ዝክረ ረመዳን አምናና ዘንድሮ
ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ
ምስጋና ለአላህ አምሳያ ለሌለው
እዝነት በረከቱ ለሁሉም ሚደርሰው
አዛኝ ነው ሩህሩህ ከጉድለት የጠራ
ሰጥቶ ማያልቅበት ድህነት ማይፈራ
ለባሮቹ ክብር ካለው አዘኔታ
ፉርሳ ያመቻቻል በጊዜ በቦታ
ብዙ እድሎችን ለኛ ያመቻቻል
ነቄው ይጠቀማል ቂሉ ይሸወዳል
ከነዚህ ፉርሳዎች ከልዩ እድሎች
አንዱ አካቦናል ንቁ የአላህ ባሮች
መጥቷል ከፊትለፊት እየገሰገሰ
ታላቁ እንግዳ ሊገባ ደረሰ
ቀኑ ቆጠረና የተቀጠረበት
በጊዜው ደረሰ ሳይጎል ሳያልፍበት
ዘንድሮም እንደ አምና ያለምንም ስራ
በባዶ እንዳይሄድ አላህን እንፍራ
ከጀምዐ ከጁምዐ መስጂድ ተከልክለን
ለይልና ተራዊህ እንዳንሰግድ ታግደን
መስጂዶች ተራቁተው ሙስሊሞች ተራርቀው
የዒድ ሰላታቸው ከመስገድ ታግደው
የዒቲካፍ ጀምዓ ከመስጂድ ሲመለስ
ልባቸው በሀዘን ዐይናቸው ሲያለቅስ
መንገዱ ተዘግቶ የሀጅና ዑምራ
የኮሮናው ክስተት አያልቅም ቢወራ
አላህ በጥበቡ ያሻውን ይሰራል
በውሳኔው ማመን ኢማን ይጨምራል
የአምናው አለፈና የያዘውን ይዞ
የዘንድሮው መጣ አመቱን ተጉዞ
እንዴት ነው ዝግጅት ያ ኡመተል ኢስላም
ለሲያም ለቂርኣት ለአዝካር ለቂያም
ስንቶቹ ነበሩ የአምናው የፆሙት
የዘንድሮው ሳይደርስ አኼራ የሄዱት
እኛም ካደረሰን አላህ ከወፈቀን
ከዚህ ትርፋማ ወር እንውጣ ሸምተን
መንዙማ ነሺዳ በሱዳን ሙዚቃ
እንዳንጭበረበር መሸዋወድ ይብቃ
ተከታታይ ፊልሞች ወይንም ድራማ
ሁሉም አስወግደህ ቁርኣን ብቻ ስማ
ቀንህን በመፆም ለሊትህ በመቆም
ደረጃህ ከፍ ይበል ከጌታህ ፊት ስትቆም
ፆምህ ጥርት ይበል ከሀሜት ከውሸት
አሉባልታ ወሬ እለፈው ከርቀት
ቁርኣንህ ዘርግተህ አንብበው ቀን ማታ
ከዱዐ ከአዝካር አትቋረጥ ለአፍታ
ሰላትህ በመስጂድ ከሙስሊሞች ጋራ
ሁሉንም በኢኽላስ በሱና እንስራ
ዝናቡን እንዲወርድ በሽታው እንዲነሳ
እንለምን ጌታችን እጃችን እናንሳ
የተራበ አብልተን ፆመኛ አስፈጥረን
ይህን ከባድ ጊዜ እንለፍ ተባብረን
ያስቀየምነው ካለ አፉታ እንጠይቅ
ያስቀየመን ካለ ሄደን እንታረቅ
ድንበር ያለፍኩበት ካለ ያስቀየምኩት
አውቄም ይሁን ሳላውቅ ቅስሙን የሰበርኩት
ለአላህ ይበልና ሁሉም አፍው ይበለኝ
እኔም ብዬዋለሁ አላህ ይቀበለኝ
ለፊጥር ከበቃን ረመዳን ፆመን
አላህ እናመስግን ልክ እንደ አዘዘን
ቢያልቅ ረመዳን ጌታችን ህያው ነው
ሞታችን እስኪደርስ ሁሌም እንገዛው
ከረመዳን ህይወት ሳይኖር ተለውጧት
በዒባዳ እንቀጥል ያለ ተቀዩሯት
ሐምዱ ቋንጤ
ከፉርቃን ሰማይ ስር
ሚያዝያ 03/2013
https://t.me/joinchat/Q0mf35Z6QEmajDQB
ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ
ምስጋና ለአላህ አምሳያ ለሌለው
እዝነት በረከቱ ለሁሉም ሚደርሰው
አዛኝ ነው ሩህሩህ ከጉድለት የጠራ
ሰጥቶ ማያልቅበት ድህነት ማይፈራ
ለባሮቹ ክብር ካለው አዘኔታ
ፉርሳ ያመቻቻል በጊዜ በቦታ
ብዙ እድሎችን ለኛ ያመቻቻል
ነቄው ይጠቀማል ቂሉ ይሸወዳል
ከነዚህ ፉርሳዎች ከልዩ እድሎች
አንዱ አካቦናል ንቁ የአላህ ባሮች
መጥቷል ከፊትለፊት እየገሰገሰ
ታላቁ እንግዳ ሊገባ ደረሰ
ቀኑ ቆጠረና የተቀጠረበት
በጊዜው ደረሰ ሳይጎል ሳያልፍበት
ዘንድሮም እንደ አምና ያለምንም ስራ
በባዶ እንዳይሄድ አላህን እንፍራ
ከጀምዐ ከጁምዐ መስጂድ ተከልክለን
ለይልና ተራዊህ እንዳንሰግድ ታግደን
መስጂዶች ተራቁተው ሙስሊሞች ተራርቀው
የዒድ ሰላታቸው ከመስገድ ታግደው
የዒቲካፍ ጀምዓ ከመስጂድ ሲመለስ
ልባቸው በሀዘን ዐይናቸው ሲያለቅስ
መንገዱ ተዘግቶ የሀጅና ዑምራ
የኮሮናው ክስተት አያልቅም ቢወራ
አላህ በጥበቡ ያሻውን ይሰራል
በውሳኔው ማመን ኢማን ይጨምራል
የአምናው አለፈና የያዘውን ይዞ
የዘንድሮው መጣ አመቱን ተጉዞ
እንዴት ነው ዝግጅት ያ ኡመተል ኢስላም
ለሲያም ለቂርኣት ለአዝካር ለቂያም
ስንቶቹ ነበሩ የአምናው የፆሙት
የዘንድሮው ሳይደርስ አኼራ የሄዱት
እኛም ካደረሰን አላህ ከወፈቀን
ከዚህ ትርፋማ ወር እንውጣ ሸምተን
መንዙማ ነሺዳ በሱዳን ሙዚቃ
እንዳንጭበረበር መሸዋወድ ይብቃ
ተከታታይ ፊልሞች ወይንም ድራማ
ሁሉም አስወግደህ ቁርኣን ብቻ ስማ
ቀንህን በመፆም ለሊትህ በመቆም
ደረጃህ ከፍ ይበል ከጌታህ ፊት ስትቆም
ፆምህ ጥርት ይበል ከሀሜት ከውሸት
አሉባልታ ወሬ እለፈው ከርቀት
ቁርኣንህ ዘርግተህ አንብበው ቀን ማታ
ከዱዐ ከአዝካር አትቋረጥ ለአፍታ
ሰላትህ በመስጂድ ከሙስሊሞች ጋራ
ሁሉንም በኢኽላስ በሱና እንስራ
ዝናቡን እንዲወርድ በሽታው እንዲነሳ
እንለምን ጌታችን እጃችን እናንሳ
የተራበ አብልተን ፆመኛ አስፈጥረን
ይህን ከባድ ጊዜ እንለፍ ተባብረን
ያስቀየምነው ካለ አፉታ እንጠይቅ
ያስቀየመን ካለ ሄደን እንታረቅ
ድንበር ያለፍኩበት ካለ ያስቀየምኩት
አውቄም ይሁን ሳላውቅ ቅስሙን የሰበርኩት
ለአላህ ይበልና ሁሉም አፍው ይበለኝ
እኔም ብዬዋለሁ አላህ ይቀበለኝ
ለፊጥር ከበቃን ረመዳን ፆመን
አላህ እናመስግን ልክ እንደ አዘዘን
ቢያልቅ ረመዳን ጌታችን ህያው ነው
ሞታችን እስኪደርስ ሁሌም እንገዛው
ከረመዳን ህይወት ሳይኖር ተለውጧት
በዒባዳ እንቀጥል ያለ ተቀዩሯት
ሐምዱ ቋንጤ
ከፉርቃን ሰማይ ስር
ሚያዝያ 03/2013
https://t.me/joinchat/Q0mf35Z6QEmajDQB