ሀምዱ ቋንጤ
ረመዳን መጣ ይኸው አመት ዞሮ
ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ
ረመዳን መጣ ይኸው አመት ዞሮ
ከቀናት ሳምንታት ወራት አስቆጥሮ
እንዴት ነው ዝግጅት ለቂርዐት ለሰላት
ከወንጀል ርቆ ዒባዳን ለማብዛት
ከሰፊው ራህመት ሸምቶ ለመውጣት
በሉ ተዘጋጁ በንቃት ጠብቁ
ከእዝነቱ ለማፈስ ካሁኑ ታጠቁ
ማዕሲያና ገፍላ ሁሉንም ራቁ
አላህ ካደረሰን ለተከበረው ወር
ወሬና ጭቅጭቅ ሩቅ በመወርወር
ለመግባት እንጣር ከሰፊው ጀነት በር
ሀሜት ቂለ ወቃል ቀይረን በአዝካር
ለ ለይል ሰላታችን ወገብን በማሰር
ቁርኣንም በመቅራት በቆንጆ ተደቡር
ዱዐና ሰደቃ ሁሉም በማዘውተር
ጀነትን እንግዛት ያቺ ውዷ ሀገር
ተውበት በማድረግ ላለፉ ወንጀሎች
በኸይር እንዲያልቁ ቀሪ የእድሜ ቀኖች
እንለምን ጌታችን ሆነን ደጋግ ባሮች
ይቀበላልና አላህ ከሙዕሚኖች
ደካሞች ረድተን ምስኪኖች አግዘን
ተሳሳች መልሰን ዝንጉዎችም መክረን
ከዚህ ትርፋማ ወር እንውጣ ሸምተን
እስቲግፋር እናብዛ በተውባ እንጠንክር
ለሰላት ለቁርኣት ወገብን እንሰር
እንዳንሆን እንፍራ ከነዝያ ከሳሪ
መቀበል ያልቻሉ የጀነት ተጣሪ
ከአረህማን ዕዝነት ሆኑ ተባራሪ
እርኩስ ሸይጣን ታስሮ ጀሀነም ተዘግቶ
ለሙዕሚኖች ክብር ጀነትን ተከፍቶ
ሰፊው የአላህ እዝነት እንዲህ ተዘርግቶ
ተኝቶ ሊታደር ይህን እድል ትቶ
ለአፍታ መዘናጋት አይታሰብም ከቶ
ብዙ ነው በኛ ላይ የአረህማን ውለታ
ይህንን በማሰብ ለዒባዳ እንበርታ
ቂርኣቱም ሰላቱም ሁሉም በየተራ
ሰብስበን ስንጨርስ የቻልነውን ስራ
ልንፈራ ይገባል እንዳይሆን አቧራ
ከመስራቱ በፊት እንዲሁም በኋላ
ስራችን እንዳይከስር አላህን እንፍራ
በኢኽላስ እናርገው አደራ አደራ
ሐምዱ ቋንጤ
ከፉርቃን ሰማይ ስር
[ከ2 አመት በፊት የተገጠመ]
https://t.me/joinchat/Q0mf35Z6QEmajDQB
ረመዳን መጣ ይኸው አመት ዞሮ
ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ
ረመዳን መጣ ይኸው አመት ዞሮ
ከቀናት ሳምንታት ወራት አስቆጥሮ
እንዴት ነው ዝግጅት ለቂርዐት ለሰላት
ከወንጀል ርቆ ዒባዳን ለማብዛት
ከሰፊው ራህመት ሸምቶ ለመውጣት
በሉ ተዘጋጁ በንቃት ጠብቁ
ከእዝነቱ ለማፈስ ካሁኑ ታጠቁ
ማዕሲያና ገፍላ ሁሉንም ራቁ
አላህ ካደረሰን ለተከበረው ወር
ወሬና ጭቅጭቅ ሩቅ በመወርወር
ለመግባት እንጣር ከሰፊው ጀነት በር
ሀሜት ቂለ ወቃል ቀይረን በአዝካር
ለ ለይል ሰላታችን ወገብን በማሰር
ቁርኣንም በመቅራት በቆንጆ ተደቡር
ዱዐና ሰደቃ ሁሉም በማዘውተር
ጀነትን እንግዛት ያቺ ውዷ ሀገር
ተውበት በማድረግ ላለፉ ወንጀሎች
በኸይር እንዲያልቁ ቀሪ የእድሜ ቀኖች
እንለምን ጌታችን ሆነን ደጋግ ባሮች
ይቀበላልና አላህ ከሙዕሚኖች
ደካሞች ረድተን ምስኪኖች አግዘን
ተሳሳች መልሰን ዝንጉዎችም መክረን
ከዚህ ትርፋማ ወር እንውጣ ሸምተን
እስቲግፋር እናብዛ በተውባ እንጠንክር
ለሰላት ለቁርኣት ወገብን እንሰር
እንዳንሆን እንፍራ ከነዝያ ከሳሪ
መቀበል ያልቻሉ የጀነት ተጣሪ
ከአረህማን ዕዝነት ሆኑ ተባራሪ
እርኩስ ሸይጣን ታስሮ ጀሀነም ተዘግቶ
ለሙዕሚኖች ክብር ጀነትን ተከፍቶ
ሰፊው የአላህ እዝነት እንዲህ ተዘርግቶ
ተኝቶ ሊታደር ይህን እድል ትቶ
ለአፍታ መዘናጋት አይታሰብም ከቶ
ብዙ ነው በኛ ላይ የአረህማን ውለታ
ይህንን በማሰብ ለዒባዳ እንበርታ
ቂርኣቱም ሰላቱም ሁሉም በየተራ
ሰብስበን ስንጨርስ የቻልነውን ስራ
ልንፈራ ይገባል እንዳይሆን አቧራ
ከመስራቱ በፊት እንዲሁም በኋላ
ስራችን እንዳይከስር አላህን እንፍራ
በኢኽላስ እናርገው አደራ አደራ
ሐምዱ ቋንጤ
ከፉርቃን ሰማይ ስር
[ከ2 አመት በፊት የተገጠመ]
https://t.me/joinchat/Q0mf35Z6QEmajDQB