ሀምዱ ቋንጤ
ﺭﻣﻀﺎﻥ ﻣﺒﺎﺭﻙ
ረመዷን ሙባረክ
በመላው አለም ለምትገኙ ሙስሊሞች በአጠቃላይ እንኳን ለ1442ኛው
የረመዷን ፆም በሰላም አደረሳችሁ
አቡ ሁረይራ ከአላህ መልዕክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ
በማለት ያስተላልፋል፦
ﻛﺎﻥ ﺭﺳﻮﻝ ﺍﻟﻠﻪ ﷺ ﻳُﺒَﺸِّﺮ ﺃﺻﺤﺎﺑﻪ ﺑﻘﺪﻭﻡ ﺭﻣﻀﺎﻥ ﻳﻘﻮﻝ : " ﻗﺪ ﺟﺎﺀﻛﻢ ﺷﻬﺮ ﺭﻣﻀﺎﻥ ﺷﻬﺮٌ
ﻣﺒﺎﺭﻙ ، ﻛﺘﺐ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻜﻢ ﺻﻴﺎﻣﻪ ، ﻓﻴﻪ ﺗﻔﺘﺢ ﺃﺑﻮﺍﺏ ﺍﻟﺠﻨﺔ ﻭﺗﻐﻠﻖ ﻓﻴﻪ ﺃﺑﻮﺍﺏ ﺍﻟﺠﺤﻴﻢ ، ﻭﺗﻐﻞ
ﻓﻴﻪ ﺍﻟﺸﻴﺎﻃﻴﻦ ، ﻓﻴﻪ ﻟﻴﻠﺔٌ ﺧﻴﺮٌ ﻣﻦ ﺃﻟﻒ ﺷﻬﺮ ، ﻣﻦ ﺣُﺮِﻡَ ﺧﻴﺮﻫﺎ ﻓﻘﺪ ﺣُﺮِﻡ .
[ ﺻﺤﺤﻪ ﺍﻷﻟﺒﺎﻧﻲ ﻓﻲ ﺻﺤﻴﺢ ﺍﻟﺘﺮﻏﻴﺐ ( 1/490) ]
} የአላህ መልዕክተኛ ረመዷን ሲደርስ ለባልደረቦቻቸው ያበስሯቸው ነበር።
እንዲህም ይሏቸዋል
"በእርግጥም የተባረከ የሆነው የረመዷን ወር መጥቶላችኋል፣ አላህ በእናንተ
ላይ እንድትፆሙት ግድ አድርጎባችኋል፣ በእሱ ውስጥ የጀነት በሮች ይከፈታሉ፣
የጀሀነም በሮች ይዘጋሉ፣ ሸይጣኖችንም ይታሰራሉ፣ በእሱም ውስጥ ከአንድ
ሺህ ወር የምትበልጥ የሆነች ሌሊት አለችበት፣ ከእሷ መልካምነት የተከለከለ
ሰው በእርግጥም የተከለከለ ሰው ነው " {
ኢብኑ ረጀብ የተባለው ሊቅ አላህ ይዘንለትና ስለዚህ ሐዲስ ሲናገር
እንዲህ ይላል ;
" ከፊል ዑለማዎች ይህን ሐዲስ ሰዎች ከፊላቸው ለከፊላቸው «ለረመዷን
ወር እንኳን አደረሰህ» መባባል እንዳለባቸው መሰረታዊ ሐዲስ (መረጃ) ነው።
ይልና ቀጥሎም እንዲህ ይላል
ሙዕሚን የሆነ ሰው የጀነት በር በመከፈቱ እንዴት አይደሰትም
ወንጀለኛ የሆነ ሰው የጀሀነም በር በመዘጋቱ እንዴት አይደሰትም
አዕምሮ ያለው የሆነ ሰው ሸይጣኖች በመታሰራቸው እንዴት አይደሰትም
የዚህ ዐይነት የመሰለ ጊዜ ከየት ይገኛል
[ ﻟﻄﺎﺋﻒ ﺍﻟﻤﻌﺎﺭﻑ ( 1/158) ]
እኛም ይህንን ሐዲስ ላይ በመደገፍ
ለሁሉም ሙስሊም ወንድም እህቶቻችን በአጠቃላይ
ለዚህ የተከበረ ለሆነው ትልቁ የበረካ ወር ለረመዷን ወር አላህ እንኳን
በሰላም አደረሳችሁ ማለት እንወዳለን
አላህ በአዘዘው መልኩ ፆመው እና ሰግደው፣
አላህ ወዶላቸው እና ተቀብሏቸው ተጠቃሚ ከሚሆኑ ባሮቹ ያደርገን ዘንድ
እንማፀነዋለን
https://t.me/joinchat/Q0mf35Z6QEmajDQB