዕብ ም ፯ ቁ ፩-፭
ይሁዳ ም ፩ ቁ ፲፩-፲፯
ግብ.ሐዋ ም ፭ ቁ ፲፯-፳፮

❖ ምስባክ ❖

እግዚአብሔርሰ ገሃደ ይመጽእ
ወአምላክነሂ ኢያረምም
እሳት ይነደድ ቅድሜሁ

🙏 ትርጉም 🙏

እግዚአብሔር ግልጥ ሆኖ ይመጣል
አምላካችን ይመጣል ዝምም አይልም
እሳት በፊቱ ይነዳል
 
    መዝ ፵፱-፪
          49   2

❖ ወንጌል ❖

ማቴ ም ፳፭ ቁ ፴፩-ፍ.ም
            25    31   ፍፃሜው

❖ ቅዳሴ ❖

ያዕቆብ ዘሥሩግ(ተንሥኡ)

" የብርሃናት ፈጣሪ ሆይ ጨለማን የደፋው ጣዖትንም የሻረው በሞቱ ሞት ያጠፋው "
     ቅዳሴ ያዕቆብ ዘሥሩግ
           ም ፩ ቁ ፹፫
                1     83

✝ በዓሉ በዓለ ምህረት በዓለ ድኀነት ያድርግልን ቸሩ መድኃኔዓለም በቸርነቱ ይማረን እመ አምላክ እግዝእትነ ማርያም በምልጇዋ ትጠብቅን ከሊቀ መላዕክት ቅዱስ ሩፋኤል በረድኤቱ ይጠብቅን ካህኑ መልከጼዴቅ በረከቱ ይደርብን ድርሳነ ሩፋኤል ገድለ ቅዱሳን ዕጣነ አሮን መስዋዕት መልከጼዴቅ የተቀበለች የኛም ፆም ፀሎት ጥምቀት ምሕላ በቸርነቱ በብሩህ ገጽ ይቀበልልን ለበዓለ ዓውደ ዓመት በሰላም ያድርሰን ✝

                  ✧ ምስባክ ✧

#ድምፀ_ተዋህዶ

           YouTube chnnl
👇🏽🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘 🔻👇🏽
        
የይቱብ ቻናላችን
             🔔
  🔺 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘🔺‌‌


❤️በናታኒም ቲዩብ❤️
         👇🏽👇🏽
https://youtu.be/MsXeCVCPxX
4
https://youtu.be/MsXeCVCPxX4
htt
ps://youtu.be/MsXeCVCPxX4


🎤🌼ድምፀ ተዋህዶ🌼🎤 dan repost
✞ ነሐሴ ፲፫ ቀን ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ከ፱ቱ ዓበይት በዓል አንዱ የሆነ በዓለ ደብረ ታቦር ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበት በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረስን ✞

✥ ቅዱስ ዳዊት ✥

ታቦር ወአርሞንኤም በስመ ዚአከ ይትፌሥሑ
ወይሴብሑ ለስምከ
መዝራዕትከ ምስለ ኃይል

✤ ቅዱስ ያሬድ ✤

ወሪዶሙ እምደብር ታቦር አዘዞሙ ለይንግሩ ዘርእዩ

✢ አባ ጊዮርጊስ ✢

ከመ ቀስተ ደመና የዓውዶ ሱራሂ

እንደ ደመና ምልክት ብርሃንን ይከበዋል

❖ አባ አርከ ሥሉስ ❖

ጸርሐ አብ ኪያከ በውዳሴ ወበርእስከ ጸለለ መንፈስ ቅዱስ አመ ገበርከ እግዚኦ በታቦር ምስለ ሐዋርያት ክናሴ መንገለ ሀሎ ኤልያስ ወኀበ ሀለወ ሙሴ ለመለኮትሰ ወልድ ከሠትከ ሥላሴ

✟ የመልክዐ ኢየሱስ ደራሲ የደብረ መጓዬና ኮከብ ሊቁ አባ ዓምደ ሐዋርያት በድርሰታቸው ✟

ሰላም ለልሳንከ በደብረ ታቦር ዘአልኆሰሰ ለብርሃን ዐቢይ እስከ ጸላሎቱ ተሐውሰ ነበልባለ እሳት ክርስቶስ ዘተዋሐድከ ጳጦስ በዋዕየ ፍቅርከ ከመ ሥርወ አዕዋም ጠብሰ ውሳጤ ኀሊናየ ነደ ወልብየ ጤሰ

✥ ቅዱስ ዲዮስቆሮስ በቅዳሴው

ከፀሐይና ከጨረቃ ከከዋክብትም በፊት ከብርሃናትም መመላለስ በፊት እግዚአብሔር በመንግሥቱ ነበረ

✝ ቅዱስ ማቴዎስ በወንጌል ✝

ወእንዘ ይትናገር ናሁ ደመና ብሩህ ጸለሎሙ ወናሁ ቃል እምውስተ ደመና ትብል ዝውእቱ ወልድየ ዘአፈቅረ ዘቦቱ ሠመርኩ ወሎቱ ስምዕዎ

ርሱም ገና ሲናገር እነሆ ብሩህ ደመና ጋረዳቸው እንሆም ከደመናው በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው እርሱን ስሙት የሚል ድምጽ መጣ

በዓሉን በዓለ ድኀነት ያድርግልን ብርሃን መለኮቱን ይላክልን አምላክ ቅዱሳን

ነሐሴ ፲፫ በዓለ ደብረ ታቦር

  ተጻፈ ✏ ምኑን በኀበ ሰብእ ✏ ፳፻፲፬ ዓ.ም

        #ድምፀ_ተዋህዶ
          


🎤🌼ድምፀ ተዋህዶ🌼🎤 dan repost
➣ አፉየ አስተንፈሰ ወልሳንየ አልኆሰሰ ለክብረ ፍልሰትኪ ድንግል ሶበ አቈርብ ተውዳሰ ማርያም ዘኮንኪ ቅድስተ ቅዱሳን መቅደስ በቅድሜኪ እግዝእትየ እመ ረከብኩ ሞገስ በየማንኪ ባርክኒ ሥልስ ➣

አንደበቴ ተናገረ አፌም ዘመረ ለዕረገትሽ ክብር ዝማሬን በአቀረብኩ ጊዜ ቅድስተ ቅዱሳን መቅደስ የሆንሽ እመቤቴ ማርያም ኾይ በፊትሽስ ባለሟልነትን ባገኝ  በቀኝ እጅሽ ሶስት ጊዜ ባርኪኝ

  መልክአ ፍልሰታ ዘደረሰ አፄ ዘርዓያዕቆብ

ለቅዱሳን የተለመነች ለኛም ትለመነን ቸሪቱ ድንግል ማርያም

               #ድምፀ_ተዋህዶ

YouTube chnnl
👇🏽🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘 🔻👇🏽
         የይቱብ ቻናላችን
             🔔
  🔺 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘🔺‌‌


❤️በናታኒም ቲዩብ❤️
         👇🏽👇🏽
https://youtu.be/MsXeCVCPxX4
https://youtu.be/MsXeCVCPxX4
https://youtu.be/MsXeCVCPxX4

16 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.