ኑ ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: ko‘rsatilmagan


#ወደ_ኤፌሶን_ሰዎች_ምዕ 4፥5

#አንድ ጌታ #አንድ ሃይማኖት #አንዲት ጥምቀት
ከዅሉ በላይ የሚኾን በዅሉም የሚሠራ በዅሉም የሚኖር #አንድ አምላክ የዅሉም አባት አለ።
ነገር ግን እንደክርስቶስ ስጦታ መጠን ለያንዳንዳችን ጸጋ ተሰጠን።
#ማንኛውም_አስተያየት_ሀሳብ 👉 @kasechtadese

@yetwahdotemrtmaskemch

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri








የእግዚአብሔር ሕግ ንጹሕ ነው ነፍስንም ይመለሳል፤ የእግዚአብሔር ምስክር የታመነ ነው ሕጻናትንም ጠቢባን ያደርጋል። የእግዚአብሔር ሥርዓት ቅን ነው ፤ልብን ደስ ያሰኛል ።የእግዚአብሔር ትእዛዝ ብሩህ ነው፤ አይኖችንም ያበራል ::እግዚአብሔርን መፍራት ንጹሕ ነው ለዘለዓለም ያኖራል የእግዚአብሔር ፍርድ እውነት እና ቅንነት በአንድነት ነው ::ከወርቅ እና ከክቡር እንቁ ይልቅ ይወደዳል ፤ከማርና ከማር ወለላም ይልቅ ይጣፍጣል:: ባርያህ ደግሞ ይጠብቀዋል በመጠበቁም ብዙ ዋጋ ይቀበላል ::

(መዝሙር ፲፰፥፯-፲፩)




በእንተ ቅዱሳን ኅሩያን (ከገድላት አንደበት) dan repost
የየትኛውም ብሔር ተወላጅ ብትኾን መጀመሪያ በራስህ፤ ቀጥሎ በቤተሰብህ፤ ከዚያም በቅድስት ቤተ ክርስቲያንህ እና በመጨረሻም በሀገር ላይ ይመጣ ያለውን አስከፊ እልቂትና መከራ ሳይታክቱ ሌት ተቀን ነግረውሃልና እነዚኽ ኹለት ሰዎች የኢትዮጵያ ሕዝብ ባለ ዕዳዎች ናቸው። ግለሰቦቹን ወደድካቸውም ጠላኻቸውም፤ ሰማኻቸውም አልሰማኻቸውም እርሱ ለቤተ ክርስቲያንና ለሀገር ነቢይም ሐዋርያም መምህርም ኾነው ትናንትም ዛሬም ሲጮኹ አይተንና ሰምተን እንደ እብድ ብንቈጥራቸውም ነገ ጅብ ከሔደ በኋላ የውሻ ጩኸት የምንጮኸው እኛ ነን። ይኽ በእርግጥ ሩቅ አይደለም። የዐዋጅ ነጋሪ ቃል ሲጮህ አልሰማ ብለህ ለንስሓ ያልተዘጋጀህ ኹላ አይዞህ ጊዜው ሩቅ አይደለም። አራጁ ቢላውን ስሎ ሞርዶ ከደጅ ቆሞልሃል፤ አንተም አንገትህን አደንድነህ ጠብቀው።


"" ሰው ሁሉ ሐሰተኛ ነው! "" (መዝ. ፻፲፭:፪)

☞ክፍል ፩/1

"ዝክረ ቅዱስ ዳዊት - ዘወርኀ ጥር"

(ጥር 23 - 2017)

https://t.me/zikirekdusn




ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ ለንስሓ ልጁ በሰርጓ ቀን መገኘት ባለመቻሉ የላከላት ደብዳቤ

“ልጄ! ለሰርግሽ የነፍስ አባትሽ እኔ ጐርጐርዮስ ይህን ግጥም ስጦታ አድርጌ ልኬልሻለሁ፡፡ አባት ለሚወዳት ልጁ ሊሰጣት የሚችለው የተሻለው ምክርም ይህ እንደ ኾነ አምናለሁ፡፡

ኦሎምፒያታ ሆይ፥ እውነተኛ ክርስቲያን ለመኾን ያለሽን ፍላጎት ዐውቃለሁና በደንብ አድምጪኝ! እውነተኛ ክርስቲያን እንዲሁ መኾንን የሚመኝ ብቻ ሳይኾን እንደዚያ ለመኾን ሊጥር ይገባዋል፡፡

ከኹሉም በላይ፥ እግዚአብሔርን ልታከብሪውና ልትወጂው ይገባሻል፡፡ ከእርሱ ቀጥሎም በቅዱስ ወንጌል እንደ ታዘዘው እንደ ጌታችንና መድኃኒታችን [ኢየሱስ ክርስቶስ] አድርገሽ ባልሽን ልታከብሪውና ልትወጂው ይገባሻል፡፡ ስለዚህ እጠይቅሻለሁ! ጌታዋንና ፈጣሪዋን [ኢየሱስ ክርስቶስን] የማታከብርና የማትወድ ሴት በዚህ መንገድ ባልዋን እንዴት አድርጋ ልታከብረውና ልትወደው ትችላለች?

“በጋብቻሽ ውስጥ የትዳር አጋርሽ ይኾን ዘንድ እግዚአብሔር መርጦ ለሰጠሽ ባል ያለሽ መውደድ፣ ስሜትና ፍቅር እጅግ ኃያል ሊኾን ይገባዋል፡፡ ይህ ሰው አሁን የሕይወትሽ ዓይን፣ የልብሽም ደስታ ነውና፡፡

እግዚአብሔርን እንደምትወጂው፥ ባልሽንም ያለ ቅድመ ኹኔታ ልታከብሪውና ልትወጂው ይገባሻል፡፡ አንቺ ሴት እንደ ኾንሽና ታላቅ የኾነ ዓላማና ግብ እንዳለሽ፥ ኾኖም ዓላማሽና ግብሽ የቤትሽ ራስ ሊኾን ከሚገባው ባልሽ የተለየ እንደ ኾነ ዕወቂ፤ ተረጂም፡፡ ባንቺ ዕድሜ ላይ ያሉት አንዳንዶች ኹለቱም ፆታዎች እኩል [ራስ ናቸው] ብለው የሚሰብኩትን አትስሚ፤ የጋብቻንም ግዴታ [ወይም ዋና ዓላማ] አስቢ፡፡ እነዚህን ግዴታዎች [ወይም ዓላማዎች] ስታውቂ የቤተሰብሽን ተግባራት ለማከናወን እንደ ምን ያለ ትዕግሥትና ጽናት እንደሚያስፈልግሽ ታውቂያለሽና፡፡ እንደ ሚስት እጅግ ጥንካሬን ገንዘብ የምታደርጊውም በዚህ መንገድ ነው፡፡

“ወንዶች እንዴት በቀላሉ የሚቈጡ መኾናቸውን በርግጥ ልታውቂ ይገባሻል፡፡ አይችሉም፤ ብዙ ጊዜም እንደ በረኻ አንበሳ ይኾናሉ፡፡ እንግዲህ ሚስት ጸንታ ልትቆምና የነፍስ ልዕልናዋን ልታሳይ የሚገባት በዚህች ቅጽበት ነው፡፡ አንበሳን የማስለመድ ሥራ መሥራት አለብሽ፡፡ አንበሳን የሚያስለምድ ሰው አንበሳ ሲያገሳ የሚያደርገው ምንድን ነው? ከየትኛውም ጊዜ በላይ ዝም ጸጥ ይላል፡፡ በጸጥታውና በርጋታውም የአንበሳውን ቊጣ ይቈጣጠራል፡፡ በርጋታና በለሆሳስ ኾኖ ያናግረዋል፤ ይደባብሰዋል፤ በቀስታ ያሻሸዋል፤ በጥቂት በጥቂቱም አንበሳው ቊጣውን ይተዋል፡፡

ባልሽ ስሕተት ሲሠራ በፍጹም ልትነቅፊው፣ ልትንቂው ወይም ልታስነውሪው አይገባም፡፡ በተመሳሳይ መንገድ አንድ መሥራት ያለበትን ነገር ባይሠራና ከዚሁ የተነሣም ውጤቱ ደስ የማያሰኝ ቢኾን፣ ወይም እጅግ የምትፈልጊውና አግባብ ነው ብለሽ የምታስቢውን ባያደርግ እንኳን ባልሽን መናቅ ከአንቺ ልታርቂ ይገባል፡፡ ክፉዎች አጋንንት ዘወትር ቤታችሁን ለማፍረስና የጥንዶች መንፈሳዊ አንድነትን ለመበተን እንደሚሞክሩ ዕወቂ፡፡”

(ከገብረ እግዚአብሔር ኪደ ከትንሿ ቤተክርስቲያን መጽሐፍ የተወሰደ)


የማርቆስ ወንጌል ም.፲

21: ኢየሱስም ወደ እርሱ ተመልክቶ ወደደውና እንዲህ አለው፦ “አንድ ነገር ጐደለህ፤ ሂድ፥ ያለህን ሁሉ ሽጠህ ለድሆች ስጥ፥ በሰማይም መዝገብ ታገኛለህ፥ መስቀሉንም ተሸክመህ፡ ና፥ ተከተለኝ።”
22: ነገር ግን ስለዚህ ነገር ፊቱ ጠቈረ፥ ብዙ ንብረት ነበረውና እያዘነም ሄደ።
23: ኢየሱስም ዘወር ብሎ አይቶ ደቀ መዛሙርቱን፦ “ገንዘብ ላላቸው ወደ እግዚአብሔር መንግሥት መግባት እንዴት ጭንቅ ይሆናል፡” አላቸው።
24: ደቀ መዛሙርቱም እነዚህን ቃሎች አደነቁ። ኢየሱስም ደግሞ መልሶ፦ “ልጆች ሆይ፥ በገንዘብ ለሚታመኑ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት መግባት እንዴት ጭንቅ ነው።
25: ባለ ጠጋ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ከሚገባ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ቢያልፍ ይቀላል፡” አላቸው።
26: እነርሱም ያለ መጠን ተገረሙና እርስ በርሳቸው፦ “እንግዲያ ማን ሊድን ይችላል?” ተባባሉ።
27: ኢየሱስም ተመለከታቸውና፦ “ይህ በእግዚአብሔር ዘንድ እንጂ በሰው ዘንድ አይቻልም፤ በእግዚአብሔር ዘንድ ሁሉ ይቻላልና፡” አለ።
28: ጴጥሮስም፦ “እነሆ፥ እኛ ሁሉን ትተን ተከተልንህ፡” ይለው ጀመር።
29: ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለ፦ “እውነት እላችኋለሁ፥ ስለ እኔና ስለ ወንጌል ቤትን ወይም ወንድሞችን ወይም እኅቶችን ወይም አባትን ወይም እናትን ወይም ሚስትን ወይም ልጆችን ወይም እርሻን የተወ፤
30: አሁን በዚህ ዘመን ከስደት ጋር ቤቶችን ወንድሞችንና እኅቶችንም እናቶችንም ልጆችንም እርሻንም መቶ እጥፍ፥ በሚመጣውም ዓለም የዘላለም ሕይወት የማይቀበል ማንም የለም።
31: ግን ብዙ ፊተኞች ኋለኞች ኋለኞችም ፊተኞች ይሆናሉ።”


2ኛ ቆሮንቶስ ም.፲፪

6: ልመካ ብወድስ ሞኝ አልሆንም፥ እውነትን እላለሁና፤ ነገር ግን ማንም ከሚያይ ከእኔም ከሚሰማ የምበልጥ አድርጎ እንዳይቆጥረኝ ትቼአለሁ።
7: ስለዚህም በመገለጥ ታላቅነት እንዳልታበይ የሥጋዬ መውጊያ፥ እርሱም የሚጎስመኝ የሰይጣን መልእክተኛ ተሰጠኝ፤ ይኸውም እንዳልታበይ ነው።
8: ስለዚህ ነገር ከእኔ እንዲለይ ሦስት ጊዜ ጌታን ለመንሁ።
9: እርሱም፦ “ጸጋዬ ይበቃሃል፥ ኃይሌ በድካም ይፈጸማልና፡” አለኝ። እንግዲህ የክርስቶስ ኃይል ያድርብኝ ዘንድ በብዙ ደስታ በድካሜ ልመካ እወዳለሁ።
10: ስለዚህ ስለ ክርስቶስ በድካም በመንገላታትም በችግርም በስደትም በጭንቀትም ደስ ይለኛል፤ ስደክም ያን ጊዜ ኃይለኛ ነኝና።


የዮሐንስ ወንጌል ም.፮

25: በባሕር ማዶም ሲያገኙት፦ “መምህር ሆይ፥ ወደዚህ መቼ መጣህ?” አሉት።
26: ኢየሱስም መልሶ፦ “እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ የምትፈልጉኝ እንጀራን ስለ በላችሁና ስለ ጠገባችሁ ነው እንጂ ምልክቶችን ስላያችሁ አይደለም።
27: ለሚጠፋ መብል አትሥሩ፤ ነገር ግን ለዘላለም ሕይወት ለሚኖር መብል የሰው ልጅ ለሚሰጣችሁ ሥሩ፤ እርሱን እግዚአብሔር አብ አትሞታልና።”
28: እንግዲህ፦ “የእግዚአብሔርን ሥራ እንድንሠራ ምን እናድርግ?” አሉት።
29: ኢየሱስ መልሶ፦ “ይህ የእግዚአብሔር ሥራ እርሱ በላከው እንድታምኑ ነው፡” አላቸው።






"" ስንክሳር - ጥር ፳፭/25 ""

❖በዓለ ቅዱሳን መርቆሬዎስ ፥ ወስብስትያኖስ፥ ወጴጥሮስ

(ጥር 24 - 2017)

https://t.me/zikirekdusn


💕ከዘማሪያን የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይ ፈ ል ጋ ሉ ? 🔔 💕

[┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
[┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ዘማሪ አቤል መክብብ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕ዘማሪት ሲስተር ህይወት ተፈራ💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕ዘማሪ ዲያቆን ሙሉቀን ከበደ💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ዘማሪት ፋሲካ ድንቁ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛


🌷👥 የሁሉንም ዘማሪያን መዝሙር ለማግኘት 🔔 👇
🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧


ኦርቶዶክሳዊ ቻናል dan repost
መልካም ዜና ለአእላፍት ዝማሬ ቤተሰቦች ❤️‍🔥

የአእላፍት ዝማሬ መዝሙሮችን በነፃ የምታገኙበት አዲስ ቻናል ተገኝቷል፣ በቀላሉ ቻናሉን ለማግኘት
👇


አንድ ደቂቃ ወስደው ያንብቡት ድንቅ ምክር ነው
(ለሌሎች ያጋሩት)

በሠርጉ ዋዜማ እናት ወንድ ልጇን ምን አለችው?


የኔ ልጅ አሁን አንተ ትልቅ ሰው ነህ። ነገ ሌላ እናት ታገኛለህ አዲስ ሰው ምግብህን ያበስላል ምስጢርህን ይካፋላል እኔ ከእንግዲህ ይህንን አላደርግም አዲሷን እናትህን ውደዳት። እሰከመጨረሻው በእጆቿ ላይ ከመተኛትህ በፊት ምክሬን ልስጥህ!

አንድ ቀን ከአባትህ ጋር እየተነጋገርን ነበር በጣም በስሜት ሆነን እንጯጯህ ነበር በቁጣ ስሜት ውስጥ ሆነን ሳላ እኔ በድንገት አንተ የማትረባ ስለው በጣም ተሸማቀቀ ወደ እኔ እየተመለከተ እንዴት እንደሱ ትያለሽ ? ሲለኝ ቀበል አድርጌ አዎ አንተ የማትረባ ሞኝ እብድ ብዬ ያለ የሌለውን የስድብ ናዳ አወረድኩበት ታድያ እሱ ምን እንዳደረገ ታውቃለህ? እሲቲ ገምት? ሊደበድበኝ ይችል ነበር ግን እጆቹን ሳያነሳ ምንም ሳይለኝ መዝግያውን አላትሞ ወጥቶ ሄደ።

ልጄ አባትህ ቢመታኝና ፊቴን ቢያበላሸው አንተ ዛሬ በተበላሸው ፊቴ ታዝንብኝና ታፍርብኝ ነበር እሱንም እንደ አባት አትቆጥረውም ሁሌ ታዝንበት ነበር የምትኮራበት አባት አይሆንህም ነበር።

ልጄ ሚስትህን እንዳትመታት! ብትሰድብህም ብታዋርድህም ከአጠገቧ ለግዜው ዞር በል ኋላ ላይ ነገሮች ይስተካከላሉ። እንግዲህ ሚስትህ ስታበሳጭህ ይህንን የእኔን ታሪክ አስታውስ!

ካቋረጥኩበት ልቀጥል...... ልክ ብቻየን ትቶኝ እንደሄደ ስለሰደብኩት በጣም ፀፀተኝ .. ታድያ የተጣላን ቀን ምሽት አንድ አልጋ ላይ አብረን አደርን በሚቀጥለው ቀን ማድረግ የሚገባኝን ሁሉ አድርጌ ይቅርታ ጠየኩት እርሱም ተቀበለኝ .. ታድያ የዛን ቀን ምን አደረኩ መሰለህ የሚወደውን ምግብ አዘጋጅቼ ስሰጠው ደስ እያለው በላ ካዛ ቀን በኋላ ከአፌ ክፉ ቃል አልወጣኝም ለእሱ ያለኝ ክብር እስር እጥፍ እየጨመረ መጣ።

አንድ በጣም አስፈላጊ ነገር ማድርግ ያለብህ ነገር አለ። ሚስትህን። በደንብ አድምጣት ጋሻና መከታ ሁናት በጭንቅ ግዜ ከጎኗሁን ጓደኞችህ ቢጠሉዋትም ያንተ ንግስት እንደሆነች አሳያቸው ታውቃለህ አጎትህ አይወደኝም ነበር አባትህ ግን ስለኔ ያለውን አሳምኖት ሓሳቡን አስለውጦት እኔን ይደግፈኝ ነበር።

ልጄ.. . አንድ ቀን አባትህ 3 ሰዎች ወደ ቤት ጋብዟቸው ነበር አንደኛው የስራ አለቃው ሲሆን ሁለቱ ጓደኞቹ ነበሩ ምግብ አብስዬ ሁሉን አሟልቼ ካቀረብኩ በኋላ አንድ ነገር ረሳሁ ጨው አልጨመርኩም ነበር በጣም አፈርኩኝ አባትህ ወድያው ምግቡን እንደቀመሰ ወደኔ ተመልክቶ ወደ እነሱ ዞር አለና በጤና እክል ምክንያት ከወር በፊት ምግብ ውስጥ ጨው እንዳትጨምር አዝዣት ነበር ብሎ ሲስቅ ሁሉም ሳቁና እባክሽ ጨው ስጭን ብለው ሁሉም እንደፍላጎቱ ጨምረው ተመገቡ።

እንግዶችም በሄዱ ግዜ ተንበርክኮ ጌታ ሆይ ስለዋሸው ይቅር በለኝ አለ።

ሚስትህ ልክ እንደ ህፃን ናት አንዳንዴ ምን ማለት ወይም ማድረግ እንዳለባት አታውቅ ይሆናል ነገር ግን ተነስተህ ስለ እሷ ስትል ተናገርላት።

ልጄ.. . ስለ ግብረስጋ ግኑኝነት ልንገርህ.. .ወሲብ ጥሩ ነገር ነው።ሚስትህ በወሲብ የምትደሰተው ካንተ በላይ ከሆነ አይግረምህ። ታውቃለህ አንዳንድ ቀን እኔን በጣም ያስፈልገኛል እሱ ግን እስከዚህም ይሆናል ሌላ ግዜ ደግሞ እሱን በጣም ያስፈልገዋል እኔ ግን እስከዚህ እሆናለው... አንድ ማውቅ ያለብህ ነገር እራስ ወዳድ አትሁን አንደኛው ሌላኛውን መረዳት አለበት።

አስቸጋሪ ግዜያት ይመጣል አባትህን ለመደገፍ ስል ሁለት ቦታ ስራ እሰራ ነበር  ታድያ አንድ ቀን ምሽት በጣም ደክሞኝ ወደ መኝታ ክፍል ሳመራ እሱ በጣም ተነቃቅቶ ጠበቀኝ ግን አልተቃወምኩም ቢደክመኝም ፍላጎት እንዳለው ሰው ሆንኩለት ነገር ግን እንደጠበቀው ስላልሆንኩለት ፊቴን አይቶ በመረዳት ምን ሆነሻል? አለኝ ምንም አልኩት ከዚያ ስለተረዳኝ እቅፍ አድርጎ የመኝታ ታሪኮችን/bed time story/ እየነገረኝ እንቅልፍ ወሰደኝ ... ወሲብ የሁለት ሰው የእዕምሮና የአካል ዝግጁነት ይጠይቃል። አንዳንዴ ሚስትህን በደንብ ተመልከታትና ተረዳት።

ልጄ.. .ከሚስትህ ጋር የትም መሄድ ልማድ አድርገው ከስራህ ውጭ ሰትሆን ከሚስትህ ጋር አሳልፍ አንድ ሰው ከሚስትህ ውጭ ብቻህን ቤቱ እንድትመጣ ከጋበዘህ ተጠንቀቅ ብልህ ሁን።

እኔን እንደምትወደኝ ችግሮችህን እንደምትነግረኝ አውቃለው አሁን ግን ይህ ሁኔታ ተቀይሮአል። ከነገ በኋላ ሚስትህ ሁሉንም ነገር ማወቅ አለባት። ከእሷ ጋር ስትጋጭ ወድያው ወደኔ አትሩጥ ለአንድ ወይም ለሁለት ቀን ታገሳት ከዚያ ነገሩ ጋብ ሲል ተነጋገሩ ፀልዩበት ስለ እሷ ለሌላ ሰው ለማንም አትናገር ።

በመጨረሻም በየወሩ ከሚስትህ ጋር እየመጣችው ጠይቁኝ ጥሩ ትዳር እንደሚኖርህ ተስፋ አደርጋለው አንተ ምርጥ ልጄ ነህ እግዚአብሔር ይባርክህ ወደ ፈጣሪ ፀልይ ሁሌም የእርሱን እርዳታ እሻ!!

(Anani Moti)


2ኛ ቆሮንቶስ ም.፲፩

1: በጥቂቱ ሞኝነቴ ብትታገሡኝ መልካም ይሆን ነበር፤ ቢሆንም በእርግጥ ታገሡኝ።
2: በእግዚአብሔር ቅንዓት እቀናላችኋለሁና፥ እንደ ንጽሕት ድንግል እናንተን ለክርስቶስ ላቀርብ ለአንድ ወንድ አጭቻችኋለሁና፤
3: ነገር ግን እባብ በተንኮሉ ሔዋንን እንዳሳታት፥ አሳባችሁ ተበላሽቶ ለክርስቶስ ከሚሆን ቅንነትና ንጽሕና ምናልባት እንዳይለወጥ ብዬ እፈራለሁ።
4: የሚመጣውም ያልሰበክነውን ሌላ ኢየሱስ ቢሰብክ፥ ወይም ያላገኛችሁትን ልዩ መንፈስ ወይም ያልተቀበላችሁትን ልዩ ወንጌል ብታገኙ፥ በመልካም ትታገሡታላችሁ።
5: ከእነዚህ ከዋነኞቹ ሐዋርያት በአንድ ነገር እንኳ እንደ ጎደልሁ ራሴን አልቆጥርም።
6: በአነጋገሬ ያልተማርሁ ብሆን እንኳ፥ በእውቀት ግን እንዲህ አይደለሁም። ነገር ግን በሰው ሁሉ መካከል በነገር ሁሉ ተገልጠንላችኋል።
7: ወይስ የእግዚአብሔርን ወንጌል ያለ ደመወዝ ስለ ሰበክሁላችሁ፥ እናንተ ከፍ እንድትችሉ ራሴን እያዋረድሁ ኃጢአት አድርጌ ይሆንን?
8: እናንተን ለማገልገል ደመወዝ እየተቀበልሁ ሌሎችን አብያተ ክርስቲያናት ዘረፍሁ።
9: ከእናንተም ጋር ሳለሁ በጎደለኝ ጊዜ፥ በማንም አልከበድሁበትም፤ ከመቄዶንያ የመጡት ወንድሞች የጎደለኝን በሙሉ ሰጥተዋልና፤ በነገርም ሁሉ እንዳልከብድባችሁ ተጠነቀቅሁ እጠነቀቅማለሁ።

26: ብዙ ጊዜ በመንገድ ሄድሁ፤ በወንዝ ፍርሃት፥ በወንበዴዎች ፍርሃት፥ በወገኔ በኩል ፍርሃት፥ በአሕዛብ በኩል ፍርሃት፥ በከተማ ፍርሃት፥ በምድረ በዳ ፍርሃት፥ በባሕር ፍርሃት፥ በውሸተኞች ወንድሞች በኩል ፍርሃት ነበረብኝ፤
27: በድካምና በጥረት ብዙ ጊዜም እንቅልፍ በማጣት፥ በራብና በጥም ብዙ ጊዜም በመጦም፥ በብርድና በራቁትነት ነበርሁ።
28: የቀረውንም ነገር ሳልቆጥር፥ ዕለት ዕለት የሚከብድብኝ የአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ አሳብ ነው።


የዮሐንስ ወንጌል ም.፭

39: እናንተ በመጻሕፍት የዘላለም ሕይወት እንዳላችሁ ይመስላችኋልና እነርሱን ትመረምራላችሁ፤ እነርሱም ስለ እኔ የሚመሰክሩ ናቸው፤
40: ነገር ግን ሕይወት እንዲሆንላችሁ ወደ እኔ ልትመጡ አትወዱም።
41-42: ከሰው ክብርን አልቀበልም፤ ዳሩ ግን የእግዚአብሔር ፍቅር በራሳችሁ እንደ ሌላችሁ አውቃችኋለሁ።
43: እኔ በአባቴ ስም መጥቻለሁ አልተቀበላችሁኝምም፤ ሌላው በራሱ ስም ቢመጣ እርሱን ትቀበሉታላችሁ።
44: እናንተ እርስ በርሳችሁ ክብር የምትቀባበሉ ከአንዱም ከእግዚአብሔር ያለውን ክብር የማትፈልጉ፥ እንዴት ልታምኑ ትችላላችሁ?
45: እኔ በአብ ዘንድ የምከሳችሁ አይምሰላችሁ፤ የሚከሳችሁ አለ፤ እርሱም ተስፋ የምታደርጉት ሙሴ ነው።

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.